No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 29 ቀን 2014ዓ/ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ሐብታሙ እርቅይሁን መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ አበበ ብርሃን አድማሴ አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- የፍደራል ጠቅላይ ዐ/ህግ የቀረበ የለም።
መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፈደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ ጥር 12ቀን 2012ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የሰጠውን የጥፊተኝትም ሆነ የቅጣት ውሣኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ተብል እንዱታረምለት አመልካች ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች 1ኛ ተከሣሽ፣ አቶ ጌታሰው ተሰማ 2ኛ ተከሣሽ፣ አቶ በላይነህ ፈንታ 3ኛ ተከሣሽ፣ አቶ አክሉለ ብርሃን 4ኛ ተከሣሽ እና አቶ አብዮት ተስፊዬ 5ኛ ተከሣሽ ነበሩ።
ተጠሪ ነሐሴ 03 ቀን 2009ዓ/ም በተፃፈ ክሱ አመልካችና ላልች ተከሣሾች የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(ለ)፣33 እና የሙስና ወንጀልችን ለመደንገግ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 10(3) ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ አመልካችና 2ኛ ተከሳሽ በፋዳራል ጠቅላይ ዐ/ህግ የኢኮኖሚክ ነክ ወንጀልች ዲይረክቶሬት ዐ/ሕግ ሆነው በመስራት ላይ እያለ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ መ/ቤት አብረዋቸዉ ይሰሩና ወንጀለ በተፈፀመበት ጊዚ በተለያዩ የግል ስራ ተሰማርተዉ ከሚገኙ 3ኛ፣4ኛና 5ኛ ተከሳሾች ከነበሩት ጋር በመመሳጠር በእነ ሲ/ሲ/ኤስ ኮም ሰርቪስ ሶለሽን ኃ/ተ/የ/ገግ/ማህበር ተብል በሚጠራዉ መዛገብ የወንጀል ምርመራዉን ከመምራት ጀምሮ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዉ በድርጅቱና ሰራተኞች ላይ የወንጀል ክስ ከመሰረቱ በኋላ በዋስ እንዱወጡ ክሱን በማቅለልና በኃላም በነፃ እንድለቀቁ ለማድረግ ሚ/ር ደ.ዩና ሚ/ር ው ዡንግ ከተባለት ቻይናያውን ጉቦ ለመቀበል አቅደዉ፡- 1ኛ) 4ኛ ተከሳሽ የነበረው ለሚ/ር ደ.ዮ ስልክ ደውል በአካል ለማግኘት ቀጠሮ አስይዜ ፍሬንድሽፕ ህንፃ 3ኛ ፍቅ ላይ ካለዉ ካፍቴሪያ ካኘው በኋላ በታክስ ማጭበርበር ወንጀል ድርጅታችሁ መከሰሱን አዉቃለሁ ክሱን የያዘት አበበ (አመልካችን)ና ጌታሰዉ የተባለትን ዐቃቢያነ-ሕግ አውቃቸዋለሁ ብል ፍቶ ግራፊቸውን አሣይቶ በቀረበበት ክስ እንደሚረዲው ገልጾ በልላ ጊዚ ለዐቃቢያነ ሕግ 3 ሚሉዮን ለራሱ 1.5 ሚሉዮን ብር እንዱከፍለት ማግባባቱን፤
2ኛ) 3ተኛ ተከሳሽ የነበረው በበኩለ የግል ተበዲዮች ለአመልካችና 2ተኛ ተከሳሽ ገንዖቡን በቀጥታ ሣይቀበለ ከግል ተበዲዮች ጉቦ እንዱቀበለና ለማድረግ ራሱም የድርሻዉን ለማግኘት አስቦ ከላልች ተከሳሾች ጋር ተመሳጥሮ ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ/ም ለተበዲይ ስልክ ደዉል በታክስ ጉዲይ ክስ ካቀረቡበት ዐቃቢያነ ሕግ ጋር ቅርበት ያለው መሆኑን ገልፆ ከዘህ በኋላም በቢሮው ውስጥ አመልካችኛ 2ኛ ተከሣሽ እንዱገኙ አድርጎ ካስተዋወቃቸው በኋላ ለሚ/ር ደ.ዩ ደውል 5,000,000 (አምስት ሚሉዮን) ብር ከከፈለ ክሱ እንዱሚቋረጥ ነግሮ ሲያግባባው ሚ/ር ደ.ዩ በበኩለ ገንዖቡን ሲከፍል አመልካችና 2ኛ ተከሣሽ እንዱኖሩ ከተስማማ በኋላ ሐምል 10ቀን 2009 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 ቦላ ኤርፖርት ጀርባ በ5ኛ ተከሣሽ መኪና እንዱመጡ አደርጎ ከአመልካችና ከ2ኛ ተከሣሽ ጋር እንዱገናኙ በማድረግ በጥሬ ገንዖብ ሐምሳ ሽኅ ብር በቼክ 4.95 ሚሉዮን ብር ቼክ በመቀበለን 3ኛ) 5ተኛ ተከሣሽ በበኩለ የግል ተበዲዮች 3ኛ ተከሳሽን አምነው ገንዖቡን እንዱሰጡትና እንዱቀበል ለማድረግ በማሰብ ሐምል 6ቀን 2009 ዓ/ም አመልካችና 2ኛ ተከሣሽ 3ኛ ተከሣሽ ቢሮ እንዱገኙ በማድረግና የሚከፈላቸውን ገንዖብ ተወያይተው እንዱሚገልፁለት ለሚ/ር ደዩ በመንገሩና ገንዖቡን በተቀባበለ ጊዚም አመልካችንና 2ኛ ተከሣሽን በራሱ መኪና ይዜ በቦታው መገኘቱን 4ኛ) አመልካችና ሁለተኛ ተከሣሽ ገንዖቡን ለመቀበል ከላልች ተከሣሾች ጋር በመመሣጠር የግል ተበዲዮች ዐ/ሕጎችን ማግኘት አለብን ብለው ስለጠየቁ በተያዖው ቀጠሮ መሰረት ሐምል 6ቀን 2009ዓ/ም ቦላ ፍሬንድ ሽፕ ሕንፃ በሚገኘው 3ኛ ተከሣሽ ቢሮ መገኘታቸውን፤ ገንዖቡን ከከፈለት ከሚ/ር ደዩና ሚ/ር ዣንግን ከተባለት ቻይናውያን ጋር መተዋወቃቸውን፤
እንዱሁም ሐምል 10ቀን 2009ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 በሚሆንበት ጊዚ ቦላ ኤርፖርት በ5ኛ ተከሣሽ መኪና ውስጥ ሆነው ገንዖቡን ለ3ኛ ተከሣሽ እንዱሰጥ ለሚ/ር ደ.ዩ መንገራቸውን በመዖርዖር በጠቅላላው አመልካችና ላልች ተከሣሾች ሙለ ሐሳባቸው ተካፊይ በመሆን 50 ሽሕ በጥሬ ገንዖብ 4,950,000.00 በቼክ ጉቦ ሲቀበለ እጅ ከፍንጅ ስለተያዘ የሙስና ወንጀልን ፈፅመዋል በማለት ክስ አቅርቦባቸዋል።
አመልካችና ላልች ተከሳሾች ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሲደረግ ድርጊቱን አልፈፀምንም ሲለ የእምነት ክህደት ቃላቸውን በማስመዛገባቸው የተጠሪ ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎች ቀርበው ተደምጠዋል። የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ ያቀረባቸውን ማስረጃዎች መርምሮ አመልካችን ጨምሮ ላልች ተከሣሾች የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 33 እና የሙስና ወንጀልችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 10(3) የሚከለክለውን በመተላለፍ ጉቦ የመቀበል የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል መሆኑን አመልካችም ከግል ተበዲዮች በ3ተኛ ተከሳሽ በኩል ጉቦ ለመቀበል አስቦ ሐምል 5ቀን 2009 ዓ/ም 3ኛው ተከሣሽ ቢሮ በመገኘት ከግል ተበዲዮች ጋር ከተዋወቀ በኋላ ሐምል 10ቀን 2009ዓ/ም ከምሽቱ 3፡30 ሲሆን 3ኛ ተከሣሽ በክሱ ላይ የተገለፀውን ገንዖብ ሲቀበል 5ተኛ ተከሣሽ መኪና ውስጥ በመሆን የግል ተበዲይ ገንዖቡን እንዱሰጥ ስለማድረጉ ተመስክሮበታል ካለ በኋላ የአመልካችን የስልጣን ደረጃ ግምት ውስጥ በማስገባት የተከሰሰበትን የሕግ ድንጋጌ ወደ አንቀፅ 10(2) በመቀየር እንዱከላከል ብይን ሰጥቷል።
በዘህ መሰረት አመልካች በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 142(3) መሰረት ለፍርድ ቤቱ ከሰጠው ቃል በተማሪ ከላልች ተከሳሾች የጋራና የግል መከላከያ ማስረጃ አቅርቧል። ከፍተኛው ፍርድ ቤትም የአመልካችን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች የተጠሪን ማስረጃ አላስተባበለም ሲል አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 10(2) የሚደነግገውን ክልከላ በመተላለፍ ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው ሲል ፍርድ ሰጥቶ በአራት ዓመት ፅኑ እስራትና በአምስት ሽህ ብር መቀጮ እንዱቀጣ ወስኖበታል። ይህን ውሣኔ በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ስላፀናው አመልካች ይህን የሰበር አቤቱታ አቅርቧል።
አመልካች ጥቅምት 23ቀን 2013ዓ/ም ፅፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታው በቀረበበት ክስ ተከሳሽ ሆነው የክርክሩን ሂደት እስከ ምስክር መስማት ድረስ የተከታተለትን ተከሳሾች የቀረበባቸው ክስ ተቋርጦ ወደ ምስክር በማዜር በተጠሪ የተገባላቸውን የተስፊ ቃልና የደረሰባቸውን መገደድ መሰረት በማድረግ በአመልካች ላይ እንዱመሰክሩ ተደርጎ የሰጡትን ምስክርነት ቃል መሰረት በማድረግ ጥፊተኛ መባለ፤ የቀረበበት ክስ ከ3ኛና 5ተኛ ተከሣሽ ጋር በመሆን በግል ተበዲዮች ላይ የቀረበባቸውን የወንጀል ክስ ለማቅለል፣ በዋስትና እንዱወጡና በኋላም እንዱለቀቁ ለማድረግ ጉቦ ተቀብላችኋል በሚል ሀኖ ሣለ በክሱ ላይ ባልተጠቀሰና በማስረጃ ባልተረጋገጠ ድርጊት ክስ እንዱነሣ አደርጋለሁ በሚል ጉቦ መቀበለ ተረጋግጧል በሚል ጥፊተኛ መባለ፤
ወንጀለ ተፈፀመ ከተባለበት ቀን በማግስቱ ስራ ቦታው ተገኝቶ ስራውን በመስራት ላይ ሣለ እንደሚፈለግ ተነግሮት ተወስድ ሣለ ወንጀለን ሲፈፅመም እጅ ከፈንጅ እንደተያዖ በማስመሰል ጥፊተኛ መባለ፤ የስር ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ማስረጃ ከነሙለ ይዖቱ መመዖን ሲገባው አመልካችን ጥፊተኛ ሉያስብል የሚችለውን ብቻ በመምረጥ እንዱሁም ባልቀረበና ሕጋዊነት በላለው ማስረጃ ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ክርክር በመዖርዖር እንዱታረምለት ጠይቋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ከአመልካች ጋር በሙስና ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ክስ ተነስቶላቸው በአመልካች ላይ በምስክርነት እንዱቀርቡና እንዱሰሙ ተደርጎ አመልካችን በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 10(2) ስር ጥፊተኛ ተብል ቅጣት የተወሰነበትን አግባብ ከአዋጁ አንቀፅ 8 ድንጋጌና ላልች አግባብነት ካላቸው ሕግጋት እንዱሁም ከመሰረታዊ የክርክር አመራር መርሆዎች አንፃር እንዱመረመር ተጠሪም የመልስ ክርክር እንዱያቀርብ ታዜ የግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር ተጠናቋል።
ተጠሪ በበኩለ ጥር 21 ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ መልሱ በጥቅለ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ማስረጃ ምዖናን መሰረት ያደረገ መሆኑን ሰበር ሰሚ ችልት ማስረጃን የመመዖን የዲኝነት ስልጣን ያልተሰጠው መሆኑን፣ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካች ወንጀለን ለመፈፀሙ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ቀርቦበት ባለማስተባበለ ጥፊተኛ ተብል ቅጣት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚያስብል አለመሆኑን በመዖርዖር የስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ እንዱፀናለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ ክርክር አቅርቧል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከትነው የጉዲዩን አመጣጥና በማስቀረቢያ ነጥቡ ላይ ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ክርክር ሲሆን በአንድ በኩል ከአመልካች ጋር ጉቦ የመቀበል የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው ክስ የቀረበባቸውን ተከሣሾች ክስ ተነስቶላቸው ወደ ምስክርነት ተለውጠው ከእነርሱ ጋር ተከሣሽ በነበረው አመልካች ላይ የምስክርነት ቃል እንዱሰጡ ተደርጎ አመልካች ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱን ከአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 8 ድንጋጌና ከወንጀል ማስረጃ ተገቢነት(ተቀባይት) መርህ አንፃርና በልላ በኩል አመልካች ጥፊተኛ ተብል በተቀጣበት ድንጋጌ ተከሣሽ የነበሩት የተጠሪ ምስክሮች ከእነሱና በአመልካች ላይ የቀረበውን የተጠሪ ማስረጃ ካዲመጡ በኋላ መጨረሻ ላይ ወደ ምስክርነት ተለውጠው የሰጡት ምስክርነት ሉሰጠው ከሚገባው ክብደት ወይም ዋጋ አንፃር የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን በሚመለከት መልስ ለመስጠት ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች ጥፊተኛ ተብል ቅጣት የተወሰነበት የሙስና ወንጀልችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 10(2) የሚደነግገውን ክልከላ በመተላለፍ ጉቦ በመቀበለ የሙስና ወንጀል መፈፀሙ በተጠሪ ማስረጃ በበቂ ሁኔታ ተረጋግጦበት አላስተባበለም ተብል ነው። አመልካች ጉቦ የመቀበል የሙስና ወንጀል መፈፀሙን ለማረጋጥ ተጠሪ ምስከሮች፣ ልዩ ልዩ የፅሁፍና የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል። ከተጠሪ ምስከሮች መካከል በ7ኛና በ8ኛ ተራቁጥር የተደመጡት የተጠሪ ምስክሮች ከአመልካች ጋር በግበረ-አበርነት ጉቦ ተቀብለዋል ተብለው ክስ ቀርቦባቸው በመካዲቸው ወንጀለን የፈፀሙ መሆኑን ለማስረዲት የተጠሪ ስድስት ምስክሮች ከተደመጡ እና የሰነድ ማስረጃም ከቀረቡባቸው በኋላ የአዋጁን አንቀፅ 8 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ ወደ ምስክርነት የተለወጡ ስለመሆናቸው የክርክሩ አመጣጥ ያስገነዛባል።
አመልካች ከእሱ ጋር ተከሣሽ የነበሩት ምስክሮች የቀረበባቸውን ክስ ስለካደ የተጠሪ ማስረጃ ከተደመጠ በኋላ በዘያው ክስ ላይ ምስክር ሆነው ቀርበው መደመጣቸው መሰረታዊ የሕግ የተፈፀመበት ነው በሚል የሚያቀርበው ክርክር የማስረጃ ተገቢነት ወይም ተቀባይነት (admissibility of evidence) መርህንና የሰጡት የምስክርነት ቃል ሉሰጠው የሚገባውን ክብደት ወይም ዋጋ መሰረት ያደረገ ነው። የማስረጃ ተገቢነት ወይም ተቀባይነት ክርክሩ የአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 8(1) ድንጋጌን የጣሰ ነው በሚል ነው። ለአመልካች ክርክር ተገቢውን ሕጋዊ መልስ ለመስጠት የአዋጅ ቁጥር881/2007 አንቀፅ 8(1) ድንጋጌ የፀረ ሙስና ልዩ ልዩ የሥነ ስርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 እንደተሻሻ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀፅ 41 ጋር ተጣምሮ መታየት ይኖርበታል። እነዘህ ድንጋጌዎች በሙለ የሙስና ወንጀልችን ግበረ-አበርነት የፈፀሙ ሰዎች ከክስ ነፃ የሚሆኑበትንና ወደ ምስክር የሚዜሩበትን መንገድ እንዱሁም ከክሱ ነፃ ማድረጉና ወይም ወደ ምስክርነት ማዜሩ መቸ እንደሚፈፀም የሚደነግጉ ናቸው። በጥቅለ የሚመለከተው የሕግ አስፈፃሚው አካል በአንድ ተፈፅመዋል በተባለ የሙስና ወንጀል በግብረ-አበርነት ተካፊይ የነበረ ሰው የወንጀለ ምርምራ ተጠናቆ ወደ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፉት ስለተፈፀመው የሙስና ወንጀል ድርጊትና ስለተካፊዮች ሚና ጠቃሚ መረጃ ከሰጠው ከክሽ ነፃ ሉያደርገውና ከፈለገም ከተከሣሽነት ወደ ምስክርነት ማዜር እንደሚችል ተደንግጓል። የእነዘህ ድንጋጌዎች አይነተኛ ዓላማ ወንጀለን የሚያጋልጡ ሰዎች በቂ ማበረታቻ አግኝተው የሙስና ወንጀል ፈፀሚዎች የፈፀሙት ወንጀል እና በሙስና ያካበቱት ንብረት ተደብቆ እንዲይቀር ወደ ሕግ ቀርበው ተገቢ ቅጣት እንዱወሰንባቸው ለማስቻል፤ የሙስና ወንጀል መርምሪዎችም በቂ ማስረጃ እንዱያገኙ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ታስቦ የተደነገጉ እንጅ አመልካች እንደሚያቀርበው ክርክር የሙስና ወንጀል ግብረ-አበርነት ፈፅሟል ተብል ክስ የቀረበበት ሰው አንዳ ክስ ከቀረበበት በኋላ ክሱ ተነስቶለት ምስክር ሆኖ መቅረቡን ከጅምሩ ተገቢነት ወይም ተቀባይት የላለው (inadmessible) ማስረጃ መሆኑን ለመደንገግ ታስቦ አይደለም። በዘህ ጉዲይ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዛገብ ውሣኔ ሲሰጥ ተመሣሣይ አቋም በመያዛ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በመሆኑም የሙስና ወንጀልችን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 8(1) የተደነገገው የሙስና ወንጀልን በግብረ-አበርነት የፈፀሙ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ክሱ ተነስቶላቸው ወደ ምስክርነት መዜራቸውን ለመከልከል ይህ ታልፍም በምስክርነት ከቀረቡም ከወዱሁ ተገቢነት ወይም ተቀባይነት እንዲይኖራቸው ለመደንገግ ታስቦ የተደነገገ ባለመሆኑ አመልካች በዘህ ረገድ የሚያቀርበው ክርክር የሕግ መሰረት የለውም ብለናል።
በልላ በኩል መርመር የሚኖርበት ነጥብ በግብረ-አበርነት የሙስና ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች ወደ ምስክርነት ዜረው የሰጡት ምስክርን ቃል በፍርድ ቤቶች ሲመዖን ሉሰጠው የሚገባው ክብደት ወይም ዋጋ ምን ለሆን ይገባል የሚለው ይሆናል። በሙስና ወንጀል በግብረ-አበርነት ተካፊይ የሆነ ሰው ከክስ ነፃ ሆኖ የሚሰጠው ምስክርነት ቃል ክብደት ማንኛውም ምስክር ከሚሰጠው ምስክርነት እኩል ዋጋ እንዲለው የአዋጅ ቁጥር 434/1997 እንደተሻሻለ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀፅ 41(5) ይደነግጋል። በመሆኑም ክስ ከመቅረቡ በፉት ጠቃሚ ማስረጃ የሰጡ ሰዎች ከተከሻስነት ወደ ምስክርነት ተቀይረው በላልች ግበረ-አበሮቻቸው ላይ የሰጡት ምስክርነት ዋጋ ልዩነት ሣይደረግበት እንዱመዖን ሕጉ ጥበቃ አድርጓል።
የዘህን ችልት መልስ የሚያሻው ጉዲይ ከሳሽ ወገን አንድን የሙስና ወንጀል በግብር-አበርነት ፈፅመዋል በሚል ከአንድ በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ክስ ካቀረበና ማስረጃ ማሰማት ከጀመረ በኋላ የተወሰኑትን ተከሣሾች ክስ አንስቶ ክስ ባልተነሳላቸው ተከሳሶች ላይ ምስክር እንዱሆኑ አድርጎ ቀድሞ ተከሣሽ የነበሩት ሰዎች የሰጡት ምስክርነት ቃል ዋጋው ምን ላሆን ይገባል የሚለው ነጥብ ነው። ይህ ነጥብ መልስ ሉያገኝ የሚችለው የማስረጃ ምዖና መርህን መሰረት በማድረግ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለጉዲዩ ቀጥተኛ መልስ የሚሰጥ የሕግ ድንጋጌ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግም ሆነ በፀረ-ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና የማስረጃ ሕግ ማግኘት አይቻልም። በልላ በኩል ለፍርድ ቤት በቀረበ ማናቸውም የወንጀል ክስ ምስክር ሆኖ የቀረበ ሰው ይመሰክራል ተብል የሚጠበቀው ስለተያዖው አከራካሪ ጭብጥ በቀጥታም ይሁን በተዙዋሪ የሚያውቀውን እንደሚሆን የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 137(1) ይደነግጋል። ይህ ማለት አንድ ምስክር የሰጠው የምስክርነት ቃል ወንጀለ ከመፈፀሙ፣ ከተፈፀመ ወይም እና በተፈፀመበት ወቅት በቀጥታም ይሁን በተዙዋሪ ስለወንጀለ መፈፀም ወይም አለመፈፀም ስለሚያውቀው እውነት ብቻ ይመሰክራል ተብል ይጠበቃል። በእንዱህ ዓይነት ሁኔታ የተሰጠ ምስክርነት ቃል የሚሰጠው ዋጋ ወይም የአስረጅነት ደረጃና በግበረ-አበርነት የተከሰሰበትን ወንጀል በሚዲኘው ችልት ተከሣሽ ሆኖ ቀርቦ የከሳሽን ሙለ ማስረጃ ክርክር አዲምጦ ያገኘውን ግንዙቤ አስቀድሞ ስለጉዲዩ የነበረውን እውቅና በማዲበር እንዱሁም የከሣሽ ወገንን የማስረጃ ክፍተት እና ፍላጎት ከተረዲ በኋላ የተገባለትን የተስፊ ቃል እያሰበ በጫና ውስጥ ሆኖ የሰጠው ምስክርነት ቃል ሉሰጠው የሚገባው ዋጋ እኩል ላሆን አይገባም።
በቀረበልን ጉዲይ ተጠሪ በምስክርነት ካቀረባቸው ሰዎች መካከል 7ኛ ምስክር አቶ ጌታሰው ተሰማ እና 8ኛ ምስክር አቶ አክሉለ ብርሀን የተባለት ምስክር ከመሆናቸው በፉት አመልካች ጥፊተኛ የተባለበትን ጉቦ በመቀበል የሙስና ወንጀል ከአመልካች ጋር በግብረ-አበርነት ፈፅመዋል ተብለው ሁለተኛና አራተኛ ተከሣሾች ነበሩ። እነዘህ ምስክሮች በተጠሪ ምስክርነት ከመደመጣቸው በፉት የቀረበባቸውን ክስ ክደው በመከራከራቸው ስድሰት የተጠሪ ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል እና በአጠቃላይ የክርክሩን ሂደት በችልት ተከታትለዋል። በልላ በኩል አመልካች ጥፊተኛ ተብል ቅጣት እንዱቀጣ ካስቻለት ማስረጃዎች እነዘህ ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት ቃል ትልቅ ክብደት የተሰጠው መሆኑን የውሣኔው ቅጅ ያስገነዛባል።
የተጠሪ ማስረጃ በፍርድ ቤቱ ተደምጦ መጨረሻ ላይ የተጠቀሱት የተጠሪ ምስክሮች ከተከሣሽነት ወደ ምስክርነት እንዱቀየሩ የመወሰኑ ምክንያት በላልች የተጠሪ ማስረጃዎች አመልካችንና ላልች ተከሣሾችን ጥፊተኛ ማስባል እንደማይቻል ስለታመነበት መሆኑን የተጠሪ መስሪያ ቤት የበላይ ሀላፉዎች ለአመልካች መከላከያ ምስክሮች የገለፁላቸው መሆኑንም መስክረዋል።
በያዛው ጉዲይ ላይ ተገቢውን ውሣኔ ለመስጠት ከተከሳሽነት ወደ ምስክርነት የተቀየሩት ምስክሮች ከሰጡት ምስክርነት ቃል ውጪ ላልች ምስክሮችና ማስረጃዎች በአመልካች ላይ ካረጋገጡት ፍሬ ነገር አኳያ የስር ፍርድ ቤቱ የደረሰበትን መደምደሚያ ተገቢነት መርምረናል።
በዘህም መሰረት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራቁጥር የተመዖገቡት የተጠሪ ምስክሮች በጥቅለ አመልካች ጥፊተኛ በተባለበት ወንጀል ምርምራ ላይ የተሣተፈ እንዱሁም አመልካች እንደሚያቀርበው ክርክር ለመከሰሱ ምክንያት የሆነውንና በግል ተበዲይ ላይ የተጣራውን የታክስ ማጭበርበር ወንጀል ከአመልካች ጋር የመረመሩ ሰዎች መሆናቸውን ከገለፁ በኋላ አመልካች ብሩን ሲቀበል እጅ ከፈንጅ ተያዖ ተብል ክስ ቢቀርብበትም በእለቱ እንዲልነበር የመሰከሩ ናቸው። አራተኛ ምስክር ብሩ ለ3ኛ ተከሣሽ ሲሰጥ እጅ ከፈንጅ ተያዖ በተባለበት ቀን ብሩ በተያዖበት ሕንፃ ጥበቃ ሰራተኛ ቢሆንም ብሩ ሲያዛ አመልካች አብሮ ስለመያዘ አልመሰከረም። አምስተኛና ስድስተኛ ምስክሮች የግል ተበዲይ ድርጅት ሰራተኛ እና ስራስኪያጅ የሆኑ ቻይናውያን ሲሆኑ አመልካችን በሚመለከት የሙስና ወንጀለ ፍፃሜ እንዱያገኝ ከጅምሩ ጀምሮ አመቻችቷል በተባለው 3ኛ ተከሣሽ ቢሮ ማግኘታቸውን ነገር ግን ስጉዲዩ አመልካች ጋር የተነጋገሩበት ነገር አለመኖሩን መስክረዋል። በተጨማሪም ስድሰተኛ ምስክር ገንዖቡን ለሶስተኛ ተከሣሽ በሰጠበት እለት በቦታው አመልካችን አግኝቶት ገንዖቡን ለሶስተኛ ተከሣሽ እንዱሰጠው ነግሮኛል ሲል የመሰከረ ቢሆንም በቦታው አብሮት የነበረው አምስተኛ ምስክር ገንዖቡን ለሶስተኛ ተከሣሽ እሱና ስድስተኛ ምስክር ሲሰጡት አመልካች አለመኖሩን መስክሯል። ይህ በእንዱህ እንዲለ ሶስተኛ ምስክር የነበረውና አመልካችና ላልች ተከሣሾች ጉቦ ሲቀበለ እጅ ከፈንጅ ለመያዛ በበላይ አመራር የታዖዖው የፖሉስ አባል ገንዖቡን ከሶስተኛ ተከሣሽ መኪና ውስጥ ሲይዘ አመልካች በቦታው እንዲልነበር መስክሯል። በሶስተኛ፣ በአምስተኛ እና በስድተኛ ምስክር መካከል የተፈጠረው ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ አመልካች ገንዖቡን ለመቀበል በቦታው ከተገኘ በፖሉሶች ለምን አልተያዖም የሚለውን ጥያቄ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ማስረጃ ክርክር መልስ ያላገኘ ጥያቄ ሆኖ ማለፈን የውሣኔው ቅጅ ያስገነዛባል። ላልች የፅሁፍና የሰነድ ማስረጃዎችም ራሣቸውን ችለው አመልካችን ጥፊተኛ ሉያስብለ የሚችለ ማስረጃዎች አለመሆናቸውን የውሣኔው ቅጅ ያስገነዛባል።
ሲጠቃለል የስር ፍርድ ቤት በአንድ በቀረበ የወንጀል ክስ ምስክር ሆኖ የቀረበ አንድ ምስክር የሚሰጠው ምስክርነት ቃል ወንጀለ ከመፈፀሙ፣ ከተፈፀመ ወይም እና በተፈፀመበት ወቅት በቀጥታም ይሁን በተዙዋሪ ስለወንጀለ መፈፀም ወይም አለመፈፀም ስለሚያውቀው እውነት ብቻ መሆን እንደሚገባው የሚደነግገውን የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 137 መርህ በመጣስ 7ኛ እና 8ኛ የተጠሪ ምስክሮች ከአመልካች ጋር በግበረ-አበርነት በተከሰሰቡት የሙስና ወንጀልን ለማስረዲት የቀረቡትን የተጠሪ ሙለ ማስረጃዎች አዲምጠው ያገኙትን ግንዙቤ እንዱሁም የከሣሽ ወገንን የማስረጃ ክፍተት እና ፍላጎት ከተረደ በኋላ የተገባላቸውን የተስፊ ቃል እያሰቡ አመልካችን ሉጠቅም የሚችል ምስክርነት ቃል ቢሰጡ የተገባላቸው የክስ መነሣት ቀርቶ በተከሣሽነት እንደሚቀጥለ እያሰቡ በጫና ውስጥ ሆነው የሰጡትን ምስክርነት ቃል ነው በሚል በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 141 ድንጋጌ መሰረት አመልካች መከላከል ሣያስፈልገው በነፃ እንዱሰናበት መወሰን ሲገባው መከላከል እንዱጀምር ማዖዘ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 141 እና 142(1) መርህን መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩ ተወስኗል።
ውሣኔ
የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ግንቦት 8ቀን 2011 እና ግንቦት 26ቀን 2011 ዓ/ም የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ እንዱሁም የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ ጥር 12 ቀን 2012ዓ/ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 195(2)(ለ)(2) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሐ)፣33 እና የሙስና ወንጀልችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 10(3) ድንጋጌን በመተላለፍ ጉቦ የመቀበል የሙስና ወንጀል መፈፀሙን የሚያረጋግጥ በቂና ለጉዲዩ ገልልተኛ ማስረጃ ቀርቦ ያልተረጋገጠበት በመሆኑ የቀረበበትን ክስ መከላከል ሳያስፈልገው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 141 መሰረት በነፃ እንዱሰናበት ተወስኗል።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.