No summary available.
ቀን፡- 26/02/2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ ረሂማ አብደላሂ ተጠሪዎች፡- 1.ከዱር ዮሱፍ በከር 2. ሰይዲ ረመዲን መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የጋራ የሆነ የእርሻ መሬት በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገ ነዉ የተባለዉ ዉል ቀሪ እንዱደረግና ይዞታዉን ለማስለቀቅ እንዱሁም አላባ ለማስከፈል የቀረበ ክስ የመዲኝት ሥልጣን የሚመለከት ነዉ።
አመልካች በተጠሪዎችና በስር 1ኛ ተከሳሽ አቶ ሙስጠፊ ዩሱፍ ላይ በሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ለ30 ዓመታት በትዲር ተሳስረን አብረን ስንኖር በሐረር ክልል በድሬ ጠያራ ወረዲ በአቦከር ሙጢ ቀበላ ገበሬ ማኅበር ዉስጥ ያለንን አንድ ጥማድ ከግማሽ የሆነ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰዉን የእርሻ መሬት ያለእኔ ፈቃድ በሕገ-ወጥ መንገድ ለአሁን ተጠሪዎች በሽያጭ አስተላልፈዋል። በዚህ ምክንያት በአመት 20 ኩንታል ማሽላ በማምረት ማግኘት የምንችለዉን በኩንታል በብር 1200.00 ሂሳብ ብር 24,000.00 አሳጥተዉኛል።እየተቃወምኩ በመሬቱ ላይ ተጠሪዎች ቤት ሰርተዉበታል።ስለሆነም ዉለ ሕገ-ወጥ ስለሆነ እንዱፈርስና የገነቡትን ቤት አፍርሰዉ ይዞታዬን እንዱለቁ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የስር 1ኛ ተከሳሽ ለክሱ በሰጡት መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት ከአመልካች ጋር በጋራ የያዙት መሬት እንደሆነና ያለአመልካች ፈቃድ በማንኛዉም ሁኔታ ማስተላለፍ እንደላለብኝ ባለማወቅ ለተጠሪዎች በማስተላለፋ ተጠሪዎች በእርሻ መሬታችን ላይ ቤት ሉሰሩበት ስለቻለ በአመልካች ጥያቄ መሰረት ቢወሰን አልቃወምም የሚል ይዘት ያለዉ መልስ ሰጥተዋል።2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በሰጡት መልስ መኖሪያ ቤት ለመግዛት እየፈለጉ ባለበት የስር 1ኛ ተከሳሽ በመሬቱ የመጠቀም መብታቸዉን ለማስተላለፍ ፈልገዉ የመጠቀም መብታቸዉን ብር 100,100.00 ሽጠዉልናል። የመሬት ባለቤትነት ለመዉሰድ በሂደት ላይ እንገኛለን።መሬቱ በዚህ አግባብ እንደተላለፈልንና ቤት ስንሰራም አመልካች እያወቁ አልተቃወሙንም በማለት ክሱ ዉድቅ እንዱደረግላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮች ሰምቶና መርምሮ በቀን 26/01/2012 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ የስር 1ኛ ተከሳሽ ያለተጠሪ ፈቃድ ባልና ሚስት ሆነዉ ከአመልካች ጋር በጋራ ባለይዞታ የሆኑበትን የመሬት ይዞታ ለተጠሪዎች በሽያጭ በማስተላለፍ ያደረጉት ዉል የፋዳራል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 68ን የሚቃረን በመሆኑ በዚሁ ሕግ አንቀጽ 69 መሰረት ዉለ ፈርሶ ተጠሪዎች የገነቡትን ግንባታ በራሳቸዉ ወጪ አፍርሰዉ መሬቱን ለቀዉ እንዱወጡና ወደነበሩበት እንዱመለሱ ሲል ወስኗል።
ተጠሪዎች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 22/10/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች ክስ የመሰረቱት ፍርድ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 መሰረት ጉዲዩን ለመዲኘት ሥልጣን አለዉ በማለት ቢሆንም ግራ ቀኝ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች በመሆናቸዉ፣ዉለ የተደረገበት የመሬት ይዞታ የሚገኘዉ በሐረሪ ክልል ዉስጥ የሚገኝ በመሆኑ ጉዲዩን የፋዳራል ጉዲይ የሚያደርግ ምክንያት በላለበት እንደፋዳራል ጉዲይ ተቀብል መዲኘቱ ስህተት ነዉ።እንዱሁም አመልካች ክስ ሲመሰርቱ በግምት ብር 24,000.00 ምርት የሚገኝበት መሬት እንደሆነ ጠቅሰዉ ያቀረቡት ክስ ስለሆነ የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህ ልክ የሚገመት ክስ በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት ሥልጣን ተቀብል ለመዲኘት የሚያስችል ስልጣን ሳይኖረዉ የሰጠዉ ዉሳኔ ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ሽሯል።በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች የሰበር አቤቱታቸዉን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም በመ/ ላይ በቀን 24/03/2013ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ አቤቱታቸዉን ሰርዞባቸዋል።
አመልካች በቀን 07/10/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ግራ ቀኝ በተለያዩ ክልልች ነዋሪ መሆናችን ስለተረጋገጠ የስር የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን እንደ ፋዳራል ጉዲይ በመቁጠር ዉሳኔ መስጠቱ ተገቢ ሆኖ ሳለ ተጠሪዎችም ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የመዲኘት ስልጣን እንደላለዉ ገልጸዉ ያቀረቡት መቃወሚያ ሳይኖር ዉሳኔዉ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሻሩ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5/2 ስር የተደነገገዉንና በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን ዉሳኔ የሚቃረን በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ።እንዱሁም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረብኩትን የሰበር አቤቱታ ምርምሮ ለሰበር እንዱቀርብ አዞ ግራ ቀኝ የጽሁፍ ክርክር አቅርበን ለዉሳኔ በተቀጠረበት ቀን ጉዲዩ ለሰበር አያስቀርብም በማለት ዉሳኔ የሰጠበት አግባብ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 እና ከቁጥር 339-348 ስር ስለዉሳኔ አሰጣጥ የተደነገገዉን ሥነ ሥርዓት የተከተለ ባለመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ለማጣራት ያስቀርባል ብል ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ወደኋላ ተመልሶ አያስቀርብም በማለት ዉሳኔ የሰጠበት አግባብ ተጠሪዎች ባለበት እንዱመረመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በቀን 05/11/2013 ዓ/ም የተፃፈ መልስ በማቅረብ ግራ ቀኝ በአንድ ክልል ዉስጥ ነዋሪ ስለሆንና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬትም በሐረሪ ክልል የሐረሪ ከተማ አካል ሆኖ የሚገኝ በመሆኑ ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን ያለዉ የከተማ ነክ ፍርድ ቤት በመሆኑ የስር የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በፋዳራል ዲኝነት ሥልጣን ተቀብል መዲኘቱ ስህተት ነዉ ተብል በመሻሩ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት መልሳቸዉን ሰጥተዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ በተጨማሪ የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን እንደፋዳራል ጉዲይ ቆጥሮ በዉክልና ሥልጣን አከራክሮ መወሰኑ ተገቢ አይደለም ተብል በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዉሳኔዉ በመሻሩ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካችና ተጠሪዎች ነዋሪነታቸዉ በአንድ ክልል ዉስጥ እንደሆነ ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ነዉ።የክሱ ስረ ነገር እና በአመልካች የተጠየቀዉ ዲኝነት አመልካች ያለፈቃደ የጋራ ባለይዞታ የሆንኩበትን የእርሻ መሬት ባለቤቴ ለተጠሪዎች በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገዉ ዉል ቀሪ ሆኖ ተጠሪዎች እየተቃወምኩ የሰራሁትን ቤት አፍርሰዉ መሬቱን እንዱለቁ ይወሰንልኝ የሚል እንደሆነ ከክርክሩ ተገንዝበናል።እንዱሁም ለክሱ መሰረት የሆነዉ ዉልም የተደረገዉም ሆነ ተሸጠ የተባለዉ መሬት የሚገኘዉ በሐረሪ ክልል ዉስጥ መሆኑ አከራካሪ አይደለም።የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዘንድ ክሱ ሲቀርብ በሥራ ላይ በነበረዉ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5/2 መሰረት መደበኛ ነዋሪነታቸዉ በተለያዩ ክልልች ዉስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚነሱ ክርክሮችን የመዲኘት ሥልጣን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች እንደሆነ በተደነገገዉ መሰረት የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ መደበኛ የመኖሪያ አድራሻ በተለያዩ ክልልች ዉስጥ መሆኑ ከተረጋገጠና ክርክር ያስነሳዉ ንብረት ግምት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ሥልጣን ሥር የሚወድቅ መሆኑ ካረጋገጠ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/4 መሰረት በዉክልና ጉዲዩን ተቀብል የመዲኘት ሥልጣን ይኖረዋል።ሆኖም በተያዘዉ ጉዲይ የግራ ቀኙ መደበኛ አድራሻ በአንድ ክልል ዉስጥ መሆኑ ከመረጋገጡም በላይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ዉል የተደረገዉና እንዱፈጸም የታቀደዉ መሬቱ በሚገኝበት ሐረሪ ክልል ዉስጥ በመሆኑ ጉዲዩን የፋዳራል ጉዲይ የሚያደርግ ምክንያት የለም።ስለሆነም የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን እንደፋዳራል ጉዲይ በመቁጠር በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት ሥልጣን አከራክሮ መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት መሻሩና ጉዲዩ የክልል ጉዲይ ነዉ ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል ስህተት የተፈጸመበት አይደለም።
በልላ በኩል የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በሰጠዉ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ተጠሪዎችን ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ካደረገ በኋላ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337ን በመጥቀስ የክልለ ሰበር የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መሰረዙን ከቀረበዉ ክርክር ተገንዝበናል። እስካሁን የሰበር ችልት ክርክሮችን የሚመራበት የተለየ ሥነ ሥርዓት ሕግ ባለመኖሩ በሥነ ሥርዓት ሕጎች ለመደበኛ ክስና ለይግባኝ ክርክሮች አመራር የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ለሰበር በሚሆን መልኩ አመሳስል ተግባራዊ የማድረግ የዲበረ የሰበር ችልቶች አሰራር መኖሩ ግልጽ ነዉ።በዚህ አግባብ የክልልም ሆነ የፋዳራል የሰበር ሰሚ ችልቶች የሥነ ሥርዓት ሕጉን ድንጋጌዎች ሲጠቀሙ በሥነ ሥርዓት ሕጎች የተዘረጋዉን የክርክር ሂደቶች አፈጻጸም ቅደም ተከተል በተቻለ መጠን በጥንቃቄ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።ለፍትሐ ብሓር ይግባኝ ክርክር አመራር በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 እና 338/1 መሰረት የይግባኝ ማመልከቻዉንና የመጀመሪያዉ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍርድ የሰጠበትን መዝገብ ግልባጭ በመመርምርና ይግባኝ ባይን በመስማት መልስ ሰጭ ቀርቦ እንዱከራከር ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ከሰጠ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ እንዱሁም ሕግን መርምሮ እንደነገሩ ሁኔታ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 341፣343/1 እና 348/1 መሰረት ዉሳኔ ላሰጥ ይገባል እንጂ ወደኋላ ተመልሶ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337ን በመጥቀስ የይግባኝ ማመልከቻዉ በመሰረዝ መወሰን የሚችልበት ሥነ ሥርዓት አግባብ የለም።በተመሳሳይ ለይግባኝ ክርክር አመራር የተቀመጠዉን ሥነ ሥርዓት በመጠቀም የሰበር ክርክር ሲመራም የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ የሆነ ወገን መልስ አቅርቦ እንዱከራከር ከተደረገ በኋላ በስር ፍርድ ቤት የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩ ተመርምሮ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ከተባለ እንዱታረም ካልሆነም የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱጸና ከሚወሰን በስተቀር ሂደቱን ወደኋላ በመመለስ የፍ/ብሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 ተጠቅሶ በሰበር ችልት እንዱመረመር የሚያስችል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ተብል የሰበር አቤቱታዉ የሚሰረዝበት አግባብ የለም።
በያዝነዉ ጉዲይ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩ በሰበር ችልት እንዱመረመር ትእዛዝ ሰጥቶ ተጠሪዎች መልስ ሰጥተዉ ከተከራከሩ በኋላ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337ን በመጥቀስ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በመሰረዝ ትእዛዝ የሰጠበት መንገድ ሉታረም የሚገባዉ የክርክር አመራር ጉድለት ነዉ።ሆኖም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት የይግባኝ ማመልከቻም ሆነ የሰበር አቤቱታን በመሰረዝ የሚሰጠዉ ዉሳኔ ከዉጤት አንጻር ሲታይ የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ የማጽናት ያክል ሕጋዊ ዉጤት ያለዉ ነዉ።በመሆኑም ከመነሻዉም ክርክሩ የፋዳራል ጉዲይ ባልሆነበት እንደፋዳራል ጉዲይ ተቆጥሮ የተወሰነበት የክርክር አመራር ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑና ጉዲዩ የክልል ጉዲይ ስለሆነ እንደአዱስ ክስ ቀርቦበት ሥልጣን ባለዉ በሐረሪ ክልል ፍርድ ቤት ታይቶ ሉወሰን የሚገባ ከመሆኑ አንጻር በማየት ከዚህ አኳያ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ዘንድ የተፈጠረዉን የክርክር አመራር ጉድለት አልፈነዋል።ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 26/01/2012 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 22/10/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ በመሻር የወሰነዉና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ በመ/ ላይ በቀን 24/03/2013ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንተዋል።
ይህ ዉሳኔ አመልካች ሥልጣን ባለዉ የክልለ ፍርድ ቤት ክስ ከማቅረብ አያግዲቸዉም።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ብለናል።
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዔግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.