No summary available.
ቀን፡- ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ አመልካች፡- አቶ ይስማው ድረስ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ፤ ተጠሪዎች ተከሳሾች ሆነው ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የተጀመረው በእስቴ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በ15/07/2013 ዓ/ም ባቀረቡት ክስ በ1989 ዓ/ም እስቴ ወረዲ ልጫ ቀበላ በዛሬው ስነ-ህይወት ከተማ መጠኑ አንድ ቃዲ መሬት ተሰጥቼ ደብተር አሰርቼ የያዝኩትን መሬት በምስራቅ በኩል ተጠሪዎች በግምት 500 ካሬ ሜትር በ1994 ዓ/ም በኪራይ ቤት አማካኝተው ቤቱን ከሰሩ በኋላ በመሬቱ ላይ በድብቅ ደብተር በማሰራት መሬቱን ስለያዘብኝ የሰሩትን ቤት አፍርሰው መሬቱን እንዱለቁልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች በ29/07/2013 ዓ/ም ባቀረቡት የመከላከያ መልስ በአመልካች ደብተር የተጠቀሰውን መሬት አልያዝንም፤ ከሃያ ዓመት በፉት ከባህር ዲር መንገድ ዲር በህገ-ወጥ መንገድ ሰርተን የያዝነው ይዞታ ስለነበር ከተማው ሲጠና እና በመሀንዱስ ሲሸነሸን 369 ካሬ ሜትር ጸድቆልን የያዝነው ነው። በ2011 ዓ/ም በድንበር ግፉ ተጣልተን ድንበራችንን ሲሚዛ አድርገን ገደብ 5000 ብር አስቀምጠን ታርቀን እያለ ክስ መመስረቱ አግባብ አይደለም። ቦታው ወደ ከተማ ገብቶ ሲሸነሸን በገጠሩ እና በከተማው ህዝብ የልጫ ስነ-ህይወት ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስገምግሞ የማንም ሳይሆን የእኛ ይዞታ መሆኑ ተረጋግጦ አመልካች አብሮ ገምግሞ ነው ካርታ የተሰራልን። አመልካችም ምንአልባት ቦታው የእሱ ከሆነ መጠየቅ ያለበት የሰጠበትን አካል እንጂ እኛን ስላልሆነ ክሱ ውድቅ እንዱደረግልን፤ ከፈለገም ቦታውን እና ቤቱን ያጸደቀው የልጫ ስነ-ህይወት ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋቢ ይለፍልን በማለት የመከላከያ መልሳቸውን አቅርበዋል።
የእስቴ ወረዲ ፍርድ ቤቱም ማስረጃ በመስማት መሬቱን አመልካች በ1989 ዓ/ም ከተመራው መሬት ላይ በ1994 ዓ/ም ለተጠሪ 600 ብር ባድውን እንደሸጠላቸው፤ የተጠሪን ቤት የሰሩት ያለ አመልካች ተቃውሞ መሆኑን፤ ሙለው ቦታ ላይ ቤት እንደሰሩበት ተረጋግጧል። ባድ ቦታ ደግሞ እንደማይሸጥ እና እንደማይለወጥ የህገ-መንግስቱ ቀጥር 40/3 እና የክልለ የመሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 ቁጥር 5/1 የሚደነግጉ በመሆኑ የባድ ቦታ ሽያጭ ውል ህገ ወጥ ውል ነው፤ ሕገ-ወጥ ውል ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ሉመለሱ ወይም በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1817 መሰረት ውለ ጉድለት ቢኖርበትም ውለ የሚረጋበት ሁኔታ ሉኖር እንደሚችል ይደነግጋል። ድንጋጌውም ውለ በመፍረሱ ምክንያት አንደኛው ተዋዋይ ወገን ያልተገባ ጥቅም እንዱያገኝ አንደኛው ተዋዋይ ወገን ደግሞ ውለ በመፍረሱ ወይም በመሰረዙ ምክንያት የከፊ እና የማይተካ ጉዲት እንዲይደርስበት ለማጣጣም ያለመ ነው። አሁን በተያዘው ጉዲይ ላይም ተጠሪዎች ባድ ቦታ ገዝተው ቤቱ የሰሩበት መሆኑ ቢረጋገጥም ሙለ ቦታው ላይም ቤት እንደሰሩበት ስለተረጋገጠና ቤቱ ይፍረስ ቢባል ተጠሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዲት የሚያስከትል በመሆኑ የሽያጭ ውለ ሉጸና ይገባል፤ አመልካችም ተጠሪዎች ቤቱን አፍርሰው ቦታውን እንዱለቁት ሉጠየቅ አይገባም በማለት ወስኗል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን የይግባኝ አቤቱታ ባለመቀበል ሰርዘዋል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የውለ መፍረስ ውጤት ወደ ነበሩበት መመለስ በመሆኑ ግራ ቀኙ ያልተገባ ጥቅም የማያስገኝ እና በአንደኛው ወገን ላይ ከፍ ያለ ጉዲት የማይደርስ መሆኑ ሲረጋገጥ የሚፈጸም ሲሆን በተያዘው ጉዲይ የሽያጭ ውለ የተከናወነው በ1994 ዓ/ም ሆኖ ተጠሪዎች ቤት ሰርተው እየኖሩበት ያለ በመሆኑ እና ወደ ነበሩበት ይመለሱ ቢባል ቤት ማፍረስ እና አንስቶ መልቀቅ በተጠሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዲት የሚያደርስ በመሆኑ ላላ ማጣራት የሚያስፈልገው ፍሬ ነገር ስለሆነ እና ጉዲዩም ዲኝነት ያልተጠየቀበት ነጥብ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ወሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለው ሆኖ አላገኘነውም በማለት ውሳኔውን አጽንቷል።
No topics extracted.
ይሕ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። አመልካች በቀን 04/09/2014 ዓ/ም በጻፈት የሰበር አቤቱታ ይዞታው በ1989 ዓ/ም፣ በ1996/97 በተደረገው የመሬት ቆጠራ እና ምዝገባ ወቅት የአመልካች ሆኖ የተመዘገበ መሆኑ፤ ተጠሪዎች በተጭበረበረ መንገድ የወሰደት ደብተር በመ/ቁ ገ/ጠ/አስ/አጠ/5105/38 በ12/20/2010 ዓ/ም የተሰረዘ መሆኑ በወረዲ ፍርድ ቤት ተረጋግጦ፤ በወረዲ ፍርድ ቤት በተደረገው የማጣራት ሂደት ተጠሪዎች መሬቱን የያዙት በግዢ እንደሆነ ተረጋግጦ እያለ ይህንን በሚቃረን መልኩ የወረዲ ፍርድ ቤት ህገ-ወጥ ውል ቢሆንም ወደነበረበት ቢመለስ በተጠሪዎች ላይ የከፊ ጉዲት ሉደርስ ስለሚችል የጸና ውል ነው ማለቱ የአመልካችን መብት የሚጎዲ ስለሆነ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ተሽሮ ትክክለኛ ውሳኔ እንዱሰጠኝ የሚል ነው።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ የስር ፍርድ ቤቶች በአመልካች እና ተጠሪዎች መካከል የተፈጸመው የመሬት ሽያጭ ውል ህገ-ወጥ ቢሆንም ውለ ፈርሶ ወደ ነበሩበት እንዱመለስ ማድረግ በአንደኛው ወገን ላይ ከፍ ያለ ጉዲት የማያደርስ ከሆነ ብቻ ነው፤ በተያዘው ጉዲይ ላይ በተጠሪ ላይ ከፍ ያለ ጉዲት የሚያደርስ ስለሆነ ውለ ሉፈርስ አይገባም ተብል የተወሰነበት አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩን ለመመርመር ተጠሪዎች የመከላከያ መልሳቸውን ይዘው እንዱቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተጠሪዎች በ15/05/2015 ዓ/ም በተጻፈ የመከላከያ መልስ ክርክራችን ድንበር ገፊኸኝ ስለሆነ መጣራት ያለበት ተጠሪዎች የአመልካችን ይዞታ ገፍተው ቤት ሰርተዋል ወይስ አልሰሩም የሚለው ነው መሆን ያለበት። ይዞታው በምንም መልኩ ይያዝ ይዞታውን ከ1994 ዓ/ም ጀምሮ የያዘው መሆኑ በህዝብ የተረጋገጠ እና የይዞታ ደብተሬን አስረክቤ ካርታ እና ፔላን የተሰጠኝ በመሆኑ፤
በተሰጠኝ መሬት ከአመልካች ጋር በድንበር ግፉ ተስማምተን ድንበራችን ለይተን አመልካችም ይዞታው የእኔ መሆኑን አረጋግጦ ማንም ሳይቃወመኝ በ396 ካሬ ሜትር ላይ ሙለውን ቤት ሰርቼ ቤተሰቦቼን የማስተዲድርበት ቤት መሆኑ በበቂ ማስረጃ የተረጋገጠ እና ድንበራችንን ለይተን የተስማማን ለመሆኑ ያመነ በመሆኑ፤ የአመልካች እና የተጠሪ አዋሳኝ የተለያየ እና አንዲችን ለአንዲችን ድንበር ያልገፊን ለመሆኑ በተሰጠን ካርታ ማዘጋጃ ቤት አረጋግጦ ማስረጃ የሰጠ በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግልን። ተጠሪ በስር መልሴ ላይ የአመልካች አዋሳኝ እና የተጠሪ አዋሳኝ የተለያየ እና የየራሳችንን ካርታ የያዝን ሲሆን በመዘጋጃ የተሰጠኝን ካርታ በማስረጃነት አያይዤ አቅርቤያለሁ። ተጠሪ በይዞታው ላይ ከ1994 ዓ/ም ጀምሮ ቤት የሰራሁት አመልካች ሳይቃወመኝ በመሆኑ እና 20 ቤተሰብ አባላን በዚህ ቦታ የማስተዲድር እና ከ22 ዓመት በላይ የያዝኩትን ከዚህም በላይ ቤት እና ቦታው የእኔ ለመሆኑ ተረጋግጦ በ1996 ዓ/ም አረንጓዳ ደብተር ሲሰጥ አመልካችም አብሮ ያስተቸ ለመሆኑ በምስክር አረጋግጫለሁ። አመልካች ብለቅ ከፍ ያለ ጉዲት የሚያስከትል እና በአስተዲደር አካል የተሰጠን ካርታ ፍርድ ቤት ሉሰርዘው የሚችልበት አግባብ የላለ እና እንዱሰረዝም ዲኝነት ያልተጠየቀ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሉጸና ይገባል ብለዋል። አመልካች በ13/06/2015 ዓ/ም በሰጡት የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች በ15/07/2013 ዓ/ም ባቀረቡት ክስ በ1989 ዓ/ም እስቴ ወረዲ ልጫ ቀበላ በዛሬው ስነ-ህይወት ከተማ መጠኑ አንድ ቃዲ መሬት ተሰጥቼ ደብተር አሰርቼ የያዝኩትን መሬት በምስራቅ በኩል ተጠሪዎች በግምት 500 ካሬ ሜትር በ1994 ዓ/ም በኪራይ ቤት አማካኝተው ቤቱን ከሰሩ በኋላ በመሬቱ ላይ በድብቅ ደብተር በማሰራት መሬቱን ስለያዘብኝ የሰሩትን ቤት አፍርሰው መሬቱን እንዱለቁልኝ በማለት ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸው በሕገ-ወጥ መንገድ ይዞታው ላይ ቤት ሰርተን በመያዝ በኋላም በማዘጋጃ ቤቱ ሕጋዊ ተደርጎ የተመዘገብልን ንብረታችን ነው በማለት ተከራክረዋል። ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፉነት ሲሆን በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ዓላማዎች የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰለትን ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን መብት ይነካል። ክርክር የሚወሰነው በተጠየቀው ዲኝነት አግባብ እንደሆነ የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 182(2) ላይ ተመልክቷል። ፍርድ ቤቱም ከቀረበው ዲኝነት አኳያ ከግራ ቀኙ ክርክር በመነሳት በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 246 እና ተከታዮቹ መሰረት በተነሱት ጉዲዮች ጭብጥ መስርቶ ውሳኔ የመስጠት ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ በሰበር መዝገብ ሆነ በላልች በርካታ መዝገቦች ላይ አስገዲጅ ትርጉም የተሰጠበት ነው።
በፍ/ሕ/ቁ. 2001 የተመለከተው የአንድን ነገር መኖር ገልጾ የተከራከረ ወገን የጠቀሰው ፍሬ ነገር መኖሩን ሆነ ትክክለኛነቱን የማስረዲት ኃላፉነት አለበት (the one who alleges shall prove it) የሚለው የማስረጃ አቀራረብ መርህን ፍርድ ቤቶች ተከትለው ሉወሰኑ ይገባል። በክርክር ሂደት ፍሬ ነገሮችን ማረጋገጥ የሚቻልባቸው ዘዳዎች ማስረጃ፣ በፍርድ ቤት በሚሰጥ የእምነት ቃል፣ ፍርድ ቤት በራሱ ግንዛቤ ሉወስድባቸው የሚችለ ጉዲዮች፣ የሕግ ግምት እና የመሒላ ቃል ናቸው። በፍትሐ ብሓር ክርክር የምንከተለው የማስረዲት ደረጃ ከሁለቱ ወገን የተሻለ ያስረዲው ማን ነው (preponderance of evidence) የሚለውን በመመርመር በመሆኑ አመልካቾች ግዳታቸውን ከተወጡ በኋላ የተጠሪ ማስረጃን በመስማት ማመዛዘን ይገባል። የማስረጃ ተገቢነት (relevancy test)፣ የማስረጃው ተቀባይነትን (admissibility) ደንቦችን መከተል እና ለማስረጃው የሚሰጠውን ክብደት (weight of evidence) በመለየት የመወሰን ኃላፉነት ማስረጃ ለመስማትና ለመመዘን ኃላፉነት ያለባቸው ፍርድ ቤቶች ዋና ተግባር ነው።
ፍርድ ቤት ጭብጥ ሉይዝ ሆነ በማስረጃ ሉያጣራ የሚገባው በግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የተነሳን ፍሬ ነገር መሰረት በማድረግ ላሆን ይገባል። በተያዘው ጉዲይ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የተመሰረተው ተጠሪዎች ይዞታውን በሽያጭ ውል ያገኙት መሆን አለመሆኑ እና የሽያጭ ውለ ሕገ-ወጥ መሆን ያለውን ሕጋዊ ውጤትን በመመርመር ነው። አመልካች በክስ አቤቱታቸው ላይ በኪራይ አማካኝተው ያዙብኝ ከማለት ባለፈ በሥር ፍርድ ቤት ይዞታው በሽያጭ ውል የተላለፈ ነው በማለት በሥር ፍርድ ቤት አልተከራከሩም። ተጠሪዎችም ሰነድ አልባ ይዞታ በመያዝ በኋላም ሕጋዊ ባለይዞታ ሆነናል ከማለት ባለፈ ከአመልካች ጋር በሽያጭ ውል ግንኙነት ያገኘነው ንብረት ነው በማለት አልተከራከሩም።
ስለሽያጭ ውል የተጠቀሰው በምስክሮችና ማስረጃ በሰጠው አካል ነው። ምስክር ሆነ ማስረጃ የሚቀርበው ተከራካሪዎች ያቀረቡትን ፍሬ ነገር መኖር አለመኖር ወይም ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንጂ አዱስ ክርክር ለማቅረብ/ለመቀበል አይደለም። በግራ ቀኙ ተከራካሪዎች ያልተነሳን ፍሬ ነገር መሰረት በማድረግ የሥር ፍርድ ቤቶች ጭብጥ በመያዘ መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ግድፈት የተፈጸመበት ነው። ክሱ የቀረበው ውልን መሰረት በማድረግ ሳይሆን ንብረትን መብትን ለማስከበር በመፊለም ቅርጽ ሆኖ እያለ በቀረበው ክስ እና በተጠሪዎች ክርክር መሰረት ንብረቱ ላይ ባለመብት የሆነው ሰው ማን ነው የሚለውን መሰረት አድርገው መወሰን ሲገባቸው ባልተነሳና ከተጠየቀው ዲኝነት ውጭ በሆነ ጭብጥ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ/ም፣ የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ/ም እና የእስቴ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ 6 ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የእስቴ ወረዲ ፍርድ ቤት የዘጋውን መዝብ በማንቀሳቀስ አመልካች ባቀረቡት ዲኝነትና በተጠሪዎች ክርክር መሰረት ይዞታው/ንብረቱ የማን ነው የሚለውን ጭብጥ በመያዝ በማስረጃ አጣርቶ የመሰለውን እንዱወሰን ጉዲዩን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት መልሰናል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ት ዔ ዛ ዝ የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። የእስቴ ወረዲ ፍርድ ቤት በውሳኔው መሰረት እንዱፈጸም አዘናል። ይጻፍ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ/ም የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።