ሟች በኑዛዜ የሚያስተላልፈው ንብረት የራሱን ንብረት በመሆኑ ሟች ባደረገው ኑዛዜ በውርስ ያስተላለፈው በድርሻው ላይ ብቻ ሳይሆን የላላ ሰውን ድርሻ ጨምሮ ከሆነ ኑዛዜው ሉፈርስ የሚገባው ሙለ በሙለ ሳይሆን በልላው ሰው ድርሻ ላይ የተደረገው የኑዛዜ ክፍል ብቻ እንጂ ኑዛዜው ሙለ በሙለ እንዱፈርስ በሚል ውሳኔ የሚሰጥ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 829 እና ተከታይ እነ ወ/ሮ ነጻነት ደምሴ (3 ሰዎች) እና ሲሳይ ታደሰ
No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- አቶ አብደሰላም ፊራህ አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ አደም ኡመር **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች ክስ ያቀረበበትና የሟች አባቱ የውርስ ሀብት መሆኑን የገለጸው የእርሻ ይዞታ አስቀድሞ ክስ መስርቶበትና ጉዲዩ በሽምግልና ያለቀ መሆኑ ተረጋግጦ ውሳኔ የተሰጠበት በመሆኑ ክሱ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ ነው ተብል ውድቅ መደረጉን በመቃወም ነው።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው በፋ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት (ድሬዲዋ ምድብ ችልት) የአሁን አመልካች በቀን 16/03/2013 ዓ.ም ባቀረቡት የውርስ ይጣራልኝ አቤቱታ ወላጅ አባታቸው አቶ ፊራህ ደአላ በቀን 01/01/1996 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ መሆኑን፤ አባታቸው ያፈሩት እና አሁን ድረስ በከሳሽ እጅ የሚገኝ በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ጎል አደግ ገጠር ቀበላ ክልል ውስጥ የሚገኝ ስፊቱ 10 ካ/ሜ የሆነ የእርሻ ቦታ ያለ መሆኑን ጠቅሰው ይኸው የአባታቸው የውርስ ሀብት የውርስ አጣሪ ተሹሞ እና ተጣርቶ የወራሽነት ድርሻቸው ለሚመለከተው አካል በመሸኛ እንዱተላለፍላቸው ጠይቀዋል።
ፍ/ቤቱም የውርስ አጣሪ በመሾም የውርስ ሀብቱ በመጣራት ሂደት ላይ እያለ ጣ/ገብ (የአሁን ተጠሪ) ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተው ባቀረቡት አቤቱታ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ክስ የቀረበበት ንብረት ከዚህ ቀደም ፍ/ቤቱ በቀን 07/02/2012 ዓ.ም በሰጠው ብይን ከሳሽ በጉዲዩ ላይ ክስ የማቅረብ መብትና ጥቅም የላለው መሆኑን እንዱሁም ጉዲዩ አስቀድሞ በሽምግልና ታይቶ ያለቀ መሆኑን በማረጋገጥ መዝገቡን የዘጋው በመሆኑ አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ ከሳሽ አቤቱታ ሉያቀርብ አይገባም እንዱባል፤ ይህን የእርሻ ይዞታ ከሳሽም ሆነ አባቱ ይዘውትም ሆነ ተጠቅመውበት የማያውቁ መሆኑን በአንጻሩ ከደርግ ጊዜ ጀምሮ ይዞ የሚጠቀምበት እራሱ እንደሆነ፤ የገጠር ይዞታ ማረጋገጫ የተሰጠው በ2010 ዓ.ም መሆኑን ጠቅሶ ከሳሽ በዚህ የእርሻ ይዞታ ላይ የውርስ ማጣራት አቤቱታ ሉያቀርብ የሚችልበት አንዲችም መብትና ጥቅም የለውም፤ እንዱሁም የእርሻ ይዞታውን ከመሬት ላራሹ ጊዜ ጀምሮ ይዞ እያስተዲደረ እና እየተጠቀመበት በመሆኑ አቤቱታው በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት ክርክሩንና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ከግራ ቀኙ ክርክርና አስቀድሞ በፍርድ ካለቀው መዝገብ (መ/) ለመገንዘብ እንደተቻለው በሁለቱም መዝገቦች ለተነሳው ክርክር የስረ ነገር መነሻው ከሳሽ የሟች አባቱ የውርስ ሀብት መሆኑን የገለጸው በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ጎለአደግ ገጠር ቀበላ ማህበር የሚገኝ የእርሻ ይዞታ ነው፤ ይህም በሁለቱም መዝገቦች የቀረበው የስረ ነገር ክርክር ጭብጥ የሟች ፊራህ ደአላ የውርስ ሀብትን የሚመለከት እንደመሆኑ መጠን በዚህ መዝገብ የተጀመረው የውርስ ሀብት ማጣራት በመ/ ተከፍቶ እልባት ካገኘው ለክርክር መነሻ የሆነው የውርስ ሀብት ይለቀቅልኝ ክስ ጋር የተለያዩ ናቸው ልባል የሚችል ሆኖ አልተገኘም፤ በልላ በኩል ከሳሽ በመ/ የነበረው ክርክር በብይን ሉዘጋ የቻለው መብትና ጥቅም የለውም በሚል እና አሁን ደግሞ መብትና ጥቅሙን አረጋግጦ የመጣ በመሆኑ አሁን ያቀረበው የውርስ ማጣራት አቤቱታ ለማቅረብ የሚከለክለው ህጋዊ ምክንያት የላለ መሆኑን ገልጾ ቢከራከርም ፍ/ቤቱ ከቀደመው መዝገብ ለማረጋገጥ እንደተቻለው በቀድሞው መዝገብ ፍ/ቤቱ በብይን ላይ እንዲሰፈረው ከሳሽ ወራሽ መሆኑን ሳያረጋግጥ ክስ የመሰረተ እና ይህም ሁኔታ በጉዲዩ ላይ መብትና ጥቅም የላለው መሆኑን እንደሚያሳይ የጠቀሰ ቢሆንም በዋነኛነት ክሱን በብይን ሉዘጋው የቻለው ግን ጉዲዩ በሽምግልና ታይቶ የተቋጨ መሆኑን በመጥቀስ ነው፤ ከዚህ አንጻር ከሳሽ የቀድሞ መዝገብ ሉዘጋ የቻለው መብትና ጥቅም የለህም ተብል ነው በማለት ያቀረበው መከራከሪያ ተገቢነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ከሳሽ አሁን ክስ የመሰረተበትን እና የሟች አባቱ የውርስ ሀብት መሆኑን የገለጸው የእርሻ ይዞታ አስቀድሞ በመ/ በጣ/ገብ ላይ ክስ መስርቶበትና ጉዲዩ በሽምግልና ያለቀ መሆኑ ተረጋግጦ ውሳኔ ተሰጥቶበት ያለቀ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5(1) መሰረት አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ብይን ሰጥቷል።
በዚህ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ብይኑ የሚነቀፍ አይደለም ተብል ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዟል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው።
አመልካች በቀን 14/06/2014 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር ማመልከቻ በስር ፍ/ቤት አስቀድሞ በመ/ የተካሄደው ክርክር አመልካች በተጠሪ እና ላልች የክፍለ ቀበላ አመራር አካላት ላይ የመፊለም ክስ ለማቅረብ የተረጋገጠ መብት እና ጥቅም የለህም እንዱሁም ጉዲዩ አስቀድሞ በሽምግልና ያለቀ ነው በማለት ክሴን ውድቅ በማድረግ በብይን መዝገቡ የተዘጋበት ነው። ይሁን እንጂ የሟች አባቴ ሚስት እና ወራሽ የሆኑ ላልች ልጆች ጭምር ያለበት እንደመሆኑ መጠን አስቀድሞ በተደረገው ክርክር በወራሽነቴ ሳይሆን በራሴ የባለቤትነት ክስ ማቅረቤ ከዚያ በኋላ መብትና ጥቅሜን ለማረጋገጥ ውርሱ እንዱጣራ የመጠየቅ መብቴን የማያጣብብ ከመሆኑም ላላ በእኔ ስም የተደረገ የሽምግልና ውሳኔ የለም እንጂ አለ ቢባል እንኳ በራሴ ላይ ብቻ ውጤቱ ከሚወሰን ባሻገር የአባቴ የውርስ ሀብትና ወራሾች ላይ የሚያመጣው አንዲችም ውጤት በላለበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤት የመፊለም እና የውርስ ህጎችን በአግባቡ መለየት ሳይችል ቀርቶ መከራከሪያዬን ወደ ጎን በመተው የሰጠው ብይን አግባብነት የላለው ነው። የውርስ ማጣራት ውጤቱ ከማስረጃነት በዘለለ የሚያመጣው አንዲችም አስገዲጅነት የላለው ሆኖ ሳለ ተጠሪ በዚህ ሂደት ላይ ጣልቃ ገብተው ለመከራከር የሚያበቃ በቂ ምክንያት በላለበት ሁኔታ ከጅምሩ ጣልቃ እንዱገቡ የተደረገበት ሂደት አግባብነት የላለው ከመሆኑም በተጨማሪ በእጄ በሚገኘው ይዞታ ላይ ምንም አይነት የፍሬ ነገር ማጣራት እና ማረጋገጥ ሳይኖር እንዱሁም በስሜም ሆነ በአባቴ ስም የተደረገ አግባብነት ያለው የሽምግልና ሂደት እና ውሳኔ ሳይኖር ተጠሪ በደፈናው የእኔን መብት በመጋፊት ባለመብት እንዱሆኑ የሚያስችላቸው ሁኔታ መፈጠሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ብይንና ትዕዛዝ ተሽሮ የውርስ ማጣራቱ እንዱቀጥል ውሳኔ እንዱሰጥልኝ በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልትም በዚህ ጉዲይ በመፊለም ቀርቦ የነበረው ክስን አሁን በውርስ የቀረበው ክስ አንድ አይነት ክርክርና ጭብጥ እንዲለው ተቆጥሮ ድጋሚ የቀረበ ነው መባለ ከፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 5 ድንጋጌ አንጻር አግባብነቱን ለማጣራት በሚል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን 17/10/2014 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ አመልካች ከአሁን በፉት በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በውርስ የተላለፈልኝን መሬት ተጠሪ ስለያዘብኝ ለቆ እንዱያስረክበኝ በማለት ዲኝነት ጠይቆ በብይን ውድቅ ተደርጎ እያለ ይህ የጸና የፍ/ቤት ውሳኔ ባልተሻረበት በዚሁ ሀብትና ንብረት ላይ የውርስ ሀብት ተጣርቶ እንዱተላለፍለት የጠየቀው ዲኝነት ቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው መባለ አግባብ ነው፤ አመልካች ቀድሞውኑም በስረ ነገር ደረጃ ያቀረቡት መከራከሪያና የጠየቁት ዲኝነት ከሟች አባቴ በውርስ የተላለፈልኝ የውርስ ሀብት እያለ ዲግም ይህንኑ የውርስ ሀብት ይጣራልኝ የሚለበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም። በመ/ የተሰጠው ብይን መብትና ጥቅም መሰረት ያደረገ ሳይሆን በአመልካችና በተጠሪ መካከል ይህን የእርሻ መሬት በተመለከተ ጉዲያቸው ከፍ/ቤት ውጭ በአማራጭ ሙግት መፍቻ በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተቋጨ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(2)(ረ) መሰረት ክስ ላቀርብ አይገባም በማለት የተሰጠ ነው። ይህ ብይን ጸንቶ ባለበት አመልካች በዚሁ የውርስ ሀብት ላይ የጠየቀው የውርስ ሀብት ይጣራልኝ ጉዲይ በሽምግልና ያለቀ መሆኑ ተረጋግጦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5(1) እና 245(2) መሰረት መሰረዙ አግባብ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ሉጸና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረውም በዚህ ሁኔታ ነው።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተገለፀው ሲሆን በበኩላችን የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረጉት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው በመ/ የአሁን አመልካች ተጠሪን ጨምሮ በሶስት ሰዎች ላይ ባቀረቡት ክስ መሬቱ ለአሁን ተጠሪ መተላለፈ አላግባብ ነው ተብል አከራካሪው መሬት እንዱመለስላቸው፣ ለተጠሪ የተሰጠው ማስረጃ እንዱሰረዝ እንዱሁም ተጠሪ በመሬቱ ላይ የወሰደው የካሳ ገንዘብ .00 (ሰላሳ ሺህ) እንዱመለስላቸው ዲኝነት ጠይቀው ነበር። ተከሳሾችም በዚህ ጉዲይ በሽምግልና ገብተን ዔርቅ የፈፀምን እና በስምምነት የተቋጨ በመሆኑ ዲግመኛ ልንከሰስ አይገባም የሚለና ላልች መቃወሚያዎች አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በ07/02/2012 ዓ.ም በሰጠው ብይን በደረሰበት መደምደሚያ ጉዲዩ አስቀድሞ በሽምግልና ያለቀ መሆኑ ስለተረጋገጠ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244(2)(ረ) መሰረት ዲግመኛ ክስ ላቀርብበት አይገባም በማለት ክሱን ውደቅ አድርጓል።
ከዚህ በኋላ አመልካች ይህንኑ የእርሻ ቦታ ጠቅሰው ይኸው የአባታቸው የውርስ ሀብት በመሆኑ የውርስ አጣሪ ተሹሞና ተጣርቶ የወራሽነት ድርሻቸው ተለይቶ ለሚመለከተው አካል በመሸኛ እንዱተላለፍላቸው እንዱወሰን ዲኝነት ጠይቀዋል።
ክርክሩንና ፍሬ ነገሩን ለማጣራት በህግ ስልጣን የተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች ግራቀኙ ያደረጉትንና በዔርቅ የተቋጨበትን ስምምነት መሰረት በማድረግ አስቀድሞ የተሰጠውን ብይን ይዘት መርምረው አመልካች አሁን ያቀረቡት በመሬቱ ላይ የውርስ ሀብት ይጣራልኝ ጥያቄ አስቀድሞ በዔርቅ ስምምነት ዔልባት ያገኘ መሆኑንና ይኸው በበላይ ፍርድ ቤት ያልተለወጠ መሆኑን በፍሬ ነገር ደረጃ በማረጋገጥ ውሳኔ ሰጥተዋል።
እንደሚታወቀው አንድ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ በሕግ በተደነገገው ሥርዓት መሰረት በይግባኝ ሥርዓት ወይም በሰበር ካልታረመ በጉዲዩ ላይ የመጨረሻና አስገዲጅነት ያለው ስለመሆኑ ከፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1/ ግልጽ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል። አመልካች በዔርቅ ስምምነታቸው መሰረት ክርክሩ እንዱቋጭ መደረጉ አግባብ አልነበረም የሚለ ቢሆን እንኳ ይግባኝ በማቅረብ አላስለወጡም ወይም አላሻሩም።
ስለሆነም በዔርቅ በስምምነታቸው መሰረት እልባት ያገኘው ጉዲይ ባልተሻረበት ወይም ባለተለወጠበት ሁኔታ አመልካች በስምምነት አልቋል ተብል ውሳኔ ባረፈበት ንብረት ላይ ውርስ እንዱጣራ በሚል ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄና ክርክር የፍርድ ቤቱን ውሣኔ/ትዕዛዝ አስገዲጅነትና ተፈፃሚነት መርህንና የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1/ የሚጥስ ነው። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች ይህን ምክንያትና መሰረታዊ የዲኝነት ሥራ አካሄድ መርሆች መሰረት በማድረግ የአመልካችን ክርክር ውድቅ ማድረጋቸው የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም የተላለፈው ብይንና ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 17/09/2013 ዓ.ም የሰጠው ብይን እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 15/03/2014 ዓ.ም ያሳለፈው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ግራ ቀኙ በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ።
No topics extracted.