አንድ ጉዲይ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ታይቶ ውሳኔ ያገኘ መሆኑ ከተረጋገጠ አዱስ የቀረበውን ክስ በድጋሚ አይቶ ውሳኔ መስጠት የሥነ ሥርዓት ሕግን አይነተኛ ዓላማ የማያሳካ እና በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ የተጣረሰ ውሳኔ ላሰጥ የሚችልበትን ዔድል የሚፈጥር በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ሕጉን በጥብቅ ሉተገብሩት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 ንዐስ ቁጥር (1)
No summary available.
ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ ሐብታሙ እርቅ ይሁን አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች የካቲት 06 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የጎሮ ጉቱ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ. ሚያዝያ 21 ቀን 2014 ዓ.ም የአመልካቾች ክስ ድጋሚ የቀረበ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት የሰጠው ብይን፤ ይህንኑ ብይን በማጽናት በየደረጃው ያለ የሥር የክልለ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የእርሻ መሬት ውርስን በሚመለከት የቀረበን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የጎሮ ጉቱ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በስር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- የሟች ወንድማችን አቶ አሕመድ በከር ወራሾች መሆናችን ተረጋግጧል፤ ስለሆነም ተጠሪ አዋሳኙ በክሱ የተገለጸውን ይዞታ እንዱያካፍለን ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። ተጠሪ በሰጡት መልስ ከዚህ ቀደም በመ. አከራካሪውን ይዞታ በተመለከተ ውሳኔ ተሰጥቶበታል፤ ስለሆነም የአመልካቾች ክስ ድጋሚ የቀረበ ክስ ነው ተብል ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም በተጠሪ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አመልካቾች ካቀረቡት ክስ እና በመ. ከተሰጠው ውሳኔ ጋር በማገናዘብ መርምሮ አመልካቾች አከራካሪውን ይዞታ በሚመለከት ከዚህ ቀደም በመ. ክስ አቅርበው ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጥቶበታል፤ ስለሆነም ይህንኑ ይዞታ በሚለከት በድጋሚ ያቀረቡት ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት በብይን ውድቅ አድርጎታል። ይህም ብይን በየደረጃው ባለ የሥር የክልለ ፍርድ ቤቶች ጸንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ይዘቱም፡- አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ክስ ያቀረብነው የወራሽነት መብታችን ተጠብቆ የሟች ወንድማችንን የውርስ ይዞታ እንድንካፈል ነው፤
ስለሆነም ክርክሩ ተገቢነት ባለው ማስረጃ ሳይጣራ የአመልካቾች ክስ ድጋሚ የቀረበ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪው ችልት ተመርምሮ 1ኛ አመልካች ከዚህ በፉት በወረዲ ፍርድ ቤት በመ. ያቀረቡት ዲኝነት ተጠሪ በጉልበት የያዘውን የጫት ይዞታ እንዱመልስ የሚል ሲሆን አሁን የጠየቁት ዲኝነት ደግሞ የሟች ወንድማችን ውርስ ይዞታ ያስረክበን የሚል ከመሆኑ አኳያ ከዚህ ቀደም የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ነው በሚል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ ተይዞ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- በመ. 1ኛ አመልካች አከራካሪውን ይዞታ ለመውረስ መብት የላትም በማለት ተወስኗል፤ 2ኛ አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ አቅርባ አከራካሪውን ይዞታ ለመውረስም ሆነ ለመጠየቅ መብት የላትም በሚል ተወስኗል፤ ይህ ውሳኔ በይግባኝ አልተሻረም፤ ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ድጋሚ የቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ስለሆነ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካቾችም በሰጡት የመልስ መልስ በመ. በቀረበው ክስ መጠየቅ ይገባው የነበረው ዲኝነት የውርስ ንብረት ይከፊፈል የሚል መሆን ሲገባው በጸሐፉ ስሕተት ተጠሪ አከራካሪውን የጫት ይዞታ በጉልበት ስለያዘብኝ ይልቀቅልኝ በሚል ዲኝነት ተጠይቆ ለተጠሪ ተወስኖለታል፤ ይህ ውሳኔ አመልካቾች የውርስ ድርሻችንን ክስ አቅርበን ከመጠየቅ አያግደንም በማለት የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸውን ይመስላል። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ያስቀርባል ሲባል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ እንደቻልነው ተጠሪ ከዚህ ቀደም በመ. በአሁን 1ኛ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ 1ኛ አመልካች ከሕግ ውጪ የያዘችውን አከራካሪውን ይዞታ እንድትለቅ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀው 1ኛ አመልካች በጉዲዩ ላይ መልስ ሰጥተው ጥቅምት 08 ቀን 2014 ዓ.ም 1ኛ አመልካች ይዞታውን እንዱለቁ ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን፤ 2ኛ አመልካችን ይህን ውሳኔ በመቃወም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ አቅርበው ውሳኔው ሳይለወጥ የቀረ መሆኑን፤
አመልካቾች አሁን ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ በሆነው የስር መዝገብ ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዲኝነት ቀደም ሲል በመ. ውሳኔ ያረፈበትን ይዞታ የሚመለከት መሆኑን፤ ከዚህ ቀደም በመ. በተደረገው ክርክር እና አሁን ለዚህ ሰበር አቤቱታ በሆነው ጉዲይ የክሱ መሰረት የሆነው ጉዲይ በክሱ የተገለጸው አከራካሪው የጫት ይዞታ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በልላ በልዩ ሕግ ካልተገደበ በቀር የፍትሐብሕር ክርክር የሚመራው በፍትሐብቤር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ነው። የዚሁ ሕግ ዋና ዓላማም የሰው ልጆች ፍትሐ ብሓራዊ ከሆኑ መሰረታዊ የስረ ነገር ሕግጋት እና ዉልች ያገኟቸዉ መብቶችና ጥቅሞች እንዱሁም የገቧቸዉ ግዳታዎች እና ኃላፉነቶች ጊዜን ጉልበትን እና ወጪን ቆጣቢ በሆነ መንገድ በተግባር እንዱተረጎሙ በማድረግ ፍትሐዊ የሆነ ውሳኔ መስጠት ነው። የሥነ ሥርዓት ሕጉ ይህንን ግብ ለማሳካት ከዘረጋቸዉ ሥነ ሥርዓቶች መካከል አንደ የመጨረሻ ውሳኔ ስላገኙ የሚደነግገው ክፍል ነው።
የመጨረሻ ውሳኔ ስላገኙ ጉዲዮች የሚደነግገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 በንዐስ ቁጥር (1) ላይ በሕግ ስልጣን የተሰጠው ማንኛውም ፍርድ ቤት ክርክሩን ተቀብል የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ቀድሞ በፍርድ የተወሰነው ክርክር ሥረ ነገር እና የተያዘው ጭብጥ አንድ ዓይነት ከሆነ በክርክሩ ላይ የነበሩት ወይም ከተከራካሪዎቹ መብት ያገኙ ሶስተኛ ወገኖች በዚያው ነገር ሁለተኛ ክስ ወይም ማናቸውንም ዓይነት ላላ ክርክር ለማቅረብ አይችለም በማለት ይደነግጋል። በዚህ አግባብ የሚቀርበው መቃወሚያም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚቀርብበትን ሥርዓት አስመልክቶ በተደነገገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244 ድንጋጌ ላይ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የሚቀርቡ ናቸው ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ አንደ ነው።
በሕግ ሥልጣን በተሰጠው ማናቸውም ፍርድ ቤት ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ጉዲይ ድጋሚ ክስ ላቀርብበት አይገባም በማለት የተደነገገበት ዋና ዓላማ አንድ ተከራካሪ ወገን በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ በተለያየ ጊዜ ክስ እየቀረበበት ጊዜውን እንዲያባክን፤ ተጨማሪ ወጪ እንዲያወጣ እና እንዲይሸማቀቅ ለማድረግ፤ አንድ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በበላይ ፍርድ ቤት እስካልተሻረ ድረስ በሕብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዱኖረው ለማድረግ፤ ክርክሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ መቋጫ እንዱኖራቸው ለማድረግ፤
ሕጉ ላልተፈለገበት ዓላማ እንዲይውል በመከላከል የፍትሕ አስተዲደር ሥርዓቱ ተገማች እና ፍትሐዊ እንዱሆን ለማድረግ ስለመሆኑ በዘርፈ ከዲበረው ሥነ ሕግ መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም አንድ ጉዲይ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ታይቶ ውሳኔ ያገኘ መሆኑ ከተረጋጠ አዱስ የቀረበውን ክስ በድጋሚ አይቶ ውሳኔ መስጠት ከላይ የተመለከተውን የሥነ ሥርዓት ሕጉን አይነተኛ ዓላማ የማያሳካ እና በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ የተጣረሰ ውሳኔ ላሰጥ የሚችልበትን ዔድል የሚፈጥር በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ሕጉን በጥብቅ ሉተገብሩት ይገባል።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች እና ተጠሪ የሚከራከሩበት የጫት ይዞታ ከዚህ ቀደም ተጠሪ በመ.
1ኛ አመልካች ከሕግ ውጪ ይዛብኛለች በማለት ክስ አቅርበው 1ኛ አመልካች መልስ እንዱሰጡት ተደርጎ ይዞታውን እንዱለቁ ውሳኔ ተሰጥቷል። የአሁን 2ኛ አመልካችም የክርክሩ ተካፊይ ሳልሆነ የተሰጠው ውሳኔ መብቴን ይነካል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ አቅርበው ውሳኔው ሳይለወጥ ቀርቷል። አመልካቾች አሁን ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ በሆነው የስር መዝገብ ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዲኝነት ቀደም ሲል በመ. ውሳኔ ያረፈበትን ያንኑ ይዞታ የሚመለከት ነው፤ ይህም ከዚህ ቀደም በመ. በተደረገው ክርክር እና አሁን ለዚህ ሰበር አቤቱታ በሆነው ጉዲይ በተደረገው ክርክር የክሱ መሰረት የሆነው ይዞታ ተመሳሳይ ይዞታ መሆኑን እና ተከራካሪዎችም ተመሳሳይ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። አመልካቾች ቀደም ሲል በነበረው ክርክር ይዞታው የእኛ ነው በሚል በተከሳሽነት ዘንግ የተከራከሩ ሲሆን አሁን ባቀረቡት ክስ ላይ በውርስ የሚገባን ይዞታ ነው በሚል መብቱን ያገኙበትን መንገድ በመለወጥ የተከራከሩ ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5/2 መሰረት በቀድሞ ክርክር የመከላከያ ክርክር አካል ላሆን የሚገባው ጉዲይ አብሮ እንዲለቀ የሚቆጠር ስለመሆኑ ከተመለከተው አንፃር ስንመለከተው የውርስ ነው የሚለው ክርክር በቀድሞ መዝገብ ላይ ክርክሩን አንስተው ሉከራከሩበት የሚችለት ጉዲይ ከመሆኑ አንጻር የወረዲው ፍርድ ቤት የአመልካቾች ክስ ድጋሚ የቀረበ ነው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት በብይን ውድቅ ማድረጉ በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አላገኘንበትም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የጎሮ ጉቱ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ. ሚያዝያ 21 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ብይን፤ ይህንኑ ብይን በማጽናት የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሰኔ 29 ቀን 2014 የሰጠው ውሳኔ፤ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሕዲር 21 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፤ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.