No summary available.
የሰ.መ.
የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው ሐብታሙ እርቅ ይሁን ብርሃኑ መንግስቱ አመልካች፡- አቶ ሳምሶን ተሾመ - ጠበቃ አድነው አቡሼ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፍትሕ ሚኒስቴር ዓቃቤሕግ - አልቀረቡም መዛገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ሐምል 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም በአመልካች ላይ ያስተላለፈው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
ጉዲዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው።
የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች እና በስር 2ኛ ተከሳሽ ላይ ያቀረበው ክስ ይዖት በአጭሩ፡ተከሳሾች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 692(1) ድንጋጌን በመተላለፍ የማይገባ ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በቀን 24/11/2013 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ሲሆን በአራዲ ክፍለከተማ ወረዲ 01 ልዩ ቦታው አምባሳደር አካባቢ የግል ተበዲይ ዖሪሁን ገረሱን አመልካች ኢንቨስትመንት አብረን እንሰራለን የላስቲክ ወንበሮች እና ባቄላ አሽገን ወደ ውጪ እንልካለን ድላር እናባዙለን በማለት አሳሳች ነገር በመናገር 2ኛ ተከሳሽ ጥሬ ገንዖብ ብር 556,320 እና 3,500 የአሜሪካ ድላር በኢትዮጲያ ሲመነዖር ብር 159,600 በአጠቃላይ ብር 715,920 የወሰደበት በመሆኑ በዋና ወንጀል አድርጊነት ተካፊይ በመሆን በፈጸሙት የማታለል ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
ተከሳሾች ክሱ ተነቦላቸው እንዱረደት ከተደረገ በኋላ መቃወሚያ አቅርበው ውድቅ የተደረገ ሲሆን የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ሲጠየቁ ድርጊቱን አልፈጸምንም ብለው ክደው በመከራከራቸው ፍርድ ቤቱ የዓቃቤሕግን ማስረጃ ከሰማ በኋላ ክሱን እንዱከላከለ ሲል ብይን ሰጥቷል። አመልካችም በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 143/2 መሰረት ቃለን የሰጠ ሲሆን የመከላከያ ማስረጃውን አስቀርቦ አሰምቷል። ፍርድ ቤቱም በመቀጠል የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ በአመልካች የቀረበው መከላከያ ማስረጃ በዓቃቤሕግ በኩል የቀረበውን ማስረጃ ጥርጣሬ ላይ የሚጥል አይደለም በማለት በተከሰሰበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 692(1) ድንጋጌ መሰረት ጥፊተኛ በማለት ቅጣቱን አስልቶ በሁለት ዓመት ከሶስት ወር ጽኑ እሥራት እና በብር 6,000 / ስድስት ሺህ የገንዖብ መቀጮ እንዱቀጣ ሲል ወስኗል። አመልካች ቅጣቱ እንዱገደብ ያቀረበውን ጥያቄ በሚመለከት ደግሞ ከወንጀለ አደገኝነት አኳያ አስተማሪነት ስለላላው ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች ይህን ወሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ ተቀባይነት አላገኘም።
አመልካች ሐምል 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ይህን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ ሲሆን ይዖቱም፡- አመልካች ገንዖቡን እንዲልተቀበልኩ ተረጋግጧል፤ ባንኮቹ በደረሳቸው ትዔዙዛ የግል ተበዲይ ምንም ዓይነት ድላር እንዲላወጣ ለፍርድ ቤቱ አረጋግጠዋል፤ አመልካች የተከሰስኩት ባልተፈጸመ ወንጀል እና ባልፈጸምኩት ድርጊት ነው፤ አመልካችን ጥፊተኛ ለማስባል በተከሰስኩበት ሕግ እና በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 ላይ የተቀመጠው የሕጉ መስፈርት አልተሟላም፤ በምክንያት እና ውጤት መካከልም ግንኙነት የለም፤ አመልካች ቅጣት ለመገደብ የሚያስችለ ሁኔታዎችን ያሟላሁ በመሆኑ ቅጣቱ ሉገደብ ይገባ ነበር፤ ስለሆነም እነኚህ ሁኔታዎች ታልፈው በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የተላለፈው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ አግባብነት ከማስረጃ ምዖና መርህ አንጻር እና ላልች ተያይዣ ነጥቦችን ለማጣራት የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዛ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ጉዲዩ ለዘህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው መልስ ይዖት በአጭሩ፡- በስር ፍርድ ቤት የተፈጠረ የሕግ አተረጓጎም ስሕተት የለም፤ አመልካች የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸሙ በዓቃቤሕግ ማስረጃ በሚገባ ተረጋግጧል፤ አመልካች በክሱ የተጠቀሰውን ገንዖብ ራሱ ባይቀበልም ከተጠያቂነት ነጻ አያደርገውም፤ የዓቃቤሕግ ክስ አመልካች የኢንቨስትመንት ስራ እንሰራለን ወንበር እና ባቄላ አሽገን ወደ ውጪ እንልካለን ድላር እናባዙለን በሚል የግል ተበዲይን ሲያታልል ላላኘው ግብረአበሩ ገንዖቡን ተቀብል ተሰውሯል የሚል ነው፤ የግል ተበዲይ ገንዖቡን በሕገወጥ መንገድ ይዖዋል የሚባል ከሆነ በልላ ራሱን በቻለ ሕግ የሚታይ እንጂ ገንዖቡ ከባንክ ስለመውጣቱ አልተረጋጠም የሚል መከራከሪያ ላቀርብ አይገባም፤ የአመልካች ግብረአበር ገንዖቡን ከግል ተበዲይ ተቀብል የወሰደ በመሆኑ የግል ተበዲይ ላይ ጉዲት አልደረሰም ማለት አይቻልም፤ አመልካች ድርጊቱን የፈጸመው የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ነው፤ የግል ተበዲይም በአመልካች ድርጊት ምክንያት የራሳቸውን ጥቅም የሚጎዲ ድርጊት አድርገዋል፤ አመልካች ቅጣቱን ለማስገደብ የሚችለ ቅድም ሁኔታዎች አሟልተው አላቀረቡም፤ ስለሆነም የገደብ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው የሚል ነው።
No topics extracted.
አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዖውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ዓቃቤሕግ በስር ፍርድ ቤት ክስ ያቀረበው አመልካች እና የስር 2ኛ ተከሳሽ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተሳታፉ በመሆን የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 692(1) ድንጋጌን ተላልፈው የማይገባ ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በግል ተበዲይ ላይ የማታለል ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነው። በዘሁ ክስ ላይም የአመልካች ተሳትፍ ለግል ተበዲዩ ኢንቨስትመንት አብረን እንሰራለን የላስቲክ ወንበሮች እና ባቄላ አሽገን ወደ ውጪ እንልካለን ድላር እናባዙለን በማለት አሳሳች ነገር በመንገር የግል ተባዲዩ ለስር 2ኛው ተከሳሽ በክሱ የተመለከተውን የገንዖብ መጠን እንዱሰጡ ማድረግ ስለመሆኑ በግልጽ ተጠቅሷል። ይህም የግል ተበዲዩ በአመልካች ድርጊት ምክንያት ገንዖቡን ሉሰጡ የቻለ መሆኑን ወንጀለ በአመልካች እና በስር 2ኛ ተከሳሽ ተሳትፍ የተፈጸመ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ስለሆነም አመልካች በክሱ የተገለጸውን ገንዖብ ስላልተቀበልኩ ጥፊተኛ ልባል አይገባም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም። በልላ በኩል ዓቃቤሕግ አመልካች ድላር እናባዙለን በማለት አሳሳች ነገር በመናገር የግል ተበዲዩ 3,500 የአሜሪካ ድላር በኢትዮጲያ ሲመነዖር ብር 159,600 ለስር 2ኛ ተከሳሽ ሰጥተዋል በማለት የገለጸውን ፍሬነገር መሰረት በማድረግ አመልካች ጥፊተኛ የመባለን አግባብነት እንደሚከተለው መርምረናል።
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 692/1 ማንም ሰው የማይገባ ብልጽግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የላላውን ሰው የተሳሳተ እምነት ወይም ግምት በመጠቀም በማድረግም ሆነ ባለማድረግ ላላውን ሰው አታል የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገንን የንብረት ጥቅም የሚጎዲ አድራጎት እንዱፈጽም ያደረገው እንደሆነ በድንጋጌው የተመለከተውን ቅጣት ይቀጣል በማለት ይደነግጋል። ከድንጋጌው ይዖት በግልጽ መገንዖብ እንደሚቻለው የማታለል ወንጀለ የሚፈጸምበት ሰው የማታለል ተግባሩን የሚፈጽመው ሰው በፈጸመው የማታለል ተግባር ምክንያት የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገንን የንብረት ጥቅም የሚጎዲ አድራጎት የሚፈጽም ከሆነ የማታለል ተግባሩን የፈጸመው ሰው ለድርጊቱ ተጠያቂ የሚሆን መሆኑን ነው። ከዘህ ውጪ የማታለል ድርጊቱ ተፈጽሞብኛል የሚለው ሰው አብሮ የወንጀለ ፍሬ ተጠቃሚ ለመሆን የተስማማ ከሆነ የማታለል ተግባር ተፈጽሞብኛል ለማለት አይችልም።
በያዛነው ጉዲይ ድላሩን በሚመለከት አመልካች ፈጸሙት የተባለው ተግባር ድላር እናባዙለን በማለት የግል ተበዲዩ ድላሩን ለስር 2ኛ ተከሳሽ እንዱሰጡ አድርገዋል የሚል ነው። ይህም የግል ተበዲዩ ድላሩ ተባዛቶ ሲመጣ አብረው ከወንጀለ ፍሬ ለመጠቀም ያቀደ መሆናቸውን የሚያሳይ እንጂ በአመልካች ድርጊት ምክንያት ተታለው ድላሩን የሰጡ መሆኑን የሚያሳይ አይደለም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች በፈጸሙት የማታለል ድርጊት ምክንያት የግል ተበዲይ 3,500 የአሜሪካ ድላር በኢትዮጲያ ሲመነዖር ብር 159,600 ለስር 2ኛ ተከሳሽ ሰጥተዋል በማለት የሰጡት የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም አመልካች በወንጀል ሕጉን አንቀጽ 692(1) ድንጋጌን መሰረት ጥፊተኛ ልባል የሚገባው ኢንቨስትመንት አብረን እንሰራለን የላስቲክ ወንበሮች እና ባቄላ አሽገን ወደ ውጪ እንልካለን በሚል ያልሆነውን ነኝ በማለት የራሱን ሁኔታ በመሰወር እና ማንነቱን እና ስራውን በመደበቅ ነጋዳ መስል ለስራ በሚል ከግል ተበዲይ ላይ ጥሬ ገንዖብ ብር 556,320 ወስደዋል በሚለው ብቻ ላሆን ይገባል።
አመልካች የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ጥፊተኛ የተባለበት የገንዖብ መጠን በዘህ ችልት የተለወጠ ቢሆንም በቅጣት አወሳሰን መመሪያው ላይ የወንጀል ደረጃውን የማይለውጠው በመሆኑ ቅጣቱን በድጋሚ ማስላት አላስፈለገም። በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
1.የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም በአመልካች ላይ ያስተላለፈው የጥፊተኝነት ውሳኔ፤ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሎል።
2.ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተለገጸው ምክንያት አመልካች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 692(1) ድንጋጌን በመተላለፍ አሳሳች ነገሮችን በመናገር የግል ተበዲይን አታል 3,,500 የአሜሪካ ድላር በኢትዮጲያ ሲመነዖር ብር 159,600 ለስር 2ኛ ተከሳሽ እንዱሰጡ አድርጓል በማለት በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
3.አመልካች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 692(1) ድንጋጌን መሰረት ጥፊተኛ ልባል የሚገባው ኢንቨስትመንት አብረን እንሰራለን የላስቲክ ወንበሮች እና ባቄላ አሽገን ወደ ውጪ እንልካለን በሚል ያልሆነውን ነኝ በማለት የራሱን ሁኔታ በመሰወር እና ማንነቱን እና ስራውን በመደበቅ ነጋዳ መስል ለስራ በሚል ከግል ተበዲይ ላይ ጥሬ ገንዖብ ብር 556,320 ወስደዋል በሚለው ብቻ ነው በማለት ወስነናል።