ፍርድ ቤት በህግ የተረጋገጠን መብት ከማስከበር/ከማክበር በዘለለ እራሱ መብት ሉፈጥር የማይችልና በፍርድ ቤት የሚሰጥ ማንኛዉም ዉሳኔ ስርዓቱን ጠብቆ እስካልተለወጠ ወይም እስካልተሻሻለ ድረስ ተፈፃሚ ሆኖ ሉቀጥል የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ አንቀጽ 5 እና አንቀጽ 212
No summary available.
ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) እንዲሻዉ አዲነ ተሾመ ሽፈራዉ መላኩ ካሳዬ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ራዔይ በሲዲሞ ተራ ልማትና ንግድ አ/ማህበር - ስለ ራዔይ ገበየሁ ይርዲው ጠበቃ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ነኢማ ጫሞላ - ጠበቃ መኮንን ደምሴ ቀርበዋል።
መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረቡትን ክስ መነሻ ያደረገ ነዉ። የተጠሪ ክስ ይዘትም በአጭሩ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም ተደርጎ በሰነድች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት በተረጋገጠ የሽያጭ ዉል በአዱስ ከተማ ክ/ከተማ ዉስጥ የሚገኘዉን ቁጥሩ 593/2 የሆነ የንግድ ቤት አቶ ሀብቱ ብርሃኑ ከሚባል ግለሰብ ገዝቼ በቤቱ ላይ ሐምል 25 ቀን 2000 ዓ.ም የንግድ ፍቃድ በማዉጣት ጳጉሜ 3 ቀን 2000 ዓ.ም ከቀበላ ተከራይቼ የንግድ ስራ ሳከናዉን ቆይቻለሁ። መንግስት በመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ መርካቶ ዉስጥ በሕግ አግባብ ሱቅ በመያዝ የሚነግደ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ቦታቸዉ ያለበትን ስፍራ በሉዝ ገዝተዉ ህንፃ በመገንባት የገበያ ማዔከል ባለቤት እንዱሆኑ መፍቀደን ተከትል የክ/ከተማዉ አስተዲደር ባደረገዉ ጥናት ተጠሪ በቤቱ ህጋዊ ተገልጋይ መሆኔ ተረጋግጦ የማህበሩ አባል ሆኜ በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ መሰረት ታዝዤ ብር 10,000.00 ከፍያለሁ። አመልካች እያስገነባ ላለዉ ህንፃ የድርሻዬን መዋጮ እንዱከፍለ በታዘዙኩት መሰረት ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ከብር 800,000.00 በላይ መዋጮ በመክፈል ኃላፉነቴን መወጣቴን ተከትልም አመልካች ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረገዉ ስብሰባ የብር 200,000 ዋጋ ያለዉ 200 አክስዮን ባለድርሻ አድርጎ ተቀብልኝ የገበያ ማዔከለ ግንባታ በተጠናቀቀበት ወቅት በዔጣ ቁጥራቸዉ 14 እና 114 የሆኑ ሱቆችን ሰጥቶኛል። ይሁንና በሱቁ እየተገለገልኩ እያለ አመልካች ሱቆቹን ወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር ለተባለ ግለሰብ እንዱሰጥ ታዝዣለሁ በማለት በፕሉስ ኃይል የእኔ እንዱወሰድ አድርጓል።
በዚህም በንግድ ስራዬ ማግኘት እችል የነበረዉን በወር ብር 26,000.00 አሳጥቶኛል። ስለሆነም አመልካች ሱቆቹን እንዱመልስ፣ ወደ ስራ እስክገባ ድረስ ለማጣዉ ገቢ ኃላፉ እንዱሆን ይወሰንልኝ፤
ይህ ከታለፈ የአክስዪን ባለድርሻ ባደረጋቸዉ መጠን የትርፍ ተካፊይ እንዱያደርገኝ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ።
አመልካች በበኩለ ጉዲዩ አስቀድሞ ዉሳኔ የተሰጠበት ነዉ፣ ተጠሪም መብትና ጥቅም የላቸዉም የሚል የመጀመሪያ መቃወሚያ በማስቆም በፍሬ ነገር ረገድ ለክሱ በሰጠዉ መልስ ህንፃዉ የተገነባዉ ልዩ ቦታዉ ሲዲሞ ተራ ተብል በሚጠራዉ አካባቢ ንግድ ቤት ኖሮአቸዉ በሕጋዊ መንገድ ሲነግደ የነበሩ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በማህበር ተደራጅተዉ በመልሶ ማልማት ቦታዉን በሉዝ እንዱያለሙ መንግስት በፈቀደዉ ልዩ መመሪያ መሰረት ሲሆን ተጠሪ የማህበሩ አባል ሆነዉ የተመዘገቡት ሚያዝያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም አባል የሆኑት ማህበሩ በኃላ/የተ/የግ/ማህበር ደረጃ በ1998 ዓ.ም ሲቋቋም ህንፃዉ በተገነባበት ቦታ ህጋዊ የንግድ ድርጅት ከነበራቸዉ አቶ ሀብቱ ብርሃኑ እና ወ/ሮ ዉድነሽ መሸሻ ላይ ገዝተዉ ስም ሳያዛዉሩ በዚሁ ቤት አባል ሆነዉ የተመዘገቡት ወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር ሰዑድ በማህበሩ ዉስጥ የነበራቸዉን የአክስዮን ድርሻ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም ሸጠዉላቸዉ በእርሳቸዉ ምትክ እንጂ ከመጀመሪያዉ በቦታዉ ላይ የራሳቸዉ ህጋዊ ንግድ ቤት ኖሯቸዉ አይደለም። አመልካች ተጠሪን ሚያዝያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም በአባልነት ሉቀበል የቻለዉ በ2000 ዓ.ም የተደረገዉ የሽያጭ ዉል፣ በማህበሩ ያላቸዉ መብት ለተጠሪ እንዱተላለፍ ወ/ሮ ሙሀባ ቡሴር ለማህበሩ ማመልከቻ በማቅረባቸዉ እና የስም ማዛወሪያ 10,000.00 መክፈላቸዉን የሚያሳይ ሰነድ በማቅረባቸዉ ይህንኑ ከማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 9/23 በማገናዘብ ቢሆንም፣ ተጠሪን በማህበሩ የተኩት ወ/ሮ ሙሀባ ቡሰሬ ተጠሪ የተተኩበትን ሚያዝያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም ቃለ ጉባኤ በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት በማሳገድ በፋ/የመጀ/ደ/ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በአመልካች ላይ ክስ አቅርበዉ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተዉ ክርክር ከተደረገ በኋላ ከወ/ሮ ሙሀባ ወደ ተጠሪ የተዛወረዉ የአክስዮን ድርሻ መብት የለም የሚል ዉሳኔ ተሰጥቷል፤ ግራ ቀኝ በየፉናቸዉ ይግባኝ አቅርበዉ በየደረጃዉ ጸንቷል፤
ሰበር በሰ/መ/ ላይ በትዕዛዝ አጽንቶታል። ስለሆነም ተጠሪ የአክስዮን አባልነት መብት የላቸዉም። አንድ የንግድ ቤት በሁለት ሰዎች እንዱመዘገብ ማድረግ የአመልካች ማህበር የተቋቋመበትን ዓላማ የሚቃረን በመሆኑ አመልካች ተጠሪን የማህበሩ አባል አድርጎ የመመዝገብ ግዳታ የለበትም።
በመሆኑም ተጠሪ ወ/ሮ ሙሀባ ቡሴርን በመተካት የከፈለትን ብር 800,000.00 ከወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር መጠየቅ ከሚችለ በቀር በፍርድ ያጡትን የአክስዮን መብት ለማግኘት ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከርክሯል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር ከሰማ በኋላ ከሁለት ሱቆች ጋር በተያያዘ ተጠሪ ያቀረቡት የካሳ ይገባኛል ጥያቄ በብይን ዉድቅ ያደረገ ሲሆን፣ ተጠሪ ያቀረቡትን የአክስዪን ድርሻ መብት አስመልክቶ የቀረበዉን ዲኝነት በመቀበል በ200 የአክስዮን ድርሻ የሚገኘዉ መብት የሱቅ ድልድልም ሆነ ላልች መብቶች ሁለ ለተጠሪ ይከበርላቸዉ በማለት ወስኗል። ለዉሳኔዉ መሰረት ያደረገዉ ምክንያትም በአጭሩ አመልካች ለህንፃ ግንባታ በሉዝ ከመንግስት ሲተዲደር በተረከበዉ ቦታ ላይ በህጋዊ መንገድ የንግድ ስራ ሲያከናዉኑ የንግድ ማህበረሰብ አባላት የቅድሚያ መብት በመስጠት ባለ አክስዮን አድርጎ የመመዝገብ ግዳታ አመልካች በመንግስት መመሪያ ግዳታ የተጣለበት መሆኑን፤ በክ/ከተማ ደረጃ በተደረገ ማጣራት ተጠሪ የቤ/ቁጥር 593/2 የሆነዉን የንግድ ቤት ከመንግስት ተከራይተዉ የንግድ ፍቃድ አወጥተዉ የንግድ ስራ ሲሰሩ እንደነበረ እንዱሁም አመልካች ወደ አክሲዮን ማህበር ከመቀየሩ በፉት መዋጮ 800,000.00 መክፈላቸዉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ተጠሪ ማቅረባቸዉን፤ በአመልካች ማህበር ቦርድ ሚያዝያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም ተይዞ ግንቦት 26 ቀን 2009 ዓ.ም የተመዘገበዉ ቃለ ጉባኤ ህጉን ስላልተከተለ እንዱሰረዝ እና ወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር ለተጠሪ በሽያጭ አላስተላለፈም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ ላልችን መስፈርቶች አሟልተዉ እስከተገኙ ድረስ የተከራዩት ሱቅ ፈርሶ ይዞታዉ 2003 እስኪረከብ ድረስ ይዘዉ ሲገለገለበት የነበረ በመሆኑ የህግ ጥበቃ የተሰጣቸዉን የባለ አክስዮንነት መብት የሚያሳጣቸዉ አይደለም የሚል ነዉ። አመልካች በዚህ ዉሳኔ ባለመስማማት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 337 መሰረት ተሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚሁ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካች መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የጸናዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚልባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል። የሰበር አቤቱታዉ መሰረታዊ ይዘትም በአጭሩ ማህበሩ በ1998 ዓ.ም ሲቋቋም በአባልነት የተመዘገቡት በቦታዉ ላይ ህጋዊ ንግድ ቤት የነበራቸዉ፣ ህንፃዉ በተገነባበት ቦታ ላይ የንግድ ቤት ባለቤት ሆነዉ በህጋዊ መንገድ ሲነግደ ለነበሩ የንግደ ማህበረሰብ አባላት በማህበሩ ዉስጥ እንዱካተቱ ቅድሚያ መብት እንዱያገኙ በመንግስት በተወሰነ አስገዲጅ መመሪያ ነዉ፤ በወቅቱ በንግድ ቤቱ ሲሰሩ የነበሩት ወ/ሮ ሙሀባ ናቸዉ።
ተጠሪ ሚያዝያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም በተያዘ ቃለ ጉባኤ የማህበሩ አባል ሆነዉ የተመዘገቡት በንግድ ሱቅ ቁጥር 593/02 የንግድ ስራ ሲሰሩ የማህበሩ መስራች አባል ከሆኑት ወ/ሮ ሙሀባ ቡሴር ላይ የአባልነት መብትና ሱቅ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ዉል ተላልፍልኛል በማለት ነዉ።
ይሁንና ወ/ሮ ሙሀባ ቡሴር ለተጠሪ አልሸጥኩም የሚል ክርክር አቅርበዉ ለተጠሪ የተሰጠዉ የአክስዮን ድርሻ እንዱመለስ፤ ተጠሪ የተከራዩትንም ሱቅ ለሙሀባ እንዱመልሱ በሚል በፍርድ ቤት በተሰጠ ዉሳኔ ተጠሪ የአባልነት መብታቸዉን አጥተዋል። የተጠሪ የአባልነት መብት በዚህ ሁኔታ ቀሪ ሆኖ እያለ አመልካች ተጠሪን አባል አድርጎ ሉመዘግብ የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም የሚል ነዉ።
የአመልካች የሰበር አቤቱታዉ በአጣሪ ችልት ተመርምሮም የአሁን ተጠሪ የክርክሩ ተሳታፉ በሆኑበት መዝገብ ላይ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ የባለአክስዮንነት መብት እንደላላቸዉ ተወስኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ለተጠሪ የአክስዮን ድርሻ የወሰነበትን አግባብ ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል ተብሎል። በዚህም መሰረት ተጠሪ ሚያዝያ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ለሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ያደረገዉ ጭብጥ ለዚህ ክርክር መነሻ በሆነዉ መዝገብ ላይ ከሚያዝ ጭብጥ ጋር የማይገናኝ በመሆኑ በድጋሚ የቀረበዉን ዲኝነት በመቀበል የተሰጠ ዉሳኔ ነዉ በሚል አመልካች የሚያቀርበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም። ተጠሪ ባቀረቡት ክስ የአባልነት መብታቸዉ ይከበርላቸዉ ዘንድ ዲኝነት ያቀረቡት በአንድ በኩል አመልካች ሚያዝያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም በያዘዉ ቃለ ጉባኤ አባል አድርጎ መዝግቧቸዉ የነበረ በመሆኑ በልላ በኩል ተጠሪ በማህበሩ ፈቃድና ጥሪ የሱቅ ቦታ ለአመልካች ግንባታ በመዋለ የአክስዮን ባለ ድርሻ ይሆን ዘንድ ተገቢዉን መስፈርት ያሟለ ስለመሆኑ በማህበሩ እና በመንግስት በመረጋገጡ ተጠሪ የአባልነት ክፍያ ከመፈጸም በተጨማሪ የህንፃዉ ግንባታ እንዱጠናቀቅ ከጅምሩ አንስተዉ ተገቢዉም መዋጮ ማድረጋቸዉ ህጋዊ አባልና ባለድርሻ የሚያደርገኝ ነዉ። በመሆኑም እንደማንኛዉም የአክስዮን አባል መፈጸም የሚገባኝን ግዳታና የመንግስት መመሪያ ማሟላቴን በማረጋገጥ የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ በመሆኑ ሉጸና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ግንቦት 05 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር ተከራክሯል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል፣ ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታዉን ለማስቀረብ በአጣሪ ችልት የተያዘዉን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ እንደሚቻለዉ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ለጠየቁት ዲኝነት መሰረት ያደረጉት አቶ ሀብቱ ብርሃኑ ከሚባል ግለሰብ ገዝተዉ የንግድ ፍቃድ አዉጥተዉ ሲሰሩበት በነበረዉ የንግድ ቤት መነሻነት የአመልካች አክሲዮን ማህበር አባል በመሆን እንደማንኛዉም አባል የሚጠበቅባቸዉን ግዳታ የተወጡ ሆነዉ ሳለ የአመልካች ማህበር ከገነባዉ የገበያ ማዔከል ህንፃ ዉስጥ ተሰጥቶአቸዉ ሲገለገለበት የነበረዉን ሱቅ በአመልካች እንዱለቁ መደረጉ ያላግባብ መሆኑን ሲሆን፤
አመልካች በበኩለ ተጠሪ በእርግጥም የአመልካች አክስዮን ማህበር አባል መሆናቸዉን፣ በአባልነታቸዉ ምክንያት የተሰጣቸዉን ሱቅ እንዱለቁ ያደረጋቸዉ መሆኑን ሳይክድ የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ ዉድቅ ይሆን ዘንድ አጥብቆ የሚከራከረዉ ተጠሪ የባለአክስዮንነት ድርሻ እንዱኖራቸዉ ምክንያት የሆነዉን ሱቅ የገዙት ከወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር ሲሆን፣ ወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ መነሻነት ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ ተደርጎ በተደረገ ክርክር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ከወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር ወደ ተጠሪ የተዛወረ የአክስዮን ድርሻ የላላቸዉ መሆኑን ጠቅሶ አመልካች ተጠሪ የያዙትን ሱቅ ለወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር ሉያስረክብ ይገባል የሚል ዉሳኔ መስጠቱንና ዉሳኔዉም ተጠሪ የአክሲዮን ድርሻ የሚያሳጣቸዉ መሆኑን በመጥቀስ መሆኑን ነዉ።
በእርግጥም ወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር በአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በአመልካች አክስዮን ማህበር ዉስጥ በ48ኛ ተራ ቁጥር ላይ ተመዝግበዉ ለማህበሩ ብር 200,000.00 ገቢ ያደረጉ ቢሆንም ምክንያቱን በማያዉቁት ሁኔታ አመልካች ሱቁን ሉያስረክባቸዉ አለመቻለን ጠቅሰዉ በአክሲዮኑ መሰረት ሱቆቹን እንዱያስረክባቸዉ የጠየቁትን ዲኝነት ተከትል ተጠሪም በክርክሩ ጣልቃ በመግባት ክርክር ከተደረገ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ሚያዝያ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የአክስዮን መብት ከወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር ወደ ተጠሪ በህግ አግባብ ያልተዛወረ መሆኑን በመጥቀስ ዉሳኔዉ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ የተሰሩ ስራዎችንና ለአመልካች ተከፍለዋል የተባለ ክፍያዎችን ጨምሮ ስለ ላልች ኃላፉነቶች ወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር እና ተጠሪ በህግ አግባብ የሚጠያየቁ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በህጉ መስፈርት መሰረት የባለ አክስዮንነት መብት የወ/ሮ ሙሃባ ቡሴር ነዉ በማለት ወስኗል፤ በዚህ ዉሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ያጸና ሲሆን በተጨማሪም ተጠሪ በአመልካች ማህበር ባለአክስዮን የሆኑበትን ሚያዝያ 27 ቀን 2009 ዓ.ም የተያዘዉ ቃለ ጉባኤ እንዱሁም በተጠሪ እና በሙሃባ ቡሴር መካከል ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም የተደረገን የንግድ ድርጅት ሽያጭ ዉል እንዱፈርስ ወስኗል፤ ይህ ዉሳኔም በሰበር አጣሪ ችልት በሰ/መ/ ላይ በትዕዛዝ የጸና ስለመሆኑ ከመዝገቡ ለመገንዘብ ተችሎል።
የአመልካች አክስዮን ማህበር መጀመሪያ በ1998 ዓ.ም በኃ/የተ/የግ/ማህበርነት ሉቋቋም የቻለዉ ማህበሩ ህንፃ በገነባበት ቦታ ላይ የንግድ ቤት ባለቤት ሆነዉ በህጋዊ መንገድ ሲነግደ ለነበሩ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በማህበሩ ዉስጥ እንዱካተቱ የቅድሚያ መብት እንዱሰጥ በመንግስት በተቀመጠ አስገዲጅ መመሪያ ስለመሆኑ፣ ተጠሪ በአመልካች ማህበር የአክስዮን አባል ሆነዉ ሉመዘገቡ የቻለትም አክስዮን ማህበሩ በ1998 ዓ.ም ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሆኖ ሲቋቋም ለአመልካች በመልሶ ማልማት ተፈቅድለት ህንፃ በገነባበት ቦታ ላይ በንግድ ሱቅ ቁጥር 593/02 የንግድ ስራ ሲሰሩ የማህበሩ መስራች አባል ከሆኑት ወ/ሮ ሙሀባ ቡሴር ላይ የአባልነት መብትና ሱቁን ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም በመግዛታቸዉ እንጂ ማህበሩ በ1998 ዓ.ም ሲቋቋም የንግድ መስሪያ ቦታ ስለነበራቸዉ አለመሆኑ ተጠሪ ክደዉ አይከራከሩም። ይህም የሚያሳየዉ ተጠሪ በአመልካች ማህበር የአክስዮን ድርሻ እንዱያገኙ ምክንያት የሆነዉ እንደ ላልች የማህበሩ የአክስዮን አባላት ማህበሩ ሲመሰረት የአመልካች ህንፃ በተገነባበት ቦታ ላይ የንግድ ቤት ተከራይተዉ ስለነበሩ ሳይሆን፣በወቅቱ በቦታዉ የንግድ ቤት ተከራይተዉ የነበሩት ወ/ሮ ሙሀባ ቡሴር በሽያጭ ሲላስተላለፈላቸዉ መሆኑን ነዉ። ከዚህም ተጠሪ የንግድ ቤቱን ከወ/ሮ ሙሀባ ቡሴር በግዥ ባያገኙ ኖሮ ከአመልካች ማህበር የባለአክዮንነት መብት ማግኘት የማይችለ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
ይሁንና ተጠሪ የአመልካች አክስዮን ማህበር አባል ሆነዉ እንዱመዘገቡ ምክንያት የሆነዉ የሽያጭ ዉል እንዱሁም የአክስዮን አባልነት ዔዉቅና ያገኘበት ዉሳኔ (ቃለ ጉባኤ) ከፍ ሲል በተመለከቱት ግልጽ ዉሳኔዎች ተሽረዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአክስዮን ድርሻ መብት ለቀድሞ ባለቤቷ ለወ/ሮ ሙሀባ ቡሴር እንዱመለስ ተወስኗል። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለዉ ተጠሪ ከአመልካች የነበራቸዉን የአክስዮን ድርሻ መብት በፍርድ ሃይል ማጣታቸዉን ነዉ። በአመልካች ማህበር የአክስዮን ድርሻ መብት ለማግኘት ማህበሩ ህንፃዉን ባስገነባበት ቦታ ላይ ቀደም ሲል የነበሩት ሱቆች ህጋዊ ተከራይ ሆኖ መገኘት እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚታይ ከመሆኑ አኳያ፣ ተጠሪ የአክስዪን መብት እንዱያገኙ ምክንያት የሆነዉ ዉል ተሽሮ እንዱሁም የአክስዮን አባልነት መብት ከወ/ሮ ሙሀባ ቡሴር ወደ እርሳቸዉ የተዛወረበት ሁኔታም በህጋዊ መንገድ አለመሆኑ ተረጋግጦ የአክስዮን አባልነት መብት ያገኙበት ቃለጉባኤ እንዱፈርስ ተወስኖ ባለበት ሁኔታ፣ ተጠሪ ለህንፃዉ ግንባታ መዋጮ ማዋጣታቸዉ መረጋገጡ ተጠሪ ከአመልካች ማህበር የአክስዮን ድርሻ እንዱኖራቸዉ ምክንያት አይሆንም። ለሁለም ግልጽ እንደሚሆነዉ ፍርድ ቤት በህግ የተረጋገጠን መብት ከማስከበር/ከማክበር በዘለለ እራሱ መብት ሉፈጥር አይችልም።
በልላ በኩል በፍርድ ቤት የሚሰጥ ማንኛዉም ዉሳኔ ስርዓቱን ጠብቆ እስካልተለወጠ ወይም እስካልተሻሻለ ድረስ ተፈፃሚ ሆኖ ሉቀጥል የሚገባ ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ፍትሕ አስተዲደር ተቀባይነት ካገኙ መርሆዎች ዉስጥ አንደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ካልሆነ እና ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ያሳረፈባቸዉን ጉዲዮች በማንኛዉም ጊዜ እና ሁኔታ እንዱሁም በማንኛዉም አካል በዘፈቀደ እንዱሻር ወይም እንዱለወጥ መፍቀድ የፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ተገማች እንዲይሆኑ የማድረግ ዉጤት የሚያስከትል ከመሆኑም በላይ ዜጎች በፍርድ ቤት ላይ አመኔታ እንዲይኖራቸዉ ብልም የህግ የበላይነት እንዱሸረሸር ምክንያት ይሆናል። በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጋችን አንቀጽ 5 ላይ በፍርድ ያለቀ ጉዲይ በድጋሚ እንዲይቀርብ የሚከለክለዉ ድንጋጌ እንዱሁም ሥነ-ሥርዓቱን ጠብቆ እንዱታረም ያልተደረገ ዉሳኔ ተፈፃሚነቱ መቀጠል እንዲለበት በአንቀጽ 212 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌም የፍርድ ቤት ዉሳኔ በዘፈቀደ ሉሻሻል ወይም ሉለወጥ አይገባም የሚለዉ መርህ በእኛ አገር የፍትሐብሕር ፍትሕ አስተዲደር ተቀባይነት ስለማግኘቱ ማሳያዎች ናቸዉ። ክርክሮች ተገቢዉን ሥርዓት ጠብቀው የቀረቡ መሆን አለመሆናቸዉን የመቆጣጠር፣ የክርክር አመራር ሥርዓቱም ተቀባይነት ያገኙ የፍትሐብሕር ፍትሕ አስተዲደር መርሆዎችን ያገናዘበ እና የተከራካሪ ወገኖችን የመደመጥ መብት ከግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ የመምራት ኃላፉነት በዋነኝነት የፍርድ ቤት ስለመሆኑም የሚታወቅ ነዉ።
ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት ተጠሪ በልላ መዝገብ ላይ ተከራክረዉ ያጡትን መብት በልላ የፍርድ መዝገብ ለማስከበር ያቀረቡትን ዲኝነት ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ፣ ተጠሪ ለግንባታዉ አስፈላጊ የሆነዉን መዋጮ መክፈላቸዉ እና በአክስዮን መዝገብ መግባታቸዉ መረጋገጡን ብቻ መሰረት በማድረግ የባለአክስዮንነት መብት እንዱከበርላቸዉ በሚል በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የጸናዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። ተከታዩም ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ ከአመልካች ማህበር የአክስዮን ድርሻ የላቸዉም ተብል ተወስኗል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ችልት ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ እግድ ተነስቷል።
ከስር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረበዉ መዝገብ በመጣበት አኳኋያ ለፍርድ ቤቱ ይመለስ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.