የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ለክርክር ይጠቅመናል በማለት በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት ጊዜ የሚያቀርቡትን ማስረጃ አሟጦ የማሰማት መብት በህገ መንግስቱ አንቀፅ 20(4) በተደነገገው መሰረት ተከሳሽ ለክሱ መልስ በሰጠበት ወቅት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ አንቀፅ 234(1)(መ) መሰረት ከመከላከያ መልሱ ጋር የሰው ማስረጃ ዝርዝር አያይዘው ያቀረቡ ስለመሆናቸው ከሳሽ ካቀረቡት መልስ ጋር ተያይዞ የማስረጃ ዝርዝር አብሮ የቀረበ መሆኑ አከራካሪ ባልሆነበት ፍርድ ቤት የተከሳሽ ማስረጃን ያልሰማበትን ምክንያት ካለ በመዝገብ ውስጥ በግልፅ ሳይጠቅስ ተከሳሽ በተቃራኒ ማስረጃ አላስረደም በማለት የሚሰጥ ውሳኔ ማስረጃ የማሰማት ህገ መንግስታዊ መብትን የሚጥስ ስለመሆኑ ተከሳሽ የሰነድ ማስረጃ ከመንግስታዊ ተቋም በፍርድ ቤት በኩል እንዱቀርብ አመልክቶ/ታ እንዱቀርብ የተጠየቀው የሰነድ ማስረጃ እና መከላከያ መልሶች ጋር ተያይዘው የቀረቡ የሰው ምስክሮች ቃል ሳይሰማ ተከሳሽ በማስረጃ አላስረደም በማለት የሰው ማስረጃም ሆነ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ አንቀፅ 145 መሰረት በፍርድ ቤት በኩል እንዱቀርብ የተጠየቀው ማስረጃ ሳይቀርብ እና ሳይሰማ የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የላለው ም/ኢንስፓክተር በሱፍቃድ እስጢፊኖስ እና ወ/ሮ ትዔግስት እስጢፊኖስ
No summary available.
ቀን - 26/07/2016 ዓ.ም ዳኞች- ሱልጣን አባተማም ገበየሁ ፈለቀ አለማየሁ ሹናራ አብርሃ መሰለ ተናኜ ጥላሁን አመልካች- ም/ኢንስፓክተር በሱፍቃድ እስጢፊኖስ - አልቀረቡም ተጠሪ- ወ/ሮ ትዔግስት እስጢፊኖስ - አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ስለሆነ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ይዘቱ በአጭሩ በካርታ ቁጥር ቦላ10/97/724/00 ተመዝግቦ የሚገኝ በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 13 የቦታ ስፊቱ 73.5 ካሬ ሜትር የሆነውን የግል መኖሪያ ቤቴን ተከሳሽ ወንድሜ ስለሆነ ትዲር ሲይዝ እንዲይቸገር ብዬ ለጊዜው እንዱኖርበት ሰጥቼ 6 አመት ከኖረ በኋላ እንዱያስረክበኝ ስጠይቀው ለማስረከብ ፍቃደኛ ስላልሆነ ለቆ እንዱያስረክበኝ እንዱወስን የሚል ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት ካርታው በከሳሽ ስም ቢሆንም የሟች እናታችን የወ/ሮ ዘውድነሽ መኮንን የውርስ ሀብት እንጂ የከሳሽ አይደለም። ከሳሽ ታላቅ እህታችን በመሆናቸው የሁላችንም የውርስ ሀብት የሆነውን ቤት ከህግ አግባብ ውጭ በራሳቸው ስም አስመዝግበዋል። ለከሳሽ ውክልና ከሰጠናቸው በኋላ ከቅን ልቦና ውጭ በስማቸው ከማስመዝግብ ውጭ የግላቸው አይደለም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
የስር ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ቤቱን ለከሳሽ ሉያስረክብ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መርምሮ ለክርክሩ መነሻ ለሆነው ቤት ካርታ የተሰጠው በከሳሽ ስም መሆኑን፣ ቤቱን ከሳሽ ከአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቦላ ክፍለ ከተማ የቤት ማስተላለፍ ፅ/ቤት ጋር ባደረጉት የቤት ሽያጭ ውል መሰረት ያገኙ መሆኑን የሚያስረዲ የሰነድ ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ ተከሳሽ ቤቱን ለከሳሽ እንዱያስረክብ ሲል ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን የፋድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በቀን 20/03/2015 አ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት ወስኗል። የአሁን ሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ቅር በመሰኘት ነው። የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ የፋድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ አንቀፅ 145 መሰረት እንዱቀርቡልኝ የጠየቋቸውን ማስረጃዎች ሳያስቀርብ ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው። እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ፍሬ ነገሩን በሰው ምስክሮች ማረጋገጥ ሲገባው ማስረጃ ሳይሰማ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ እንዱሻርልኝ የሚል ነው።
ይህ ችልትም አመልካች በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ አንቀፅ 145 መሰረት እንዱቀርብላቸው የጠየቁትን ማስረጃ ፍርድ ቤቱ ሳያስቀርብ እና ማስረጃ አሟጦ ሳይሰማ የወሰነበት አግባብነት ከማስረጃ ምዘና መርህ አንፃር ለማጣራት ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ የበኩላቸውን መልስ አቅርበዋል። ፍሬ ቃለ በአጭሩ የስር ፍርድ ቤት ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት የሰነድ ማስረጃ አሰባስቦ ቤቱ የተጠሪ መሆኑን አረጋግጦ የሰጠው ፍርድ የሚነቀፍ አለመሆኑን፣ የስር ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ከሚመለከታቸው ፅ/ቤቶች ማስረጃ እንዱያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ አመልካች ማስረጃ አላቀረቡም፤ በቀጠሮ ቀን እራሳቸውም አልቀረቡም።
ስለዚህ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ፍርድ በማስረጃ በሚገባ አጣርቶ የሰጠው ውሳኔ በመሆኑ እንዱፀናልኝ የሚል መልስ ሰጥተዋል። አመልካች የመልስ መልሱን አቅርቦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ በተገለፀው መሰረት የተጠቃለለ በመሆኑ እኛም ያስቀርባል ከተባለው ነጥብ አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል። መርምረን እንድተረዲነው፡ - በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ በአጭሩ በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 13 የቦታ ስፊቱ 73.5 ካሬ ሜትር የሆነው የግል መኖሪያ ቤቱን ተከሳሽ ወንድሜ በመሆኑ ትዲር ሲመሰርት እንዲይቸገር ብዬ ለጊዜው እንዱኖርበት የሰጠሁትን እንዱመልስ ጠይቄ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ስላልሆነ እንዱያስረክበኝ የሚል ክስ ሲሆን የአሁን አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የከሳሻ ሳይሆን የእናታችን የወ/ሮ ዘውድነሽ መኮንን ቤት በመሆኑ የውርስ ንብረት ነው እንጂ የከሳሽ የግል ቤት አይደለም። ከሳሽ ታላቅ እህታችን በመሆናቸው ቤቱን እንዱያስተዲድሩ ውክልና ሰጥተን የቤቱ ስመ ሀብትነቱን ወደ ራሳቸው ስም አዞሩ እንጅ የውርስ ንብረት ነው በማለት መከላከያ መልስ ከማስረጃ ዝርዝር ጋር አቅርበዋል። በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ አንቀፅ 145 መሰረት የሰነድ ማስረጃ ከመንግስታዊ ተቋም በፍርድ ቤት በኩል እንዱቀርብ አመልክተዋል። የስር ፍርድ ቤትም የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ገቢዎች ቢሮ የቦላ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፊዮች ቅ/ፅ/ቤት በመጠየቅ ከተላከው ማስረጃ እና ማህደሩን በማስቀረብ መርምሮ ተከሳሽ ቤቱ በውርስ የተገኘ ነው ከማለት ውጭ በውርስ ስለመገኘቱ በምትክነት የተሰጠ ስለመሆኑ እናታቸው ለተከሳሽ እና ለልጆቻቸው ያወረሱ ስለመሆኑ እና ቤቱ የከሳሽ አለመሆኑን ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ አላስረደም በማለት ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት አመልካች (ተከሳሽ) ለተጠሪ (ከሳሽ) እንዱያስረክቡ ሲል ወስኗል። የአመልካች ቅሬታ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ አንቀፅ 145 መሰረት እንዱቀርብ የጠየቁት ሰነድ ማስረጃ እና ከመከላከያ መልሶቼ ጋር አያይዤ ያቀረብኳቸው የሰው ምስክሮች ቃል ሳይሰማ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው በማለት ተከራክሯል። በመሰረቱ የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ለክርክር ይጠቅመናል በማለት በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት ጊዜ የሚያቀርቡትን ማስረጃ አሟጦ የማሰማት መብት በህገ መንግስቱ አንቀፅ 20(4) በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል። አመልካች በዚህ ድንጋጌ መሰረት ለክሱ መልስ በሰጡበት ወቅት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ አንቀፅ 234(1)(መ) መሰረት ከመከላከያ መልሳቸው ጋር የሰው ማስረጃ ዝርዝር አያይዘው ያቀረቡ ስለመሆናቸው አመልካች ካቀረቡት መልስ ጋር ተያይዞ የማስረጃ ዝርዝር አብሮ የቀረበ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። የስር ፍርድ ቤት ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው የመንግስት መስሪያ ቤት መግለጫ እንዱልክ ካደረገ በኋላ ማህደሩንም በማስቀረብ አይቶ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች ቤቱ የውርስ ቤት ስለመሆኑ በማስረጃ አላስረደም በማለት ቤቱን እንዱለቁ የወሰነው የአመልካች የሰው ማስረጃም ሆነ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ አንቀፅ 145 መሰረት በፍርድ ቤት በኩል እንዱቀርብ የጠየቀውን ማስረጃ ሳይቀርብ እና ሳይሰማ መሆኑን መዝገቡ ያስረዲል። የስር ፍርድ ቤት የአመልካች ማስረጃ ሳይሰማ ያለፈበት ምክንያት ምን እንደሆነ በመዝገቡ ውስጥ በግልፅ አልጠቀሱም። በአመልካች በኩል የተቆጠረው ማስረጃ ሳይሰማ እና ያልሰማበት ምክንያት ካለ ምክንያቱን በግልፅ መዝገብ ውስጥ ሳይገልፅ ቤቱ የውርስ ቤት ስለመሆኑ አመልካች በተቃራኒ ማስረጃ አላስረዲም ማለቱ ማስረጃ የማሰማት ህገ መንግስታዊ መብትን የሚጥስ ውሳኔ ሆኖ አግኝተነዋል። ሲጠቃለል አመልካች ለክሱ መልስ በሚሰጡበት ጊዜ የመከላከያ ማስረጃ ዝርዝር አያይዘው አቅርበው እያለ የስር ፍርድ ቤት የአመልካች ማስረጃን ያልሰማበትን ምክንያት ካለ በመዝገብ ውስጥ በግልፅ ሳይጠቅስ አመልካች በተቃራኒ ማስረጃ አላስረደም ማለቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦላ ምድብ ችልት በመዝገብ በቀን 09/05/2014 አ.ም የሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በቀን 20/03/2015 አ.ም ያፀናው ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ አንቀፅ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ከአመልካች በኩል የተዘረዘሩ የሰው ምስክሮች እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ አንቀፅ 145 መሰረት እንዱቀርቡ የጠየቁትን የሰነድ ማስረጃ በማስቀረብ እንዱሁም ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስፈላጊ ከሆነ ተጠሪ ቤቱን ከመንግስት የገዙበትን ሁኔታ ጭምር በማስረጃ በማጣራት እንዱወስን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ አንቀፅ 343(1) መሰረት መልሰናል።
በዚህ ችልት ግራ ቀኙ ያወጡትን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻቻለ ብለናል።
No topics extracted.