No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- የሺ ኃ/የተ/የግ/ማህበር - አልቀረቡም ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ መኪና መገጣጠሚ ኩባንያ (አምቼ) - ጠበቃ በላይ ከተማ - ቀርቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ክርክሩ የመኪና ሽያጭ ውልን መሰረት ያደረገ ሲሆን ጉዲዩ በተጀመረበት የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው ክስ ከግንቦት 2004 ዓ.ም እስከ ህዲር 2007 ዓ.ም በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ 4 ውልች ቲ 38 ኤች ሲ ካብ መኪናዎች፣ ኤቬኮ ኤቲ 720 ቲኤች መኪናዎች እንዱሁም ፋንግሺን ሀይቦድ ሰሚ ትሬለሮችን ተጠሪ ለአመልካች በድምሩ በብር 100,850,000 (አንድ መቶ ሚሉዮን ስምንት መቶ ሀምሳ ሺ) ሽጧል። እስከ ጥር 22 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ወለድና ቅጣትን ጨምሮ አመልካች ከሚፈለግበት ጠቅላላ ገንዘብ ብር 111,420,995.00 (አንድ መቶ አስራ አንድ ሺ አራት መቶ ሀያ ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አምስት) ላይ ብር 80,116,620.00(ሰማንያ ሚሉዮን አንድ መቶ አስራ ስድስት ሺ ስድስት መቶ ሀያ) ክፍያ የፈጸመ ሲሆን ቀሪ ክፍያውን ብር 31,306,375 (ሰላሳ አንድ ሚሉዮን ሶስት መቶ ስድስት ሺ ሶስት መቶ ሰባ አምስት) እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
አመልካች ግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው መልስ ከተጠሪ ጋር የመኪና ሽያጭ ውል ማድረጉን ሳይክድ በውልቹ የተመለከተውን ዋጋ በቅድመ ክፍያ እና በየወሩ በደረሰኝ የከፈልን ሲሆን አሁንም እየከፈልን እንገኛለን። ተጠሪ እ.አ.አ. መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም በቁጥር 114/2016 ለአመልካች በፃፈው ደብዲቤ እስከ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ያልተከፈለው ቀሪ እዲ ብር 18,703,775.55 መሆኑን ገልጿል። ከዚህ ጊዜ በኋላ አመልካች ብር 3,132,965.31 የከፈለ ሲሆን ወ/ሮ ሮዛ ለአመልካች መክፈል የነበረባቸውን ብር 3,866,707 ከተጠሪ ለገዛናቸው መኪኖች እዲ መክፈያ እንዱሆን ጥቅምት 18 ቀን 2010 ዓ.ም በተዋዋልነው መሰረት ክፍያውን ለተጠሪ ፈፅመዋል።
አመልካች ከተጠሪ ለገዛቸው 33 ተሽከርካሪዎች ከእያንዲንደ ተሽከርካሪ የተሽከርካሪውን ዋጋ 3% ኮሚሽን ተጠሪ ለአመልካች ሉከፍል ወይም ከእዲው ተቀናሽ ላደረግ የተስማማንበት ብር 2,917,500፣ ተሽከርካሪዎቹን ከውጪ ሀገር ለማስመጣት የሚያስችል የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት በባንክ የኤልሲ ሂሳብ ሲከፈት ለአመልካች የሚከፈል 6% ኮሚሽን ብር 877,799፣ አመልካች ለገዛቸው እያንዲንደ መኪና ከዋጋው ላይ 2% ዊዝሆልዱንግ ብር 2,017,000፣ ለእያንዲንደ መኪና ብር 100,000 የሚያወጣ መለዋወጫ ሉታሰብልን ስምምነት የተደረገበት የ26 መኪኖች ብር 2,600,000 ተቀናሽ አልተደረገም።
ከላይ የተዘረዘሩት ተቀናሾች በድምሩ ብር 15,411,971.34 በደረሰኝ ከከፈልነው ብር 82,146,244.79 ጋር ተደምሮ የሚመጣው ብር 97,558,215.79 ከጠቅላላ ዋጋው ብር 100,650,000 ላይ ተቀናሽ ሲደረግ ልንከፍል የሚገባው ቀሪ ክፍያ ብር 3,291,784.21 ብቻ ነው በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ አመልካች እስከ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ያልተከፈለ ቀሪ እዲ ብር 18,703,775.55 መሆኑን ተጠሪ ገልጿል በማለት የሚከራከር ቢሆንም የደብዲቤው ይዘት የተጠቀሰው ገንዘቡ ካልተከፈለው የመኪና እዲ ጋር የሚገናኝ ስለመሆኑ አያመላክትም፤ ብር 3,132,965.31 ስለመክፈለም ያቀረበው ማስረጃ የለም። አመልካች በጠየቀው መሰረት ቀሪ እዲው በገለልተኛ ባለሞያ እንዱጣራ ታዞ ሶልያና ኪሮስ የተመሰከረላቸው የሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዱተሮች በሪፕርታቸው የአመልካች ክርክር በማስረጃ እንዲልተደገፈ ያሳወቀ በመሆኑ ይህ ገንዘብ በአመልካች እንዲልተከፈለ ፍ/ቤቱ ተገንዝቧል። ወ/ሮ ሮዛ ዱፊብር የከፈለት ብር 3,866,707 ለአመልካች እዲ የተከፈለ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የለም ሪፕርቱም ይህን ያረጋግጣል። ሰኔ 11 ቀን 2008 በተደረገው ስምምነት ተጠሪ 3% ኮሚሽን እንደሚከፍል የተገለፀ ቢሆንም ከአመልካች እዲ ላይ ተቀናሽ የሚደረግ ስለመሆኑ አልተገለፀም። ተጠሪ ክሱን ሲያቀርብ 2% ዊዝሆልዱንግ ተቀናሽ አድርጓል። በመኪና ውልቹ ተጠሪ ለሁለም መኪኖች ብር 100,000 የሚገመት የመለዋወጫ እቃ እንደሚሰጥ የተስማሙ ቢሆንም ለእያንዲንደ መኪና ብር 100,000 የሚገመት የመለዋወጫ እቃ እንደሚሰጥ የተስማሙ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የለም። በፍ/ሕ/ቀጥር 1890(2) መሰረት ውል እንዱፈጸም እና መቀጮ እንዱከፈል በአንድነት መጠየቅ የማይቻል ስለሆነ ተጠሪ መቀጮ እንዱከፈለው መጠየቁ አግባብ አይደለም። በመሆኑም በቀረበው የሂሳብ ሪፕርት መሰረት እንዲልተከፈለ የተረጋገጠው እዲ ብር 22,880,231.14፣ በውለ መሰረት ያልተከፈለና የዘገየ ወለድ ብር 1,077,812፣ ክፍያ ከተቋረጠ በኋላ ያለው ወለድ ብር 2,809,444 በድምሩ ብር 26,767,487.14 ከጥር 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍል እስኪያልቅ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት ወስኗል።
No topics extracted.
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት በአብላጫ ድምፅ ቅሬታው ተሰርዟል።
አመልካች ህዲር 2013 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታውን ያቀረበው ይህን የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማሳረም ነው። የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ አመልካች ብር 18,703,775 ያለበት መሆኑን ገልፆ ተጠሪ የፃፈውን ደብዲቤ አመልካች በማስረጃነት አቅርቧል፤ ተጠሪም ይህን ማስረጃ በማስተባበል ያቀረበው ክርክር የለም፤ አስፈላጊ ከሆነም በጉዲዩ ላይ የሰው ምስክር ሉሰማ እየተገባ ለክርክሩ መነሻ ለሆነው እዲ የተፃፈ ስለመሆኑ አያስረዲም በሚል የስር ፍ/ቤት ውድቅ ማድረጉ፤ በወ/ሮ ሮዛ ዱፊቬሪ የተከፈለው ብር 3,866,707 ከአመልካች እዲ ጋር ያለው ግንኙነት በግለሰቧ ምስክርነት አለመጣራቱ፣ አመልካች ከተጠሪ ለገዛቸው ተሽከርካሪዎች ሉከፈል የሚገባው ኮሚሽን ብር 2,917,500 ከጠቅላላ እዲው እንዱቻቻልኝ ያቀረብኩት ጥያቄ ውድቅ መደረጉ፣ በውልቹ በቅድመ ክፍያነት መከፈለ የተገለፀው በድምሩ ብር 5,350,000 ከአመልካች እዲ ላይ ተቀናሽ አለመደረጉ፣ ለእያንዲንደ መኪና ግዢ የመለዋወጫ እቃ ብር 100,000 ተቀናሽ ሳይደረግ መወሰኑ፤ በሑሳብ አጣሪ ሪፕርት ተቀናሽ መደረጉ የተገለፀው ብር 5,350,000 ከእዲው ላይ የተቀነሰበት ምክንያት አለመጣራቱ፣ ክፍያ ከተቋረጠ በኋላ የዘገየ ወለድ ውስጥ የተካተተን ወለድ ሁለት ግዜ እንድንከፍል መወሰኑ መሰረታዊ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ከደቤ የመኪና ሽያጩ ጋር በተያያዘ በቀረበው የሂሳብ ምርመራ ሪፕርት መሰረት ከአመልካች እዲ ተቀናሽ መደረግ የነበረበት የቅድመ ክፍያ ብር 5,350,000 በተመለከተ በቂ ማስረጃ አልቀረበበትም ተብል በኦዱተር ውድቅ የመደረጉን፤ አስቀድሞ ተቀናሽ መደረግ አለመደረጉን እና ተያያዥ ነጥቦች ለማጣራት ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልሱን እንዱያቀርብ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
ተጠሪ ህዲር 28 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ መልሱን አቅርቧል። የመልሱ ይዘት ባጭሩ ያልተከፈለውን እዲ እንዱመረምር የታዘዘው ገለልተኛ የሂሳብ ባለሞያ አመልካች ክፍያ ስለመፈፀሙ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ከእዲው ጋር እንደማይገናኙ እና ወለድ ሳይታሰብ ቀሪ እዲው ብር 22,880,231.14 መሆኑን አረጋግጧል። አመልካች ሪፕርቱን በመቃወም እንዱሁም ተጠሪ ወለድ አለመካተቱን ገልፆ ለፍ/ቤቱ ባቀረበው ቅሬታ መሰረት እንደገና እንዱጣራ ታዞ ቅጣት እና ወለድን ጨምሮ እዲው ብር 29,055,279.88 መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ፍ/ቤቱ መቀጮውን ቀንሶ ብር 26,767,487 እንዱከፈል መወሰኑ ተገቢ ነው። አመልካች ብር 18,703,775 እዲ እንዲለበት ተጠሪ ገልፆ የፃፈው ደብዲቤ እስከ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ያለውን ቀሪ ሂሳብ እና ወለድ የሚመለከት ሲሆን ክስ የቀረበበት ሑሳብ የተሰላው እስከ ጥር 2010 ዓ.ም ያለውን ወለድ ጨምሮ ስለሆነ የአመልካች ቅሬታ ተገቢነት የለውም።
ወ/ሮ ሮዛ ዱፊብሪ የተዋዋለት ከአመልካች ጋር ሲሆን በሰነድ መከፈለን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አልቀረበም፤ የኮሚሽን ክፍያውም በ2000 ዓ.ም ተፈርሞ በ2001 ዓ.ም ያበቃ ውል እንጂ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ከ2004 እስከ 2007 ዓ.ም የተደረገን ውል የሚመለከት አይደለም፤ አመልካች በውለ ላይ ተቀናሽ የተደረገ ብር 5,350,000 ከእዲው ተቀናሽ አለመደረጉን ጠቅሶ የሚከራከር ቢሆንም ተጠሪ ክሱን የመሰረተው አመልካች የከፈላቸውን እያንዲንደን ገንዘብ ተቀናሽ በማድረግ ሲሆን ሂሳብ አጣሪውም ይህ ገንዘብ ለመከፈለ የቀረበ ማስረጃ የላለ መሆኑን ጠቅሶ ውድቅ አድርጎታል። ወለድም ሆነ የዘገየ ወለድ የታሰበው ውለን መሰረት አድርጎ በመሆኑ አቤቱታው ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክሯክል።
አመልካችም የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ጉዲዩ ያስቀርባል ሲባል የተያዘወን ጭብጥ በስር ፍ/ቤት ከተደረጉ ክርክሮች፣ በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዱሁም ለጉዲዩ ተገቢነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
እንደመረመርነውም አመልካች በዋናነት የሚከራከረው የአመልካች እዲ ብር 18,703,775 መሆኑን ተጠሪ ገልፆ የፃፈው ደብዲቤ ከእዲው ጋር የሚገናኝ አይደለም መባለ፣ በወ/ሮ ሮዛ ዱፊቬሪ የተከፈለው ብር 3,866,707 ከአመልካች እዲ ጋር ያለው ግንኙነት በግለሰቧ ምስክርነት አለመጣራቱ፣ አመልካች ከተጠሪ ለገዛቸው ተሽከርካሪዎች ሉከፈል የሚገባው ኮሚሽን ብር 2,917,500 ከጠቅላላ እዲው እንዱቻቻል አለመወሰኑ፣ የቅድመ ክፍያ ብር 5,350,000 እንዱሁም ለእያንዲንደ መኪና ግዢ የመለዋወጫ እቃ ብር 100,000 ተቀናሽ አለመደረጉ እና ወለድ 2 ጊዜ እንዱከፍል መወሰኑ አግባብ አይደለም በማለት ነው። ተጠሪ በበኩለ አመልካች ብር 18,703,775 እዲ እንዲለበት የተፃፈው ደብዲቤ እስከ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ያለውን ቀሪ ሂሳብ እና ወለድ የሚመለከት እንጂ ክስ እስከ ቀረበበት ጥር 2010 ዓ.ም ያለውን ወለድና ዋና ገንዘብን አያካትትም፤ የኮሚሽን ክፍያውም ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ውል የሚመለከት አይደለም፤ ወ/ሮ ሮዛ ዱፊብሪ ለአመልካች እዲ ክፍያ የፈጸሙ ስለመሆኑ የቀረበ የሰነድ ማስረጃ የለም፤ ክሱም የቅድመ ክፍያ ብር 5,350,000 ተቀናሽ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ሂሳብ አጣሪውም ይህ ገንዘብ ለመከፈለ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩን ስላረጋገጠ እና ወለደም ውለን መሰረት አድርጎ የተሰላ ስለሆነ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተገቢ መሆኑን ገልፆ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቶች በተከራካሪዎች የሚቀርቡ ክርክሮችን ለጉዲዩ ተገቢነት ባለው ማስረጃ ማጣራት ያለባቸው ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 136፣ 145፣ 257-259 እና ላልች የስነ ስርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች ላይ ተመላክቷል።
በመጀመሪያ ተጠሪው የአመልካች ቀሪ እዲ ብር 18,703,775 ብቻ መሆኑን ገልፆ የፃፈው ደብዲቤ ለክርክሩ መነሻ ከሆነው እዲ ጋር ግንኙነት የለውም ተብል የመወሰኑን አግባብነት መመልከቱ ተገቢ ነው። ተጠሪ ከአመልካች ጋር በተደረጉ 4 የተለያዩ የመኪና ሽያጭ ውልች ዋጋቸው ብር 100,850,000 የሆነ መኪኖችን በደቤ መሸጡን፤ አመልካች እስከ ጥር 22 ቀን 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ ወለድ እና ቅጣትን ጨምሮ ከሚፈለግበት ብር 111,420,620 ውስጥ ያልከፈለው ቀሪ ክፍያ ብር 31,306,375 መሆኑን እና ይህን ገንዘብ እንዱከፍል እንዱወሰንለት ዲኝነት ጠይቋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ብር 18,703,775 እዲ ያለበት መሆኑን ገልፆ ተጠሪ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም የፃፈው ደብዲቤ በደቤ ከተገዙት መኪኖች እዲ ክፍያ ጋር የሚገናኝ ስለመሆኑ ይዘቱ አያመለክትም በማለት የአመልካችን ክርክር ሳይቀበለው ቀርቷል። ነገር ግን ተጠሪ ይህን ደብዲቤ ስለመፃፈ በስር ፍ/ቤቶች ክድ ያቀረበው መከራከሪያ ካለመኖሩም በላይ ለዚህ ሰበር ችልት በሰጠው መልስ በደብዲቤ የተገለጸው እዲ እስከ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ብቻ ያለውን የሚመለከት እንጂ ከዚህ ጊዜ በኋላ ያለውን ዋና እዲ እና ወለድ የሚመለከት አይደለም በማለት ተከራክሯል። ይህ የተጠሪ ክርክር በአመልካች የተጠቀሰው ደብዲቤ ከእዲው ጋር በተያያዘ የተጻፈ መሆኑን ማመኑን የሚያሳይ ሆኖ እያለ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደብዲቤው ይዘት ከእዲው ጋር ተያያዥነት ያለው አይደለም ማለቱ ተገቢ አይደለም። በልላ በኩል ተጠሪ ደብዲቤው ከእዲው ጋር ተያያዥነት ያለው መሆኑን ቢያምንም ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ከአመልካች የሚፈለገውን እዲ የሚያሳይ አለመሆኑን ገልጾ የሚከራከር በመሆኑ፡ አመልካች በበኩለ ቀሪ እዲውን ይህን የገንዘብ መጠን መሰረት በማድረግ ላልች ክፍያዎች ተቀናሽ ተደርገው ሉከፍለው የሚገባ የገንዘብ መጠን ብር 3,291,784.21 ብቻ መሆኑን ጠቅሶ የሚከራከር በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 259 መሰረት አመልካች ይህን የማስረዲት ግዳታ አለበት። ነገር ግን አመልካች እዲው በደብዲቤው ላይ የተገለፀው ብቻ ስለመሆኑ እንዱሁም ቀሪ ክፍያው ይህን መሰረት በማድረግ ሉሰላ የሚገባ ስለመሆኑ አላስረዲም። በተጨማሪም የአመልካች ትክክለኛ እዲ ምን ያህል ነው የሚለው በአግባቡ መጣራት ያለመጣራቱን በቀጣይ የምንመለከተው ሁኖ በግራ ቀኙ መካከል በተደረገው የደቤ የመኪና ሽያጭ ውል አመልካች ቀሪ እዲ በገለልተኛ የሂሳብ ባለሞያ እንዱጣራ ተደርጎ ቀሪ እዲ ያለበት መሆኑ እስከ ተረጋገጠ ድረስ የቀሪ እዲ ስላቱ የግድ በደብዲቤው የተገለፀውን የገንዘብ መጠን መሰረት ተደርጎ ሉሰላ ይገባል የሚባልበት የሕግ አግባብ የለም። ስለሆነም ምንም እንኳ የስር ፍ/ቤት ደብዲቤው ለክርክሩ መነሻ ከሆነው የደቤ የመኪና ሽያጭ ውል ጋር ግንኙነት ያለው ስለመሆኑ የደብዲቤው ይዘት አያመላክትም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ ተገቢ ባይሆንም ከላይ በተገለፀው ምክንያት በውጤት ደረጃ መሰረታዊ ልዩነት የሚያመጣ ባለመሆኑ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበውን ቅሬታ አልተቀበልነውም።
በመቀጠልም አመልካች ከወ/ሮ ሮዛ ዱፊቬሪ ጋር ባለው ግንኙነት ሉከፈለው የሚገባውን ብር 3,866,707 ለተጠሪ እንዱከፍል ተስማምቶ ግለሰቧ ገንዘቡን ለተጠሪ ስለመክፈላቸው በምስክርነት ቀርበው እንዱጣራ ያለመደረጉን አግባብነት ስንመለከት ተጠሪ ድርጅቱ ሰነድን መሰረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ገልፆ ግለሰቧ የተጠቀሰውን ገንዘብ ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ሰነድ አልቀረበም በማለት ተከራክሯል። በስር ፍ/ቤቶች አመልካች ግለሰቧ ይህን ክፍያ ለተጠሪ የከፈለ ስለመሆኑ ያቀረበው የሰነድ ማስረጃ የለም፤ የሑሳብ ባለሞያ ሪፕርቱም ይህ ገንዘብ ለተጠሪ ስለመከፈለ ሳይሆን ግለሰቧ ከአምቼ ጋር የብድር ውል ግንኙነት የነበራቸው መሆኑን የሚያመላክት መሆኑን ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤት አረጋግጧል። በአንፃሩ አመልካች ይህን ገንዘብ ግለሰቧ ለተጠሪ እንድትከፍል ስለመስማማታቸው ማስረጃ ስለመቅረቡ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ የተረጋገጠ ሲሆን አመልካችም ግለሰቧ በምስክርነት ቀርበው ቃላቸው እንዱሰጡ ጠይቆ የነበረ መሆኑን ጠቅሶ የሚያቀርበውን መከራከሪያ ተጠሪ ክድ የሚያቀርበው መከራከሪያ የለም። ይልቁንም ተጠሪ የሚከራከረው ድርጅቱ ሰነድን መሰረት አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ ጉዲዩ በሰው ምስክርነት የሚረጋገጥ አይደለም በማለት ነው። በመሰረቱ ድርጅቱ ሰነድን መሰረት አድርጎ የሚሰራ መሆን አለመሆኑ፣ ግለሰቧ ከአመልካች ወይም ከተጠሪ ድርጅት ጋር ያላቸው ግንኙነት፣ የድርጅቱን አሰራር መሰረት አድርገው ወይም ከድርጅቱ አሰራር ውጪ ክፍያ መፈፀም አለመፈጸማቸው ከሕግ አንፃር የሚኖረውን ውጤት መመዘን የሚቻለው ግለሰቧ ከሚሰጡት የምስክርነት ቃል ጋር አብሮ መመዘን ሲቻል ነው። ከዚህ በተቃራኒ የስር ፍ/ቤት የግለሰቧን የምስክርነት ቃል ሳይሰማና ከህግ አንፃር የሚኖረውን ውጤት ሳይመዝን ገንዘቡ ለአመልካች እዲ ስለመከፈለ ማስረጃ አልቀረበም በማለት መወሰኑ፣ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱም ይህን አለማረሙ የአመልካችን ከወ/ሮ ሮዛ ዱፈብሪጋ የመዋዋል መብት የሚያጠብ እና መሰረታዊ የክርክር አመራር ስነ ስርዓት ጥሰት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል።
መፍትሓ ማግኘት ያለበት 3ኛው ጉዲይ አመልካች የቅድመ ክፍያ ብር 5,350,000 ተቀናሽ አለመደረጉን በመቃወም የሚያቀርበው መከራከሪያ ተገቢነት ሲሆን ለዚህ ክርክር እልባት ለመስጠት ጉዲዩን በመጀመሪያ በተመለከተው ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ተጠሪ ያቀረበውን ክስ፣ የአመልካችን መልስ እንዱሁም በሑሳብ ባለሞያ የቀረበውን ሪፕርት መመልከቱ ተገቢ ነው። በግራ ቀኙ መካከል 4 የደቤ የመኪና ሽያጭ ውል መደረጉ አከራካሪ አይደለም። ተጠሪ ባቀረበው ክስ የመጀመሪያውን ውል አስመልክቶ አመልካቹ 5,000,000 እንዱከፍል መስማማታቸወን በኋላም ቅድመ ክፍያውን ወደ 16,000,000 ማሳደጋቸውን ፤ በ2ኛ ውል አመልካች ሉከፍል ከሚገባው 2.4 ሚሉዮን ቅድመ ክፍያ ብር 1.5 ሚሉዮን ብቻ መክፈለን፤ በ3ኛው ውል አመልካች ብር 12,250,000 ቅድመ ክፍያ ፈፅሞ ላላ የሚቀርበት መሆኑን፣ በ4ኛ ውል አመልካች ብር 2,350,000 ቅድመ ክፍያ መክፈለን እና ቀሪ ክፍያ ያለበት መሆኑን ገልፆ ተከራክሯል። በአንፃሩ አመልካች መልስ ሲሰጥ ተጠሪው የተከፈለ ቅድመ ክፍያ በሚል ከጠቀሳቸው ውስጥ ያልተካተተ የቅድመ ክፍያ አለ ሲል በግልፅ ያነሳው መከራከሪያ ባይኖርም የተለያዩ ክፍያዎች ተቀናሽ ተደርገው ሉከፍል የሚገባው ብር 3,920,124.68 ብቻ መሆኑን ገልፆ ተከራክሯል። በተጨማሪም ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መሰረት በማድረግ ጉዲዩ በገለልተኛ የሂሳብ አጣሪ ባለሞያ ተመርምሮ አመልካች ያለበት ቀሪ እዲ እንዱለይ ትዕዛዝ ሲሰጥ አመልካች ተቀናሽ እንዱደረግ የሂሳብ ባለሞያዎቹን ከጠየቀበት 6 ዝርዝሮች መካከል አንደ ከፈልኩት የሚለውን የቅድመ ክፍያ ብር 5,350,000 ነው። ይህም በሂሳብ ሪፕርቲ ገጽ 3 ላይ የሰፈረ ሲሆን ባለሞያዎቹም በዚህ ጉዲይ በቂ ማስረጃ ያልተገኘበት ተቀናሽ የተደረገ በሚል ገልፀውታል። በልላ በኩል ግንቦት 7 ቀን 2011 ዓ.ም ለፍ/ቤቱ በላኩት ማብራሪያ በቂ ማስረጃ ያልተገኘበት መሆኑን ጠቅሰው ተቀናሽ አለመደረጉን አሳውቀዋል። ተጠሪ መቀነስ የሚገባቸው ቅድመ ክፍያዎች ተቀናሽ መደረጋቸውን፣ አመልካች በበኩለ አከራካሪ የሆነው የገንዘብ መጠን ተቀናሽ ያልተደረገ እና ተቀናሽ ላደረግ የሚገባ መሆኑን ገልጾ የሚከራከር በመሆኑ እና የሂሳብ ባለሞያዎቹም በአንድ በኩል ተቀናሽ መደረጉን በልላ በኩል በቂ ማስረጃ ባለመገኘቱ ተቀናሽ አለመደረጉን አሻሚ በሆነ መልኩ በመግለፃቸው ከውሳኔ በፉት በጉዲዩ ላይ ተጨማሪ ማጣራት ላደረግ እና እውነቱ ነጥሮ ሉወጣ ይገባ ነበር። በዚህ ረገድ ተገቢው ማጣራት እንዱደረግ ሳይደረግ የተሰጠው ውሳኔ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 257 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎች የሚቃረን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው።
በአራተኛ ደረጃ አመልካች የኮሚሽን ገንዘብ ብር 2,917,500 ተቀናሽ ያለመደረጉ ገልፆ የሚያቀርበውን መከራከሪያ ስንመለከት ተጠሪ ይህ የኮሚሽን ክፍያ ስምምነት ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን ውልች የሚመለከት አይደለም በሚል የተከራከረ ቢሆንም ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የስር ፍ/ቤት በውለ ላይም ለእያንዲንደ መኪና ዋጋ ላይ 3 በመቶ ኮሚሽን የሚታሰብ መሆኑ መገለፁን አረጋግጧል።
ነገር ግን ከፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 236 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች አንፃር ተቀናሽ እንዱደረግ ወይም እንዱቻቻል የሚጠይቀው ገንዘብ መቅረብ ያለበት ለመጀመሪያ ክስ መልስ በሚሰጥበት የመጀመሪያ ጊዜ መሆን ያለበት ሲሆን አንደኛው ከሳሽ ተከሳሽ ላላኛው የተከሳሽ ከሳሽ ሁኖ እንደቀረበ ይቆጠራል፡፤
ፍ/ቤቱም በዋናው ክስ እና በመቻቻል ጥያቄው ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 236(3) ላይ ተመላክቷል። ከዚህ አንፃር የመቻቻል ጥያቄው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በሚመራበት አግባብ ላቀርብ የሚገባ መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን አመልካች በዚህ ስርዓት አላቀረበም። በተጨማሪም በውለ መሰረት ከሶ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀለት በመሆኑ በጉዲዩ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚያስብል ሁኖ አላገኘነውም።
በመጨረሻም አመልካች ወለድ ሁለት ግዜ ታስቧል በማለት የሚያቀርበውን መከራከሪያ ስንመለከት የመጀመሪያው ክፍያው እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ውለን መሰረት በማድረግ የተሰላ እና ሳይከፈል የዘገየ በወለድ ብር 1,077,812 መሆኑ ሁለተኛው የታሰበው ክፍያው ከተቋረጠ በኋላ ያለው ሁኖ ብር 2,809,444 መሆኑ ስለተረጋገጠ በዚህ ረገድ የተፈፀመ መሰረታዊ ሕግ ስህተት የለም በማለት ተከታዩን ወስነናል።
ፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሚያዝያ 5 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሆነውን መዝገብ በማንቀሳቀስ፡- 2.1 . ወ/ሮ ሮዛ ዱፊብሪን በማስቀረብ ከአመልካች ጋር ባላቸው ግንኙነት ለአመልካች ሉከፍለት የሚገባውን ብር 3,866,707 ከተጠሪ ላለበት እዲ እንዱከፈል ተስማምተው መክፍል አለመክፈላቸውን በተመለከተ የምስክርነት ቃላቸውን እንዱሰጡ በማድረግ በሕግ የሚኖረውን ውጤት ከላልች አግባብነት ካላቸው ማስረጃዎች ጋር አገናዝቦ በመመርመር እንዱወስን፤
2.2 . የስር ፍ/ቤቶች በሂሳብ አጣሪው ተጣርቶ የቀረበው የእዲ መጠን መሰረት በማድረግ ብር 26,767,487.14 አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል ከተወሰነው የገንዘብ መጠን ላይ አመልካች ተቀናሽ አለመደረጉን በመግለፅ የሚከራከረው የቅድመ ክፍያ ብር 5,350,000 ሉቀነስ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ግራ ቀኙ የሚያቀርቡትን ማስረጃ መሰረት በማድረግ የሂሳብ አጣሪ ባለሞያዎቹ በድጋሚ አጣርተው ተገቢውን ውጤት እንዱያቀርቡ በማድረግ እንዱወስን መዝገቡን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343 /1/መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ ።
ከላይ በውሳኔ ተራ ቁጥር 2.1 እና 2.2 ላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች ውጪ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ እና ትእዛዝ እንደተጠበቀ ነው።
በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ትእዛዝ በዚህ መዝገብ በ11/03/2013 ዓ.ም. በዋለው ችልት በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አፈጻጸም መዝገብ ላይ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።