በክርክር ሂደት ክርክሩ ተጠቃል ከመወሰኑ በፉት በግልጽ በከፉል የተወሰነ ካለና ከቀጠለው ክርክር ጋር ተያያዥነት የላለው እስከሆነ ድረስ መብትን ለማስከበር በጉዲዩ ላይ ይግባኝ ማቅረብ የፈለገ ተከራካሪን የሚከለክል የሥነሥርዓት ሕግ ድንጋጌ የላለ ሲሆን በልላ በኩል ተከራካሪው ክርክሩን አጠቃል ይግባኝ ወይም የሰበር አቤቱታ ከማቅረብም ግን ሉከለከል የማይገባ ስለመሆኑ የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 234(1(ረ)
No summary available.
ቀን፡- ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ አበባየሁ ብርላ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ግንቦት 22 ቀን 2011 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ የሰበር አቤቱታ ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ በመዝገብ ያቀረበ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 04 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችልት ይግባኝ ሰሚ ችልት በከፉል በሰጠበት ጉዲይ ውሳኔ ከተሰጠ ከሦስት ወር ከ4 ቀን በኋላ የቀረበና ጊዜው ያለፈበት ነው በማለት መዝገቡን ዘግቷል። አመልካች በመዝገብ ያቀረቡትን የሰበር ማስፈቀጃ አቤቱታ ፍርድ ቤት በቂ ምክንያት ያልቀረበ በመሆኑና የዘገየውም በአመልካች ቸልተኝነት ስለሆነ በማለት ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ/ም ውደቅ አድርጓል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኙ መልሰ ሰጭን ያስቀርባል ሲል በከፉል ያጸናው ስለመሆኑ አላውቅም። ከተሰጠው መጥሪያ ላይም በከፉል የጸና ስለመሆኑ አይገልጽም። በፍርድ ቤቱ ችግር እንጂ በአመልካች ቸልተኝነት ባለመሆኑ የሰበር አቤቱታ እንዲቀርብ ሉፈቀድልኝ ይገባል የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ አመልካች አጠቃለው የሰበር አቤቱታ ሲያቀርቡ ቀደም ሲል በከፉል የተሰረዘ ቅሬታ ላይ ጊዜው አልፍበታል መባለ ተገቢነቱን ለማጣራት ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ አዟል። ተጠሪዎች መጥሪያ ደርሷቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት ታይቷል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ጊዜው ያለፈበት ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው በተሻሻለው የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 17(4) መሰረት የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ 90 ቀናት ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ የሰበር አቤቱታው ጊዜ ያለፈበትና የማይመረመር ነው። አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበበትን የመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግንቦት 22 ቀን 2011 ዓ/ም ነው። አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ደግሞ ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ/ም ነው። ይሕም 90 ቀናት ከመድረሱ በፉት መቅረቡን ያረጋግጣል። የሰበር አጣሪ ችልቱ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ጊዜ ያለፈበት ነው ያለው ይግባኝ ሰሚ ችልቱ መልሰ ሰጭዎችን ያስቀርባል ያለው በተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ሲሆን የአመልካችን ክሰ በተመለከተ ውሳኔው በከፉል አጽንቷል፤ በከፉል የጸናው መጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ/ም በመሆኑ የ90 ቀናት የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ አልፍበታል በሚል ነው።
የፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ክርክር ቀልጣፊ፣ ውጤታማና ወጭና ጊዜ ቆጣቢ እንዱሁም ፍተሐዊ በሆነ ሁኔታ እንዱመራ ዓላማ አድርጎ የተቀረጸ ነው። በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 234(1(ረ) መሰረት ክስ የቀረበበት ተከሳሽ የሆነ ወገንም በከሳሹ ላይ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ እንዱያቀረብ የፈቀደበት ምክንያትም ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ እንዱመራ ካለው ሃሳብ ነው። ክርክሩ በአንድ ላይ ሲመራ የቆየ ክስ ሆነ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የቀረበበት ክርክር በይግባኝ ሆነ በሰበር አቤቱታ በሚቀርብበት ጊዜ አንድ ላይ ተጠቃል ቢቀርብ በአንድ ጉዲይ ብዙ ፊይል እንዲይከፍት የሚያደርግና የፍርድ ቤቱን ሆነ የተከራካሪዎችን ጊዜ የሚቆጥብ ነው። በክርክር ሂደት ክርክሩ ተጠቃል ከመወሰኑ በፉት በግልጽ በከፉል የተወሰነ ካለና ከቀጠለው ክርክር ጋር ተያያዥነት የላለው እስከሆነ ድረስ መብቱን ለማስከበር በጉዲዩ ላይ ይግባኝ ማቅረብ የፈለገ ተከራካሪን የሚከለክል የሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌ የለም። በልላ በኩል ተከራካሪው ክርክሩን አጠቃል ይግባኝ ወይም የሰበር አቤቱታ ከማቅረብ ግን ሉከለከል አይገባውም።
በተያዘው ጉዲይም ይግባኝ ሰሚ ችልት በከፉል የአመልካችን የይግባኝ ቅሬታ የሰረዘ ቢሆንም በከፉል የቀጠለው ክርክር ላይ ተጠቃል ውሳኔ የተሰጠው ግንቦት 22 ቀን 2011 ዓ/ም በመሆኑ አመልካች ክርክሩ ተጠቃል ከተቋጨ በኋላ የሰበር አቤቱታ 90 ቀናት ሳያልፍ አቅርበው እያለ የሰበር አጣሪ ችልት በመዝገብ ጥቅምት 04 ቀን 2012 ዓ/ም ጊዜው ያለፈበት አቤቱታ ነው በማለት መዝገቡን መዘጋቱ የአመልካችን ፍትሕ የማግኘት መብት አላግባብ የከለከለና መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ግድፈት ያለበት ሆኖ ስላገኘነው ሉታረም የሚገባ ነው ብለናል።
በልላ በኩል አመልካች መብታቸውን ለማስከበር የሰበር ማስፈቀጃ አቤቱታ በመዝገብ ያቀረቡ ሲሆን ምንም እንኳን ከላይ እንደተመለከትነው የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜው ያላለፈበት ቢሆንም በይግባኝ ሰሚ ችልት በከፉል የተሰረዘ ቅሬታ ቢኖርም አመልካች አጠቃለው የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በሥነ-ሥርዓት ሕጉ ክርክሮች ተጠቃለው ቀልጣፊ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ እንዱመሩ ያሰበውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በሚያስችል መልኩና ከአንድ ጉዲይ ለሚመነጭ የተለያየ ፊይል እንዲይከፈት ለመከላከል ሆኖ እያለ፤ በሕጉ የተዘረጋወን ሥርዓት የተከተለን ተከራካሪ የሰበር አቤቱታ አቀራረብ ላይ ቸልተኝነት አለበት ተብል የሰበር ማስፈቀጃ አቤቱታው ውድቅ መደረጉ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በመዝገብ ጥቅምት 04 ቀን 2012 ዓ/ም እና በመዝገብ ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት አመልካች በመዝገብ ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ ተቀብል በመመርመር የመሰለውን እንዱወስን ጉዲዩን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
341(1) መሰረት መልሰናል።
ውሳኔው ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በውሳኔው መሰረት እንዱፈጽም አዘናል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.