No summary available.
ሚያዛያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- መዓዙ አሸናፉ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ወ/ሮ ቀመሪያ አህመድ ተጠሪዎች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 252680 ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠውን ትዔዙዛ በማጽናት፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.
199069 ሐምል 30 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የአፈጻጸም ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን 1ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት፤
የአሁን አመልካች እና ከ2ኛ -6ኛ ተጠሪዎች ደግሞ የፍርድ ባለዔዲዎች በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች ንብረቶቹ የሚሸጡ ከሆነ የቀዲሚነት መብቴ ይጠበቅልኝ በማለታቸው ተጠሪዎችም የቀዲሚነት መብት ጠይቀዋል።
አፈጻጸሙን የመራው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1060(2) እና 1261 (1) መሰረት ተጠሪዎችም በቀዲሚነት የመግዙት መብት አላቸው፤ ንብረቶቹ በሀራጅ ከተሸጡ የፍርድ ባለመብት እና ባለዔዲዎች እንደማንኛውም ሰው በጨረታው ተወዲድረው ለማሸነፍ ከቻለ ለመግዙት እንሚችለ ለፍርድ አፈጻጸም ዲሬክቶሬት ትዔዙዛ ሰጥቷል።
አመልካች ይህንኑ ትዔዙዛ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም አመልካች የቅድሚያ ግዣ መብት እንዱሰጣቸው አመልክተው ተጠሪዎች ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጡት አስተያየት የቅድሚያ ግዣ መብት ጥያቄውን እንደሚቃወሙ እና የቅድሚያ መብት እንዱሰጣቸው ጥያቄ አቅርበዋል፤ በግራቀኙ መካከል ስምምነት የላለ ከሆነ ደግሞ ለአንደ የጋራ ባሀለሃብት የቅድሚያ ግዣ መብት የሚሰጥበት የህግ አግባብ የለም፤ ለጋራ ባለሃብቶች ከላልች 3ኛ ወገኖች በቅድሚያ የመግዙት መብት ከመስጠት ባለፈ በጋራ ባለሃብቶች መካከል በሁለቱ ወይም ከዘያ በላይ ባለ የጋራ ባለሃብቶች የቅድሚያ ግዣ መብት ጥያቄ ቢነሳ ከጋራ ባለሃብቶች መካከል ለአንደ ተለይቶ ላሰጥ እንደሚችል በህግ የተቀመጠ ድንጋጌ የለም፤ ስለሆነም አንደ የጋራ ባለሃብት የቅድሚያ ግዣ መብት እንዱሰጠው በግራ ቀኙ መካከል የተደረገ ስምምነት የላለ መሆኑን ከግራቀኙ ክርክር መረዲት የተቻለ በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቶታል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ይዖቱም፡- አመልካች ከሟች ጋር የነበራቸው የጋራ ባለንብረትነት ከሆነ ልክ እንደ ፍርድ ባለእዲ ተቆጥረው የቀዲሚነት መበት ሉሰጣቸው ይገባል፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካችን የሟች ሚስት ሆነው እያለ እንደ ወራሽ በመቁጠር በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1060(2) መሰረት አመልካች እና ተጠሪዎች የጋራ ባለሃብቶች ናቸው በማለት አመልካች በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1386 እና 1093(2) መሰረት የቀዲሚነት መብት ሉሰጣቸው አይችልም በማለት የሰጠው ውሳኔ ስህተት ነው፤ የተጠሪዎች ጥያቄ የገንዖብ ትርፍ የማግኘት ሲሆን የአመልካች ጥያቄ ደግሞ ከቤቱ ጋር ያላቸው ቁርኝነት ይከበርልኝ ነው፤ ተጠሪዎች አመልካች ያቀረቡትን የቀዲሚነት መብት ባልካደበት እና የቀዲሚ መብትም ሆነ የመጫረት መብት በግልጽ አቤቱታ ባልጠየቁበት የስር ፍርድ ቤት ለአመልካች ባቀረበችው የአፈጻጸም ክስ ላይ የሰጡትን መልስ መነሻነት በማድረግ የሰጠው ብይን የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 182 እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ. 33945 እና በመ.ቁ. 54790 ላይ የተሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሚቃረን ነው፤ በመሆኑም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ትዔዙዛ እና ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ አመልካች የንብረቱ ግማሽ ባለድርሻ በመሆናቸው የቅድሚያ መብት ይሰጠኝ ሲለ ያቀረቡት ክርክር ውድቅ የመደረጉ አግባብነት ከፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 443 አተገባበር አንፃር ለማጣራት የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዛ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ጉዲዩ ለዘህ ችልት ቀርቧል።
1ኛ ፣ 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዖት በአጭሩ፡በግራ ቀኛችን መካከል የመብት መበላለጥ በላለበት ሁኔታ ለአመልካች የቅድሚያ መብት የሚሰጥበት የህግ አግባብ የለም፤ በህጉ ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ግማሽ ባለድርሻ የሆነ ሰው የቀዲሚነት ድርሻ ይሰጠዋል የሚል ሃሳብ ቢኖር አንኳን ተጠሪዎች የንብረቱን ግማሽ ባለድርሻ በመሆናችን የቅድሚያ መብት ይሰጠን ብለን አንድ ላይ አፈጻጸሙን ለያዖው ፍርድ ቤት የጠየቅን በመሆኑ የተጠሪዎች ድርሻ ከአመልካች ድርሻ ያንሳል የሚባልበት የህግ አግባብ የለም፤ ከጅምሩ ቤቱ ለኪራይ አገልግልት ሲውል የነበረ ስለሆነ በቤቱ አካባቢ ማህበራዊ ግንኙነት አልተመሰረተም፤ አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላይ የጠቀሷቸው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ. 33945 እና በመ.ቁ. 54790 ላይ የተሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም ለግራ ቀኛችን አፈጻጸም ክርክር አግባብነት የለውም፤ በስር ፍርድ ቤት ከ1ኛ ተጠሪ ውጪ አመልካችን ጨምሮ የፍርድ ባለዔዲዎች መሆናችን በግልጽ ተሰይመን ባለበት ሁኔታ አመልካች ከተጠሪዎች በተለየ መልኩ ቅድሚያ የማግኘት መብት የላትም፤ የስር ፍርድ ቤት አመልካችን እንደወራሽ ቆጥሯል በሚል የቀረበው ክርክር ሀሰት ነው፤ በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዔዙዛ እና ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች አመልካች መጥሪያ ስለማድረሳቸው በድጋሚ ቃለመሃላ ስላቀረቡ ተጠሪዎች መጥሪያ ደርሷቸው ያልቀረቡ ስለሆነ መልስ በጽሁፍ የማቅረብ መብታቸው ታልፍ አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበው የግራ ቀኙ የጽሁፍ ልውውጥ በዘህ ተጠናቋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበውን አቤቱታ በስር ፍ/ቤት በግራ ቀኙ ከተደረገው አጠቃላይ ክርክር እና ከተሰጠ ውሣኔ እንዱሁም ከማስቀረቢያ ነጥቡ አንፃር አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካች በስር ፍ/ቤት የግዠ ቅድሚያ መብት እንዱሰጣቸው ያመለከቱ መሆኑን እና ተጠሪዎች በቀረበው ጥያቄ ላይ አስተያየት እንዱሰጡ በፍ/ቤቱ ተጠይቀው የቅድሚያ መብት ጥያቄውን የማይቀበለ እና የማይስማሙ መሆኑን ገልፀው የቅድሚያ መብት ግዠ እንዱፈቀድላቸው ፍ/ቤቱን ጠይቀው የነበረ መሆኑን ከክርክሩ ይዖት ተመልክተናል።
እያከራከረ ያለው ንብረት በባልና ሚስት የተፈራ እና ባል በሞት በመለየታቸው ምክንያት የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ ቀርቦበት ግራ ቀኙ እኩል እንዱካፈለ በመወሰኑ ምክንያት የቅድሚያ የመግዙት መብት ይገባኛል ጥያቄ ነው።ይህንኑ አስመልክቶ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁ/ 88275፣16ዐ198፣168192 እና በላልችም መዙግብት በሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ስርዓት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስትም ሆነ በክልል ሕግጋት መንግስታት የተረጋገጠውን የእኩልነት መብት መሰረት አድርጎ መከናወን ያለበት መሆኑን፣ ክፍፍለ የሚከናወንበት ስርዓትም የተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ከአንቀፅ 90 እስከ 93 ድረስ በቅደም ተከተል ባስመቀጣቸው መንገድች መሆን፣ የጋብቻ ውጤት የሆነው የጋራ ንብረት ክፍፍል ሉከናወን የሚገባው የእኩልነት መርህን መሰረት አድርጎና የተጋቢዎችን ፈቃድ በመመርኮዛ መሆኑን፣ የተጋቢዎች ስምምነት ከላለ ደግሞ ክፍፍለ መፈፀም ያለበት በሕጉ የተመለከተውን ቅደም ተከተል መሰረት አድርጎ ላሆን እንደሚገባ በመግለጽ ወስኗል። ይሀ ስርአትም በአፈፃፀም ጊዚም ልንከተለው የሚገባ ሥርአት መሆኑን ከውሣኔው ይዖት መገንዖብ ይቻላል።
የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ክፍፍል በሚከናወንበት ጊዚ የእኩልነት መርህን የተከተለ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ የጋራ ንብረት ክፍፍል በሚፈፀምበት ጊዚም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ ድንጋጌዎች መርህ አንፃር ግራ ቀኙ ከተስማሙ በዓይነት የሚካፈለበት ይህ ካልሆነ ደግሞ በገበያ ዋጋ በጨረታ ተሽጦ እኩል ሉካፈለ እንደሚገባ አስቀድሞ ከዘህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁ/ 375ዐ8 እና 35ዐዐ3 በሆነው መዛገብ ላይ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል። ወደ ያዛነው ጉዲይ ስንመለስ አመልካችና ተጠሪዎች የድርሻ ክፍፍል ይደረግልን የሚለ ቢሆኑም የሚከፊፈለት ንብረት አመልካች እና የአመልካች ባለቤት የነበሩት የተጠሪዎች አባት በጋራ ያፈሩትን ንብረት በመሆኑ ተጠሪዎች ሟቹን የጋራ ባለሀብት ተክተው የአባታቸውን ድርሻ ለመካፈል በመሆኑ በንብረቱ ላይ እኩል ባለድርሻ ናቸው። በመሆኑም የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ጥያቄ የሚስተናገደው የእኩልነት መርህን ተከትል በመሆኑ አመልካች የግዠ ቅድሚያ መብት ይሰጠኝ ብለው የጠየቁ ቢሆንም ተጠሪዎች ግን ቅድሚያ ግዠ መብት ለአመልካች ላሰጥ አይገባም ይልቁንም ለእኛ ነው ቅድሚያ ግዠ መብት ሉሰጠን የሚገባው በማለት የተከራከሩ በመሆኑ በግራ ቀኙ መካከል በግዠ ቅድሚያ መብት ጥያቄው ላይ ስምምነት ያለመገኘቱን ተረድተናል።
በመሆኑም የግዠ ቅድሚያ መብት ጥያቄው ላይ ግራ ቀኙ ያልተስማሙ በሆነ ግዚ የግዠ ቅድሚያ መብት ጥያቄው ከግራ ቀኙ ለአንደ ሉፈቀድ የማይገባው እና ንብረቱ በጨረታ ተሽጦ ክፍፍል የሚደረግበት ሲሆን ነገር ግን ግራ ቀኙ እንደማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተወዲድረው ንብረቱን ማስቀረት ከሚችለ በቀር የቅድያ መብት ጥያቄው ለእኔ ላሰጥ ይገባው ነበር በሚል የስር ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ሉታረም ይገባል በማለት አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የላለው በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ውሣኔ የሚነቀፍና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም ብለን ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በይ/መ/ቁ/ 199ዐ69 በ3ዐ/11/2ዐ13 ዓ.ም.
በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 25268ዐ በ23/2/2ዐ13 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዘህ ሰበር ሰሚ ችልት በግራ ቀኙ የወጣ ወጪ ካለ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
መዛገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.