No summary available.
ሐምል 30 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- አቶ ሀብታሙ አሻግሬ - ቀረቡ ተጠሪ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ - ነ/ፈጅ ሃ/መርያም ብርሃሄ - ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረውም በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን አመልካች በቀን 25/07/2011 ዓ.ም ባቀረው ክስ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በደንበኞች አገልግልት ሱፏርቫይዖርነት ሳገለግል ቆይቼ በሙስና ወንጀል ተጠርጥሬ ክስ ቀርቦብኝ ስከራከር ቆይቼ በታህሳስ ወር 2011 ዓ.ም በነፃ ተሰናብቻለሁ፤ ተጠሪው ሆን ብል ክሱ እንዱቀርብብኝ ያደረገ ሲሆን ከእስር ከተፈታሁ በኋላ ወደ ስራዬ ለመመለስ ስጠይቅ ከቀን 11/06/2011 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ውላ የተቋረጠ መሆኑን በደብዲቤ ገልፆልኛል፤ ነገር ግን ስንብቱ ህጋዊ ባለመሆኑ ወደ ስራየ እንድመለስ፣ የሁለት ዓመት ከአምስት ወር ደሞዛ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ፤ ይህ ካልሆነ ደግሞ የሁለት ዓመት ከአራት ወር ደሞዛና ጥቅማጥቅምን ጨምሮ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 40 እና 41 መሰረት ካሳና የስራ ስንብት ክፍያ እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪ በበኩለ በቀን 27/07/2011 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ የአመልካች የስራ ውል የተቋረጠው አመልካች ከስድስት ወር በላይ በስራው ላይ ባለመገኘቱ ነው፤ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውላ ተቋረጠ ለሚለው በድርጅቱ 10ኛው የህብረት ስምምነት መሰረት በእስር ምክንያት ከስድስት ወር በላይ ከስራው የቀረ ሰራተኛን ያለማስጠንቀቂያ ማሰናበት እንደሚቻል ተደንግጓል፤ አመልካች ከቀረበበት የወንጀል ክስ በነፃ መሰናበቱ ብቻውን ስንብቱን ህገ-ወጥ አያደርገውም፤ ላልተሰራ ስራም ደሞዛ ለመክፈል አንገደድም፤ እንዱሁም የስራ ምስክር ወረቀት ክሉራንስ ሲያቀርብ ይሰጠዋል በማለት ክሱ ውድቅ እንዱደረግለት ጠይቋል።
ጉዲዩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ አመልካች ከሁለት ዓመት በላይ ቢታሰርም ጥፊተኛ አልተባለም፤ ጥፊተኛ ባልተባለበት የስራ ውለ መቋረጡ ተገቢ ስላልሆነ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ካለ በኋላ አመልካች ወደ ስራው እንዱመለስ ቢደረግ ክርክሩ ረዣም ጊዚ የወሰደ ስለሆነና ግንኙነቱ ቢቀጥል ችግር ሉያስከትል ስለሚችል ወደ ስራው ሉመለስ አይገባም በማለት ካሳ ብር 50,742.00፣ የስራ ስንብት ክፍያ ብር 22,409,67 በድምሩ ብር 73,151.67 እንዱከፈለው እና የምስክር ወረቀት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዱሰጠው በማለት ወስኗል። አመልካች ወደ ስራ ልትመለስ አይገባም ተብል የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኙን ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዜበታል። ለዘህ ፍርድ መነሻ የሆነውን የሰበር አቤቱታ ያቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 05/06/2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው 04 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈጽመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዖርዖር በዘህ ችልት እንዱታረሙለት ጠይቋል።
የአቤቱታው ይዖትም በአጭሩ ሰራተኛው ወደ ስራው ተመልሶ በአሰሪውና በሰራተኛው መካከል የስራ ግንኙነቱ ቢቀጥል ከፍተኛ የሚባል ችግር ወይም የስራ ግንኙነቱን የሚያሻክር ችግር ይፈጠራል ተብል ከታመነ ሰራተኛው ካሳ ተከፍልት ሉሰናበት እንደሚችል ቢደነገግም የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ምክንያት ግን በአመልካች እና በተጠሪ የተደረገው ክርክር ብዘ ጊዚ ወስዶል የሚል ሲሆን ይህም ህጉን የተረጎመበት መንገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት መሆኑን ያሳያል፤ ክርክሩ ሉረዛም የቻለው በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያት ፍርድ ቤቶች ዛግ በመሆናቸው ነው፤ ተጠሪ አመልካች ወደ ስራ ቢመለስ ችግር ይፈጠራል በማለት ያቀረበው መከራከሪያ ብቻ መሰረት ተደርጎ ወደ ስራ ልትመለስ አይገባም መባለ ከዘህ በፉት ይህ ችልት የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ያላገናዖበ ስለሆነ ውሳኔው ተሽሮ ወደ ስራ እንድመለስ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
ጉዲዩ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ክርክሩ ረዣም ጊዚ የወሰደው ከአመልካች አቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ከመሆኑ አንፃር የስር ፍርድ ቤት ወደ ስራ ሉመለስ አይገባም ሲል የሰጠው ውሳኔ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43(3) ድንጋጌን ያገናዖበ ነበር ወይ? የሚለው መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ለዘህ ሰበር ችልት ቀርቧል። ተጠሪም መልስ እንዱሰጥበት ጥሪ ተደርጎለት በቀን 27/07/2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ አመልካች ከዘህ ቀደም ይሰራበት የነበረው የስራ መደብ አመልካች ሲሰራበት በነበረበት ጊዚ ካለው የአሰራር ስርዓት ሙለ በሙለ የተቀየረ ሲሆን አመልካች ወደ ስራ ይመለስ ቢባል ቢያንስ የስድስት ወር መደበኛ ስልጠና እና የስድስት ወር ተግባራዊ ስልጠና ይጠይቃል፤ ይህ ደግሞ ተጠሪን ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ እና ጉዲት የሚያስከትል ነው፤ እንዱሁም አመልካች ናሁ ተቪ በተባለ የቴላቪዣን ሚዱያ ላይ በመቅረብ ስሙን ቀይሮ በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም በተሰራ እና “ከአየር መንገድ ጣሪያ ስር ያለ ጉድች” በተባለ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ ድርጅቱ የሰራተኛ ሰብዓዊ ክብር የማይጠብቅ እና በፖሉሲ ደረጃ ህገ-ወጥ ፖሉሲዎችን ቀርፆ ሰራተኞቸ ላይ በደል እንደሚፈጽም፤ ሰራተኞቹን በንቀት የሚያስተዲድር እንደሆነ በመግለጽ የሃሰት መረጃ በመስጠት የድርጅቱን መልካም ስም እና ዛና የሚጎዲ ድርጊት በመፈፀም ከድርጅቱ ጋር ያለው የስራ ግንኙነት ስለተበላሸ ወደ ስራ ሉመለስ አይገባም በማለት ተከራክሯል። አመልካች በበኩለ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቶ ተከራክሯል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዖት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ከተያዖው ጭብጥ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መዛገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም አመልካች ከስራ የተሰናበተበት አግባብ ህገ ወጥ ስለመሆኑ አላከራከረም። ግራ ቀኝን ያከራከረዉ ጉዲይ ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ ከተባለ አመልካች ወደ ስራዉ የማይመለስበት ህጋዊ እና አሳማኝ ምክንያት መኖር ያለመኖሩ ነዉ። አንድ ሰራተኛ ከስራ የተሰናበተበት ሁኔታ ህገ ወጥ መሆኑ ከተረጋገጠ ዉጤቱን በመወሰን ረገድ በአንድ በኩል ሰራተኛዉን ወደ ስራዉ በመመለስ የሰራተኛዉን የስራ ዋስትና ማረጋገጥ፣ በልላ በኩል ደግሞ በሰራተኛዉ ወደ ስራ መመለስ ምክንያት በአሰሪዉ ላይ ሉደርስ የሚችለዉን ጉዲት ግምት ዉስጥ በማስገባት በሁለቱም በኩል ያለትን ተፃራሪ ጥቅሞችን ማስታረቅ በሚቻል መልኩ ላሆን ይገባል። የስራ ክርክሮችን የሚወስነው አካል ከስራ ግንኙነቱ ጠባይ የተነሳ የስራ ግንኙነቱ ቢቀጥል ከፍተኛ ችግር (ሰረዛ የተጨመረበት) ያስከትላል ብል ካመነ ሰራተኛው ወደ ስራው መመለስ ቢፈልግ እንኳን ካሳ ተከፍልት እንዱሰናበት ለመወሰን እንደሚችል በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 እንቀፅ 43(3) ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌም ይህንኑ የሚያስገነዖብ ነዉ። ከዘህ የአዋጁ ድንጋጌ አቀራረጽ መገንዖብ የሚቻለዉም ስራዉ በህገ-ወጥ መንገድ የተቋረጠበት ሰራተኛ ወደ ስራዉ ተመልሶ ለመስራት ፍላጎት ያለዉ መሆኑ ከተረጋገጠ፣ ክርክሩ የቀረበለት የስራ ክርክር ችልት ሰራተኛዉ ወደ ስራዉ እንዱመለስ የመወሰን ግዳታ ያለበት ሲሆን ሰራተኛዉ ካሳ ተከፍልት እንዱሰናበት መወሰን የሚችለዉ ወደ ስራዉ መመለሱ በአሰሪዉ ስራ ላይ ከፍተኛ ችግር የሚያስከትል መሆኑን የተረዲ እንደሆነ ብቻ መሆኑን ነዉ።
ስለሆነም የስራ ክርክሩን የሚያይ ፍርድ ቤት ሰራተኛዉ ወደ ስራዉ ሉመለስ አይገባም በሚል ድምዲሜ ላይ ከመድረሱ በፉት የሰራተኛዉ ወደ ስራዉ መመለስ በአሰሪዉ ላይ ከፍተኛ ችግር የማድረስ ዉጤት የሚያስከትል መሆን አለመሆኑን በአግባቡ የማጤን እና የመመርመር ኃላፉነት ይኖርበታል።
ከዘህ አንፃር የተያዖዉን ጉዲይ ስንመለከት ተጠሪ አመልካች ወደ ስራ ሉመለስ አይገባም በማለት በዘህ ችልት ባቀረበዉ መልስ አመልካች በናሁ ቲቪ ላይ ቀርቦ ባደረገዉ ቃለ ምልልስ የሐሰት መረጃ በመስጠት የተጠሪን ድርጅት መልካም ስም እና ዛና የሚጎዲ ድርጊት በመፈጸሙ ምክንያት በመካከላቸዉ የነበረዉ የስራ ግንኙነት እንደተበላሸ እና በልላ በኩል የስራ ግንኙነቱ ከፍተኛ መተማመንን እንደሚጠይቅ እንዱሁም በመደቡ ላይ ተመድቦ ለመስራት የስድስት ወር መደበኛ ስልጠና እና የስድስት ወር ተግባራዊ ስልጠና የሚጠይቅ መሆኑን በመጥቀስ ይከራከራል፤ ይሁንና አመልካች ይህን መፈጸሙ እንዱሁም ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ቢረጋገጥም እንኳ ብቻዉን አመልካች ወደ ስራዉ እንዲይመለስ ምክንያት ላሆን ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠሪ ይህን ክርክር በስር ፍርድ ቤት ስለማንሳቱ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ይዖት አያሳይም። ይልቁንም በዘህ ረገድ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበዉ ክርክር ግንኙነቱ ከተቋረጠ ረጅም ጊዚ በመሆኑ ወደ ስራ ሉመለስ አይገባም የሚል ነዉ። ከላይ እንደተመለከተዉ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ወደ ስራዉ ሉመለስ አይገባም ሲል ሲወስን መሰረት ያደረገዉም ይህንኑ ነዉ። ይሁንና ግንኙነቱ ከተቋረጠ ረጅም ጊዚ መሆኑ ግንኙነቱ ቢቀጥል በአዋጁ አንቀጽ 43(3) ላይ በተመለከተዉ አግባብ በተጠሪ ላይ ከፍተኛ ጉዲት ይደርሳል በሚል ድምዲሜ ላይ የሚያደርስ አይሆንም።
ከዘህ ሁለ አንፃር ሲታይ አመልካች ወደ ስራ ሉመለስ አይገባም በማለት በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትዔዙዛ የፀናዉ ዉሳኔ የስራ ዉል በህገ ወጥ መንገድ የተቋረጠበት ሰራተኛ ወደ ስራ ሉመለስ እንደሚገባዉ በመርህ ደረጃ በአዋጁ አንቀጽ 43(3) ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ ያላገናዖበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
አመልካች ወደ ስራ ሉመለስ አይገባም በማለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 24/02/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 14/04/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ይህንኑ በማጽናት የሰጠዉ ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ይህ ዉሳኔ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ ያለዉን የአመልካችን የአንድ ዓመት ዉዛፍ ደመወዛ ከፍል አመልካችን ወደ ስራዉ እንዱመልስ ተወስኗል።
በዘህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.