No summary available.
ቀን 29/07/2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተፈሪ ገብሩ ቀነዓ ቂጣታ አይሸሽም መለስ ጸሐይ መንክር አመልካች፡- ኮልኔል ዓለም ትኩዔ -ቤተሰብ ወንድወሰን ተፈራ ቀረቡ ተጠሪ፡- የምእራብ እዛ ወታደራዊ ዓቃቤ ሕግ ሻንበል ፊንታ ሳላ ቀረቡ መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች ወታደራዊ ማዔረግ “ኮልኔል” ሆኖ እያለ በዲኝነት የተሰየሙት መኮነኖች ከአመልካች ጋር ቢያንስ አቻ ማዔረግ ያላቸው መሆን ሲገባቸው፣ አመልካች የተከሰሱበት ወንጀል ከአምስት ባላነሱ ዳኞች፣ ላታይ ይገባው የነበረ መሆኑንና አለመሆኑን በሰበር ችልት አጣርቶ ለመወሰን የሚል ጭብጥ ተመስርቶ ነው። ቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት ሚያዘያ 27 ቀን 2007 ዓ.ም ፍርድ የሰጠው፣ የዳኞችን ስምና ማዔረግ ሳይሰይም ዳኞች “አልተለወጡም” በማለት በመሆኑ፣ የአመልካችን ጉዲይ በዲኝነት አይተው ፍርድ የሰጡትን ዳኞች ስም፣ ማዔረግና ጉዲዩን ለማየት በዲኝነት የተሰየሙትን ዳኞች ቁጥር ለማረጋገጥ፣ የቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት የመዛገብ ቁጥር 268/07 በትእዙዛ በማስቀረብ ተመልክተናል።
ይህ የሰበር ችልት በትእዙዛ ካስቀረበው የቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት የመዛገብ ቁጥር 268/2007 እንደተረዲነው የአመልካች ጉዲይ የታየው ሶስት ዳኞች በተሰየሙበት የቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት ችልት መሆኑንና ጉዲዩን በዲኝነት ካዩት ውስጥ ሰብሳቢው ዲኛ የኮልኔል ማዔረግ ያላቸው፣ ላልች ሁለት ዳኞች ደግሞ የሻንበል ማዔረግ ያላቸው መሆኑን ተረድተናል። የአመልካችን ጉዲይ ያለው ቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት ችልት የዲኞቹን ማዔረግ፣ ሙለ ስም በፍርደ ላይ አለመግለጹ የፍርድ አጻጻፍ ስህተት ያለበት መሆኑን ያሳያል። በልላ በኩል ከተያዖው ጭብጥ አንጻር ስንመለከተው፣ አመልካች በወንጀል ተጠርጥሮ የተያዖው የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑንና የአመልካች ጉዲይ ለቀዲሚው ወታደራዊ ፍ/ቤት ተጠሪ የወንጀል ክስ ያቀረበው የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑን በትእዙዛ ካስቀረብነው መዛገብ ተረድተናል።
ይህም የአመልካች ጉዲይ በቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት በሚታይበት ጊዚ፣ የሰበር አጣሪ ችልት ጭብጥ ለመያዛ መሰረት ያደረጋቸው አዋጅ ቁጥር 27/1988 ፣ በአዋጅ ቁጥር 123/90 እና በአዋጅ ቁጥር 343/95 እንደተሻሻለ ከታህሳስ 24 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በነጋሪት ጋዚጣ ታትሞ ስራ ላይ በዋለው በአዋጅ ቁጥር 809/2006 በአንቀጽ 74 ንዐስ አንቀጽ 1 ሙለ በሙለ የተሻሩ መሆኑን ተረድተናል። ከዘህ አንጻር ሲታይ በአዋጅ ቁጥር 809/2006 አንቀጽ 45 ከአምስት አመት በታች በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሳሽ ሰው አንድ ዲኛ በሚሰይምበት ችልት ከአምስት አመት በላይ በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሰሰ ሰው ሶስት ዳኞች በሚሰየሙበት ችልት የሚታይ መሆኑ በንዐስ አንቀጽ 1 እና በንዐስ አንቀጽ 2 በግልጽ ተደንግጓል። የዳኞችን ማዔረግ በተመለከተም በቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት ከሚሰየሙ ዳኞች መካከል ቢያንስ ሰብሳቢው ዲኛ በወንጀል ተጠርጥሮ ከተከሰሰው ሰው የበለጠ ወይም አቻ ማእረግ ሉኖረው የሚገባ መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 809/2006 አንቀጽ 45 ንዐስ አንቀጽ 7 በግልጽ ተደንግጓል።
አመልካች በወንጀል ተጠርጥሮ በተከሰበት ጊዚ፣ አዋጅ ቁጥር 27/88 በአዋጅ ቁጥር 123/90 እና በአዋጅ ቁጥር 343/95 እንደተሻሻለ ሙለ በሙለ ተሽሯል። አመልካች ጉዲዩ ሲታይ የተሻሩና ተፈጻሚነት የላላቸውን አዋጆች መሰረት በማድረግ የቀረበው የሰበር አቤቱታ የሕግ መሰረት እና ድጋፍ የለውም። የአመልካች ጉዲይ የታየው ከታህሳስ 24 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ በዋለው አዋጅ ቁጥር 809/2006 አንቀጽ 45 ንዐስ አንቀጽ 2 በተደነገገው መሰረት ሶስት ዳኞች በተሰየሙበት ቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት መሆኑንና በዲኝነት የተሰየሙት ሶስት ዳኞች ውስጥ ሰብሳቢው ዲኛ የአዋጅ ቁጥር 809/2006 አንቀጽ 45 ንዐስ አንቀጽ 7 በሚደነግገው መሰረት ከአመልካች ጋር አቻ የሆነ “የኮልኔል” ማዔረግ ያላቸው መሆኑን አረጋግጠናል። በመሆኑም የአመልካች ጉዲይ በወቅቱ ስራ ላይ የነበረውን የአዋጅ ቁጥር 809/2006 በሚደነግገው መሰረታዊ የሆኑ የዳኞች ቁጥርና ማዔረግ ተሟልቶ በመሆኑ አመልካች የሕጉን መስፈርት በማያሟላ ችልት ታይቶ የተሰጠው ፍርድ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታና የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
የሰበር አጣሪ ችልት አመልካችን ጉዲይ ለዘህ ሰበር ችልት ሲያቀርብ ከመሰረተው ጭብጥ አንጻር፣ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ፣ የአመልካች ጉዲይ በታየበት ወቅት ስራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 809/2006 ድንጋጌዎች ያላገናዖበ በመሆኑ ውድቅ ተደርጓል። በማስከተል መታየት ያለበት የቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ያስተላለፈት የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ ተገቢነት ያለው መሆኑ ወይም አለመሆኑ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች የተሰጠባቸውን የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታው ያቀረበ ሲሆን ተጠሪ በፍርድ ቤቱ መልእክት ክፍል መጥሪያ ደርሶት መልሱን ባለማቅረቡ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
አመልካች በወታደራዊ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበበት አራት የወንጀል ክሶች የተገለጹትን የወንጀል ድርጊቶች ማለት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ አንቀጽ 306/3/ የተመለከተውን በመተላለፍ በጥር ወር 2007 ዓ.ም አስራ አምስት ጥይት ለቤንሻንጉል ጉሙዛ ክልል ጸጥታ ሃይል ድጋፍ እናደርጋለን ብለው ወስደው ማጥፊታቸው፣ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 306/1/ የተመለከተውን በመተላለፍ አንድ ክላሽ ጠመንጃ ከሰላሳ ጥይትና ከአንድ ካዛና ጋር መውሰደና በ 2006 ዓ.ም በወንጀል ሕግ ቁጥር 306/3/ የተመለከተውን በመተላለፍ አስራ አምስት ሺ ጥይት ወስድ ማጥፊቱና የተጠሪን የሰውና የጽሐፍ ማስረጃ የሰማውና የመረመረው የቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት በማረጋገጥ፣ አመልካች የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ ብይን ሰጥቶ፣ አመልካች የመከላከያ ማስረጃ አሰምቷል። የአመልካች ማስረጃ የተጠሪን ማስረጃ ለማስተባበል የማይችል ተዓማኒነትና ክብደት የላለው በመሆኑ አመልካች ከላይ የተገለጹትን ወንጀልች የፈጸመ ጥፊተኛ ነው በማለት ቀዲሚ ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ በሕግ የተሰጠውን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዖን ስልጣን መሰረት በማድረግ ወስኗል።
ቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት የደረሰበት የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዖና መደምደሚያ ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ ወታደራዊ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በትእዙዛ አጽንቶታል። ይኸ ሰበር ችልት ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ በመመዖን ሂደት የተፈጸመ ስህተት መኖሩን ወይም አለመኖሩን የማጣራትና በሰበር አይቶ የማረም ስልጣን የለውም።
በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 አልተሰጠውም። በመሆኑም አመልካች ያለበቂ ማስረጃ ጥፊተኛ መባላ ተገቢ አይደለም በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የሕግ መሰረት እና ድጋፍ የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
አመልካች ቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሰጡትን የጥፊተኛነት ውሳኔ በመቃወም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ውድቅ ከተደረገ በማስከተል መታየት ያለበት በአመልካች ላይ የተወሰነው የቅጣት ውሳኔ ተገቢነት ያለው መሆኑ ነው። ቀዲሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ የቅጣት ውሳኔ የወሰነው አመልካች በወንጀል ሕግ 306/3/ ጥፊተኛ የተባለባቸውን ሁለት ወንጀልች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 61/2/ መሰረት በአንድ በማጠቃለል፣ ወንጀለ ከባድ /ከፍተኛ/ ደረጃ በመመደብና መነሻ አስራ ስድስት ዓመት ጽኑ እስራት ይዝል።
አመልካች በወንጀል ህግ 306 (1) ጥፊተኛ ለተባለበትን ወንጀል ደረጃው ከፍተኛ ነው በማለት አምስት ዓመት ጽኑ እስራት መነሻ ቅጣትነት ይዜ በመደመር 21 ዓመት ጽኑ እስራት መነሻ ቅጣት እድርጎ ይዝል ይህም በመመሪያ ቁጥር 2/2006 በእርከን 36 ላይ የሚያርፍ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ተጠሪ ካቀረባቸው የቅጣት ማክበጃዎች ውስጥ ሁለት የቅጣት ማክበጃ የሚቀበል ቅጣቱ እርከን ስልሣ ስምንት ላይ አሳርፍታል። ከዘህ በኋላ አመልካች ካቀረባቸው የቅጣት ማቅለያ ምክንያት አራት የቅጣት ማቅለያዎችን በመቀበል ለእያንዲንደ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት አንድ እርከን በመቀነስ እርከን 34 ላይ አሳርፍታል። የቀዲሚ ወታደራዊ ፍርድ ቤት አመልካች በእርከን 34 በተመለከተው ከፍተኛው ቅጣት በአስራ ስምንት ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል። የወታደራዊ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የቅጣት ውሳኔ አጽንቶታል።
አመልካች ቀዲሚ ወታደራዊ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማድረግ የቅጣት ውሳኔውን አክብደው መወሰናቸው በተለይም መመሪያው ሉያዛልኝ የሚገቡ የማቅለያ ምክንያቶችን ውድቅ በማድረግ የሰጡቱት የቅጣት ውሳኔ ስህተት ስላለበት በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። በእኛ በኩል አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ (ሀ) የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያወጣቸው መመሪያ ቁጥር 1/2002 እና መመሪያ ቁጥር 2/2006 አሁን ባለበት ሁኔታ ለወታደራዊ ወንጀልች ተፈፃሚ ማድረጉ የወንጀል ህጉንና የቅጣት አወሳሰን መሰረታዊ ዓላማ ሉያሳጣ የሚችል ነው ወይስ አይደለም?
(ለ) የቅጣት አወሳሰን መመሪያዎቹ አሁን ባለበት ሁኔታ በወታደራዊ ወንጀልች ላይ ተፈፃሚ ማድረግ ምን ውጤት ይኖረዋል?
(ሐ) ለወታደራዊ ወንጀልች መሰረታዊ ባህሪ በወንጀልች የሚፈፀሙበትን ሁኔታ ጊዚና ወንጀልቹ የሚፈፅሙበትን ምክንያት ያስከተለትን ወይም ሉያስከትል የሚችለትን ጉዲት ያገናዖበ የወታደራዊ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ማውጣት ይገባዋል ወይስ አይገባውም ? መመሪያ ሉወጣ ይገባል ከተባለ መመሪያው እስከሚወጣ ወታደራዊ ወንጀልችን የመዲኘት ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ የሚሰጡት በምን ሁኔታ ነው የሚለትን የህግ ጭብጦች መመርመርና ማየት አስፈላጊ ሆኖ አግንተነዋል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወንጀል ህጉና በላልች ህጎች የወንጀል ቅጣት ህግ አውጭው የደነገገባቸው ወንጀልች በመፈፀሙ ሰዎች ላይ ፍርድ ቤቶች የሚወስኑትን የቅጣት ውሳኔ ትክክለኛነትና አንድ ወጥነት ለማረጋገጥ እንዱቻል የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ እንደሚያወጣ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 88 ንዐስ አንቀጽ 4 “የቅጣት አወሳሰን ትክክለኛነትና አንድ ወጥነት ለማረጋገጥ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ manual ይወጣል በማለት በግልጽ የደነገገ ሲሆን የወንጀል ህጉ አንቀጽ 88 ንዐስ አንቀጽ 4 የእንግሉዘኛው ቅጅ `in order to insure correctness and uniformly of sentencing the federal supreme court show issue manual relating sentencing በማለት ደንግጓል።
ይህም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ የማውጣት ስልጣን ከህግ አውጭው በግልጽ ድንጋጌ የተሰጠው በመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወታደራዊ ወንጀልች ላይ ቅጣት ስለሚወሰንበት ሁኔታና አሰራር የቅጣን ማክበጃና ማቅለያ ሁኔታዎች ደረጃ አመጣጥ ስርዓትና የቅጣት እርከንና ሬንጅ የሚደነግግ የቅጣት አወሳስን መመሪያ ለወታደራዊ ወንጀልች በቂ ዔውቀትን ክህልት ካለቸው ወታደራዊ ባስልጣናትና ባለሙያዎች ጋር በመመካከር አውጥቶ ስራ ላይ እንዱውል የማድረግ ስልጣን ያለው መሆኑን የሚያሳይ ነው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወንጀል ህግ አንቀጽ 88 ንዐስ አንቀጽ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለወታደራዊ ወንጀልች የሚያገለግል የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ማውጣት የሚችል መሆኑ የሚያከራክር ነጥብ አይደለም። አከራካሪ የሚሆነው የፋዳራል ፍርድ ቤት በወንጀል ህግ አንቀፅ 88 ንዐስ አንቀጽ 4 የተሰጠውን መሰረት በማድረግ የወጣውን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 እና መመሪያ ቁጥር 2/2006 በወታደራዊ ወንጀልች ላይ ቅጣት ለመወሰን ጥቅም ላይ ቢውለ የህግን መሰረታዊ ዓላማ ለማሰካት ያስችላለ ወይስ አያስችለም የሚለው ነው 12 የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አውጥቶ ስራ እንደውለ ያደረጋቸው መመሪያ ቁጥር 1/2002 እና መመሪያ ቁጥር 2/2006 በመመሪያው ደረጃ ያልወጣላቸው ወንጀልች ደረጃ ለማውጣት የሚያገለግለ ጠቅላላ ይዖት ያላቸው ደንቦችንና በመመሪያዎች ደረጃ የወጣላቸውን ውስን የወንጀል አይነቶች ላይ ፍርድ ቤቶች ቅጣት ሲወስን ሉከተለት የሚገባውን ስርዓት የሚደነግግ ይዖት ያላቸው ናቸው መመሪያዎቹ የወጡት በወንጀል ህጉና በላልች የወንጀል ቅጣት በሚደነግጉ የህግ ማዔቀፍችን በመተላለፍ የሚፈጸሙ ወንጀልች ደረጃ አወጣጥ የቅጣት እርከን የቅጣት ማቅላይ ምክንያትና የቅጣን ማክበጃ ምክንያቶች አያያዛ ጠቅላላ በሆነ መንገድ ለመመዖንና የቅጣት አወሳሰን ስርዓቱን ለመዖርጋት ነው።
የወጡት መመሪያዎች በአገሪቱ ውስጥ የሚፈፀሙ ሁለም አይነት ወንጀልች ላይ ተፈፃሚ እንዱሆነው የተቀረጸ በመሆናቸው የአገር መከላከያ ሰራዊት ስኬታማነት ጥብቅ የስነ ስርዓትና የዱስፕሉን ልቅና ለማረጋገጥ ታልመውና በወታደራዊ አገልግልት ሑደት ወታደሮችና የጦር መኮንኖች እንደፈፅም በህጉና አግባብነት ባለው አካል የታዖዘበትን ባለመፈፀሙ ወይም እንዲይፈፅም የተከለከለውን ተግባር ፈፅሞ በመገናኘታቸው ወታደሮች በህጉ ኃላፉ ናቸው የተባለ ላልች ሰዎች በወንጀል ተጠያቂ የሆኑባቸውን ወታደራዊ ወንጀልችና ወታደራዊ ወንጀልቹ ዛርዛር ይዖትና ወንጀልች የሚያስከትለትን ቅጣት በልዩ ሁኔታ ህግ አውጭው በወንጀል ህጉ በክፍል ሶስት ከአንቀጽ 293 እስከ አንቀጽ 339 በዛርዛር ደንግጓል።
እነዘህ ህግ አውጭው በልዩ ሁኔታ የደነገጋቸው የወታደራዊ ወንጀልች ድንጋጌዎች ማናቸውም ወታደር ወይም የጦር መኮንን ሆነ ብል ወይም በቸልተኝነት የሚፈፅማቸው የወንጀል አይነቶች የወንጆልቹን መሰረታዊ ይዖትና ባህሪያ በወንጀልች ወታደሩ ወይም የጦር መኮንኑ የፈፀሙበት ምክንያት ወንጀልች በጦርነት ቀጠና ወይም በሰላም ቀጠና የተፈፀሙ መሆኑን ወንጀልቹ በጦርነት ቀጠና ወይም በሰላም ቀጠና የተፈፀሙ መሆኑን ወንጀልቹ የወገን ጦር በጦርነት ላይ እያለ ወይም በሰላማዊ ጊዚ የተፈፀሙ መሆናቸውን ወንጀለ በወገን ጦር ግዲጅ አፈፃፀም ላይ ያስከተለውን ጉዲት ወይም በልላ መንገድ ባይታራምና ባይሽፈን ኖሮ በወገን ጦር ላይ ሉያስከትል ይችል የነበረውን ጉዲት በማመዙዖን ቅጣቱን አክብድ ወይም አቅልል መወሰንን የሚጠይቁ ናቸው።
15 ይህም ወታደራዊ ወንጀልች በመሰረታዊ ይዖታቸው ተመሣሣይ ቢሆንም በባህሪያቸው ተለዋዋጭነት ያላቸውና እንደ ወንጀልች አፈፃፀም ባህሪና ሁኔታ እየመዖነ የተለያያ መጠን ያላቸውን የወንጀል ቅጣቶችን መወሰን የሚጠይቁና ይህንንም ለማድረግ እንድችለ ለወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች ሰፉ ፈቀደ ስልጣን መስጠትን የሚጠይቁ ናቸው። ይህም ማለት ተመሳሳይ ቁጥር ያለው ጥይት ወይም መሣሪያ እንደጣፊ ወይም እንዱባክን በማድረግ ወንጀል የፈፀሙ አቻ ማዔረግ ያላቸው የጦር መኮንኖች እንደጠፊ ወይም እንዱባክን ያደረጉት ንብረት ዋጋ እኩልና ተመጣጣኝ ቢሆኑም ወንጀለን በፈፀሙት ምክንያት ሁኔታ በመለያያቱ ምክንያት ብቻ የተለያያ የወንጀል ቅጣት ሉጣልባቸው የሚችል መሆኑን የሚያመለክት ነው። ይህም ማለት አንደኛ የጦር መኮንን ጥይትና መሣሪያ የማባከን ወንጀል የፈፀመው በቁጥጥርና ክትትል ችግር ወይም የወገን ጦር እንደጎዲ አስቦ አለመሆኑና ከጠላት ጦር ጋር ምንም አይነት ሚስጥራዊ ግንኝነት ያላለው መሆኑ ቢረጋገጥና ተመሣሣይ ወንጀል የፈፀመው አቻ ባለማዔረግ መኮንኑ ጥይቱ ወይም መሣሪያው እንደጠፈ ያደረገው የወገን ጦር የትጥቅ ችግር እንዱገጥመውና ለጠላት ጥቃት ተጋላጭ አድርጎ ለመቆየት በማሰብ ከጠላት ጋር ሚስጥራዊ ግንኝነት በማድረግና የወገን ጦር በቂ ጥይትና መሣሪያ እንዲይደርሳውና ጉዲት እንዱደርሰበት በማሰብ ይህንንም ሆንብልና አቅድ የፈጸመው መሆኑ ቢረጋገጥ የቅጣት ውሳኔ ወጥነት ለማረጋገጥ ሲባል በሁለቱ አቻ ማዔረግ ባለቸው የጦር መኮንኖች ላይ ሉወሰን የሚገባው እኩልና አንድ አይነት ቅጣት ላሆን አይገባም። ከዘህ አንፃር የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አውጥቶ ስራ ላይ የዋለቸው የቅጣት አወሳሰን መመሪያዎች፣ ወንጀል የሰሩትን የጦር መኮንኖች ማዔረግ፣ ጥፊተኛ የተባለበትን የህግ ድንጋጌ፣ በወንጀል ድርጊት የጠፊውን የመንግስት ሀብት መጠን በጥቅለ በማየት የወንጀል ደረጃ እንዱወጣና የማቅሉያና ማክበጃ ሁኔታዎች ታይተው ያለውን የወንጀል ቅጣት እርከን መሰረት በማድረግ ቅጣት እንዱወሰን የሚደነገጉ በመሆናቸው ከላይ የገለጽናቸውን የወታደራዊ ወንጀልች አፈፃጸም ስልት ልዩ ባህሪ፣ ምክንያትና ላልች ሁኔታዎችን በዛርዛር መርምሮና መዛኖ ቅጣት ለመወሰን በሚያገለግለበት አግባብ ታስቦባቸው የተቀረጹ አይደለም።
በወታደራዊ ወንጀልች የቅጣት ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት፣ ሁለት ተመሳሳይ የሆነ ወንጀል በፈጸሙ ወታደሮች ወይም የጦር መኮንኖች ላይ የተለያየና ከፍተኛ ልዩነት ያላቸው የቅጣት ውሳኔዎች እንዱሰጡ የወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞችን የሚያስገድዶቸው በርካታ ክስተቶችና ነባራዊ ነገሮች ያጋጥማለ። ይህም ማለት ከፍያለ ገንዖብ የሚያወጣ ስንቅ የመስረቅ ወንጀል በሰላም ቀጣና ውስጥ የፈጸምን አንድ ወታደርና የወገን ጦር በአስቸጋሪ ሁኔታና በስንቅ እጥረት ውስጥ በሚገኝበት ሁኔታ ዋጋው ዛቅተኛ የሆነ ስንቅ የመስረቅ ወንጀል የፈጸመ ወታደር ጥፊተኛነታቸው ከተረጋገጠ በኃላ የወገን ጠሪ በአስቸጋሪ ሁኔታና በስንቅ እጥረት ላይ በሚገኝበት ጊዚ፣ ከነበረው ውስን ስንቅ ዛቅተኛ መጠን ያለውን በሰረቀው የወገን ጦር ላይ ከፍተኛ ችግር ወታደር ላይ ከፍተኛ ችግር በፈጠረው ላይ ከፍ ባለቅጣት እንዱቀጣ ውሳኔ መስጠት የሚያስገድድ ሁኔታዎች የመኖሩ መሆኑን ከግምት ውስጥ የሚያስገባ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ካልወጣ በስተቀር አሁን ስራ ላይ ባለት መመሪያዎች ይህንን መሰረታዊ አላማ ለማሳካት የሚቻል አይደለም።
ከላይ የገለጽናቸው ሁኔታዎች የሚያሳዩት ወታደራዊ ወንጀልቹን ለመዲኘት ላይ የሚገኙ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ጥፊተኛው የፈጸመውን ወንጀል ይዖት፣ የወንጀል አፈፃጸም ስልትና የወንጀለን ባህሪ፣ ወንጀለን የፈጸመበትን ጊዚ ወንጀለን የፈጸመበት ስፍራ ወንጀለን ሁኔታ፣ ወንጀለን ለመፈጸም ያነሳሳውን ምክንያት የፈጸመው ወንጀል በወገን ጦር ላይ ያስከተለው ጉዲት ወይም ክትትል የነበረውን ጉዲት በክርክር በመመርመርና በመመዖን ቅጣቱን አክብደው ወይም አቅልለው ለመወሰን የሚያስችል ሰፉ ፈቃድ ስልጣን ካልተሰጣቸው የወንጀል ህጉ ወታደራዊ ወንጀልቹን በልዩ ሁኔታ ያደረገበትንና መሰረታዊ ዓላማና ወንጀልች ሲፈጽም ጥፊተኛውም ሆነ ላላው የመከላኪያ ኃይል ተሰማርተውበት ከነበረው ወታደራዊ ግዲጅ ልዩ ባህሪና አስቸጋሪ ሁኔታ ጋር በሚጣጣም መንገድ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት አይችለም።
በመሆኑም ስለወታደራዊ አገልግልትና ወታደራዊ አገልግልትና ወታደራዊ ግዲጅ አፈፃጸም ሂደት ወንጀልች ፈጽመው ስለሚችልበት ምክንያት የወንጀል አፈፃጸም ባህሪ፣ የወታደራዊ ወንጀልች አፈፃጸም ስልት፣ ወንጀለ የተፈጸመበት ጊዚና ስፍራ እንደዘሁም ሁኔታ እንዱሁም የተፈጸመው ወይም የተሞከረው ወንጀል በመከላያ ሀይለ ወኔ፣ ወይም ሞራን/ብቃት ላይ ያስከተለውን ጉዲት ወይም ሉያስከትል ይችል የነበረውን ጉዲት ግንዙቤ ውስጥ የሚያስገባ በዖርፍ በዔውቀትና ክህልት እንደዘሁም ያዲበረ ልምድ ያላቸው ወታደራዊ መኮንኖችና ባለሙያዎች ተሳታፉ በሆኑበትና በዛርዛር የተጠና ጥናትን መሰረት በማድረግ ራሱን የቻለ ልዩ የወታደራዊ ወንጀልች የቅጣት አወሳሰን መመሪያን ሉወጣ ይገባዋል።
የቅጣት አወሳሰን መመሪያ በማውጣት ለረዣም ጊዚ ስራ ላይ በማዋል የረዣም ጊዚ ተሞክሮና ያካበተ ልምድ ያላቸው እንደሰሜን አሜርካ መንግስታት ህብረት /usA/ ያለ አገኖች ላልች ወንጀልችና ሲቭልች ለሚፈጽሟቸው ወንጀልች ላይ ቅጣት ለመወሰን ታስበው የወጡ የቅጣት አወሳሰን መመሪያዎች ባያደራጀውና ባያካፍለ የተቋሙ ፍርድ ቤቶች እንዱፈጽሙ ግዳታ የማይጥለ መሆኑን ለመገንዖብ ይቻላል። ከዘህ አንፃር ሲታይ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያወጣችው የቅጣት አወሳሰን መመሪያዎች የወንጀል ህጉ በልዩ ሁኔታ ከተዖረዖሩት ወታደራዊ ወንጀልች ልዩ ባህሪ ከግንዙቤ ውስጥ ያላስገባና፣ የመመሪያዎች የግቦች ጠቅላላ የሆነ ይዖት ያላቸው፣ በመመሪያዎቹ ለወታደራዊ ወንጀልች ደረጃ ያልወጣላቸው አሁን ባለበት አቀራረጽና ይዖታቸው ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች በእለት ከእለት ስራቸው ተፈፃ እንዱያደርጓቸው በአስገዲጅነት ቢቀመጡ የወንጀል ህጉ ወታደራዊ ወንጀልቹን በክፍል ሶስት በልዩ ሁኔታ የመረመረበትንና የደነገገበትን መሰረታዊ ዓላማ ለማሳካት የማይችለና ዳኞች ወታደሩ ወይም የጦር መኮነኑ ወንጀለን ሲፈጽም ተሰጥቶት የነበረውን ግዲጅ፣ ወንጀለ የተፈጸመበትን ሁኔታና ላልች ከላይ ባስፈጸመው በሰፉው የዖረዖርናቸውን ልዩ ሁኔታዎች በማገናዖብና ለእያንዲንደ ልዩ ሁኔታ በመመዖን ቅጣት አቅለው ወይም አክብደው እንዱወስኑ በወንጀል ህጉና በእያንዲንደ ወታደራዊ ወንጀል በሚደነግግ ድንጋጌ የተሰጣቸውን ሰፉ ፈቅደ ስልጣን የሚያሳጣ ስለመሆን ይሆናል።
ከላይ በዛርዛር የገለጽናቸውን መሰረታዊ ሁኔታዎች መነሻ በማድረግ ቀዲማዊ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ለዘህ ክርክር መነሻ በሆነው ጉዲይ ላይ፣ ለአመልካች ላይ ቅጣት የወሰነው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 በመከተል፣ አመልካች የፈጸመው የወንጀል ህግ አንቀጽ 306/1/ እና የወንጀል ህግ አንቀጽ 306/3/ በቅጣት አወሳሰን በመመሪያው ደረጃ ያልወጣላቸው በመሆኑ ደረጃ በማውጣትና ለእያንዲንደ ማክበጃ ምክንያት አንድ እርከን ከፍ በማድረግ ለእያንዲንደ የቅጣት ማቅሉያ ምክንያት አንድ እርከን በመቀነስ እንደሆነ ተረድተናል። ይህም አመልካች ወንጀለን የፈጸመበትን ሁኔታ፣ የአመልካችን ተሰማርቶበት የነበረውን ወታደራዊ ግዲጅ፣ በግዲጅ አፈፃጸሙ ያስመዖገባቸውን ድልችና ወንጀለ ያስከተለውን ጉዲት አጠቃላይ የወታደራዊ ወንጀል ባህሪን በዛርዛር ለማየት የማያስችል በመሆኑ ቀዲሚ ወታደራዊ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ የወታደራዊ ፍርድ ቤት፣የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማድረግ በአመልካች ላይ የቅጣት ውሳኔ መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
21 በአመልካች ላይ የቅጣት መወሰን ያለበት የቅጣት አወሳሰን መመሪያውን መሰረት በማድረግ ሳይሆን ከቅጣት አወሳሰን መመሪያው ውጭ የወንጀል ህጉን የቅጣት አወሳሰን መርሆችና የወንጀል ህግ አንቀጽ 320 የእያንዲንደን ወታደራዊ ወንጀል መሰረታዊ ባህሪ፣ ወንጀለ የተፈጸመው በሰላም ወይም በጦርነት ጊዚ መሆኑና ወታደራዊ ወንጀለ ያደረሰውን ጉዲትም ሉያደርስ የነበረውን ጉዲት በአንድ በኩል፣ ጥፊተኛው ከዘያ በፉት የነበረው ባህሪ፣ በግዲጅ አፈፃጸም ሂደት የፈጸመው ጀብደ፣ ወታደራዊ ግዲጅ በሚፈጸምበት ጊዚ የደረሰበት ጉዲትና የከፈለውን መስዋዔትነት፣ የቤተሰብ ሁኔታውን ላልች በወታደራዊ አገልግልት አሰጣጥ ሂደት በቅጣት ለማቅለል የሚያስችለ ምክንያቶችን በልላ በኩል በማመዙዖን መሆን ይኖርበታል።
የቀዲሚ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የወንጀል መዛገብ ቁጥር 268/07 የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔና የወታደራዊ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በወንጀል ይግባኝ መዛገብ ቁጥ 234/07 የሰጠው የጥፊኝነት ውሳኔ በማጽናት የቅጣት ውሳኔውን በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ለ/2 መሰረት በማሻሻል ወስነናል።
ከወታደራዊ ወንልች ባህሪያት ጋር በሚጣጣም መንገድ ተቀርጸው ካልወጡ በስተቀር አሁን በስራ ላይ ያለት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 እና መመሪያ ቁጥር 2/2006 በአስገዲጅነት ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ወታደራዊ ወንጀልች ላይ ቅጣት ሲወስኑ ተፈፃሚነት ሉኖራቸው አይገባም በማለት ወስነናል።
አመልካች በዘህ ጉዲይ ተጠርጥሮ እጁ ከተያዖበት የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ በሚታሰብ አስር አመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ወስነናል።
የቅጣት ውሳኔውን እንዱያስፈጽም ለክፍለ ማረሚያ ቤት ይፃፍ።
No topics extracted.