በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.182(2) እንደተመለከተው ክርክር የሚወሰነው በተጠየቀው ዲኝነት አግባብ ሲሆን ፍርድ ቤትም ከቀረበው ዲኝነት አኳያ ከግራ ቀኙ ክርክር በመነሳት በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 246 እና ተከታዮቹ መሰረት በተነሱት ጉዲዮች ጭብጥ መስርቶ ውሳኔ የመስጠት ኃላፉነት ያለበት አቶ ይስማው ድረስ እና እነ አቶ ባህሩ ዓለሙ (2 ሰዎች)
No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡- አቶ ደጋረገ ሙለ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዉብናት ላቀ - የቀረበ የለም ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል በሜጫ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተጠሪ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር አመልካች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር።
ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.74190 ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የአሁን ተጠሪ በሥር በወረዲዉ ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከአሁን አመልካች ጋር ያለን ጋብቻ እንዱፈርስ፣ በጋራ ያፈራናቸዉ ንብረቶች እንድንካፈል በማለት ዘርዝራ በማቅረብ እንዱወሰንላት ዲኝነት ጠይቃለች።
የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ባቀረቡት መልስ ተጠሪዋ ባቀረበችዉ የንብረት ጥያቄ ላይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ክርክር ያቀረበ ሲሆን፤ በራሱ በኩል ባቀረበዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ከተጠሪ ጋር ልንካፈል ይገባል የሚላቸዉን ንብረቶች በመዘርዘር በመጠየቅ፤ የሰራተኛ እዲ አራት ኩንታል በቆል አንድ ኩንታል ዲጉሳ፣ አንድ ኩንታል ጓያ አለብን ልንከፍል ይገባል በማለት ጠይቋል።
የአሁን ተጠሪ በዚህ በተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ መልስ ያቀረበች ሲሆን፣ የሰራተኛ የጋራ እዲ አለብን በማለት የቀረበዉም ሐሰት ነዉ፣ ይህ ተቀጠረ የተባለዉ ልጅ የአሁን አመልካች የግል ልጅ ነዉ የእኔም ሶስት ልጆች የግል ነበረኝ፤ የግል ከብቶች ነበራቸዉ፤ እነዚህ ልጆች አብረዉ ከእኛ ጋር ያደጉ ሲሆን ለሰሩበት ልንከፍላቸዉ አልተስማማንም አልቀጠርናቸዉም፣ የአሁን አመልካች ልጅ እንደ ልጅ ከቤት ነበረ እንጂ የተቀጠረ አይደለም።
ከዚህ በኋላ የወረዲዉ ፍ/ቤት የሰዉ ምስክሮች በመስማት በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን አመልካች በተከሳሽ ከሳሽነት የጋራ ዕዲ በማለት ያቀረበዉ የሰራተኛ እዲ 6 [ስድስት] ማዲበሪያ እህል በጋራ ሉከፍለ ይገባል፤ የባልና ሚስት ንብረቶች ላይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ሰጥቷል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለባህር ዲርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበችዉ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የባልና ሚሰት ንብረት በተመለከተ በተወሰኑ ንብረቶች ላይ የሥር ፍ/ቤት ጉዲዩን ድጋሚ አጣርቶ እንዱወስን የመለሰ ሲሆን፣ የሰራተኛ ዕዲ የተባለዉን የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን ተጠሪ አሁንም በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝታ የሰበር አቤቱታ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበች ሲሆን ችልቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ ለአራሽ ሰራተኛ አበል የተባለዉን 6 [ስድስት] ማዲበሪያ እህልን በተመለከተ የእርሻ ሥራ ሰራሁ የሚለዉ ግርማዉ ደጋረገ የተባለዉ ሰዉ ቀርቦ ሳይጠየቅ የአሁን አመልካች መብት የለዉም እና ስለ ግርማዉ ደጋረጋ ዉክልና ባልያዘበት ሁኔታ የአሁን ተጠሪ ለአራሽ አበል ከሆነዉ 6 [ስድስት] ማደበሪያ እህል ዉስጥ እዲ በመሆን ድርሻዋን ትክፈል በማለት በዚህ ረገድ የሥር ፍ/ቤቶችን ዉሳኔ በመሻር የአሁን ተጠሪ ይህን ዕዲ ልትከፍል አይገባም፣ የጋራ ንብረቶችን በተመለከተ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ በመስጠት የሥር ፍ/ቤቶችን ዉሳኔ በማሻሻል ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ6/10/2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የሥር ፍ/ቤት የሰራተኛ ደመወዝ 6 ማዲባሪያ ሰብል እዲ ያለብን ስለመሆኑ በግራ ቀኝ ምስክሮቻችን ተጣርቶና ተረጋገጦ እያለ ተጠሪም ይህን አምናበት የሰራተኛ ደመወዝ ሰብለን የከፈለች ሆኖ እያለ የሥር ፍ/ቤቱ ግን የሰራተኛ ደመወዝን እዲ ያለብንን ባለገንዘቡ ከሶ ይጠይቅ በማለት ለላላ ወጭ በሚዲርግ መልኩ በምስክሮቻችን የተረጋገጠዉን እዲ ዉድቅ ማድረጉ የህግ ስህተት ስለሆነ እንዱሻርልኝ በማለት በላልች ጉዲዮችም ላይ ቅሬታዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣የሥር የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ ለእርሻ ሰራተኛ የተከፈለ እዲን በድርሻዋ ለአመልካች ልከፍላት አይገባም በማለት የመወሰኑን አግባብነት፣ ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንድትሰጥ ባዘዘዉ መሰረት በ6/2/2012 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ የአማራ ክልል ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችልት በዚህ ጉዲይ የአሁን ተጠሪ የሰራተኛ ደመወዝ የተባለዉን በድርሻዋ ለአሁን አመልካች መክፈል አይገባም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢና ሕጋዊ ስለሆነ እንዱጸናልኝ በማለት በዝርዝር ክርክሯን አቅርባለች። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልሰ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙ ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ የአሁን አመልካች የእርሻ ሥራን ለሰራልን ለአቶ ግርማዉ ደጋረጋ ሉከፈል የሚገባዉን ደመወዝ የአሁን ተጠሪ ድርሻዋን ልትከፍል ይገባል በማለት ዲኝነት ለመጠየቅ መብትና ጥቅም አለዉ ወይስ የለዉም? የሚለዉ ነጥብ መታያት ያለበት ጉዲይ መሆኑን ተገንዝበናል። እንግዱህ አቶ ግርማዉ ደጋረጋ የአሁን አመልካች ልጅ መሆኑን ከግራ ቀኙ እና ከሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ መገንዘብ ይቻላል። አቶ ግርማዉ ደጋረጋ በግራ ቀኙ ተቀጥረዉ የእርሻ ሥራ የሰራላቸዉ ከሆነ እና ሉከፍለት የሚገባዉ የሥራ ዋጋ ወይም ደመወዝ ካለና መብት አለኝ የሚል ከሆነ አግባብነት ባለዉ የህግ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ፣በሕግ አግባብ ስልጣን ባለዉ ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ከመጠየቅ የሚከለክላቸዉ ነገር አልነበረም። የአሁን አመልካች ግን ይህን ግለሰብ ወክለዉ በዚህ ጉዲይ ዲኝነት የመጠየቅና እንዱወሰንልኝ ብል ለመጠየቅ በሕግ አግባብ የዉክልና ስልጣን የተሰጣቸዉ ወይም ከሕግ የመነጫ መብት ያላቸዉ መሆኑን የሚያሳይ ነገር የለም። ይህ ከሆነ ደግሞ አንድ ከሳሽ ለክስ ምክንያት በሆነዉ ነገር ወይም ክሱ በተመሰረተበት ነገር ሀብት ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለዉ መሆኑን ካላረጋገጠ ክስ አቅርቦ ዲኝነት ለመጠየቅ እንደማይፈቀድለት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.33 [2] ሥር ተመለክቷል። በዚህ አግባብ የተያዘዉ ጉዲይ ሲታይ የአሁን አመልካች አቶ ግርማዉ ደጋረጋ የእርሻ ሥራ ስለሰራልን በዚህ ምክንያት ልንከፍለዉ የሚገባዉን ደመወዝ የአሁን ተጠሪ ድርሻዋን እንድትከፍል በማለት ስለ ግርማዉ ደጋረጋ ክስ አቅርቦ ዲኝነት ጠይቆ እንዱወሰንለት የሚጠይቅበት የሕግ አግባብ የለም። ስለሆነም የአሁን አመልካች ለሰራተኛ የሚከፍል እዲ ቢኖር እንኳን የአሁን ተጠሪ ድርሻዋን ለገንዘብ ጠያቅዉ እንጂ ለአመልካች የምትከፍልበት አግባብ የለም፣ የሥር የወረዲዉ ፍ/ቤት እና የሥር የከፍተኛዉ ፍ/ቤት አመልካች በዚህ ጉዲይ መብትና ጥቅም የለዉም ብል የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ዉድቅ ማድረግ ሲገባቸዉ የሰጡት ዉሳኔ፣ የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመሻር የአሁን አመልካች ስለ ግርማዉ ደጋረጋ ዲኝነት እንዱወሰንለት ለመጠየቅ መብትና ጥቅም የለዉም በማለት በማረም የሰጠዉ ዉሳኔ በሕጉ አግባብ ነዉ ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአሁን አመልካች በእርሻ ሥራ ተቀጥሮ አገልግሎል በማለት የጠቀሰዉን አቶ ግርማዉ ደጋረጋ መብት በተመለከተ ይህ ግለሰብ ራሱ ሳይጠይቅ ስድስት ማዲበሪያ እህል እዲ አለብን ከዚህ ዉስጥ ተጠሪ ድርሻዋን ለአመልካች ልትከፍል አይገባም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ በሕግ አግባብ የተሰጠ እና መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.74190 ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 [1] መሰረት በአብላጫ ድምጽ ጸንቷል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ችልት በ27/12/2011 ዓ.ም የሰጠዉ የአፈጻጸም የእግድ ትዕዛዝ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል።
ይጻፍ።
No topics extracted.