በመደበኛ ፍርድ ቤት ከሚሰጥ ዉሳኔ በተለየ ሁኔታ በግልግል ዲኝነት በተሰጠ ዉሳኔ ላይ ይግባኝ የሚቀርበዉ በዘፈቀደ ሳይሆን በተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ ብቻ ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 351
No summary available.
መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) እንዲሻው አዲነ ተሾመ ሽፈራው ዋዚሞ ዋሲራ ሰናይት አድነው አመልካች- ሕብረት ኢንሹራንስ አ/ማህበር ተጠሪ- አቶ አብነት ለለ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የመድን ዋስትና ውልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በግልግል ዲኝነት ጉባኤ ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በአመልካች የመድን ዋስትና ሸፊን የተሰጠው የሰላዲ ቁጥር 3- 90277 ኢት/227791 የሆነው የተጠሪ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ከነተሳቢው ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም በሱማላ ክልል ሀረሬ ወንዝ በመሻገር ላይ እያለ በድልድይ መንሸራተት ምክንያት ተገልብጦ ወንዝ ውስጥ በመውደቁ የብር 2,000,000.00 ጉዲት ደርሶብኛል፤ አደጋ መድረሱን ለአመልካች አሳውቄ ካሳ እንዱከፍለኝ ጠይቄው ተሽርካሪውን አስነስቶ ወደ ሪከቨሪ ክፍል ውስጥ በማስገባት የሚጠገን መሆኑን ነግሮኝ ለ3 ወር አቆይቶታል፤ ሆኖም ግን ተሽከርካሪውን እንደማያስጠግንና ወጪውንም እንደማይሸፍን ስላሳወቀኝ በራሴ ወጪ በደቤ አስጠግኛለሁ፤ ስለዚህ አመልካች ለማስጠገኛ የወጣ ወጪ ብር 2,000,000.00፤ ለሶስት ወር አቆይቶ ሳያስጠግን በመመለሱ የ3 ወር የተቋረጠ ገቢ ብር 600,000.00 እንዱሁም የተሽከርካሪ ማስጫኛ (ለክሬን) ዋጋ ብል አመልካች የተቀበለኝን ብር 38,000.00 ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ።
አመልካች በበኩለ በሰጠዉ መልስ በተጠሪ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰው አደጋ ምክንያት ጎርፍ በመሆኑ በመድን ውል አንቀጽ II(12) እና በንግድ ሕግ አንቀጽ 663(1) እና 665(1) መሰረት ኃላፉነት የለብኝም፤ አሽከርካሪው የሀረሬ ወንዝ በጎርፍ መሙላቱን እያየና ሉያሳልፍ እንደማይችል እያወቀ ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረግ የደረሰ አደጋ ስለሆነና ይህም በመድን ውል አንቀጽ 6 ስር ተጠሪ ወይም አሽርካሪው ከአደጋ ወይም ከኪሳራ የመጠበቅ ግዳታ ስላልተወጣ ኃላፉነት የለብኝም፤ የድል አድ ወረዲ ፕሉስ ጽ/ቤት የአደጋውን ምክንያት ድልድይ በከፉል መናድ ነው ቢልም በአደጋው ቦታ ድልድይ የለም፤ በመሆኑም በማግለያ ድንጋጌ መሰረት ኃላፉነት የለብኝም፤ ለተሽከርካሪ ጥገና ብር 2,000,000.00 ወጪ አድርጌያለሁ በማለት የቀረበዉም የማስረጃ ድጋፍ የለውም፤ ከተሰጠው መጠን 50% በላይ ለጥገና ወጪ የሚያስፈልግ ከሆነ ካሳ ሉከፈል የሚገባው በጠቅላላ ውድመት ስለሆነ የካሳ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም፤ ተሽከርካሪውን ለማስጠገን የእጅ ዋጋ ብር 58,000.00 እና የመለዋወጫ ዔቃ ብር 822,756.76 በሰርቬር አስገምቼ በዋጋ ማቅረቢያ ሰብስቤ ስላረጋገጥኩ ሉከፈለው የሚገባው ይህ ነው፤ በመድን ውል II (2) እና VI(2) መሰረት ተጠሪ ላይ ለደረሰ የተቋረጠ ገቢ ወይም ተሸከርካሪውን ባለመጠቀም ለሚደርስ ኪሳራ ኃላፉነት የለብኝም፤ ኃላፉነት አለብህ ከተባልኩኝ ልከፍል የሚገባው ብር 822,756.76 ብቻ ነው ተብል ይወሰንልኝ በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው በአሽከርካሪው ቸልተኝነት ሳቢያ በውኃ ወደተሸፈነው የሀረሬ ወንዝ ሲነዲ ለተሽከርካሪዎች መተላለፉያ የተዘረጋው መሸጋገሪያ መንገድ በመናደና ተሸከርካሪው መንገድ በመሳቱ እንጂ በድንገተኛ ደራሽ ጎርፍ አለመሆኑን በማስረጃነት የቀረበው ቨዱዮ ጭምር የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሶ በተጠሪ ተሸከርካሪ ላይ ለደረሰ ጉዲት አመልካች ካሳ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ከሚል ድምዲሜ ላይ በመድረስ የኃላፉነት መጠንን አስመልክቶ ተጠሪ ለጥገና ወጪ እንዱከፈለው የጠየቀው ብር 2,000,000.00 ቢሆንም ይህ ጥያቄዉ እምነት በሚጣልበት ማስረጃ ተደግፍ ያልቀረበ ሲሆን በአንፃሩ አመልካች በራሱ ባለሙያ ለጋቢና ያስገመተዉን ብር 906,800.00 እንዱሁም በተጠሪ ማስረጃ የተረጋገጠዉ 161,000.00 ጨምሮ በድምሩ 0 የሚመጣ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ የአደጋ መነሻ ብር 53,390.00 ተቀንሶ ለመኪናዉ ጥገና የመለዋወጫ ዔቃ ብር 1,014,410.00 እንዱሁም ለተጎዲዉ መኪና ማጓጓዣ ተጠሪ ያወጣዉን ብር 38,000.00 ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል ካለ በኋላ ተጠሪ የገቢዉን መጠን የሚያሳይ ማስረጃ እንዱያቀርብ ታዞ አለማቅረቡን ጠቅሶ በአደጋዉ ምክንያት የተቋረጠ ጥቅም እንዱከፈለዉ ተጠሪ ያቀረቡትን ዲኝነት ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።
ግራ ቀኝ በዚህ ዉሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት በየግላቸው በመዝገብ ላይ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኝን የይግባኝ መዝገቦች አጣምሮ ካከራከረ በኋላ የግልግል ጉባኤው ኃላፉነትን በተመለከተ የሰጠውን የውሳኔ ክፍል በማፅናት በልላ በኩል ጉባኤው ጉዲት ለደረሰበት ተሽከርካሪ ማስጠገኛ እና የመለዋወጫ ዔቃዎችን ዋጋ መጠን እንዱሁም የተቋረጠ ጥቅም ዲኝነት ጥያቄን አስመልክቶ የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል በመሻር በድጋሚ አጣርቶ ተገቢዉን ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.343(1) መሰረት ለጉባኤው በመመለስ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የአመልካች የሰበር አቤቱታም የግልግል ጉባኤው እና የጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠዉን ውሳኔን በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሐምል 28 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በግልግል ዲኝነት ጉባኤው እና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተፈጽመዋል ያሎቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙለት ዲኝነት ጠይቋል። የአቤቱታው ይዘትም በአጭሩ የአደጋው ቦታ በጎርፍ ውሃ መሸፈኑን፣ አሽከርካሪው ውሃ እስከኪጎድል መጠበቅ ሲገባው ላልች ከኋላው ያለት አሽከርካሪዎች ውሃው እስኪጎድል እየተጠባበቁ የተጠሪ ተሽከርካሪ ሹፋር ግን በድፍረት በውሃ ወደተሸፈነው በመግባት መንገደን መለየት ባለመቻለ አደጋው የደረሰ ስለመሆኑ የግልግል ጉባኤውም ሆነ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት አረጋግጠዉ ነገር ግን የመድን ውለን የማግለያ ድንጋጌ ያለአግባብ በመተርጎም በተጠሪ ተሽከርካሪ ላይ አደጋ የደረሰው ድንገተኛ ደራሽ በሆነ ጎርፍ ሳይሆን በአሽከርካሪው ቸልተኝነት ምክንያት ነው በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፤ በአደጋው ቦታ ድልድይ አለመኖሩን በቨዱዮ፣ በፍቶግራፍ እና በምስክር ተረጋግጦ እያለ የድል ኦዲ ወረዲ ትራፉክ ፕሉስ ጽ/ቤት ተገቢውን የሙያ ደንብ ሳይከተል የአደጋ ምክንያት የድልድዩ ድንገተኛ በከፉል መናድ ነው ሲል የሰጠውን ሪፕርት የግልግል ጉባኤው እና የስር ፍርድ ቤት ተገቢ ነው ሲለ የሰጡት ወሳኔ ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ላይ የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሚቃረን ነው፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች የተቋረጠ ገቢ ሉከፍል ይገባል ማለቱ እና መጠኑም በርትዔም እንዱወሰን ለጉባኤው መመለሱም መሰረታዊ ስህተት ነው የሚል ነዉ።
የሰበር አቤቱታዉም በአጣሪ ችልት ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለም ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም በተፃፈ መልሳቸው ማስረጃን የሚመለከት ክርክር ለሰበር ላቀርብ አይችልም። የስር የግልግል ዲኝነት ጉባኤ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አደጋዉ የደረሰዉ በጎርፍ ሳይሆን በሾፋሩ ጥፊት ምክንያት ነዉ ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረሱ ሲሆን ለሾፋሩ ጥፊት ደግሞ አመልካች ኃላፉነት ያለበት ከመሆኑ አኳያ ውሳኔዉ ስህተት ስለላለበት አቤቱታው ውድቅ እንዱደረግልኝ በማለት ተከራክሯል። አመልካች የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክስ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ በአመልካች የመድን ሽፊን የተሰጠዉ ተሽከርካሪዉ በደረሰበት አደጋ ምክንያት ለጥገና እና ለመለዋወጫ የወጣዉን ወጪ እንዱሁም ለተቋረጠ ጥቅም ካሳ ለመክፈል አመልካች ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ሲሆን፣ አመልካች በበኩለ ጉዲት ለደረሰበት የተጠሪ ተሽከርካሪ የመድን ሽፊን መስጠቱን ሳይክድ ኃላፉነት የለብኝም በማለት አጥብቆ የሚከራከረዉ አደጋዉ የደረሰዉ በጎርፍ ምክንያት መሆኑን እና በጎርፍ ምክንያት ለደረሰዉ አደጋ ደግሞ በመድን ዉለ የማግለያ ድንጋጌ መሰረት ኃላፉነት የላለበት መሆኑን በመጥቀስ ነዉ።
በርግጥ በጎርፍ ምክንያት በተሽከርካሪዉ ላይ ለሚደርስ አደጋ አመልካች ካሳ የመክፈል ኃላፉነት እንደላለበት በመድን ዉለ የማግለያ አንቀጽ II (12) ላይ የተመለከተ ስለመሆኑ ግራ ቀኝ የሚታማመኑበት ነዉ። አከራካሪዉ ነጥብ አደጋዉ የደረሰዉ በርግጥ በጎርፍ ምክንያት ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ ነዉ። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉን ይህንኑ በጭብጥነት በመያዝ “ጎርፍ” ለሚለዉ ቃል በተለያዩ መዝገበ ቃላት የሚሰጡ ትርጉሞችን በዋቢነት በመጥቀስ የጎርፍ ዉሃ መጠኑ ከፍተኛ እንደሆነ፣ ድንገተኛ እና ከመደበኛ ቦታዉ በመዉጣት ሰፉ ቦታን በመሸፈን እና መስመርን በመጣስ የመፍሰስ ባህሪ ያለዉ መሆኑን ደምድሞ በተያዘዉ ጉዲይ በሀረሬ ወንዝ ላይ ዉሃዉ ሲፈስ የነበረዉ የፍሳሽ መስመሩን ይዞ መሆኑን፣ መኪናዉ ወደ ወንዙ የገባዉና የመገልበጥ አደጋ የደረሰበት ዉሃዉ መስመሩን ይዞ እየሄደ እንጂ በድንገት በመጣ ደራሽ ዉሃ አለመሆኑን፣ የዉሃዉ መጠንም ሰዎች ከተገለበጠዉ መኪና ወጥተዉ በቀላለ ሲጓዙበት እንደነበረ እና አደጋዉ የደረሰዉም የተጠሪ ተሽከርካሪ ሹፋር መኪናዉን ወደ ዉሃዉ በመንዲቱ እንጂ ዉሃዉ ዉስጥ ከገባ በኋላ በመጣ ዉሃ ምክንያት አለመሆኑን ከድምዲሜ ላይ ደርሷል። በዚህ ድምዲሜ ላይ ሲደርስ በዋነኝነት ዋቢ ያደረገዉም የቀረበለትን የቪዱዮ ማስረጃ ስለመሆኑ የዉሳኔዉ ይዘት ያሳያል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይህን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ተቀብልታል።
ሁለቱም የዲኝነት ሰጪ አካላት በዚህ የፍሬ ነገር ድምዲሜ ላይ ሲደርሱ ከማስረጃ አቀባበል እና የምዘና መርህ ጋር በተያያዘ የፈጸሙት ስህተት ስለመኖሩ ዉሳኔዎቹ አያሳዩም። የማግለያ ድንጋጌዉ ከላይ በተመለከተዉ ሁኔታ በመድን ዉለ የተመለከተበት ምክንያትም አስቀድሞ መገመት በማይቻል፣ ድንገተኛ እና ከቁጥጥር ዉጪ በሆነ ሁኔታ ለሚደርስ አደጋ አመልካች ኃላፉነት ሉኖርበት አይገባም በሚል መነሻ እንደሆነ ይታመናል። በመሆኑም አደጋዉ የደረሰዉ በድንገት በደረሰ ጎርፍ ምክንያት ሳይሆን አሽከርካሪዉ መስመሩን ይዞ በሚሄድ እና ሰዉም ሉሻገርበት ወደሚችል ዉሃ መኪናዉን በመንዲቱ ምክንያት የተረጋገጠ ከመሆኑ አኳያ በመድን ዉለ ላይ የተመለከተዉ የማግለያ ድንጋጌ ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈፃሚነት የለዉም። በመሆኑም አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበዉን ክርክር ዉድቅ በማድረግ በግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጸናዉ ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ከዚህ ጋር በተያያዘ አመልካች የሚያቀርበዉን ክርክር ይህ ችልት አልተቀበለዉም።
በመቀጠል መታየት ያለበት ነጥብ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመኪናዉ ጥገና እና መለዋወጫ የወጣዉን ወጪ እንዱሁም የተቋረጠ ጥቅምን አስመልክቶ በድጋሚ ተጣርቶ እንዱወሰን ጉዲዩን ወደ ግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የመለሰበትን አግባብነት ነዉ። ከላይ በተደጋጋሚ እንደተገለጸዉ ክርክሩ የተጀመረዉ በግልግል ዲኝነት ጉባኤ ላይ ነዉ። የግልግል ዲኝነት ከመደበኛ ፍርድ ቤት ዉጪ ዲኝነት ከሚታዩባቸዉ አማራጭ የሙግት መፍቻ መንገድች ዉስጥ አንደ ስለመሆኑ የሚታወቅ ነዉ።
አለመግባባቶችን በግልግል ዲኝነት መፍታት በተከራካሪ ወገኖች መካከል ያለዉ አለመግባባት በአነስተኛ ወጪ እና በአጭር ጊዜ እልባት እንዱያገኝ ማድረግ የሚያስችል እንዱሁም የፍርድ ቤቶችን የስራ ጫና እንዱቀንስ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዲለዉ የሚታወቅ ነዉ። ስለሆነም በተቻለ መጠን በግልግል ዲኝነት የሚሰጥ ዉሳኔ የመጨረሻ ሆኖ ተፈፃሚ ላሆን የሚችልበትን ሥርዓት ማበጀት እና ተግባራዊ የማድረጉ አስፈላጊነት አያጠያይቅም። የግልግል ዲኝነትንና የእርቅ ሥርዓትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 49 በግልግል ዲኝነት ዉሳኔ ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻልበትን ሁኔታ የገደበዉም በዚሁ መነሻነት እንደሆነ ይታመናል። የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉም በግልግል ዲኝነት ዉሳኔ ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻለዉ የተወሰኑ ሁኔታዎች ሲሟለ ብቻ መሆኑን በመደንገግ በይግባኝ አቀራረብ ላይ ገደብ ያስቀምጣል። በዚህም መሰረት በግልግል ዲኝነት ዉሳኔ ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻለዉ ዉሳኔዉ የተለያየ ወይም አንደ ክፍል ከላላዉ ጋር የማይገናኝ ወይም የማይስማማ ወይም ግልጽ ያልሆነ ወይም የሚያጠራጥር ወይም በቀጥታ በህግና በፍሬ ነገሩ ረገድ የተሳሳተ ሲሆን፤
ጉባኤዉ የቀረበለትን ዲኝነት ሳይወስን ከቀረ፤ ክርክሩ በሚሰማበት ጊዜ ከሥነ ሥርዓት ዉጪ የሆነ ነገር የተፈጸመ እንደሆነ እንዱሁም ከዳኞች አንደ አባል የሥነ ምግባር ግድፈት ወይም የአድልአዊነት ተግባር ያሳየ ሲሆን ብቻ ስለመሆኑ በህጉ አንቀጽ 351 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ከዚህ ሁለ የምንገነዘበዉ በመደበኛ ፍርድ ቤት ከሚሰጥ ዉሳኔ በተለየ ሁኔታ በግልግል ዲኝነት በተሰጠ ዉሳኔ ላይ ይግባኝ የሚቀርበዉ በዘፈቀደ ሳይሆን በተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ ብቻ መሆኑን ነዉ።
በተያዘዉ ጉዲይ፣ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ፣ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ጉዲት የደረሰበትን ተሽከርካሪ ለማስጠገን እና የመለዋወጫ ዔቃዎችን ለመግዛት ሉወጣ የሚችለዉን ወጪ መጠን የወሰነዉ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረባቸዉ ማስረጃዎች እምነት የሚጣልባቸዉ አለመሆኑና በአንፃሩ በአመልካች በእራሱ ባለሙያዎች ተገምቶ የቀረበዉ አሳማኝ ሆኖ መገኘቱን በመጥቀስ ነዉ። የተቋረጠ ጥቅምን አስመልክቶ ለሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ያደረገዉም የገቢ መጠንን አስመልክቶ ከህብረት ባንክ እንዱያቀርብ የታዘዘዉን ማስረጃ ተጠሪ ማቅረብ አለመቻለን በግልጽ በማመላከት ነዉ። የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ በዚህ አግባብ ዉሳኔ ሲሰጥ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 351 ስር ከተመለከቱት እና ለይግባኝ ምክንያት ሉሆኑ ከሚችለ ስህተቶች አንደንም የፈጸመ ስለመሆኑ ዉሳኔዉ አያሳይም። ከዚህ አንፃር ሲታይ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር በድጋሚ አጣርቶ ለተጠሪ የሚገባዉን የካሳ መጠን እንዱወስን ጉዲዩን ወደ ግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ በመመለስ የሰጠዉ ዉሳኔ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉን አንቀጽ 351 ድንጋጌን ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ የአመልካችን ኃላፉነት አስመልክቶ በግልግል ዲኝነት ጉባኤ የተሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ቢሆንም ለተጠሪ ሉከፈል የሚገባዉን ካሳ እና መጠኑን አስመልክቶ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ኃላፉነትን አስመልክቶ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉን ዉሳኔ በማጽናት የሰጠዉ የዉሳኔ ክፍል ጸንቷል፤ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 343(1) መሰረት ጉዲዩን ወደ ግልግል ዲኝነት በመመለስ የሰጠዉ የዉሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ
No topics extracted.