No summary available.
መ/ቁ/195390 የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡ አቶ ኃይለ ምትኩ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር ጠ. አብደላ አሉ - ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የስራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ ተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ አመልካች በተጠሪ ድርጅት ከህዲር 6 ቀን 1978 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 09 ቀን 2010 ዓ.ም በሲኒየር ኢምፖርተር መኮንንነት ሥራ መደብ በወር እየተከፈለኝ እያገለገልኩኝ ተጠሪ ያለፍቃዳ በመቀለ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አድርገው ሲሾሙኝ ሹመቱን እንዲልተቀበልኩኝ አሳውቄ በቀድሞ ስራ መደብ እየሰራሁ ተጠሪ የመቀላ ቅርንጫፍ ስራ መሪነት ላይ አልተገኘም በማለት ጥር 01 ቀን 2010 ዓ.ም በህገ ወጥ መንገድ የስራ ውል በመቋረጡ በግዳታ ያለትምህርት ዛግጅትና የስራ ልምድ የተደረገው ሹመት አግባብ እንዲልሆነና ስንብቱ ህገወጥ ነው ተብል በህጉ የተቀመጡ ክፍያዎች እንዱከፈለ ዲኝነት ጠይቋል። ተጠሪ በበኩለ የሰጠው መልስ ከህዲር 06 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ አመልካች በህብረት ስምምነት መሰረት በእድገት የመቀላ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ተደርጎ ተሹሟል፣ ነገር ግን አመልካች የተጠሪ ትእዙዛ በማክበር መቀላ ሄደው መስራት ሲገባቸው ወደ ተመደበበት ቦታ ላይ እንዱገኙ በተደጋጋሚ ያሳሰበውና በትዔግስት ቢጠብቅም አመልካች በተመደቡበት ቦታ ላይ ተገኝተው ሪፖርት አላደረጉም፣ስለዘህ አመልካች በህጉ አግባብ ስለተሰናበቱ የሚከፈላቸው ክፍያ የለም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱደረግ መከራከሩን መዛገቡ ያሳያል።
ፍ/ቤቱም የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ የአመልካችን የስራ ውል በማቋረጥ ያሰናበተበት አግባብ አመልካች የተሰጠዉን ምደባና ዛዉዉር ተቀብል በተመደበበት ቦታ ስራ ላይ ባለመገኘቱ ነዉ በሚል ስንብቱ ህጉን የተከተለ ነው በማለት ላልች የተጠየቁ ክፍያዎች ውደቅ በማድረግ አመልካች ያልተጠቀሙበት የአመት እረፍት ወደ ገንዖብ ተቀይሮ እንዱከፈል እንዱሁም በአመልካች ስም ተቀማጭ የተደረገው የመጠባበቂያ ክፍያ ፕሮቪደንት ፈንድ ታስቦ ወጪ ተደርጎ እንዱከፈል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍ/ቤቱም አመልካች በተመደቡበት ቦታ ተዙውረው የመስራት ግዳታ አለባቸው ወይ? የሚል ጭብጥ በመያዛ የግራ ቀኝ ክርክር መርምሮ በእርግጥ አሰሪው ሥራው ውጤታማ ይሆን ዖንድ ሰራተኞችን በፈለገበት ቦታ መድቦ የማሰራት አስተዲደዊ ስልጣን ያለው መሆኑን፤ነገር ግን አንድ ሰራተኛ የስራ መሪ ሲሆን በአሰሪና ሰራተኛ ህጉ የተሰጡትን መብቶችን ሉገለገልባቸው የማይችል በመሆኑ ሰራተኛው በስራ መሪነት ሲመደብ ወይም ሲሾም የአሰሪው አስተዲደራዊ መብት ብቻ ሳይሆን የሰራተኛውም ፍቃደኝነት የግድ ይላል፣ በተጨማሪ አሰሪው በፈለገበት ቦታ መድቦ ወይም አዙውሮ የማሰራት አስተዲደራዊ መብቱ ሉጠቀምበት የሚችለው ሰራተኛው በፉት ያገኝ የነበረውን መብትና ጥቅም እስካልተነካ ድረስ ብቻ በመሆኑ አመልካች በተሾመበት ቦታ በአሰሪና ሰራተኛ ህጉ የተደነገጉትን መብቶች ሁለ ሉያገኝ እንደሚችል ተጠሪ ያቀረበው መከራከሪያም ሆነ ማስረጃ የለም። ስለዘህ አመልካች በመቀላ ቅርንጫፍ በተመደቡበት ቦታ ሥራ ላይ አልተገኙም በሚል የስራ ውለን መቋረጡ ሕገወጥ ነው በማለት የጠየቁትን የካሳ ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዚ ክፍያ እና ወጪና ኪሳራ እንዱከፈላቸው ሲወስን የስራ ስንብት ክፍያን በተመለከተ አመልካች የፕሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ያላቸው ስለሆነ ክፍያው አይገባቸውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዘህ ላይ ሲሆን የአመልካች አቤቱታ ነጥብ የስራ ስንብት ክፍያ እና የፕሮቪደንት ፈንድን በተመለከተ የተሰጠ ውሳኔ ላይ ነዉ።የአመልካች አቤቱታ ይዖት ባጭሩ፤
አንድ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 39/1/ለ/ እና አዋጅ 494/1998 አንቀጽ 2/ሰ/ መሰረት የማይከፈለው በገዙ ፈቃደ ስራ ሲለቅና የፕሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ያለውና በጡረታ ህግ የተመለከተው መደበኛ የጡረታ ዔድሜ ላይ ደርሶ ከስራ ሲገለል እንደሆነ ያስረዲል፣ ነገር ግን አሰሪ በራሱ አነሳሽነት አመልካችን በህገወጥ መንገድ ከስራ ካሰናበተ ስንብቱ ህገወጥ በመሆኑ ምክንያት ብቻ ሰራተኛው የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው።የስር ፍ/ቤት ስንብቱ ህገወጥ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ የፕሮቪደንት ፈንድ ስለሚከፈለው የስራ ስንብት ክፍያ ሉከፈል አይገባም ሲል የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ የስራ ስንብት ክፍያ እንዱከፈል እንዱታዖዛልኝ በማለት አመልክቷል።
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በዘህ ጉዲይ ፕሮቪደንት ፈንድን አስመልክቶ ክርክር ቀርቦ እያለ በዛምታ መታለፍ አግባብ መሆን አለመሆን ተጠሪ ባለበት ለማጣራት ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዝል።
በተጠሪ ጠበቃ በኩል የቀረበው መልስ ባጭሩ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ በአመልካች ስም ተቀማጭ የተደረገው የመጠባበቂያ ክፍያ (ፕሮቪደንት ፈንድ) ታስቦ ወጪ ተደርጎ እንዱከፈል ተወስኗል።ስለዘህ አመልካች የስር ፍ/ቤት የፕሮቪደንት ፈንድ እንዱከፈለኝ አልወሰነልኝም ብል ያቀረበው ክርክር ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ጋር የሚቃረን ነው።የከፍተኛ ፍ/ቤትም አመልካች የፕሮቪደንት ፈንድ የሚከፈላቸው በመሆኑ የስራ ስንብት ክፍያ ሉፈፀም አይገባም ሲል የጠቀሰው የፕሮቪደንት ፈንድ እንዱከፈላቸው መወሰኑ ነው።የስራ ስንብት ክፍያን በተመለከተ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በተለያዩ መዛገቦች ላይ የፕሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ያለው ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት የላለው መሆኑን አስገዲጅ ውሳኔ ሰጥቶበታል።ስለዘህ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ ባለመሆኑ አመልካች ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልኝ በማለት ተከራክሯል። አመልካች አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርቦ ከመዛገቡ ጋር ተያይዝል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምረናል።መዛገቡን መርምረን እንደተገነዖብነዉ በተጠሪ አነሳሽነት የተደረገዉ የሥራ ዉል ማቋረጥ ዉሳኔ ህገ ወጥ ነዉ ተብል በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ በበላይ ፍርድ ቤት የተለወጠ ስለመሆኑ የቀረበ ክርክር የለም።ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ መባለን ተከትል ልዩ ልዩ ክፍያዎች ማለትም ካሳ እና የማስጠንቀቂያ ጊዚ ክፍያ እንዱከፈል በስር ፍርድ ቤት መወሰኑን መዛገቡ ያሳያል።የአመልካች የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤት ከተወሰነዉ በተጨማሪ የስንብት ክፍያ እና የፕሮቭደንት ፈንድ ያለአግባብ ታልፎል የሚል ሲሆን ሰበር አጣሪ ችልቱ የያዖዉ ጭብጥ የፕሮቭደንት ፈንድ በሚመለከት ብቻ ቢሆንም የአመልካች የሰበር አቤቱታ እንደሚያሳየዉ እና ተጠሪም አጥብቆ የተከራከረዉ አመልካች የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ስለሆነ የስንብት ክፍያ አይገባዉም የሚል በመሆኑ የስንብት ከፍን በሚመለከት በስር ፍርድ ቤት ዉድቅ መደረጉ ተገቢ መሆን አለመሆኑም ጭምር የዘህ ሰበር ችልት ዉሳኔ የሚያሻዉ ነጥብ ሆኖ አግኝተናል። በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በህግ አግባብ የተቋቋመ የስራ ዉል የሚቋረጥባቸው መንገድች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 23 ስር የተደነገገ ሲሆን ዉለ በአሰሪዉ ወይም በሰራተኛው አነሳሽነት ወይም በህግ በተደነገገው መሰረት ወይም በህብረት ስምምነት ወይም በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ሉቋረጥ እንደሚቻል የሚያመለክት ነዉ።አሰሪዉ ወይም ሰራተኛዉ ከእነዘህ ምክንያቶች ወይም ሁኔታዎች በአንደ ወይም በልላ ምክንያት የስራ ዉል ለማቋረጥ ሲፈልግ ህጉ ያስቀመጣቸዉን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ወይም ሂደቱን መከተል አስፈላጊ መሆኑን የህጉ ዛርዛር ይዖት ያስገነዛባል። ይህም እንደነገሩ ሁኔታ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ወይም ያለማስጠንቀቂያ የስራ ዉል ሉቋረጥ የሚችልባቸዉ ሁኔታዎችን መኖሩን ያመለክታል።በአሰሪዉ አነሳሽነት ስራ ዉል ከሚቋረጥባቸዉ ሁኔታዎች አንደ ሰራተኛዉ በስራ ላይ በሚፈጽመዉ ጥፊት ነዉ።የአዋጁ አንቀጽ 27/1/ እንደሚያመለክተዉ በህብረት ስምምነት በልላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር የሥራ ዉልን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ የሚቻለዉ በዘህ ድንጋጌ ስር ከተዖረዖሩት ጥፊቶች ወይም ምክንያቶች ዉስጥ አንድ ወይም ከዘያ በላይ የሆነ ድርጊት በሰራተኛዉ መፈጸሙ ሲረጋገጥ ነዉ። የሥራ ውል በተለያዩ ምክንያቶች ሲቋረጥ የሚኖረው ውጤትም እንደዘሁ በሕጉ በዛርዛር ተመልክቷል።በተለይም ለሰራተኛው ሉጠበቁ የሚገቡ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችና መብቶች በአዋጅ ቁ/ 337/96 በምእራፍ ሦስት በዛርዛር ተመልክተዋል። ከነዘህም ውስጥ የሥራ ስንብት ክፍያ በሚመለከት የተቀመጠው ድንጋጌ አንቀጽ 39 ጠቅላላ ሁኔታን የሚዖረዛር ሲሆን ከዘህም ዛርዛር ሁኔታዎች መረዲት የሚቻለው የሥራ ስንብት ክፍያን የማግኘት ጉዲይ የሁለም የሥራ ውል መቋረጥ ውጤት ሳይሆን ለውስንና የተገደቡ ምክንያቶች ብቻ መሆኑን ያስገነዛባል።
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በዘህ መዛገብ የቀረበው ጉዲይ በአሰሪ አነሳሽነት የተደረገዉ የስራ ዉል ማቋረጥ ህገ ወጥ ነዉ መባለን ተከትል የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብትን የሚመለከት ነው።በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 39 ስር እንደተመለከተዉ የስራ ስንብት ክፍያ ለሰራተኛዉ ከሚከፈልባቸዉ ሁኔታዎች አንደ በህግ ከተደነገገዉ ዉጭ በአሰሪዉ አነሳሽነት የስራ ወል ሲቋረጥ ለሰራተኛዉ የስራ ስንብት ክፍያ በአሰሪዉ የሚከፈለዉ ስለመሆኑ በንኡስ አንቀጽ 1/ለ/ስር ተመልክቷል።የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 በአዋጅ ቁጥር 494/98 ተሻሽል አንቀጽ 39(1) ስር ተጨማሪ ሁኔታዎችን ያካተተ መሆኑ እና አሁን በስራ ላይ ያለዉ አዋጅ ቁጥር 1156/11 አንቀጽ 39/1/ለ/ ተመሳሳይ ይዖት ያለዉ መሆኑ ልብ ይለዋል።
ከእነዘህ ድንጋጌዎች ይዖት መገንዖብ የሚቻለዉ በአስሪዉ አነሳሽነት የተደረገዉ የስራ ዉል ማቋረጥ ከህግ አግባብ ዉጪ መሆኑ ከተረጋገጠ አስሪዉ የስራ ስንብት ክፍያ ለሰራተኛዉ የመክፈል ግዳታ ያለበት መሆኑን ነዉ።ስለዘህም ህገ ወጥ የሥራ ዉል መቋረጥን ተከትል የሚከፈል የስራ ስንብት ክፍያ ጋር ተይይዜ ላላ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ በህጉ አልተመለከተም።ይሁንና የስር ፍርድ ቤቶች የስንብት ክፍያ ለአመልካች አይገባዉም በማለት ዉሳኔ የሰጡት ይህ ሰበር ችልት በመ/ቁ/35197 ላይ የሰጠዉን የህግ ትርጉም በመመርኮዛ ስለመሆኑ ከዉሳኔዉ ይዖት መገንዖብ ይቻላል። የሰበር ችልቱ ዉሳኔ ይዖት የሚያሳየዉ ሰራተኛዉ ከዓምስት ዓመት ያላነሰ አገልግልት ኖሮት ነገር ግን ስራዉን በራሱ ፈቃድ ከለቀቀ እና የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ መሆኑ ከተረጋገጠ የስራ ስንብት ከፍያ በተደራቢነት ሉከፈለዉ አይገባም የሚል ነዉ።(ሰበር መ/ቁ/ 35197 ቅጽ 8 ይመለከቷል)።የሰበር ችልቱ ዉሳኔ መሰረት ያደረገዉ አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/ ሰ እና ሸ/ ድንጋጌ አተገባበር ላይ የተነሳ ክርክር ለመፍታት ያለመ ነዉ።በዘህ መዛገብ የቀረበዉ ጉዲይ ህገ ወጥ ስንብት ዉጤት የሚመለከት በመሆኑ ተጠቃሹ የሰበር ችልቱ ዉሳኔ ለተያዖዉ ጉዲይ አግባብነት የለዉም።
በመሆኑም አመልካች የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ነዉ በሚል ምክንያት የስራ ስንብት ክፍያ አይገባዉም የሚለዉ የተጠሪ ክርክርም ሆነ የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ የስራ ዉለ ከህግ አግባብ ዉጪ መቋረጡን ተከትል የሥራ ስንብት ክፍያ እንደሚከፍል በግልጽ የሚደነግገዉን የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 39/1/ለ/ ድንጋጌ ይዖት ያላገናዖበ ስለሆነ ሉታረም ይገባል ብለናል።
ሁለተኛዉ የአመልካች ቅሬታ ነጥብ የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን የሥር ፍርድ ቤቶች በዛምታ አልፈዉታል የሚል ነዉ።የሥር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ይዖት ሲታይ ለአመልካች የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ሉከፈለዉ እንደሚገባ ያሳያል።ነገር ግን መጠኑ ምን ያህል ነዉ የሚለዉን አጣርተዉ አሃዘን በግልጽ አላስቀመጡም።ይህ መሆኑ ደግሞ ለአፈጻጸም አስቸጋሪና በአፈጻጸም መዛገብ ላይ ላላ የፍሬ ነገር ክርክር እንዱደረግ የሚጋብዛ ስለሚሆን ስነ ስርዓታዊ አይደለም።ስለሆነም ፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያን አስመልክቶ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ በመጠን ረገድ ግልጽነት የላለዉ በመሆኑ ተገቢዉ ማጣራት ተደርጎ የማያሻማ ዉሳኔ ላሰጥበት ይገባል ብለናል።በዘሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/222095 ላይ 08/08/2012ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ/ በተጠሪ አነሳሽነት የተደረገዉ የሥራ ዉል ማቋረጥ ከህግ ዉጭ ነዉ ተብል ካሳ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዚ እና ፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ለአመልካች እንዱከፈል በስር ፍርድ ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔ ጸንቷል።በተጨማሪም ተጠሪ የስንብት ክፍያ ለአመልካች ሉክፍለዉ ይገባል ብለናል።
3ኛ/የስንብት እና የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ መጠን በተመለከተ ተገቢዉን ማጣራት አድርጎ ዉሳኔ እንዱሰጥ በማለት መዛገቡን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 343/1/ መሰረት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መልሰናል።ይጻፍ።
4ኛ/በዘህ ሰበር ሰሚ ችልት የተደረገው ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል ይመለስ።
No topics extracted.