No summary available.
የመ/ቁ/212950 ህዲር 30/2014 ዓ.ም ዳኞች፡ ሰለሞን አረዲ እትመት አሰፊ ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡ አቶ ቶቼኖ ቶማ ተጠሪ፡ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠቷል።
ጉዲዩ የውንብድና ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩም የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ የወንጀል ህግ አንቀፅ 670 ድንጋጌን ጠቅሶ በወላይታ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው። የክሱም ይዖት አመልካች የተጠቀሰውን የወንጀል ህግ ድንጋጌን በመተላለፍ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ አልያም ለላላ ሰው ለማስገኘት አስቦ በክሱ ዛርዛር ውስጥ በተገለፀው ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት የግል ተበዲይ ወደሆኑት ወ/ሮ አበበች ባደቦ የንግድ ቤት በመሄድ የተበዲይን ጉረሮ አንቆ በመያዛ አንገታቸው ላይ የነበረ የዋጋ ግምቱ ብር 50,000(ሃምሳ ሸህ) የሚያወጣ 20 ግራም የወርቅ ሀብል፤ እንዱሁም ባንኮኒ ውስጥ የነበረውን ብር 20,000(ሃያ ሺህ) ወስድ በጓሮ በኩል ያመለጠ በመሆኑ የውንብድና ወንጀል ፈፅሟል የሚል ነው።
አመልካች ለዘሁ ክስ በሰጠው መልስ ድርጊቱን እና ጥፊተኝነቱን ክድ በመከራከሩ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ቀርበው እንዱሰሙ ከተደረገ በኋላ እንደክሱ አቀራረብ አስረድተዋል በሚል አመልካች ክሱን እንዱከላከል ታዝል። አመካችም አራት መከላከያ ምስክሮችን አሰምቷል። የመከላከያ ምስክሮቹም አመልካች እና የግል ተበዲይ ባል አና ሚስት የነበሩ መሆኑን፤ ክስ የቀረበበት ድርጊት ተፈፀመ ከተባለ በኋላ በዘያው ጉዲይ ሁለቱን ለማሸማገል ሽምግልና ተቀምጠው የነበረ መሆኑን፤ በዘሁ ጊዚ የግል ተበዲይን ስለድርጊቱ ሲጠይቋቸው አመልካች ንብረት ዖርፍኛል በሚል የከሰሷቸው ዖወትር ሰክሮ እየሄደ ስለሚረብሻቸው እንጂ የተወሰደባቸው ንብረት እንደላላ የነገሯቸው መሆኑን ተናግረዋል። ጉዲዩን የያዖው ፍርድ ቤትም ለጉዲዩ አወሳሳን ይረዲኛል በማለት የሽማግላዎቹ ሰብሳቢ የነበሩትን ፓስተር ታደሰ ታንቱ የተባለትን ግለሰብ አስቀርቦ ሰምቷል። ተጨማሪ ምስክሩም አመልካች እና የግል ተበዲይ ባልና ሚስት መሆኑቻውን፤ ክስ የቀረበበት ጉዲይ ተፈፀመ ከተባለ በኋላ የሁለቱን ጉዲይ በሽምግልና የተመለከቱ መሆኑን፤ በሽምግልናው ላይም የግል ተበዲይ በእርግጥም ዛርፉያ ተፈፅሞባቸው እንደሆን በሚል የጠየቋቸው መሆኑን፤ ተበዲይም አመልካች ዖወትር ሰክሮ ንግድ ቦታቸው እየሄደ ስለሚረብሻቸው ለመከላከል በሚል የከሰሷቸው እንጂ የተፈፀመባቸው ውንብድና እንደላለለ የነገሯቸው መሆኑን ገልፀዋል።
ከዘህ በኋላ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙ ክርክር መርምሮ እና የቀረቡትን ማስረጃዎች መዛኖ የዐቃቤ ህግ ክስ እና ማስረጃ ተስተባብሎል በሚል አመልካችን ከቀረበባቸው ክስ በነፃ አሰናብቷል።
ይህንኑ ውሳኔ በይግባኝ የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች በመከላከያ ማስረጃው ያስመሰከረውን ፍሬ ነገር አስምልክቶ በዋናው ክርክር ወቅት በመስቀልኛ ጥያቄ ያስተባበለው ነገር የለም፤ ከተበዲይ ጋር ተደርጓል የተባለውን የእርቅ ስምምነት አስምልክቶም በጽሐፍ የቀረበ የእርቅ ስምምነት የለም፤ የድርጊቱ አፈፃፀምም አመልካች ከግል ተበዲይ ጋር የነበረው ጋብቻ ከተቋረጠ በኋላ ጉልበቱን በመጠቀም ለማስቀጠል ፍላጎት ያለው መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ድርጊቱ ከውንብድና ወንጀል ይልቅ በማስገደድ መጠቀም ወንጀልን የሚያቋቁም ነው በማለት ክስ የቀረበበትን አንቀፅ ወደ አንቀፅ 713 በመቀየር አመልካችን ጥፊተኛ ብልት በ1 ዓመት ከ2 ወር ቀላል እስራት እና በብር 2,000(ሁለት ሺህ) የገንዖብ ቅጣት እንዱቀጣ ወስኗል። አመልካች ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ነሒሴ 14/2013 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለውን መሰረታዊ የህግ ስሀተት ጠቅሶ በዘህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለ ግራ ቀኙ በፅሁፍ እንዱከራሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም አመልካች የዐቃቤ ሀግ ክስ እና ማስረጃን አላስተባበለም በሚል በወንጀል ህግ አንቀፅ 713 ስር ጥፊተኛ ተብል የመቀጣቱን አግባብነት በወንጀል ጉዲት ተከሳሽ የሆነ ሰው በመከላከያ ማስረጃው ማስረዲት ከሚጠበቅበት የማስረዲት ደረጃ አኳያ መርምሯል።
በወንጀል ጉዲይ ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ አስረድቷል የሚባለው ባቀረባቸው ማስረጃዎች ክሱን በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ሲያስረዲ እንደሆነ የወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 141 ይደነግጋል። በወንጀል ክሱ ተከሳሽ የሆነው ሰውም የቀረበበትን ክስ አስምልክቶ ማስተባበያ ማስረጃ እንዱያቀርብ የሚታዖዖው ይኸው ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ከወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 141 እና 142 ድንጋጌዎች መገንዖብ ይቻላል። ከዘህ ጋር ተያይዜ አንድ ሉነሳ እና መልስ ሉሰጠው የሚገባው ነጥብ “በወንጀል የተከሰሰ ሰው በመከላከያ ማስረጃው ማስረዲት/ማረጋገጥ/ የሚጠበቅበት የማስረዲት ደረጃ ምን ያክል ነው?” የሚለው ነው። በልላ አገላለፅ በወንጀል ተከስሶ ክሱን እንድከላከል ከተነገረው ተከሳሽ የሚጠበቀው ዐቃቤ ህግ ባስረዲው ልክ በመከላከያ ማስረጃው በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልለ መረጋገጥ ነው ወይስ የዐቃቤ ሀግ ማስረጃ ላይ ጥርጣሬ እንዱፈጠር ማድረግ ነው እንደማለት ነው።
እንግዱህ ከላይ እንደተመለከተው በወንጀል የተከሰሰ ሰው መከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ የሚታዖዖው በዐቃቤ ህግ ማስረጃ የተረጋገጠበትን ክስ እና ማስረጃን እንዱያስተባብል ነው።
ማስተባበል ማለት ደግሞ የተከሳሹን የወንጀል ድርጊት እና ጥፊተኝነት አረጋግጠዋል በተባለት ማስረጃዎች ላይ በአንድም ይሁን በልላ መንገድ ጥርጣሬ እንዱፈጠር በማድረግ በማስረጃዎቹ የማስረዲት አቅም ላይ መተማመን እንዲይኖር ማድረግ ስለመሆኑ ከማስረጃ ህግ መሰረተ ሀሳብ እና በዘሁ ዘሪያ ከተደረጉ የምርምር ፅሁፍች የምንረዲው ጉዲይ ነው። ይህ ደግሞ ከተከሰሰው ሰው የሚጠበቀው በመከላከያ ማስረጃው በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዲት ሳይሆን የዐቃቤ ሀግ ማስረጃን አስመልክቶ ቀድሞ በተያዖው አቋም ላይ ጥርጣሬን መፍጠር ብቻ መሆኑን ያስገነዛባል።
ወደተያዖው ጉዲይ ስንመለስ ዐቃቤ ህግ ክሱን ለማረጋገጥ ያቀረበው የሰው ምስክር ብቻ ነው።
ቀርበው የተሰሙት የዐቃቤ ህግ ምስክሮችም እንደ ክሱ አቀራረብ አመልካች በግል ተበዲይ ላይ የውንብድና ወንጀል ሲፈጽም መመልክታቸውን ተናገረዋል። ሆኖም አመልካች ከተከሰሰበት የወንጅል ድርጊት ጋር በተያያዖ በአመልክች እን የግል ተበዲይ መካከል ሽምግልና ተቀምጠው የነበሩት የአመልካች መከላከያ ምስክሮች እና በፍርድ ቤት ትዔዙዛ በማጣሪያ ምስክርነት የተሰሙት ሽማግላዎቹ ሰብሳቢ የግል ተበዲይዋ በሽምግልናው ላይ አመልካችን በወንጀል የከሰሷችው ዖወትር ሰክሮ በመሄድ ስለሚረብሻቸው እንጂ የፈፀመባቸው የወንብድና ድርጊት እንደላለ የነገሯቸው ስለመሆኑ ተናግረዋል። በእንዘህ አሸማጋይ ሽማግላዎች ይህ ሁኔታ መረጋገጡ ቀድሞ በተሰሙት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የምስክርነት ቃል ላይ ጥርጣሬ እንዱኖር የሚያደርግ ነው።
ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአመልካች እና የግል ተበዲይ መካከል ተደርጓል የተባለው የእርቅ ስምምነት በፅሁፍ አልቀረበም፤ እንዱሁም አመልካች በመከላከያ ማስረጃው ያረጋገጠውን ፍሬ ነገር በመስቀልኛ ጥያቄ አልጠየቀም በሚል ምክንያት የአመልካችን መከላከያ ማስረጃ ውድቅ ማድረጉ የቀረበው ጉዲዩ የወንጀል ክርክር መሆኑን እና በወንጀል ጉዲይ ተከሳሽ የሚጠበቅበትን የማስረዲት ደረጃ ያላገናዖበ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የደቡብ ብሓሮች፣ ብሓረሰቦች እና ህዛቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/34748 ላይ ግንቦት 04/2013 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ እና ይህንኑ ውሳኔን በማፅናት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/36060 ላይ ነሐሴ 04/2013 የሰጠው ትዔዙዛ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁር 195(2(ለ(2))) መሰረት ተሽሯል።
የወላይታ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/46898 ላይ ታህሳስ 19/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት አመልካችን ከተከሰሰበት ወንጀል ነፃ በመልቀቅ የሰጠው ውሳኔ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(2(ለ(2))) ፀንቷል።
ትዔዙዛ
አመልካች በዘህ መዛገብ ላይ ከተከሰሰበት ወንጀል በነፃ የተሰናበተ በመሆኑ በልላ ወንጀል የማይፈለግ መሆኑን አረጋግጦ በአስቸኳይ ከእስር እንዱለቀው ለሚገኝበት ማረሚያ ቤት ይፃፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል። ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።