No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 05 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ አገልግልት ሶማላ ሪጅን - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- አቶ አህመድ እስማኤል የሱፍ - አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የይግባኝ ማስፈቀጃን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በሶማላ ክልል መንግስት የፊፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረው ፍርድ ቤቱ በ18/06/2012 ዓ.ም. ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለማቅረብ ጊዜ ያለፈበት መሆኑን ጠቅሶ ለማቅረብ እንዱፈቀድለት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ22/11/2012 ዓ.ም.
የተጻፈ አቤቱታ አቅርቦ የአመልካች የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ የይግባኝ ቅሬታውን እንዱያቀርብ ተፈቅድለታል። አመልካችም የይግባኝ መዝገብ አስከፍቶ የይግባኝ ክርክሩ ቀጥል እያለ ፍርድ ቤቱ ተጠሪ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ አልፎል በማለት ያቀረቡትን ተቃውሞ በመቀበል የአመልካች የይግባኝ ቅሬታ የይግባኝ ማቅረቢያ 60 ቀን ካለፈ በኋላ የቀረበ ነው በማለት የይግባኝ መዝገቡን ዘግቶታል።
አመልካች በ10/05/2013 ዓ.ም. የተጻፈ የሰበር ቅሬታ ያቀረበው የሱማላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታውን የማቅረቢያ ጊዜ ያለፈበት ነው በማለት መዝገቡን መዝጋቱን በመቃወም ለማሳረም ነው። የቅሬታው ይዘት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የይግባኝ ማስፈቀጃ አቅርቦ ይግባኙ እንዱከፈት ተፈቅድልኛል። የይግባኝ ፊይል ተከፍቶ ወደክርክር ከተገባ በኋላ ይግባኙ ሉከፈት ይገባል ያለው ፍርድ ቤት የይግባኝ ጊዜው አልፎል በማለት መዝገቡን መዝጋቱ በአንድ ጉዲይ ሁለት የተለያየ ውሳኔ በመስጠት መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸሙን ያመለክታል። የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ሉያልፍ የቻለውም የውሳኔ ግልባጭ ዘግይቶ ስለደረሰን ነው። የውሳኔ ግልባጭ በደረሰን በ8 ቀን ውስጥ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኙን አዘጋጅተን ቀርበናል። በመሆኑም በፍርድ ቤቱ ምክንያት የባከነው ጊዜ በይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ውስጥ ሉካተት ስለማይገባ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ትእዛዝ ይታረምልኝ በማለት ጠይቋል።
የሰበር አጣሪ ችልትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ አመልካች ያቀረበው የይግባኝ ማስፈቀጃ ተቀባይነት አግኝቶ ወደክርክር ከተገባ በኋላ የይግባኙን መዘጋት አግባብነት ከፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 326/1 አተገባበር አንጻር ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ አዟል።
ተጠሪም በ30/06/2013 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት መልስ አመልካች የይግባኝ ማስፈቀጃ አላቀረበም።
ፍርድ ቤቱም በቀረበው ማስፈቀጃ ላይ ተጠሪን አስተያየት እንድሰጥ አላደረገም። አመልካች በ10 ቀን ውስጥ ይግባኙን እንዱያቀርብ የተሰጠ ትእዛዝም የለም። አመልካች የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈበት በበቂ ምክንያት ከሆነም የሰበር ቅሬታ ከማቅረብ ይልቅ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ማስፈቀጃ ማቅረብ ነበረበት። በመሆኑም የአመልካች የሰበር ቅሬታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
አመልካችም በ13/07/2013 ዓ.ም. የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታውን አጠናክሯል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም መዝገቡን ለማስቀረብ በሰበር አጣሪ የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
እንደመረመረዉም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካች የይግባኝ አቤቱታ የቀረበዉ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜዉ ካለፈ በኋላ ነዉ በማለት ዉድቅ ማድረጉን ለመገንዘብ ተችሎል። በልላ በኩል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እራሱ የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ ቀርቦለት ይግባኙ እንዱከፈት የፈቀደ መሆኑን አመልካች ገልፆ ይከራከራል። ተጠሪ በበኩላቸው የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ አመልካች አለማቅረቡን እና አመልካች ይግባኙን እንዱያቀርብ ያልተፈቀደ መሆኑን በመግለጽ ክርክር አቅርበዋል። የሰበር አጣሪ ችልት አመልካች የይግባኝ ማስፈቀጃ አቅርቦ የተሰጠውን ትዕዛዝ ግልባጭ ከዚህ መዝገብ ጋር አያይዟል። ትዔዛዙን መርምረን እንደተረዲነዉ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ያለፈ መሆኑን ጠቅሶ የይግባኝ ማስፈቀጃ ያቀረበበት ምክንያት ተቀባይነት እንዲገኘ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 05-1- 161-12 በ01/12/2012 ዓ.ም. በዋለዉ ችልት ትእዛዝ በመስጠት አመልካች ይግባኙን እንዱያቀርብ ፈቅዶል። ይህን ካደረገ በኋላ እንደገና ተመልሶ ተጠሪ ይግባኙ ጊዜው ካለፈ በኋላ የቀረበ ነው የሚል መቃወሚያ ማንሳታቸውን ተከትል በ25/02/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የአመልካች የይግባኝ አቤቱታ የቀረበው የማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ነዉ በማለት አቤቱታዉን ዉድቅ ማድረጉንም ከትእዛዙ ለመገንዘብ ተችሎል።
በመሰረቱ ከፍትሐብሕር ጉዲዮች አመራር ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤቱ የሚሰጣቸዉ ትዔዛዞች እና ዉሳኔዎች የሚከለሱባቸዉ ሥርዓቶች በመሰረታዊነት ሁለት ሲሆኑ አንድም ፍርደን/ዉሳኔዉን/ትዔዛዙን በሰጠዉ ፍርድ ቤት በእራሱ (review by the court of rendition) ሲሆን ሁለተኛዉ በይግባኝ ሥርዓት ነዉ። ፍርድ ቤት እራሱ የሰጠዉን ፍርድ/ዉሳኔ/ትዕዛዝ እራሱ የሚከልስባቸዉ ሁኔታዎችም አንደኛ የዲግም ዲኝነት ጥያቄ ሲቀርብ (አንቀጽ 6)፣ ሁለተኛ የሥ/ሥርዓት ግድፈት የተፈጸመ ሲሆን (አንቀጽ 207-211) እና ሦስተኛ የመቃወም አቤቱታ ሲቀርብ (አንቀጽ 358) ስለመሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል። የፍትሐብሕር ክርክሮች በዘፈቀደ ሳይሆን በስርዓት መመራት እንዲለባቸዉም የሚታወቅ ነዉ። የትኛዉ ጉዲይ በማን፣ እንዳት እና መቼ መፈጸም (መከናወን) እንደሚገባዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ በተለያዩ አንቀፆች ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎችም ይህንኑ ያስገነዝባለ። ይህም ማለት ክርክሮች በሥርዓት እንጂ በዘፈቀደ ሉመሩ አይገባም በሚል ሃሳብ መነሻነት ፍርድ ቤቶች በፍትሐብሕር ጉዲዮች አመራር ረገድ የሚሰጧቸዉ ዉሳኔዎች/ትዔዛዞች ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያላቸዉን የሥ/ሥርዓት ህጉን ድንጋጌዎች እና መርሆዎችን መሰረት ያደረጉ ስለመሆኑ የማረጋገጥ ኃላፉነት እንዲለባቸዉም እሙን ነዉ።
በተያዘዉ ጉዲይ ላይ ከይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ጋር በተያያዘ የሚቀርበዉ ክርክር በባህሪዉ ፍርድ ቤት በእራሱ የእራሱን ዉሳኔ/ትዕዛዝ ሉከልስ ከሚችልባቸዉ ሁኔታዎች ዉስጥ የሚካተት አይደለም።
ስለሆነም የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ አላለፈበትም የሚል ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ እንደገና ይህንኑ ትዕዛዝ እራሱ በመከለስ የማቅረቢያ ጊዜዉ አላለፈም በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሉወስን የሚችልበት የህግ ምክንያት የለም። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተጠሪ አመልካች የይግባኝ ማስፈቀጃ ሲያቀርብ አስተያየት እንድሰጥ አልተደረገም በሚል ያቀረቡትን ክርክር ስንመለከት በእርግጥ አመልካች ይግባኝ እንዱያቀርቡ በተፈቀደበት ትእዛዝ ላይ ተጠሪ በአመልካች የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ ላይ አስተያየት እንዱሰጡ ስለመደረጉ አያሳይም። የይግባኝ ማስፈቀጃ ሲቀርብ ፍርድ ቤቱ የፈቃድ ጥያቄ ማመልከቻው ተቀባይነት ያገኛል ብል ሲያስብ መልስ ሰጪ ወይም ተጠሪ የሆነ ወገን አስተያየት እንዱሰጥ ማድረግ እንደሚገባው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 325/3 ላይ ተመልክቷል። በዚህ መልኩ ተጠሪ አስተያየት እንዱሰጡ አለመደረጉ የስነ ስርዓት ግድፈት የተፈጸመበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ስህተቱ ሉታረም የሚችለው ተጠሪ ደረጃውን ጠብቀው ይግባኝ በማቅረብ እንጂ በዚህ ደረጃ ስህተቱ የሚታረምበት የህግ አግባብ የላለ በመሆኑ ተጠሪ በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልነውም። በመሆኑም የሶማላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የክርክር አመራር ሥርዓት ግድፈት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ ሆኖ ስለተገኘ ተከታዩ ተወስኗል።
የሶማላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 05-1-161/12 በቀን 25/02/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተዘግቶ የነበረዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ ከዋናዉ ጉዲይ ጋር በተያያዘ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የመሰለዉን እንዱወስን መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 341(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት የተደረገው ክርከር ያስከተለውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.