ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት የሚረዲ ተጨማሪ ማስረጃ ማያያዝ የሚችል መሆኑ በተደነገገው መሰረት ፍርድ ቤት በዚህ ድንጋጌ ማዔቀፍ ማስረጃ መቀበለ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ጥሰት ተፈጽሟል የማያስብል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 345(1)(ለ) እና 327(3)
No summary available.
ቀን፡- 30/02/2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ሕዲሴ ቴላኮም አ/ማ ተጠሪ፡-
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች የስር ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ተከሳሾች ሆነው ተከራክረዋል። አመልካች ያቀረበው ክስ 1ኛ ተጠሪ የአመልካች የሽያጭ ሰራተኛ ሆነው ሲሰሩ በውስጥ ኦዱት በሚደረግበት ጊዜ ብር 204,250.00 በጉድለት ስለተገኘ ገንዘቡን እንዱከፍለ፤ 2ኛ ተጠሪም የ1ኛ ተጠሪ ዋስና ተያዥ በመሆናቸው እስከ 100,000.00 በአንድነትና ነጠላ ኃላፉነት እንዱከፍለ የሚል ነው። 1ኛ ተጠሪ የሰጡት መልስ ገቢና ወጪውን ያልለየ፣ ከመቼ እስከመቼ የተደረገ ኦዱት ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም።
በውጭ ኦዱተር ኦዱት ይደረግልኝ ብለዋል። 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ጉድለት የለም፣ ዋስ የሆንኩት 1ኛ ተጠሪ የመስመር ሰራተኛ እያለ ነው፤ ልጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግራ ቀኙን አከራክሮና በተፈቀደለት የሂሳብ ባለሙያ ድጋሚ ኦዱቱ እንዱሰራ በማድረግ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ 1ኛ ተጠሪ እንዱከፍለና 2ኛ ተጠሪ እስከ ብር 100,000.00 ድረስ በአንድነት እንዱከፍለ ወስኗል። ተጠሪዎች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡትን ይግባኝ ተቀብል በድጋሚ ኦዱቱ እንዱሰራ ካዘዘ በኋላ 1ኛ ተጠሪ ብር 204,250.00 ገንዘብ ማጉደላቸውን የቀረበው ማስረጃ ያሳያል። ነገር ግን ይህንኑ ገንዘብ 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት GSM Mobile Prepaid Card certificate ገቢ ስለመሆኑ ማስረጃ ያቀረቡ ቢሆንም በትክክል ገንዘቡ ገቢ ስለመሆኑ የሚረጋገጠው ቅጽ 7 (ውስጣዊ ደረሰኝ) ያላቀረቡ መሆኑን በመግለጽ ኦዱት የሰራው ተቋም ገልጿል። 1ኛ ተጠሪ ገንዘቡ ገቢ ስለመሆኑ ቅጽ 7 ደረሰኝ ከአመልካች ተቋም ማግኘታቸውን በመግለጽ በተጨማሪ ማስረጃነት እንዱያያዝላቸው የጠየቁ ሲሆን አመልካች አዱስ ማስረጃ ሉያያዝ አይገባም፤ ይያያዝ ቢባል እንኳን የሽያጭ ገንዘቡ ወደባንክ ገቢ ከሆነው ስሉፔ ጋር ያልቀረበ በመሆኑ ፍርድ ቤቱን ለማሳሳት የቀረበ ነው ሲል አስተያየቱን አቅርቧል። የቀረበው ማስረጃ የአመልካች ማሕተም ያረፈበት፣ የአመልካች ሰነድ አለመሆኑ ያልተካደ በመሆኑና ማስረጃው ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት የሚያግዝ በመሆኑ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 345 መሰረት ፍርድ ቤቱ ተቀብል በማያያዝ በጉድለት ተገኘ የተባለው ብር 204,250.00 ለአመልካች በቅጽ 7 (የውስጥ ደረሰኝ) ገቢ የተደረገ ስለመሆኑ ስለተረጋገጠ 1ኛ ተጠሪ ያጎደለት ገንዘብ የለም በማለት የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር ክሱን ውድቅ አድርጓል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአመልካችን የይግባኝ አቤቱታ ባለመቀበል ሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የገንዘብ ጉድለቱ በኦዱት ምርመራ ተረጋግጧል። ከሥነ-ሥርዓት ውጭ አዱስ ማስረጃ መቀበለ ተገቢ አይደለም።
ማስረጃው የገቢ ሰነድ ማስረጃ አይደለም። የውስጥ ደረሰኝ አይደለም፤ ቢሆን እንኳን ከባንክ ስሉፔ ጋር ያልቀረበ ስለሆነ ውጤት ሉኖረው አይችልም የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ ማስረጃው የተያያዘበት አግባብነትና ማስረጃው ገንዘብ ገቢ ማድረጋቸውን የሚያሳይ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርብ በማዘዙ ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ የቅጽ 7 ሰነድ ከሥራ ተሰናብቼ ስለነበር ማግኘት ባለመቻላ ያልቀረበ ሲሆን በኋላ ግን 1ኛ ተጠሪ የአመልካች ኃላፉን አስፈቅድ ሰነድችን ፈትሾ ያገኘው ነው። ሰነደ የገቢ ደረሰኝ ሲሆን የገቢ ደረሰኝ አለመሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ያልተካደ ነው። ማስረጃው ተመዝኖ የተሰጠው ውሳኔ ሉፀና ይገባል ብለዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የክርክር አመራር ተገቢ መሆን አለመሆኑን እና የማስረጃ ምዘና መርህን መሰረት አድርጎ መወሰን አለመወሰኑን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች ያቀረበው ክስ 1ኛ ተጠሪ የአመልካች የሽያጭ ሰራተኛ ሆነው ሲሰሩ በውስጥ ኦዱት በሚደረግበት ጊዜ ብር 204,250.00 በጉድለት ስለተገኘ ገንዘቡን እንዱከፍለ፤ 2ኛ ተጠሪም የ1ኛ ተጠሪ ዋስና ተያዥ በመሆናቸው እስከ 100,000.00 በአንድነትና ነጠላ ኃላፉነት እንዱከፍለ የሚል ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸው ገንዘቡ አልጎደለም፤ የኦዱት አሰራሩ ተገቢነት የለውም፣ ድጋሚ ኦዱት ይደረግልን ለክሱ ልንጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል። ፍርድ ቤት የቀረበለትን የፍትሐ ብሓር ክርክር ጉዲዩን ለማስረዲት በሕግ ተቀባይነት ባለውና ለጉዲዩ አግባብነት ባለው ማስረጃ በማረጋገጥ ማን የተሻለ እንዲስረዲ የመወሰን ኃላፉነት አለበት። ክርክርን ለማስረዲት ማስረጃ የሚቀርብበት ሥርዓት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 223 መሰረት የሰው ማስረጃ ዝርዝር እና በዔጁ የሚገኝ የፅሁፍ ማስረጃን የሚቀርብበት ሲሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 145 መሰረት ደግሞ በተከራካሪ ዔጅ የላለ ወይም ለማቅረብ ከፍተኛ ወጭ የሚጠይቁ ማስረጃዎች በፍርድ ቤት እገዛ የሚቀርቡበት ነው።
የሰነድ ማስረጃ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 137 መሰረት ክሱ እስከሚሰማበት ጊዜ ድረስ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን በእነዚህ ሂደቶች ማስረጃው ያልቀረበው ተከራካሪው ባለማወቁ ወይም አዱስ የተገኘ ማስረጃ ከሆነ ደግሞ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 256 አግባብ ማስረጃው እንዱቀርብ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ላቀርብ ይችላል።
በዚህ አግባብ ማስረጃ እንዱቀርብ የሚጠየቀው ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት ላሆን ይገባል። ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በይግባኝ ደረጃ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 327(3) እና 345 መሰረት በልዩ ሁኔታ ማስረጃ የሚስተናገድበት ሥርዓትም ተዘርግቷል።
ተጠሪ ክሱን ለማስረዲት የኦዱት ውጤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤት የማስረጃውን ትክክለኛነት ማጣራት ከፈለገ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 264 በተሰጠው ስልጣንና ኃላፉነት ድጋሚ ኦዱት እንዱሰራ በማዘዝ ክርክሩን መወሰን ይችላል። በዚህም አግባብ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የኦዱት ሥራው በድጋሚ እንዱከናወን አዟል። የቀረበው የኦዱት ውጤት 1ኛ ተጠሪ የገንዘብ ጉድለት ያለባቸው መሆኑን ያሳያል። ነገር ግን ይህንኑ ገንዘብ 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት GSM Mobile Prepaid Card certificate ገቢ ስለመሆኑ ማስረጃ ያቀረቡ ቢሆንም በትክክል ገንዘቡ ገቢ ስለመሆኑ የሚረጋገጠው ቅጽ 7 (ውስጣዊ ደረሰኝ) ያላቀረቡ መሆኑን ኦዱት የሰራው ተቋም መግለጹ ተከትል 1ኛ ተጠሪ ገንዘቡ ገቢ ስለመሆኑ ቅጽ 7 ደረሰኝ ከአመልካች ተቋም ማግኘታቸውን በመጥቀስ በተጨማሪ ማስረጃነት እንዱያያዝላቸው የጠየቁ ሲሆን ፍርድ ቤቱ አመልካች ክርክር እንዱያቀርብበት ካደረገ በኋላ የቀረበው ማስረጃ የአመልካች ማሕተም ያረፈበት፣ የአመልካች ሰነድ አለመሆኑ ያልተካደ በመሆኑና ማስረጃው ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት የሚያግዝ በመሆኑ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 345 መሰረት ተቀብል በማያያዝ በጉድለት ተገኘ የተባለው ብር 204,250.00 ለአመልካች በቅጽ 7 (የውስጥ ደረሰኝ) ገቢ የተደረገ ስለመሆኑ ስለተረጋገጠ 1ኛ ተጠሪ ያጎደለት ገንዘብ የለም ሲል ድምዲሜ ላይ ደርሷል። የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 345(1)(ለ) እና 327(3) ላይ ይግባኝ ሰሚ ፍር ቤት ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት የሚረዲ ተጨማሪ ማስረጃ ማያያዝ የሚችል ስለመሆኑ የተመለከተ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤትም በዚህ ድንጋጌ ማዔቀፍ ማስረጃውን በመቀበለ የፈጸመው የሥነ-ሥርዓት ሕግ ጥሰት የለም ብለናል።
ለቀረበው ክስ የግራ ቀኙን ማስረጃ ፍርድ ቤቱ ከተቀበለ በኋላ በፍትሐ ብሓር ክርክር የምንከተለው የማስረዲት ደረጃ ከሁለቱ ወገን የተሻለ ያስረዲው ማን ነው (preponderance of evidence) የሚለውን በመመርመር እና የማስረጃ ተገቢነት፣ የማስረጃው ተቀባይነትን ደንቦችን መከተል እና ለማስረጃው የሚሰጠውን ክብደት (weight of evidence) በመለየት የመወሰን ኃላፉነት ማስረጃ ለመስማትና ለመመዘን ኃላፉነት ያለባቸው ፍርድ ቤቶች ዋና ተግባር ነው። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 80(3) በመጨረሻ ውሳኔ ላይ በተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ ማስረጃው ተመዝኖ የተደረሰበትን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ላይ እንዱመለከት ሥልጣን አልተሰጠውም። የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራቀኙ ያቀረቡትን ማስረጃ መዝኖ 1ኛ ተጠሪ ገንዘብ ስለማጉደላቸው አልተረጋገጠም በሚል የደረሰበት የፍሬ ነገር ድምዲሜና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የጸናው ውሳኔ ላይ የተፈጸመ የማስረጃ ምዘና መርሕ ስህተት ያልተገኘበት ስለሆነ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ/ም እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 14 ቀን 2012 የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.