No summary available.
ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አማን ባርጌቾ -- ጠበቃ ታረቀኝ አበራ -- ቀረቡ ተጠሪ፡- ነጃት ባርጌቾ -- ቀረቡ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።
በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ተጠሪው በቦላ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ ወረዲ 12 ልዩ ስሙ መንደር 3 የሚገኝ ሰነድ አልባ ቤት አመልካች ከአረብ አገር በላኩለት ገንዘብ ገዝቶልኛል፤ ከውጪ ሐገር ስመለስ የተለያዩ ዔቃዎችን በመያዝ በቤቱ ውስጥ ለአንድ ዓመት ኖሬበታለሁ፤ ሆኖም በመካከላችን በተፈጠረው አለመግባባበት ምንም ዓይነት ንብረት ሳልይዝ ከቤቱ አስወጥቶኛል፤ ስለሆነም አመልካቹ ቤቱን እና ዔቃውን እንዱያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁን አመልካች በሰጡት መልስ ተጠሪ በማስረጃነት ያቀረቡት የባለቤትነት ማስረጃ ሐሰተኛ ነው፤ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት እና ጥቅም የላቸውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ነገሩ ላይ ደግሞ ተጠሪ በተለያየ ጊዜ ከአረብ አገር የላከችውን ገንዘብ በአደራ አስቀምጬ ስትመጣ እኔ ጋ በማረፍ ገንዘቡን በፈለገችበት ጊዜ ስትወስድ ቆይታለች፤ ያልወሰደችው /ሰማንያ ሺህ / አላት፤ ቤቱ በተጠሪ ስም አልተገዛም፤ ቤቱ የተገዛው ተጠሪ አረብ አገር ከመሄዶ በፉት ነው፤ ቤቱ የተገዛው በግል ገንዘቤ ነው፤ ቁሳቁስ እና ጌጥ ከፉለ አለ፤ ከፉለ ግን የተጋነነ እና በሀሰት የቀረበ ነው፤ ተጠሪ ቤቱን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በቦላ ምድብ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. ክስ አቅርባ በእርቅ ተስማምተን ተዘግቷል፤ ስለሆነም ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት በታመኑት ጉዲዮች ላይ አስቀድሞ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን በተካደ ላይ ደግሞ የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ተጠሪ ቀሪ ንብረቶች በአመልካች እጅ የሚገኘ መሆናቸውን አላረጋገጠችም፤ ቤቱን በሚመለከት ግን ከአመልካች በተሻለ ማስረጃ አስረድታለች፤ ስለሆነም አመልካች የተጠሪ ንብረት መሆናቸውን በዝርዝር ያመናቸውን የቤት ዔቃዎች እና አልባሳት እንዱሁም ክስ የቀረበበትን ቤት ያስረክባት በማለት ወስኗል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት አቤቱታቸው ተሰርዟል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም፡- ተጠሪ ከዚህ ቀደም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍድ ቤት ቦላ ምድብ ችልት በመ. በቤቱ ጉዲይ ክስ መስርተው ጉዲዩ በሽምግልና አልቋል ብለው መዝገቡን ያዘጉ በመሆኑ በድጋሚ ሉከሱ አይገባም በማለት ያቀረብኩት መቃወሚያ መታለፈ አግባብ አይደለም፤ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም በስር ፍርድ ቤት መቃወሚያው አልቀረበም በማለት በራሱ አነሳሽነት ይግባኙን የዘጋው ቢሆንም መቃወሚያው በስር ፍርድ ቤት ቀርቧል፤ አመልካች ተጠሪ በውጪ አገር ትልክ የነበረውን ገንዘብ ማስቀመጡ ቤቱ የተጠሪ መሆኑን የሚያመለክት አይደለም፤ ቤቱ የተገዛው በአመልካች ስም እንጂ በተጠሪ ስም አይደለም፤ ተጠሪ ልትጠይቀኝ ከተገባ ገንዘቡን እንጂ ቤቱን አይደለም፤ ስለሆነም ይህ ታልፍ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ አመልካች ጉዲዩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. በስምምነት ተቋጭቶ ያለቀና የተዘጋ ነው በማለት ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የታለፈበትን አግባብነት ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ቀርቧል።
No topics extracted.
ተጠሪ ሚያዝያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ጉዲዩ በድጋሚ ላታይ አይገባውም ነበር የሚለው መቃወሚያ እንደ አዱስ ማቅረብ የሥነ ሥርዓት ሕጉ አይፈቅድም፤ ማንሳት በነበረባቸው ጊዜ ባለማቅረባቸው ምክንያት የስር ፍርድ ቤት ይህን መቃወሚያ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ባለመቁጠር አልፍ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ ነው፤ ከዚህ በፉት የተከፈተው ፊይል ሉዘጋ የቻለው አመልካች እና በሀይማኖታችን ትልቅ ቦታ የምሰጣቸው የሀይማኖት አባቶች መዝገቡን ካላዘጋሽ እንረግምሻለን ብለው ጫና ስለፈጠሩብኝ መሆኑን ገልጫለሁ፤ ስለሆነም በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።
ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤
ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ለቀረበባቸው ክስ መልስ ሲሰጡ ተጠሪ በማስረጃነት ያቀረቡት የባለቤትነት ማስረጃ ሐሰተኛ ነው፤ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት እና ጥቅም የላቸውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ መሆኑን እና በፍሬ ነገሩ ላይ በሰጡት መልስ ደግሞ ቤቱን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦላ ምድብ ችልት በመ. ክስ አቅርባ በእርቅ በስምምነት የተዘጋ መሆኑን እና ላልችንም መከራከሪያ ሐሳቦች በማቅረብ የተከራከሩ መሆኑን ነው። ይህም አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያው ላይ ባይገልጹትም በፍሬ ነገር ክርክራቸው ላይ ጉዲዩ ከዚህ በፉት በፍርድ ቤት ታይቶ እልባት ያገኘ መሆኑን በመግለጽ መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
በመሰረቱ ማስረጃ ተቀብል ከመመርመሩ ወይም ምስክሮችን ከመስማቱ አስቀድሞ ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ደረጃ ለቀረበለት እና ማናቸውም ተከራካሪ ወገን ላቀረበው መቃወሚያ ውሳኔ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ፤ የነገርን ጭብጥ መያዝ የሚቻለውም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እንዲለ ከተወሰነ በኋላ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244/1 እና 246/1 ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ ተመልክቷል።
በያዝነው ጉዲይ የሥር ከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪዋ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት ወይም ጥቅም የላቸውም በማለት ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መርምሮ ሕዲር 17 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው ብይን ውድቅ ያደረገው ቢሆንም አመልካች ተጠሪ ቤቱን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦላ ምድብ ችልት በመ. ክስ አቅርባብኝ በእርቅ ተስማምተን ተዘግቷል በማለት ያቀረቡትን ክርክር በዝምታ አልፍታል። አመልካች ቤቱን በሚመለከት ከዚህ በፉት ተጠሪ ክስ አቅርባብኝ በስምምነት ተዘግቷል በማለት ያቀረቡትን ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያው ላይ ባይገልጹትም በፍሬ ነገር ክርክራቸው ላይ ቤቱን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦላ ምድብ ችልት በመ. ተጠሪዋ ክስ አቅርባ በእርቅ በስምምነት ተዘግቷል በማለት በግልጽ እስከተከራከሩ ጊዜ ድረስ ይህ ክርክራቸው እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተቆጥሮ በቅድሚያ አልባት ሉሰጠው የሚገባ ነው። ስለሆነም ጉዲዩ የቀረበለት የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይህን ሳያደርግ ቤቱን አስመልክቶ በዋናው ጉዲይ ላይ የሰጠው ውሳኔ ከላይ የተመለከቱትን የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉን ድንጋጌዎች ያላገናዘበ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.
የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሻሽሎል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ቤቱን አስመልክቶ የሰጠው የውሳኔ ክፍል፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል። ከዚህ ውጪ ያለው የውሳኔ ክፍል አልተነካም።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔ የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ቤቱን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦላ ምድብ ችልት በመ. ተጠሪዋ ክስ አቅርባ በእርቅ በስምምነት ተዘግቷል በማለት በፍሬ ነገር ክርክሩ ላይ የሰጡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ይዘት ያለው መሆኑን ተረድቶ በቅድሚያ በዚሁ ነጥብ ላይ ተገቢውን ብይን እንዱሰጥበት፤ የሚሰጠው ብይን ክርክሩን የማያስቆም ከሆነ በፍሬ ነገሩ ላይ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341/1 መሰረት ጉዲዩን መልሰንለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመ. የሆነው መዝገብ ወደመጣበት ይመለስ።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል። ይመለስ አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት