የቤት ሽያጭ ውል ከተደረገ በኋላ እንደ ውለ ባለመፈጸሙ ሻጭ በውለ መሰረት ቤቱን እና የቤቱን ሰነድች ሆነ ላላ አስፈላጊ ተግባር እንዱፈጽሙ ክስ ከቀረበ ውለ የፍ/ሕ/ቁ. 1723 በሚያዘው አግባብ በውል አዋዋይ ፉት ያልተደረገ ቢሆንም ሻጭ ውል መኖሩን ያመነ ከሆነ በሻጭ እና በገዥ መካከል ሕጋዊ የሆነ የፀና ውል አለ ማለት የሚቻል ሲሆን የፀና ውል ካለ ደግሞ ሻጭ በውል የገባውን ግዳታ፤ በፍ/ሕ/ቁ. 1731(1) እንደተደነገገው ውል በተዋዋዮች መካከል እንደ ሕግ የሚቆጠር ስለሆነ እና ውል እንዱፈጸም የተጠየቀው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በመሆኑ ገዥ ልዩ ፍላጎት ንብረቱ ላይ እንዲለው ግምት ስለሚወሰድ፤ ሻጭ የመፈጸም ግዳታ ያለበት ኒው ክሬሽን ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን እና ጭላል ኢንተርፔራይዝ ኃ/የተ/የግል ማህበር
No summary available.
የሰበር መዝገብ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ወ/ሮ ማኔ ጫፊ ቀርቧል ወ/ሮ እራሼ ጫፊ ተጠሪ፡- አቶ ተስፊዬ ቡንዲሬ - ቀርቧል ለምርመራ ተቀጥሮ የነበረው መዝገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
አመልካቾች የቦላ ሶሬ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 56/13 ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት አስቀድሞ የሰጠውን የዔግድ ትዕዛዝ ማሻሻለን በመቃወም ያቀረቡትን ይግባኝ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 21 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት መሰረዙ፣ የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወላይታ ምድብ ችልት በመዝገብ ሚያዚያ 8 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን ማፀናቱ እንዱሁም የሰበር አጣሪ ችልቱ በሰበር መዝገብ ሚያዚያ 8 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት በሥር ሶስቱም ፍርድ ቤቶች የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም በማለት የአመልካቾችን የሰበር አቤቱታ መሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት በሰበር ለማሳረም የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ መዝገቡ ለችልት ቀርቧል።
ጉዲዩ አመልካቾች የውርስ ይጣራ ክስ አቅርበው በግራ ቀኙ መካከል ክርክሩ ቀጥል እያለ አመልካቾች ተጠሪ የውርስ ንብረቶቹን ለሶስተኛ ወገን እያስተላለፈ ነው በማለት ካሳገደ በኋላ ተጠሪ የዔግድ ይነሳልኝ አቤቱታ አቅርቦ አመልካቾችም መልስ እና ከጉርሞ ማዘጋጃ ቤት አስቀድሞ የተሰጠውን ዔግድ በተመለከተ የተፃፈ ደብዲቤ ያቀረቡ ሲሆን የቦላ ሶሬ ወረዲ ፍርድ ቤት ወቅቱ የመንግስት ግብር የሚከፈልበት በመሆኑና የተጠሪ ገቢ ምንጭም ከእርሻ የሚገኝ መሆኑን በመረዲት እንዱሁም አንድ ባህር ዛፍ ለማገድ እንድጠቀም አስፈላጊ መሆኑን በማመን ከታገደት 9ንብረቶች ውሰጥ ጫት፣ ጌሾ፣ ማንጎ፣ ካሽሚር፤ ቡና፣ እንሰት፣ ለማገድነት የሚያገለግል አንድ ባህር ዛፍ እንዱሁም በክርከሩ መሬት ውስጥ ያልተጠቀሱ ሁለት የንግድ ቤቶች እና በክሱ ውስጥ ያልተጠቀሱ ሁለት ሰርቪስ ቤቶች ላይ የተሰጠው ዔግድ ለጊዜው ተነስቶ በላልች ንብረቶች ላይ የተሰጠው የዔግድ ትዕዛዝ እንዱቆይ ትእዛዝ የሰጠ ሲሆን ከጉርሞ ማዘጋጃ ቤት ተጠሪ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ዔገዲ ጥሷል በማለት የተፃፈው ደብዲቤ እውነትነት የለውም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል። አመልካቾች ይህን ትዕዛዝ በመቃወም ያቀረቡትን የይግባኝ አቤቱታ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰረዘው ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወላይታ ምድብ ችልት ግራ ቀኙን አከራክሮ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ሲያፀና የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት የሶስቱም ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በማለት የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ለሰበር ሰሚ ችልቱ አያስቀርብም በማለት መዝገቡን ዘግቷል።
አመልካቾች በየደረጃው ያለት የሥር የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ እና ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል በማለት በሰበር ለማሰረም ሚያዚያ 12 ቀን 2013 ዓ/ም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዘት፡- የውርስ ማጣራት ክስ ቀርቦ ጉዲዩ ተጣርቶ ውሳኔ እስክያገኝ ድረስ በውርስ ይዞታው ላይ ያለ ቋሚ አትክልቶች ታግድ እና ተከብሮ እንዱቆዩ አቤቱታ አቅርበው የወረዲው ፍርድ ቤት ለጉርሞ ኮይሻ ማዘጋጃ ቤት ታግድ እና ተከብሮ እንዱቆዩ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ተጠሪ ዔገዲውን በመጣስ ታግድ ያለ ንብረቶችን እየተጠቀመ መሆኑን አመልካቾች አቤቱታ አቅርበው ተጠሪ የታገደ እንጨቶችን ነቃቅል በመጣል እንዱሁም ቡና እና ጫት እየተጠቀመ መሆኑን ከጉርሞ ኮይሻ ማዘጋጃ ቤት መግለጫ ቀርቦ እያለ ዔግደ በመጣሱ የቦላ ሶሬ ወረዲ ፍርድ ቤት እርምጃ መወሰድ ሲገባው ዔገዲውን በከፉል ማንሳቱ የወራሾችን መብት የሚነካ እና የውርስ ንብረት ተጠሪ እንዱያጠፊ የሚያደርግ ነው በማለት ያቀረቡት የይግባኝ እና ሰበር ቅሬታ ተቀባይነት በማጣቱ ጠቅላላ ግምቱ 1,93,000.00( አንድ ሚልዮን ዘጠና ሶስት) ሺ ብር የሚሆን ንብረት እንዱጠፊ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ሰህተት በመሆኑ ጉዲዩ ተጣርቶ ውሳኔ እሰከሚያገኝ ድርስ የዔግድ ትዔዛዙ ፀንቶ እንዱቆይ እንድታዘዝላቸው ጠይቀዋል።
የአመልካቾችን የሰበር አቤቱታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልቱ፡- የሥር ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ መካከል ባለው የውርስ ንብረት ክርክር ጉዲይ የእግድ ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ በተጠሪ የዔግድ ይነሳልኝ አቤቱታ የንግድ ቤቶች እና በላልችም ንብረቶች ላይ የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ የማንሳቱን አግባብነት ለመመርምር ለሰበር ሰሚ ችልቱ ይቅረብ በማለቱ ተጠሪ በሰጠው መልስ፡- ዔገዲ ለመጣሱ ከጉርሞ ኮይሻ ማዘጋጃ ቤት የተሰጠ መግለጫ ባለመኖሩ እንዱሁም ዔገዲ የተነሳላቸው ንብረቶች የተጠሪ የግል ንብረቶች በመሆናቸው በላይ ጫት እና ጌሾ በየሶስት ወሩ ከልተለቀሙ ተጠሪ በየጊዜው ማግኘት ያለበትን ጥቅም በመሳጣት ሉተካ የማይችል ጉዲት የሚደርስበት በመሆኑ እና ቡናም ከመታገደ በፉት አፍርቶ ፍሬው በመሬት ላይ ረግፍ እየተበላሸ ስለነበረ ተጠሪም በርካታ ቤተሰብ የሚያስተዲድር አማራጭ የገቢ ምንጭ የላለው አርሶ አደር በመሆኑ ለዔለት ኑሮው አስፈላጊ በሆኑት እና በክርክሩ ውስጥ በላለ ንብረቶች ላይ ዔግደ መነሳቱ አግባብ ነው በማለት ተከራክረዋል። የአመልካቾች መልስ መልስም ቀርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና ግራ ቀኙ በዚህ ችልት ያደረጉት የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን ችልቱ አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ አንፃር እንደሚከተለው መርምሮታል። በክርክር ሂደት ተከሳሽ ንብረት በማሸሽ ወይንም ለላላ ሰው በማስተላለፍ የክርክሩን ሂደት ውጤት አልባ በማድረግ ከሳሽ ላይ የማይተካ ጉዲት ሉያደርስ የሚችልበትን ሁኔታ ለማስቀረት ከፍርድ በፉት ንብረት እንደምከበር ወይም ዔግድ እንደምሰጥ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ከቁጥር 147 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ያመለክታለ። ከፍርድ በፉት ንብረት እንዱያዝ ወይንም እንዱታገድ የሚሰጠው ትዕዛዝ የተከሳሽን የንብረት መብት ከማገድ አልፍ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይም አለታዊ ተፅኖ ሉያስከትል ስለሚችል የሚሰጠው ትዕዛዝ እነዚህን ተነፃፃሪ መብቶች ያማከለ መሆን አለበት። ንብረት ማስከበር የክርክሩ ሂደት ተጠናቆ ለሚሰጠው ፍርድ ማስፈፀሚያነት ይውል ዘንድ ንብረት ተይዞ በፍርድ ቤት ቁጥጥር ሥር ባለበት ሁኔታ በማቆየት ከሳሽ በፍርድ የሚያገኘው መብት ተጠቃሚ እንዱሆን ማስቻል ነው። ንብረት የሚከበረው ወይንም የሚታገደው ተከሣሽ ንብረቱን በማሸሽ ወይንም ለላላ ሰው በማስተላፍ አፈፃፀሙን በማሰናከል እና በማዘግየት የከሳሽን ጥቅም ለመጉዲት ለመዘጋጀቱ በቂ ምክንያት መኖሩ በፍርድ ቤት ተረጋጦ በከሳሽ ላይ ሉደርስ የሚችለው ጉዲት ለማስቀረት ወይንም ለመከላከል የሚሰጥ ትዕዛዝ ነው።
በተያዘው ጉዲይ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑን ንብረቶች ተጠሪ ለሶስተኛ ወገን እያስተላለፈ ነው በማለት አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ዔግድ ከተሰጠ በኋላ ተጠሪ የዔግድ ይነሳልኝ አቤቱታ አቅርቦ አመልካቾችም መልስ እና አስቀድሞ የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ መጣሱን ይገልፃል ያለትን ማስረጃ ከጉርሞ ማዘጋጃ ቤት በማቅረብ የተከራከሩ ሲሆን፤ የቦላ ሶሬ ወረዲ ፍርድ ቤት የተጠሪን ገቢ ምንጭ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለዔለት ኑሮ አስፈላጊ በሆኑት አንድ የባህርዛፍ እንጨት፣ ጫት፣ ጌሾ፣ ማንጎ፣ ካሽሚር፤ ቡና እና እንሰት ላይ አስቀድሞ የሰጠውን የዔግድ ትእዛዝ ማሻሻለ እንዱሁም በየደረጃው ያለ ፍርድ ቤቶችም እነዚህን ንብረቶች በሚመለከት የተሰጠውን የዔግድ ትዕዛዝ መሻሻለን በመቃወም አመልካቾች ያቀረቡትን የይግባኝ እና ሰበር አቤቱታ መሰረዛቸው የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም።
ይሁን እንጂ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ንብረቶች ተጠሪ ለሶስተኛ ወገን ለማስተላለፍ መዘጋጀቱ በአመልካቾች የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ታምኖበት የዔግድ ትእዛዝ ከተሰጠባቸው ንብረቶች ውስጥ ሁለት የንግድ ቤቶች እና ሁለት ሰርቪስ ቤቶች ላይ ክርክሩ ቀጥል ባለበት እና በንብረቶቹ ላይ ትክክለኛ ባለመብት ማን እንደሆነ ሳይጣራ በክሱ ውስጥ እና በክርክሩ መሬት ውስጥ አልተጠቀሱም በማለት በእነዚህ ንብረቶች ላይ የተሰጠው ዔገዲ መነሳቱ ተጠሪ ንብረቶቹን ለ3ኛ ወገን በማስተላለፍ በአመልካቾች ላይ ጉዲት ሉያደርስ ስለሚችል የሚነቀፍ ሆኖ እያለ ጉዲዩን በይግባኝ እና በሰበር ያዩት ፍርድ ቤቶችም ይህን ትዕዛዝ ማጽናታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የፈፀመበት በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል።
የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በሰበር መዝገብ ሚያዚያ 8 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ፣ ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወላይታ ምድብ ችልት በመዝገብ ሚያዚያ 8 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ፣ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 21 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ እና የቦላ ሶሬ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 56/13 ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት አስቀድሞ የሰጠውን የዔግድ ትዕዛዝ በማሻሻል የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
ጫት፣ ጌሾ፣ ማንጎ፣ ካሽሚር፤ ቡና፣ እንሰት፣ ለማገድነት የሚያገለግል አንድ ባህር ዛፍ እንጨት ላይ ተሰጥቶ የነበረውን የዔግድ ትዕዛዝ በማሻሻል የቦላ ሶሬ ወረዲ ፍርድ ቤት ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ እና በየደረጃው ያለት ፍርድ ቤቶች ያፀኑት ውሳኔ ፀንቷል።
ሁለቱ የንግድ ቤቶች እና ሁለት ሰርቪስ ቤቶችን አስመልክቶ የተሰጠው የትዕዛዝ ክፍል ተሽሯል።
በተራ ቁጥር “3” ሥር የተጠቀሱት ንብረቶች ጉዲዩ እልባት እስክያገኝ ድረስ ባለበት ሁኔታ ታግድ እንዱቆዩ ብለናል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ውጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የግላቸውን ይቻለ።
በዚህ መዝገብ ላይ ተሰጥቶ የነበረው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
ውሳኔው ህዲር 1 ቀን 2014 ዓ/ም በችልት ተነቧል።
No topics extracted.