No summary available.
የመ.ቁ.203253 የካቲት 25/2014 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡ አቶ በሪሁን አጥናፍ አልተጠሩም ተጠሪ፡ የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የቀረበ የለም አቤቱታ አቅራቢ፡ መኳንንት ቢምር መዛገቡ በውሳኔ ከተዖጋ በኋላ ለችልት ላቀርብ የቻለው አቤቱታ አቅራቢ ህዲር 27/2014 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ በዘህ መዛገብ ላይ አመልካችን አስምልክቶ መስከረም 28/2014 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ እርሱንም የሚጠቅመው መሆኑን ገልፆ የውሳኔው ውጤት በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 196(2) መሰረት ተፈፃሚ እንዱሆንለት በማመልከቱ ምክንያት ነው። የቀረበው አቤቱታ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በዘህ መዛገብ ላይ ቀድሞ ውሳኔ ያገኘውን አመልካችን እና የአሁን አቤቱታ አቅራቢን ጨምሮ በሶስት ተከሳሾች ላይ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1(ሀ)) እና 669(1(ለ)) ድንጋጌን ጠቅሶ በሰሜን አቼፈር ወረዲ ፍ/ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው። በቀረበው ክስ ውስጥ የአሁን አቤቱታ አቅራቢ 3ኛ ተከሳሽ ነበር። የክሱም ጭብጥ አቤቱታ አቅራቢው ከስር ፍርድ ቤት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ከነበሩት ጋር በመሆን የተጠቀሰውን የወንጀል ህግ ድንጋጌን ተላልፈው መስከረም 28 ለ29 ቀን 2013 ዓ.ም አጥቢያ ከላሉቱ 7፡30 ሰዓት አካባቢ የተለየ ጠባቂ የላለውን እና ለይስማዔላ ከተማ ህዛብ የውሃ አገልግልት የሚሰጠውን ግምቱ ብር 160,000 (አንድ መቶ ስልሳ ሽህ ብር) የሆነ የውሃ ኮንትሮል ፓኔል ቦርድ ሰርቀው ወስደው በተደረገ ጥቆማ 1ኛ ተከሳሽ የነበረው ተይዜ ወደተከራየው ቤት ሲወሰድ 1ኛ ተከሳሽ ቤቱን እንዱከፍት ሲጠየቅ “ቁልፍ ጠፍቶብኛል” በማለቱ የቤቱ ቁልፍ ተሰብሮ ሲገባ ከአመልካች እና የአሁን አቤቱታ አቅራቢ ጋር እቃው በቤቱ ውስጥ የተገኘ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፊይ በመሆን ከባድ የስርቆት ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ነው።
ተከሳሾቹም ቀርበው ክሱን ሳይቃወሙ 1ኛ ተከሳሽ የነበረው የተከሰሰበትን የስርቆት ወንጀል ብቻውን ስለመፈፀሙ ገልፆ ድርጊቱን እና ጥፊተኝነቱን በሙለ በማመኑ በሰጠው የእምነት ቃል ብቻ ጥፊተኛ ተብሎል። አመልካች እና አቤቱታ አቅራቢ ደግሞ በቤቱ የተገኙት በእንግድነት ሲሆን የስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረው ቤቱን ቆልፍባቸው በመሄደ ምክንያት ሲጠብቁት በቤቱ ውስጥ ከመገኘታው ውጭ ክስ የቀረበበትን ወንጀል ያልፈፀሙ መሆኑን ገልፀው ክደው ተከራክረዋል።
በዘሁ ምክንያት አመልካች እና አቤቱታ አቅራቢን አስመልክቶ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ እንዱከላከለ ሲነገራቸው መከላከያ ማስረጃ የላላቸው መሆኑን በመግለፃቸው ታልፍ በተከሰሱበት አንቀፅ ስር ጥፊተኛ ተብለው እያንዲንዲው በ6(ስድስት) ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጡ ተወስኗል። ይኸው ውሳኔ በየደረጃ ባለት የክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶችም ፀንቷል።
በዘህ መዛገብ ላይ አመልካች የሆነው ይህንኑ ውሳኔን በመቃወም ለዘህ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርቦ የግራ ቀኙ ክርክር ከተሰማ በኋላ መስከረም 28/2014 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ አመልካች በነፃ ተሰናብቷል። በአሁን አቤቱታ አቅራቢ የቀረበው ጥያቄም የስር ፍርድ ቤቶን ውሳኔ ተቃውሜ የሰበር አቤቱታ ያላቀረበኩ ቢሆንም በዘህ መዛገብ ላይ አመልካችን አስመልክቶ የተሰጠው ውሳኔ የሚጠቅመኝ በመሆኑ ውጤቱ ለእኔም ተፈፃሚ ላሆን ይገባል የሚል ነው። ተጠሪ በዘሀ ጥያቄ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዖዖው መሰረት ሁለት ጊዚ ተለዋጭ ቀጠሮ ጠይቆ ጥር 27/2014 ዓ.ም ከተያዖው የምርመራ ቀን በፉት የጽሐፍ መልሱን ከመዛገብ እንዱያያይዛ የታዖዖ ቢሆንም አላቀረበም።
ችልቱም የቀረበውን አቤቱታ ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዖብ መርምሯል።
በመሰረቱ ስልጣን ባለው የዲኝነት አካል በወንጀል ጥፊተኛ ተብል የተቀጣ ሰው ጥፊተኛ ከተባለበት ወንጀል በነፃ ሉሰናበት አልያም በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ሉሻሻል የሚገባው ጥፊተኛ የተባለው ሰው የሥነ ሥርዓት ህጉ በሚፈቅደው መሰረት የይግባኝ ቅሬውን አቅርቦ በሚያሰማው መከራከሪያ መነሻነት ስለመሆኑ በወንጀል ጉዲይ የይግባኝ ክርክር ስለሚመራበት ሁኔታ ከሚደነግገው የወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት አምስተኛ መፀሒፍ አንደኛ አንቀፅ ከቁጥር 181 እስከ 195 ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች ይዖት መገንዖብ ይቻላል።
መርሆው ይህ ቢሆንም በስር ፍርድ ቤት በጋራ ከተከሰሱ ሰዎች ውስጥ አንደ ይግባኝ ጠይቆ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ይግባኝ ባዩ የሚጠቅም በሆነ ጊዚ ከይግባኝ ባይ ጋር በጋራ የተከሰሱት ሰዎችም ይግባኝ ቢለ ኖሮ በተሰጠው ውሰኔ ተጠቃሚ ሉሆኑ ይችለ የነበረ ለመሆኑ ከተረጋገጠ ውሳኔው ይግባኝ ላላቀረቡት ተከሳሾችም ጭምር ተፈፃሚ መሆን የሚገባው ስለመሆኑ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 196(1(ሀ) እና (ለ)) ይደነግጋል።
No topics extracted.
በወንጀል ጥፊተኛ የተባለ ሰው ላላ ሰው በተከራከረበት ጉዲይ በተሰጠ ውሳኔ ተጠቃሚ እንዱሆን በዘህ ድንጋጌ ስር የተመለከተው ሁኔታ ከላይ ለተጠቀሰው መርሆ ልዩ ሁኔታ/በስተቀር/ ነው ብል መውሰድ ይቻላል። የዘህ ቁጥር ድንጋጌ በሰበር ሰሚ ችልት ታይቶ ውሳኔ ላገኘ ጉዲይም ተፈፃሚነት ያለው ለመሆኑ ይኸው ችልት ከዘህ ቀደም በሰ/መ/ቁ/96378 ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።
በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 196 ስር የተመለከተው ድንጋጌው ልዩ ሁኔታ/በስተቀር/ በመሆኑ ተፈፃሚ የሚሆንበት መመዖኛዎች ተለይተው ተቀምጠዋል። አንደኛው አመልካቹ ባልተከራከረበት ጉዲይ የተሰጠው ውሳኔ እርሱን የሚጠቅመው ሆኖ ሲገኝ ሲሆን ላላኛው ደግሞ አመልካቹ ይግባኝ ቢል/የሰበር አቤቱታ አቅርቦ ቢሆን/ ኖሮ በተሰጠው ፍርድ/ውሳኔ ተጠቃሚ ላሆን ይችል የነበረ ከሆነ የሚለት ናቸው። በእርግጥ አመልካቹ ተከራካሪ ባልሆነበት የተሰጠው ውሳኔ ለእርሱ ጠቃሚ የሚሆነው በምን ሁኔታ እንደሆነ ድንጋጌው የሚገልፀው ነገር የለም። ሆኖም ድንጋጌው ልዩ ሁኔታ እንደመሆኑ መጠን ስለይግባኝ ክርክር አመራር የተቀመጠውን መርሆ በማያፊልስ መልኩ በጠባቡ ሉተረጎም እንደሚገባ ይታመናል።
በዘሁ መሰረት አንድ ሰው በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 196 መሰረት ቀድሞ በተሰጠ ፍርድ/ውሳኔ/ ተጠቃሚ ለመሆን የሰበር ተከራካሪውም ሆነ የሰበር አቤቱታ ያላቀረበው ሰው ጥፊተኛ ተብለው የተቀጡበት ወንጀል አንድ ሲሆን እና ውሳኔው የግል ሁኔታን መሰረት ያደረገ ሳይሆን በቀጥታ ከህግ አተረጓጎም እና አተገባበር ጋር የተያያዖ ላሆን ይገባል። በልላ መልኩ በወንጀል የተፈረደባቸው ሰዎች በርካታ ቢሆኑም ጥፊተኛ የተባለበት ወንጀል አንድ ካልሆነ ወይም ወንጀለ አንድ ቢሆንም እንኳን የጥፊተኝንትም ሆነ የቅጣት ውሳኔው የግል ሁኔታን መሰረት በማድረግ የተሰጠ ከሆኑ ከእነርሱ መሀል አንደ ይግባኝ/የሰበር አቤቱታ/ አቅርቦ በእርሱ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ይግባኝ ላላለው ፍርደኛ ተፈፃሚ ላሆን አይገባም ማለት ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች እና አቤቱታ አቅራቢ የተከሰሱት በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፊይ በመሆኑ ከስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ ጋር በመሆኑ ከባድ የስርቆት ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ነው። በዘህ የወንጀል ድርጊት ውስጥ የአመልካችም ሆነ የአሁን አቤቱታ አቅራቢ የወንጀል ተሳትፍ ተብል የተገለፀው ተሰረቀ ከተባለው ዔቃ ጋር በተያያዖ የስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረው በጥርጣሬ ተይዜ ለብርበራ ወደ ቤቱ ሲወሰድ የአሁን አመልካች እና አቤቱታ አቅራቢ በቤቱ ውስጥ በሩ በውጭ ተቆልፍባቸው ተገኝተዋል የሚል ነው። ቀድሞ በተሰጠው ውሳኔ ላይ አመልካች በነፃ የተሰናበተውም የቀረበው ክስ አመልካቹ ተሰረቀ ከተባለው ዔቃ ጋር ቤት ውስጥ ተቆልፍበት ከመገኘቱ ውጭ በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ የአመልካቹ የወንጀል ተሳትፍ ምን እንደነበር ክስ ከቀረበበት የወንጀል ህጉ ወንጀል ማቋቋሚያ ፍሬ ነገር አንፃር ተለይቶ የተጠቀሰ ነገር የለም፤ በማስረጃም ያልተረጋገጠ በመሆኑ ወንጀል ተፈፅሟል ለማለት አይቻልም በሚል ምክንያት ነው። ይህ ውሳኔ የግል ሁኔታን መሰረት ያደረገ ሳይሆን አመልካችም ሆነ የአሁን አቤቱታ አቅራቢ ፈፅመዋል ከተባለት የወንጀል ድርጊት አለመኖር ጋር የተያየዖ ነው። አመልካችም ሆነ አቤቱታ አቅራቢ ፈፅመዋል ተብል በክሱ ዛርዛር የተመለከተው ተግባር አንድ ዓይነት በመሆኑ እና ለቀደመው ውሳኔ መሰረት የሆነው ወንጀል አልተፈፀመም የሚል በመሆኑ ውሳኔው ለአሁን አቤቱታ አቅራቢም የሚጠቅመው መሆኑን መገንዖብ ይቻላል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
በዘህ መዛገብ ላይ መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችልት የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/03-99294 ላይ ታህሳስ 13/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠውን ትዔዙዛ በመሻር የተሰጠው ውሳኔ ለአሁን አቤቱታ አቅራቢ አቶ መኳንንት ቢምር የሚጠቅም ሆኖ በመገኘቱ ውሳኔው በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 196(1(ሀ) እና (ለ)) ተፈፃሚ እንዱሆንለት ተደርጎ ከቀረበበት ክስ በነፃ ተሰናብቷል።
በውሳኔ ተራ ቁጥር 1 ስር በተሰጠው ውሳኔ መሰረት አቤቱታ አቅራቢ አቶ መኳንንት ቢምር በልላ ወንጀል የማይፈለግ መሆኑን አረጋግጦ በአስቸኳይ ከእስር እንዱለቀው ለሚገኝበት የክልለ ማረሚያ ቤት አስተዲዲር ይፃፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል። ይመለስ።
አ/መ