አንድ ጉዲይ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ታይቶ ውሳኔ ያገኘ መሆኑ ከተረጋገጠ አዱስ የቀረበውን ክስ በድጋሚ አይቶ ውሳኔ መስጠት የሥነ ሥርዓት ሕግን አይነተኛ ዓላማ የማያሳካ እና በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ የተጣረሰ ውሳኔ ላሰጥ የሚችልበትን ዔድል የሚፈጥር በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ሕጉን በጥብቅ ሉተገብሩት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 ንዐስ ቁጥር (1)
No summary available.
ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አንሲፍ ኮንስትራክሽ - ጠበቃ ሁሴን ይመር - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጥላሁን አበበ - አልቀረቡም መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ተከሳሽ፤ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ ነበሩ። ተጠሪ የሥራ ውላቸው አላግባብ ተቋርጧል በማለት ክስ አቅርበው አመልካች መጥሪያ ደርሶት አልቀረበም በሚል በላለበት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለተጠሪ ክፍያዎችን እንዱከፍል ተወስኗል። አመልካች ሐምል 13 ቀን 2012 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ በ08/07/2012 ዓ/ም የተሰጠውን ውሳኔ ያወቅነው የአፈጻጸም መጥሪያ በደረሰን ጊዜ ነው። የተጠሪ ክስና መጥሪያ አልደረሰንም። ስለሆነም ውሳኔው ተነስቶ ክርክሩ አመልካች ባለበት እንደገና እንዱሰማ እንዱታዘዝልን በማለት በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት አቅርቧል። ተጠሪ ያቀረቡት መልስ አመልካች መጥሪያ ደርሶታል። መጥሪያውን አልቀበልም በማለቱ የቃለ መሃላ ማመልከቻ ማረጋገጫ ቀርቦ በላለበት ታይቷል። አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን ማመልከቻ መርምሮ አመልካች መልስ የማቅረብ መብቱ ታልፍ በላለበት ውሳኔ የተሰጠው የአመልካች ድርጅት የሰው ሀብት ክፍል ኃላፉ መጥሪያውን አልቀበልም ማለቱ በተጠሪ ምስክሮች ተረጋግጧል። መጥሪያ ለአመልካች የደረሰው ስለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ስለተገነዘበ በላለበት የተሰጠው ውሳኔ ሉነሳ አይገባም በማለት ወስኗል። አመልካች ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበውን ይግባኝ ባለመቀበል ሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም አመልካች የንግድ ድርጅት ሲሆን ተጠሪ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 97(ሀ) ለተመለከቱት ሰዎች መጥሪያው መድረሱን አላረጋገጡም። መጥሪያውን አልቀበለም ካለ ምትክ መጥሪያ ሉወጣ ይገባ ነበር። መዝገቡ ተዝግቶ ሲንቀሳቀስ ድጋሚ መጥሪያ ላሰጥ ሲገባ መዝገቡ ተንቀሳቅሶ ክርክሩ አመልካች በላለበት መቀጠለ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አይደለም የሚል ነው። የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ የአመልካች ጥያቄ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት መስተናገደ ተገቢነቱን ለመመርመር ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ አዟል። ተጠሪ የሰጡት መልስ የአመልካች አቤቱታ በላለበት የተሰጠው ውሳኔ ሉነሳ ይገባል የሚል ሲሆን ማስረጃ ተሰምቶ መጥሪያ መድረሱ ተረጋግጦ የተወሰነ ስለሆነ ውሳኔው ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለዋል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት የቀረበው ማመልከቻ ውድቅ መደረጉ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ ስለመሆን አለመሆኑ? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት ያቀረበው ማመልከቻ ውሳኔ መሰጠቱን ያወቅነው የአፈጻጸም መጥሪያ በደረሰን ጊዜ ነው። የተጠሪዎች ክስና መጥሪያ አልደረሰንም። ውሳኔው ተነስቶ ክርክሩ አመልካች ባለበት እንደገና እንዱሰማ እንዱታዘዝልን የሚል ነው። ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፉነት ሲሆን በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ዓላማዎች የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰለትን ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን መብት ይነካል። የሕግ ሥርዓት ሂደት ሙግት ከፍርድ ሉቀድም ይገባል የሚለውን መርህ የሚከተል ሲሆን በፍትሐ ብሓር ሆነ በወንጀል ክርክር ሂደቶች ያለ መብት ነው። ከተከሳሽ አኳያ በነፃና ገለልተኛ የዲኝነት አካል የመዲኘት፣ ክሱን የማወቅ መብት፣ የመደመጥ መብት (መከላከያ ክርክር ማቅረብ፣ የከሳሽን ማስረጃ የማወቅና በማስረጃው ላይ ክርክር ማቅረብና ምስክሮችን የመጠየቅ መብት እና የራሱን ማስረጃ የማቅረብ መብትን ያካትታል።)፣ የሚሰጠው ውሳኔ በሕግና በምክንያት ላይ የተመሰረተ ብቻ እንዱሆን እና ላልች ተያያዥ መብቶችን ያካተተ ሰፉ መብት ነው። በፍትሐ ብሓር ክርክር ተከሳሽ በከሳሽ የቀረበበትን ክስ እንዱያውቅ ማድረግ መሰረታዊ ሂደት ነው። ክሱን ከማወቅ ባሻገር የመደመጥ መብቱን ማክበር ሂደቱን ሙለ ያደርገዋል።
መልስ የማቅረብ መብት በሥነ-ስርዓታዊ የሕግ ሥርዓት ሂደት ውስጥ ያለ መብት በመሆኑ የሥነስርዓታዊ የሕግ ሥርዓት ሂደት የያዛቸውን ዝርዝር ፍሬ ነገሮች መመልከቱ ተገቢ ነው። ሥነ-ስርዓታዊ የሕግ ሥርዓት ሂደት የራሱ ክፍልች አለት። በመጀመሪያ በልዩ ሁኔታ ተከሳሽ ጉዲዩ በላለበት ቢታይም በመርህ ደረጃ ተከሳሹ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ የመሳተፍ መብት አለው የሚለው ነው።
ክሱን እንዱያውቀው መደረግ አለበት። የቅድሚያ ማወቅ መብት ለተከሳሹ ጉዲዩ መድረሱን በሚገባ ማረጋገጥና ለተከሳሹ የደረሰውም ለመከላከል በሚያስችል መልኩ የክሱና የሁኔታው ዝርዝር ነገር ስለመሆኑ የሚያካትት ነው። ተከሳሹ ክስ እንደቀረበበት ካላወቀ በፍርድ አሰጣጡ ሂደት ሉሳተፍ አይችልም፤ የመደመጥ መብት ካልተከበረ፤ ተከሳሹ ክርክሩንና ማስረጃውን እንዲያቀርብ ያደርገዋል እንዱሁም የዲኝነት አካለ ክርክሩን ከግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ካላደመጠ ደግሞ ለእውነቱ የቀረበና ውጤታማ ፍርድ መስጠት አይችልም። ፍርድ ቤቶች የተከሳሽን መልስ የማቅረብ መብት ከማለፊቸው በፉት ተገቢውን ጥንቃቄ እንዱያደርጉ ሕጉ ኃላፉነት ጥልባቸዋል። መልስ የማቅረብ መብቱ ታልፍ ጉዲዩ በላለበት የተወሰነ ተከራካሪ መብቱን የሚያስከብርበት ሥርዓት መቀረጹም የመደመጥ መብቱ አካል ነው።
ፍርድ ቤቶች መጥሪያ ሲልኩ ተከሳሽ የሆነው ወገን የተፈጥሮ ሰው ወይም የንግድ ድርጅት መሆን አለመሆኑን በመለየት በሥነ-ሥርዓት ሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት አግባብ መጥሪያው ወጪ መሆኑንና መድረሱን በማረጋገጥ የመደመጥ መብት መከበሩን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፉነት አለባቸው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች በንግድ ሕጉ መሰረት የተመዘገበ የንግድ ማሕበር/ድርጅት አይደለም፤
አመልካች ነጋዳ ቢሆንም የንግድ ድርጅት ባለመሆኑ ከመነሻውም ክሱ በንግድ ሥሙ ቀርቦ ክርክሩ መመራቱ ተገቢ አይደለም። የንግድ ድርጅት ባለመሆኑ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 97 የተመለከተውን የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት ሉከተል አይችልም። ነጋዳ ሥራውን ሉሰራለት የሚችል ሰራተኛ መቅጠር የሚችል ቢሆንም ሰራተኛው ነጋዳውን ወክል መጥሪያ ለመቀበል ሥልጣን ያለው መሆኑ እስካልተረጋጠ ድረስ የሥነ-ሥርዓት ሕጉ ዓላማ የሆኑትን አንጻራዊ እውነት የመፈለግና ፍትሐዊነትን በሚያሳካ መልኩ የመደመጥ መብትን በተሟላ አግባብ በሚያስከብር ሁኔታ ለሕጉ ውጤት ሉሰጠው ስለሚገባ መጥሪያው ሉደርስ የሚገባው በአካል የተፈጥሮ ሰው ለሆነው ለነጋዳው ነው። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ መጥሪያውን ለመስጠት የሞከሩት ለአመልካች ሰራተኛ ሲሆን ሰራተኛው የሰው ኃይል ክፍል ኃላፉ ቢሆንም መጥሪያ ለመቀበል ውክልና እስከላላቸው ድረስ መጥሪያውን አልቀበልም ማለታቸው ሕጋዊ ተግባር ነው። ስለሆነም የአመልካች ሰራተኛ መጥሪያውን አልቀበልም ብለዋል በሚል አመልካች ክርክሩ በላለበት መታየቱ ሆነ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት ያቀረበው ማመልከቻ ውደቅ መደረጉ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋውን የመደመጥ መብት ያላከበረና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ/ም እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሕዲር 22 ቀን 2013 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 08 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ተነስቷል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ላቀረቡት ክስ አመልካች የጽሁፍ መልስ እንዱያቀርብ በማድረግ ክርክሩን በሕግ መሰረት በመምራት እንዱወስን ጉዲዩን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341(1) መሰረት መልሰናል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በውሳኔው መሰረት እንዱፈጽም አዘናል። ይጻፍ አፈጻጸሙ ላይ የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.