No summary available.
የሰበር መዛገብ የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ወ/ሮ እቴነሽ መለሰ-መከተ አዖናው ተወካይ- ቀርቧል ተጠሪ፡- ማራናታ የቤት ህብረት ሥራ ማህበር-አልቀረቡም ለምርመራ ተቀጥሮ የነበረው መዛገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የሰሜን ሸዋ መስተዲድር ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ህዲር 25 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት ተጠሪ አመልካችን ከማኀበሩ ማሰናበቱ አግባብ ነው በማለት የሰጠውን ውሳኔ የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረ ብርሀን ምድብ በመዛገብ 2 ጥር 28 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት ማጽናቱ እንዱሁም ሰበር አጣሪ ችልት መጋቢት 8 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰበር መዛገብ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ሰህተት አልተገኘበትም በማለት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ወድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት በሰበር ለማሳረም አመልካች ሰኔ 7 ቀን 2013 ዓ/ም የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ መዛገቡ ለችልት ቀርቧል፡፤
ጉዲዩ አመልካችን ከተጠሪ ማህበር አባልነት በማሰናበት የተሰጠ ውሳኔ እንዱሰረዛ ለሸዋሮቢት ከተማ አስተዲደር ወረዲ ፍርድ ቤት የቀረበ ክስ ሆኖ አመልካች በከሰሻነት ተጠሪ ደግሞ በ1ኛ ተከሳሽነት ተከራክረዋል። የክስ አቤቱታው ይዖትም፡- አመልካች ተወልደው ለ17 ዓመታት በመምህርነት ባገለገለበት ሸዋሮቢት ከተማ የቤት መስሪያ ቦታ ስላልነበራቸው በመምህርነታቸው በተጠሪ ማህበር ተደራጅተው ለአምስት ዓመት የቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ እያለ ባለቤታቸው የፍደራል ፖሉስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ባልደረባ በመሆናቸው ከጥቀምት ወር 2012 ዓ/ም ከትዲር አጋራቸው ወደለበት አዱስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ዛውውር ተደርጎላቸው ፤ በከተማው በማስተማር ላይ ቢሆኑም ዋና መኖሪያቸው ሸዋሮቢት ከተማ ሆኖ እያለ ፣ የአማራ ክልል ባወጣው ደንብ ቁጥር 150/2000 እና መመሪያ ቁጥር 28/2009 አንድ መምህር ሲያስተምርበት ከነበረው ከተማ ወደ ላላ ከተማ ሲዙወር ከማኀበር እንደሚሰናበት ባልተደነገገበት ሁኔታ እንዱሁም የሥር 2ኛ ተከሳሽ አመልካችን ከማኀበር አባልነት ለማሰናበት ስልጣን ሳይኖረው አመልካች ወደ አዱስ አበባ ከተማ ስለተዙወሩ ተጠሪን ከማህበሩ እንዱያሰናብት የፃፈለትን ደብዲቤ መሰረት አድርጎ ተጠሪ አመልካችን ከማህበሩ ማሰናበቱን የገለፀላት መሆኑን በመግለፅ ፤ መደበኛ ነዋሪነቷ ሸዋሮቢት ሆኖ እያለ እና በአዱስ አበባ ከተማ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ እንዲልሆነች በማስረጃ ተረጋግጦ ባለበት ተጠሪ አመልካች ከማህበር እንድትሰናበት መወሰኑ አላግባብ ስለሆነ ውሳኔው ተሰርዜ አመልካች ወደ ማኀበሩ እንድትመለስ እንዱወሰን ጠይቀዋል።
ተጠሪም በመልሱ፡- አመልካች የማኀበሩን የስራ ክልል ለቃ ስለሄደች በማኀበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 14(4) መሰረት ከማኀበሩ እንድትሰናበት የሥር 2ኛ ተከሳሽ እንዲሳወቃቸው ለአመልካች በማሳወቅ ፤ ከ23 የማኀበሩ አባላት አራቱ ብቻ ባልተገኙበት ምልዐተ ጉባዓ ተሟልቶ አመልካች ከማኀበሩ እንድትሰናበት የተላለፈ ውሳኔ በመሆኑ አመልካች ያቀረቡት ክስ ውድቅ ሆኖ ተጠሪ ከማኀበሩ እንድትሰናበት ያስተላለፈው ውሳኔ ተቀባይነት አግኝቶ እንዱፀና ጠይቀዋል። የሥር 2ኛ ተከሳሽም አመልካችን ከማኀበር ስላላሰናበተ የቀረበበት ክስ ተገቢነት የለውም በማለት ተቃውሞ በፍሬ ነገሩ ላይም መልስ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱም በሥር 2ኛ ተከሳሽ የተነሳውን መቃወሚያ በመቀበል ከክርክሩ አሰናብቶ በፍሬ ነገሩ ላይ ግራቀኙን አከራክሮ እና የአመልካችን ምስክሮች ሰምቶ በሰጠው ውሳኔ ፤ አባላት ከማኀበሩ የሚሰናበቱበት ምከንያት በአዋጁ የተሸፈነ ሲሆን በማኀበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 14(4) ሥር የተቀመጠው አንድ አባል የማኀበሩን የሥራ ክልል ለቆ ከሄደ ከማኀበሩ ይሰናበታል በማለት የሚደነግግ ቢሆንም በአዋጁ ቁጥር 64(2) ሥር ማንኛውም ከአዋጁ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ሕግ ፣ ደንብ ፣ መመሪያ እና የተለምድ አሰራር በአዋጁ ውስጥ በተመለከቱት ጉዲዮች ላይ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው የደነገገ በመሆኑ የማኀበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 14(4) ሥር የተመለከተው አዋጁን የሚቃረን በመሆኑ ተፈፃሚነት ሉኖረው የማይገባ ሲሆን ፤ መተዲደርሪያ ደንቡ አዋጁን አይቃረንም ቢባል እንኳን አመልካች የምትተዲደርበት ንብረቷ ፣ መኖሪያዋ እና ማህበራዊ ህይወቷ ያለው ሸዋሮቢት ከተማ መሆኑ በዛውውር ምክንያት የሥራ ቦታዋ አዱስ አበባ ቢሆንም እየተመላለሰች የምትሰራ መሆኑ በማስረጃ ስለተረጋገጠ እንዱሁም አመልካች ከማኀበሩ እንድትሰናበት የተያዖው ቃለጉባኤ አባላት ሳይሰባሰቡ በአንድ ሰው ብቻ ቀደም ብል የተዖጋጀ በጉዲዩ ላይ አባላት የሰጡትን ሃሳብ ያላካተተ በመሆኑ አመልካች ከማኀበሩ መሰናበቷ አግባብ አይደለም በማለት ወስኗል።
ጉዲዩን ተጠሪ ባቀረቡት ይግባኝ የተመለከተው የሰሜን ሸዋ ዜን መስተዲድር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመምህራን መኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ አሰጣጥና የተገነቡ ቤቶች ድልድል ማስፈፀሚያ ደንብ ቁጥር 150/2009 ተፈፃሚነት ወሰኑ በክልለ በመንግስት ትምህርት ቤቶች በማስተማር ሥራ ላይ ተሰማርተው ለሚገኙ መምህራን ብቻ ሆኖ የደንቡ መሰረታዊ ዓላማም በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ መምህራን ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የመምህራን ፍልሰት በመቀነስ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ መሆኑን መረዲት የሚቻል ሲሆን ፤ አመልካች አዱስ አበባ ከተማ ተዙውራ የምትሰራ መሆኑ በሯሷ ምስክሮች ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑ ፤
በአማራ ክልል ውስጥ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ መምህራን በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው የሕግ ማዔቀፍ መሰረት ለመጠቀም የምታቀርበው ክርክር ተገቢነት የላለው ሆኖ ፤ ተጠሪ አመልካችን ከማኀበሩ ያሰናበተበት አግባብ የማኀበሩን ሕገ ደንብ እና ላልች ሕጎችን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር ስንብቱ ሕገ ወጥ ልባል የሚችል አይደለም በማለት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሻረ ሲሆን ፤ ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም አመልካች በመምህርነቷ ከሸዋሮቢት ወደ አዱስ አበባ ከተማ ዛውውር የተደረገላት መሆኑ የታመነ ፍሬ ነገር በመሆኑ መምህርነት የሙለ ጊዚ ሥራ በመሆኑ ፤
ምንም እንኳን የአመልካች ምስክሮች ሸዋሮቢት ከተማ ለቃ እንዲልሄደች እና እንደምትመላለስ የገለፁ ቢሆንም ፤ ከቦታ ርቀት አንፃር እና አመልካች ወደ አዱስ አበባ ለመዙወር ከጠየቀበችበት ምክንያት አንፃር አሳማኝ ባለመሆኑ እና የፍትሐብሕር ሕጉን ቁጥር 185 ድንጋጌን ሉያስነሳ የሚችል አጠራጣሪ የመኖሪያ ስፍራ ስለላለ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 183 ድንጋጌ መሰረት የጉዲዮቿ እና ጥቅሞቿ ዋና ስፍራ የሙለ ጊዚ ሥራዋን የምትሰራበት አዱስ አበባ ከተማ ሲሆን ከተጠሪ የሥራ ክልል የለቀቀች በመሆኑ የማሕበሩ መተዲደረያ ደንብ ቁጥር 9(2) እና 14(4) ሥር የተደነገገው በመተላለፍ ግዳታዋን ባለመወጣቷ የተሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም በማለት የሰሜን ሸዋ ዜን መስተዲድር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን ያፀና ሲሆን ፤
የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪ ችልቱም የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተገኘበትም በማለት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ሰርዜታል።
አመልካች በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን ውሳኔ በሰበር ለማሳረም ያቀረቡት አቤቱታ ይዖት፡አመልካች በሳምንት አልያም በአስራ አምስት ቀን የምትመላለስ መሆኑ ፤ ማሕበራዊ ሕይወቷ ፣ ዔድሯ እና የቤት ንብረቷ በሸዋሮቢት ከተማ እንደሚገኝ ፣ ከአዱስ አበባ ከተማ የቤት ተጠቃሚ ያለመሆኗ ተረጋግጦ እያለ የፍትሐብሕር ሕጉን ቁጥር 185 ድንጋጌ በሚፃረር መልኩ የሥራ ዛውውር በማድረጓ ብቻ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 90 ፣ 32 እና 41 በሚቃረን መልኩ ፤ መደበኛ መኖሪያዋን እንደቀየረች መቆጠሩ ፤ የማኀበሩ መተዲደሪያ ደንብ በጠቅላ ጉባኤ ያልፀደቀ ረቂቅ ሆኖ ተፈፃሚነት የላለው ከመሆኑም በላይ በአዋጅ ቁጥር 220/2007 ቁጥር 18 ሥር ከተደነገገው ውጭ አንድ አባል የማህበሩን የሥራ ክልል ለቆ ከሄደ እንደሚሰናበት ተጨማሪ መስፈርት መደንገጉ አዋጁን የሚቃረን በመሆኑ ተፈፃሚነት የላለው ሆኖ ሳለ የስር ፍርድ ቤቶች ለውሳኔያቸው መሰረት ማድረጋቸው ፤ አመልካች በመምህርነት ሳይሆን እንደማንኛውም ነዋሪ ቦታ ለማግኘት ተደራጅታ ሁለን ነገር ብታሟላም መንግስት በጊዚ ቦታውን ባለማቅረቡ ምክንያት የቤት መስሪያ ቦታ ሳታገኝ የሥራ ዛውውር በማድረጓ ተወልዲ አድጋ ለ17 ዓመት በመምህርነት ባገለገለችበት ከተማ የቤት መስሪያ ቦታ እንዲታገኝ ከተጠሪ ማኀበር መሰናበቷ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ውሳኔው ተሽሮ የወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቶ ወደ ማኀበሩ እንድትመልስ እንዱወሰን አመልክተዋል። የሰበር አጣሪ ችልቱ አመልካች በሥራ ዛውውር እንጅ መደበኛ የመኖሪያ አድራሻቸውን ያልቀየሩ ማኀበራዊ ኑሮአቸው ሸዋሮቢት ከተማ መሆኑን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዲደር ወረዲ ፍርድ ቤት በሰነድ እና በሰው ማስረጃ አጣርቶ የሰጠው ውሳኔ ጉዲዩን በይግባኝ ያዩት ፍርድ ቤቶች አመልካች ከማኀበሩ ሉሰናበቱ ይገባል ያለበትን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 220/2007 ዓላማ አንፃር መጣራት አለበት በማለቱ ተጠሪ በሰጠው መልስ፡- አመልካች በቋሚነት በዛውውር አዱስ አበባ ከተማ በመምህርነት እየሰራች ለመሆኑ በአቤቱታዋ ጭምር አረጋግጣ ባለችበት ሁኔታ አድራሻዬ ሸዋሮቢት ነው የሚለው መከራከሪያ አግባብነት የላለው ከመሆኑም ባሻገር የመንግስት ሰራተኞች ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ቦታ አንድ መኖሪያ እንደሚኖራቸው የሚደነግገውን የፍትሐብሕር ሕጉን ቁጥር 179 የሚቃረን ተቀባይነት የላለው መሆኑን ፤
የማኀበሩ የሥራ ክልል ሸዋሮቢት ከተማን ለቃ በዛውውር አዱስ አበባ ከተማ በቋሚነት እየሰራች በመሆኑ በማኀበሩ ደንብ መሰረት በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ከአባልነት መሰናበቷ ሕጋዊ ሆኖ እያለ አመልካች ያቀረበችው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት ሉኖረው የማይገባ መሆኑን ፤
አባላት በበቂ ምክንያት ከማኀበር ሉሰናበቱ እንደሚችል በአዋጁ የተቀመጠ ሲሆን ለማሰናበት የሚያበቁት ምክንያቶች ደግሞ በማኀበሩ ደንብ ላይ በግልጽ በመቀመጣቸው በአዋጅ ቁጥር 220/2007 አንቀጽ 18 መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ አባላትን ሲያሰናብት የሰሩትን ጥፊት በዛርዛር ማስቀመጡ አስፈላጊ በመሆኑ አመልካች በጠቅላላ አባላት በፀደቀው ደንብ መሰረት በበቂ መክንያት ከማኀበሩ ተሰናብታ እያለ የማኀበሩ ደንብ ቁጥር 14(4) ድንጋጌ የአዋጅ ቁጥር 220/2007 ቁጥር 18 ድንጋጌን እንደሚቃረን የቀረበው መከራከሪያ የአዋጁንና የደንቡን ዓላማ ከግምት ያስገባ አለመሆኑን ፤ አመልካች ከአማራ ክልል ውጭ በመምህርነት እየሰራች የደንብ ቁጥር 150/2009 ቁጥር 3 እና 4 ድንጋጌን በሚቃረን መልኩ ወደ ማኀበር አባልነት ለመመለስ የምታቀርበው አቤቱታ አግባነት የላለው መሆኑን ፤ በጠቅላላ ጉባዓ ፀድቆ እና አግባብ ባለው ባለሥልጣን ተመዛግቦ ለማኀበሩ ህጋዊ ሰርተፍኬት ተሰጥቶ ባለበት የማኀበሩን መተዲደሪያ ደንብ ረቂቂ ነው በማለት አመልካች የምታቀርበው መከራከሪያ ተገቢ ባለመሆኑ ይግባኝ ሰሚዎቹ የሥር ፍርድ ቤቶች የሸዋሮቢት ከተማ አስተዲደር ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔን መሻራቸው የሚነቀፍ ባለመሆኑ ለሰበር ቅሬታው መሰረት የሆነው ውሳኔ ፀንቶ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ሆኖ ከወጪ እና ኪሳራ ጋር እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑ እንደሚከተለው ተመርምሯል። አመልካች ለ17 ዓመታት በመምህርነት ባገለገለበት ሸዋሮቢት ከተማ የቤት መስሪያ ቦታ ስላልነበራቸው የአማራ ክልል ባወጣው ደንብ ቁጥር 150/2000 እና መመሪያ ቁጥር 28/2009 መሰረት አድርጎ በተጠሪ ማህበር ተደራጅተው ለአምስት ዓመት የቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ እያለ ባለቤታቸው የፍደራል ፖሉስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ባልደረባ በመሆናቸው የትዲር አጋራቸው ወደለበት አዱስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በጥቅምት ወር 2012 ዓ/ም ዛውውር ተደርጎላቸው በከተማው በማስተማር ላይ ቢሆኑም መደበኛ መኖሪያቸው ሸዋሮቢት ከተማ ሆኖ እያለ እና በአዱስ አበባ ከተማ የመኖረያ ቤት ተጠቃሚ እንዲልሆኑ ተረጋግጦ እያለ ተጠሪን የሥር 2ኛ ተከሳሽ ከማህበሩ እንዱያሰናብት የፃፈለትን ደብዲቤ መሰረት አድርጎ ተጠሪ አመልካችን ከማህበሩ ማሰናበቱን አግባብ ባለመሆኑ ውሳኔው ተሰርዜ ወደ ማኀበር አባልነታቸው እንዱመለሱ እንዱወሰንላቸው ላቀረቡት ክስ ተጠሪ በሰጠው ምላሽ፡- የስራ ክልል ለቃ ስለሄደች በማኀበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 14(4) መሰረት ከማኀበሩ እንድትሰናበት የሥር 2ኛ ተከሳሽ እንዲሳወቃቸው ለአመልካች በመግለፅ ምልዐተ ጉባዓ ተሟልቶ አመልካች ከማኀበሩ እንድትሰናበት የተላለፈ ውሳኔ እንዱፀና ጠይቀዋል። አመልካች በተጠሪ ማኀበር የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታን ለማግኘት የተደራጁት በመምህርነት ባገኙት ልዩ መብት መሆን አለመሆኑ? በመምህርነት ያገኙት ልዩ መብት ነው ከተባለ በመምህርነት ሙያቸው የትዲር አጋራቸው ወደ አለበት አዱስ አበባ ከተማ ዛውውር በማግኘታቸው ለመምህራን የተሰጠውን ልዩ መብት አላግባብ ተጠቅመዋል ተብል ከማኀበር አባልነታቸው ሉሰረዘ ይገባል? የሚለትን ጭብጦች ለጉዲዩ ተገቢነት ካለው ሕግ አንፃር ማየት ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። የመምህርነት ሙያ ለሀገር ሁለንተናዊ ዔድገት የሚጫወተው ቁልፍ ሚና ለማሳካት የበኩለን ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ መምህራን የሚጠበቅባቸውን ሙያዊ ግዳታቸውን በተነቃቃ መንፈስ መወጣት እንዱችለ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት በሙያው ብቃት ያላቸው መምህራን ፍልሰት ለመቀነስ የመኖሪያ አካባቢን በማመቻቸት ማኀበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን በማቃለል ቤተሰቦቻቸው እና መላው ህብረተሰቡ ለሙያው አዎንታዊ አመለካከት ኖሯቸው የበኩላቸውን ድጋፍ እንዱያደርጉ የህግ ማዔቀፍ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ታምኖበት የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የመምህራን መኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አሰጣጥና የተገነቡ ቤቶች ድልድል ለማስፈፀም ደንብ ቁጥር 150/2009 የወጣ መሆኑን ደንቡ ያመለክታል። እነዘህ ለመምህራን የሚደረጉት ማትግያዎች በሚያስተምሩት አካባቢ በመንግስት ወይንም በህዛብ ተሳትፍ የሚሰሩ ቤቶችን በነፃ ወይንም በተመጣጣኝ ኪራይ ማግኘት ፣ በሚያስተሚሩበት ቦታ ወይንም አካባቢ በሚገኝ ቀበላ እና ከተማ የቤት መስሪያ ቦታ እንዱሰጣቸው ጥያቄ ባቀረቡ ጊዚ እንደማንኛው ዚጋ በማኀበር ተደራጅተው በህጉ የተመለከተውን መስፈርት አሟልተው የቤት መሥሪያ ቦታን ከአነስተኛ ፣ መካከለኛ እና ሜትሮፖሉታን ከተሞች ማግኘት የሚችለ መሆኑን ከደንቡ ቁጥር 6 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል። መምህራን በሚሰሩበት ወረዲ ውስጥ ካለት ከተሞች መካከል በመረጡት ከተማ ቤት የመስራት ፍላጎት ኖሯቸው መመሪያ ቁጥር 28/2009 በሚፈቅደው መሰረት እንደማንኛውም ዚጋ 14 እና ከዘያ በላይ ሆነው በማኀበር ተደራጅተውና ከቤት መስሪያ ዋጋው 20 በመቶ መቆጠባቸውን አረጋግጠው ቦታ መጠየቅ የሚችለ መሆኑን ቁጥር 6(4) ያመለክታል። ደንብ ቁጥር 150/2009 መምህራን ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት በተለየ ያስቀመጠው ነገር ቢኖር በከተማ ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ከሚዖጋጀው ቦታ ውስጥ 20-30 በመቶ የሚሆነው ለመምህራን ቅድሚያ ተሰጥቶ የሚመደብ መሆኑ ቁጥር 6(6) ,7(4), 8(5) እና 9(5) ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል። መምህራን እንደ ማንኛውም ዚጋ በመኖሪያ ህብረት ሥራ ማኀበራት ተደራጅተው የከተማ መኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታን ከሚያገኙ በቀር በመምህርነታቸው የተለየ መብት ተሰጥቷቸዋል ብል ለመናገር ብዘም የሚያስደፍር አይደለም። የተለየ መብት ተሰጥቷቸዋል ቢባል እንኳን በመጀመሪያ ደንቡ የወጣበት ዓላማ መነሻ ያደረገው የአማራን ብሓራዊ ክልላዊ መንግስትን ቢሆንም ጥራት ያለው ትምህርት ለዚጎች ማዲረስ እንደ ሀገር የተያዖ መዲረሻ ግብ በመሆኑ አመልካች በያዘት ሙያ ወደ አዱስ አበባ ከተማ ዛውውር ስላገኙ መብቱን ከዓላማው ውጪ ተጠቅሞበታል የሚያስብል አይሆንም። ሁለተኛ አመልካች በህገ መንግስቱ አንቀጽ 33(2) በዚግነታቸው ህግ የሚያስገኘውን መብት ጥበቃ እና ጥቅም የማግኘት መብት ያላቸው በመሆኑ በአንቀፅ 41(1) እና 32(1) መሰረት እንደቅደምተከተላቸው በመረጡት የመምህርነት ሙያ መሰማራት እና በመረጡት የሀገርቱ አካባቢ የመኖር መብታቸውን ማንኛውም የመንግስት አካል የማክበርና ማስከበር ኃላፉነት እና ግዳታ ያለበት መሆኑን የህገ መንግስቱ አንቀጽ 13(1) ይደነግጋል። አመልካች ባለትዲር መሆናቸው እና የባለቤታቸው ሥራ ቦታ አዱስ አበባ መሆኑ ግራቀኙን ያላከራከረ ሲሆን ፤ ባልና ሚስት አብሮ ለመኖር የሚገደደ መሆኑና ተለያይተው መኖር የሚችለት ለተወሰ ጊዚ መሆኑን የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 64(1) እና 66(1) ያስገነዛባለ። አመልካች ከትዲር አጋራቸው ለማገናኘት ሲባል ዛውውር መደረጉ በቤተሰብ ሕጉም ሆነ በሲቭል ሰርቪስ ህጉ ተቀባይነት ያለው ሆኖ እያለ አመልካች በመምህርነታቸው ከአዱስ አበባ ከተማ የቤት ተጠቃሚ መሆናቸው ባልተረጋገጠበት ፣ አመልካች በደንብ ቁጥር 150/2009 ቁጥር 10 መሰረት በራሳቸውም ሆነ በትዲር አጋራቸው ስም አስቀድሞ የተመዖገበ የመኖሪያ ቤት ወይንም ቦታ ያላቸው መሆኑ ክርክር እና ማስረጃ ባልቀረበበት ፤ እንዱሁም ቦታ ለማግኘት የተደረጀ ሰው በሥራ ወደ ላለ ቦታ በመዙወሩ ምክንያት ከመኖሪያ ቤት የኀብረት ሥራ ማኀበር አባልነቱ ይሰረዙል የሚል በአዋጅ ቁጥር 220/2007 ቁጥር 18 ሥር ባልተደነገገበት የአመልካች ከማኀበር አባልነት መሰረዛ ሕጉን የተከተለ አይደለም። በአነስተኛ ፣ መካከለኛ እና ሜትሮፖሉታን ከተማ አስተዲደሮች የሚያስተምሩ መምህራን ቁጥር ከ14 በታች በሆነ ጊዚ በተናጥል በሉዛ መነሻ ዋጋ የቤት መሥሪያ ቦታ የማግኘት መብት አላቸው። (ደንብ ቁጥር 7(3) , 8(3) እና 9(3) ድንጋጌን ይመለከቷል።) ስለዘህ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ማግኘት መብት በማኀበር በመደራጀት የሚገኝ ሳይሆን ከሕግ የሚመነጭ ነው። በአዋጁ ቁጥር 220/2007 የመደራጀት ዓላማው ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ችግሮችን በጋራ ጥረት በመቋቋምና በማስወገድ ፣ በግል ቢሰራ የሚደርሰውን ጉዲት እና ኪሳራ በመከላከል የእያንዲንደን ጉዲት እና ኪሳራ በመቀነስ የአባላቱን ጥቅም ማስከበር መሆኑን ከቁጥር 4(4) እና 4(8) ድንጋጌ መረዲት ይቻላል። ምንም እንኳን የማኀበሩ መተዲደሪያ ደንብ አባላት ከማኀበሩ የሚወጡበትና የሚመለሱበትን ሁኔታ የሚያካትት መሆኑ በአዋጁ ቁጥር 14 (2) (ሰ) ሥር የተደነገገ ቢሆንም ድንጋጌው መታየት ያለበት ከአባልነት መብት እና ግዳታቸውን ከመወጣት አንፃር እንጅ ፤ የአባላቱን ጥቅም በተሻለ መልኩ ለማስጠበቅ የተቋቋመ ማኀበር በህጉ ያልተቀመጠውን መስፈርት በመተዲደሪያ ደንቡ ላይ በማስፈር አባላቱን ባልተገባ ምክንያት ከማኀበር በማሰናበት በህግ የሚያገኙትን መብት ማሳጣት በማኀበር የመደራጀት ዓላማ አይደለም። ሲጠቃለል አመልካች በመምህርነታቸው የቤት መሥሪያ ቦታ ለማግኘት በተጠሪ ማኀበር ተደራጅተው በመጠባበቅ ላይ እያለ በመምህርነት ሙያቸው የትዲር አጋራቻው ወደሚሰሩት አዱስ አበባ ከተማ በመዙወራቸው ምክንያት ከተጠሪ ማኀበር መሰናበታቸው ከላይ በዛርዛር በተመለከቱት ምክንያቶች ተገቢነት የላለው በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል።
2 የሸዋሮቢት ከተማ አስተዲደር ወረዲ ፍርድ ቤት በመዛገብ ሐምል 14 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ ፣ ውሳኔ እና ትእዙዛ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
3 በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የግላቸውን ይቻለ።
4 ውሳኔው መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም በችልት ተነቧል።
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዖግቷል።
No topics extracted.