No summary available.
የሰ.መ.
ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ ኪነጥበብ አዲነ ተጠሪዎች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ሚያዛያ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ.ቁ 03-30317 በቀን 09/07/2013 የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የአፈጻጸም ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የተሁለደሬ ወረዲ ፍ/ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር በዘህ የሰበር ክርክር የላለ እነ ለባባ ካሳው የአፈጻጸም ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪዎች የአፈጻጸም ተከሳሾች፤
የአሁን አመልካች ደግሞ የጨረታ አሸናፉ በመሆን ተከራክረዋል። አፈጻጸሙን የመራው የወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡለትን የቅድሚያ ግዠ መብት ጥያቄ መርምሮ የጋራ ባለሀብቶች የቅድሚያ የግዠ መብት የሚጠበቅላቸው ቢሆንም ይህ የሚሆነው ግን ይኸው የቀዲሚነት ግዠ ይገባኛል የሚለው ወገን በቅድሚያ ወደ ጨረታው ለመግባት አስፈቅድ የጨረታ ተሳታፉ ሲሆን እንጂ የጨረታውን ውጤት በመጠባበቅ የሚቀርብ አይደለም፤
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 443 ድንጋጌ ይዖትም የሚያረጋግጠው ይህንኑ ነው፤ ስለሆነም በተጠሪዎች የቀረበው የቅድሚያ ግዠ መብት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት በብይን ውድቅ አድርጎታል።
ተጠሪዎች ይህን ብይን በመቃወም ለደቡብ ወል መስተዲድር ዜን ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል። ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ተጠሪዎች የንብረቱ ተካፊይ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1126 እና 2161 እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. በሰጠው ውሳኔ መሰረት የቀዲሚነት መብት አላቸው በማለት ወስናል።
አመልካች በበኩላቸው ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል። ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራቀኙን ካከራከረ በኃለ የስር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ተመሳሳይ ምክንያት በመስጠት አጽንቶቷል።
ተጠሪዎች በተራቸው ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። አቤቱው የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ የስር ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካች ሚያዛያ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል የቀረበ ሲሆን ይዖቱም፡በፍትሐብሕር ሕጉ ላይ ስለጋራ ባለሀብቶች ቀዲሚ የግዣ መብት የተደነገገቱ ድንጋጌዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 443 የተመለከተውን የቀዲሚነት መብቱን ለማግኘት አስቀድሞ በጨረታ ተወዲዲሪ የመሆን ግዳታ የሚያስቀሩ አይደለም፤ ተጠሪዎች በጨረታ አልተሳተፈም፤
ተጠሪዎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1403 የተመለከተውን ሙለ ዋጋ የማቅረብ ወይም ዋስትና የመስጠት ግዳቸውን ሳይወጡ ያቀረቡት የቀዲሚነት መብት ጥያቄ አግባብ አይደለም፤ በቀዲሚ የመግዙት መብት የሚፈቀደው ለስጋ ዖመድች እንጂ ለጋብቻ ዛመድች አይደለም፤ የቅድሚያ ግዠ መብቱ በጋራ እንዱሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄም ከሕግ ውጪ ነው፤ ስለሆነም በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ የሰበር ተጠሪዎች የጨረታ ተወዲዲሪ ባልሆኑበት የቀዲሚነት መብት አላቸው ተብል የተሰጠው የአፈጻጸም ውሳኔ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 403፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1403፤1386፤1389 እና 1390 ድንጋጌዎችን በአግባቡ ያገናዖበ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዛ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ጉዲዩ ለዘህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪዎች ሚያዛያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዖት በአጭሩ፡- አመልካች ሙለ ዋጋ የማቅረብ የዋስትና ግዳታቸውን አልተወጡም በማለት ያቀረበው ክርከር በስር ፍርድ ቤት ያልቀረበ አዱስ ክርክር ነው፤ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 443 በጨረታ አለመሳተፍ የቀዲሚነት ግዠ መብትን የሚያሳጣ ስለመሆኑ አይደነግግም፤ ተጠሪዎች በጨረታ ከወጣው ንብረት ላይ የድርሻችን መብት ያለን እንጂ ባለዔዲ አይደለንም፤ የጋራ ንብረት ለመካፈል የንብረቱ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ግምት ውስጥ ሉገባ ይገባል፤ ስለሆነም የክፍፍለን ድርሻ ለመወሰን የጨረታ አሸናፉ የሆነው አካል እንደማይገዙ እየታወቀ ጨረታው ሉወጣ ይችላል፤ ስለሆነም የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው።
No topics extracted.
አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዖውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዖብ የቻልነው የአሁን አመልካች በጨረታ ተወዲድረው የጨረታ አሸናፉ በሆኑበት ንብረት ላይ የስር የአፈጻጸም ከሳሾች እና የአሁን ተጠሪዎች ድርሻ ያላቸው መሆኑን፤ ንብረቱ በጨረታ ከመሸጡ በፉት አመልካቾች አፈጻጸሙን ለሚመራው ችልት ያቀረቡት የቀዲሚነት ግዠ መብት ጥያቄ የላለ መሆኑን፤ ጨረታው ወጥቶ አመልካች የጨረታው አሸናፉ መሆናቸው ከታወቀ በኋላ ተጠሪዎች ለአፈጻጸም ችልቱ የቀዲሚነት ግዞ መብት እንዱጠበቅላቸው ጥያቄ ያቀረቡ መሆኑን ነው። ስለሆነም በዘህ ችልት ምላሸ ሉያገኝ የሚገባው የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ ተጠሪዎች የጋራ ባለሐብት የሆኑበት ንብረት በጨረታ ከመሸጡ በፉት ያቀረቡት የቀዲሚነት የግዠ መብት ጥያቄ ሳይቀርብ ጨረታው ተከናውኖ የጨረታው አሸናፉ ከታወቀ በኋላ ያቀረቡት የቀዲሚነት ግዠ መብት ጥያቄ ተቀባይነት ሉኖረው ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚለው ነው።
በመሰረቱ የጋራ ባለሀብቶች የሆኑ ሰዎች ያልተከፊፈለውን የጋራ ንብረት ከማንኛውም ሶስተኛ ወገን በፉት በቀደምትነት በግዣ የማስቀረት ሕጋዊ መብት ያላቸው ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕገ ቁጥር 1261 (1) የተደነገገ ሲሆን ይህ መብት ተግባራዊ የሚደረግበት ስርዓትም በዘሁ ሕግ ከቁጥር 1386 እስከ 1409 በግልጸ ተደንግጎ ይገኛል። በልላ በኩል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 443 ድንጋጌ በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ተይዜ የሚሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች በሕብረት የያዘት እና ያልተከፊፈለት በሆነ ጊዚ ከተካፊዮቹ አንደ ንብረቱን ለመግዙት በጨረታ ተወዲዲሪ ሆኖ የቀረበ እንደሆነ የፍርድ ባለዔዲው እንደቀረበ ተቆጥሮ የተቀዲሚነት መብት ይሰጠዋል በማለት ይደነግጋል።
ከላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዖት መገንዖብ የሚቻለው የጋራ ባለንብረቱ በጨረታ ተወዲዲሪ የሚሆነው እና የተቀዲሚነት መብት የሚያገኘው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 430 (1) ላይ እንደተደነገገው በሐራጅ የሚሸጠውን ንብረት ያለፈቃድ የመግዙት ክልከላ እንደተደረገበት የፍርድ ባለመብት ሳይሆን የሚሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት የጋራ ባለሀብት በመሆኑ ምክንያት ብቻ በሕጉ በተጠበቀለት መብት መሰረት መሆኑን ነው። ይህም የጋራ ባለሐብቱ ያለፍርድ ቤት ፈቃድ በጨረታው ለመሳተፍ መብት ያለው መሆኑን የሚያሳይ ነው። ይህን ካልን ዖንዲ በሕግ በተጠበቀለት መብት መሰረት ያለፍርድ ቤት ፈቃድ በጨረታ ለመወዲደር መብት ያለው የጋራ ባለሐብት በጨረታው ሳይወዲደር ጨረታው ተከናውኖ አሸናፉው ከታወቀ በኋላ የሚያቀርበው የቀዲሚነት የግዠ መብት ጥያቄ ሉፈቀድለት ይገባል ወይስ አይገባም የሚለው ምላሽ ሉጠው የሚገባ መሰረታዊ ነጥብ ነው።
በመሰረቱ አንድ ንብረት በጨረታ እንዱሸጥ ሲደረግ በጨረታው ሑደት ላይ ተሳታፉ የሚሆኑ ሶስተኛ ወገኖች አለ። ስለሆነም የፍርድ ባለመብቱ ወይም የፍርድ ባለዔዲው በጨረታ በተሸጠው ንብረት ለይ የሚያቀርቡት ማናቸውም የመብት ጥያቄ ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው የጨረታ አሸናፉውንም የመብት ጥያቄ ባገናዖበ መልኩ ላሆን ይገባል። በጨረታ በሚሸጠው ንብረት ላይ የጋራ ባለሐብት በመሆኑ ምክንያት በሕግ የቀዲሚነት መብት የተጠበቀለት ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 443 ላይ በተገለጸው አግባብ ንብረቱን ለመግዙት በጨረታ ተወዲዲሪ ሆኖ ካልቀረበ በቀር ጨረታው ተከናውኖ አሸናፉው ከታወቀ በኋላ የጨረታውን ውጤት አውቆ የሚያቀርበው የቀዲሚነት መብት ጥያቄ በጨረታው አሸናፉ መብት ላይ አለታዊ ተጽእኖ ያለው በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪዎች የቀዲሚነት መብት አላቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ.ቁ 03- 30317 በቀን 09/07/2013 የሰጠው ውሳኔ እና የደቡብ ወል መስተዲድር ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በቀን 03/07/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
የተሁለደሬ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ. በቀን 18/05/2012 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.5 በቀን 20/02/2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
ሚያዛያ 04 ቀን 2013 ዓ.ም በመዛገቡ የተሰጠው የዔግድ ትዔዙዛ ተነስቷል። ይጻፍ
ስማችን በሶስተኛ እና አራተኛ መስመር ላይ የተጠቀስነው ዳኞች አብላጫው ድምፅ የክልለን ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ለመሻር በጠቀሰው ምክንያት እና በደረሰበት ድምዳሜ ያልተስማማን በመሆኑ ለልዩነት ያበቃንን ሀሳብ እንደሚከተለው አስፍረናል።
የቅድሚያ ግዥ መብት(Right of Preemption) እና ንብረትን የማስመለስ የቀዳሚነት መብት(Right of Recovery) ሁለቱም በአንድ ንብረት ላይ የሚቋቋሙ የቀደምትነት መብቶች ቢሆኑም ከመብቶቹ ምንጭ እና በአፈፃፀም ረገድ የተለያዩ ናቸው። በፍትሓ ብሕር ህጋችን ስለቅድሚያ ግዢ መብት በዋናነት የተደነገገው በአንቀፅ 8፤ ምዕራፍ 5 ከቁጥር 1410 እስከ 1443 ስር በተመለከቱት ድንጋጌዎች ነው። በዚሁ መሰረት የቅድሚያ ግዥ መብት ማለት የአንድ ንብረት ባለሃብት የሆነ ስው ይህንኑ ሃብቱን ለመሸጥ በሚወስንበት ጊዜ አንዱን ሰው በመምረጥ ሀብቱን እሸጥልሃለው ሲል ለዚሁ ለመረጠው ሰው ከሚገባለት የስምምነት ቃል የሚመነጭ መብት ማለት እንደሆነ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1410(2) ይደነግጋል። በዚህ ድንጋጌ ስር የመብቱ ምንጭ ውል እንደሆነ የተመለከተ ቢሆንም የቅድሚያ ግዥ መብት ከህግም ጭምር የሚመነጭ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1483 እና 1484 ድንጋጌዎችን በአብነት መጥቀስ ይቻላል። ስለዚህ በጥቅለ የቅድሚያ ግዥ መብት ከውል ወይም ከህግ ሉመነጭ ይችላል ማለት ነው። ይህ መብት ተግባራዊ የሚደረግውም የቅድሚያ ግዥ መብቱ የተቋቋመበት ንብረት ባለሃብት የሆነው ሰው ንብረቱን በሚሸጥበት ጊዜ ወይም ንብረቱ በሃራጅ የሚሸጥ ከሆነም የሃራጅ ሥነ ሥርዓቱ በሚከናወንበት ወቅት በህጉ ተለይቶ በተቀመጠው የጊዜ ገድብ ውስጥ ቀርቦ መብትን በመጠየቅ እና በማረጋገጥ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1417 እስከ 1421 ድንጋጌዎች ይዘት መረዳት ይቻላል።
በልላ በኩል ንብረትን የማስመለስ የቀዳሚነት መብት(Right of Recovery) በዋናነት የተመለከተው በፍ/ብ/ህጉ ከቁጥር 1386 እስከ 1409 ድረስ በተጠቀሱተ ድንጋጌዎች ነው።
በእነዚህ ድንጋዎች መሰረት ንብረትን የማስመለስ መብት ማለት የንብረቱን ዋጋ በመክፈል ንብረቱ ከተላለፈለት ሶስተኛ ወገን እጅ ለማስመለስ በህግ ተለይቶ መብቱ ለተሰጣቸው ሰዎች የተቋቋመ የቀደምትነት መብት ማለት እንደሆነ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1386 ድንጋጌ ያስገነዝባል። ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መረዳት እንደሚቻለው መብቱ የሚገኘው ከህግ ብቻ ነው። መብቱም የተጠቀበው ለማናቸውም ሰው ሳይሆን ለአንድ ንብረት የጋራ ባለሃብቶች እና በዋናው ባለሃብት ጋር የሥጋ ዝምድና ላላቸው ሰዎች ብቻ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1388፣ 1389 እና 1394 ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
በዚህ መልኩ በህግ የተቋቋመው የቀደምትነት መብት ተግባራዊ የሚደረገውም የመብቱ ባለቤት መብቱ የተቋቋመበት ንብረት ለሶስተኛ ወገን ስለመተላለፉ ከተነገረው ቀን አንስቶ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ መሆኑን፤ ስለንበረቱ መተላለፍ ያልተነገረው ከሆነ ደግሞ ንብረቱ መተላለፉን ካወቀብት ቀን አንስቶ ለጋራ ባለንበረት ከሆነ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ፤ የሥጋ ዘመዶች ከሆኑ ደግሞ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1400 እና 1401 ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። በዚህ መልኩ ንብረቱን እንዲለቅ ለሚደረገው ሶስተኛ ወገን በህግ የተቀመጠው መፍትሄም ንብረቱን የገዛበትን ዋጋ፣ ንብረቱ በእጁ ከገባ በኋላ በንብረቱ ላይ ያወጣውን ወጪ እና በንብረቱ ላይ ያደረገውን መሻሻል እንዲሁም በጉዳዩ ውስጥ ያለአግባብ የመበልፀግ ሁኔታ ተከስቶ ከሆነም ያለአግባብ ስለመበልፀግ በሚደነግገው የፍ/ብ/ህጉ አንቀፅ 2162-2178 መሰረት ተገቢው ክፍያ እንዲከፈለው መጠየቅ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1405 እስከ 1409 ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
እንግዲህ ከሁለቱ የቀደምትነት መብቶች መሰረታዊ ምንጭ እና ተግባራዊ አፈፃፀም ከሚደነግጉት የህጉ ክፍልች ይዘት በግልፅ መረዳት እንደሚቻለው የቀደምትንት መብቱ በተቋቋመበት ንብረት ሽያጭ ሂደት ቀርቦ መብትን መጠየቅ እና ማረጋጥ ግድታ የሚሆነው የግዥ የቀደምትነት መብትን (Right of Preemption) በተመለከ ብቻ ነው።
ከዚህ ባለፈ ንብረትን የማስመለስ የቀዳሚንት መብት (Right of Recovery) ያለው ሰው ንብረቱ በማናቸውም መንገድ ለሶስተኛ ወገን መተላለፉን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በህጉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ መጠየቅ እስከ ቻለ ድረስ ንብረቱን ማስመለስ የሚችል በመሆኑ በንብረት ሽያጭ ሂደት መቅረብ አይጠበቅበትም።
አሁን በቀረበው ጉዳይ ተጠሪዎች በአፈፃፀም ምክንያት እንዲሸጥ በተባለው ንብረት ላይ የጋራ ባለሃብቶች ስለመሆናቸው ያልተካደ ፍሬ ነገር ነው። ተጠሪዎች አፈፃፀሙን ሲመራ ለነበረው ፍርድ ቤት ያቀረቡት ጥያቄም በሀራጅ በተሸጠው ንብረት ላይ የጋራ ባለሃበት ድርሻ ያላቸው መሆኑን በመግለፅ የጫረታው አሸናፊ የሆኑት የአሁን አመልካች ሃራጁን ያሸነፉበትን ዋጋ ከፍለን ንብረቱን እንድናስመልስ ይፈቀድልን የሚል ነው። ይህ ጥያቄ የጋራ ባለሃብት የሆኑበት እና በአፈፃፀም ለሶስተኛ ወገን የተላለፈን ንብረት ለማስመለስ የቀረበ የቀደምትነት መብት (Right of Recovery) እንጂ የግዥ የቀደምትነት መብት ይጠበቅልን (Right of Preemption) ጥያቄ አይደለም። የተጠሪዎች ጥያቄ ይህ ከሆነ ደግሞ በንብረቱ ሽያጭ ሂደት ቀርባችሁ በሀራጁ ላይ ልትካፈለ ይገባ ነበር የሚባለበት የህግ መሰረት የለም።
በእርግጥ አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤትም ሆነ በዚሁ ችልት አብላጫ ድምጽ የያዙት የስራ ባልደረቦቻችን ለውሳኔያቸው መሰረት ያደረጉት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 443 ድንጋጌን ነው። በመሰረቱ ይህ የሥነ ሥርዓት ህጉ ድንጋጌ በአንድ በአፈፃፀም ምክንያት በሚሸጥ ንብረት ላይ የቀደምትነት መብት ያላቸው ሰዎች ንብረቱ በሚሸጥበት ሀራጅ ላይ ካልተካፈለ በቀር የቀደምትነት መብት መጠየቅ አይችለም የሚል አይደለም። ከዚህ ይልቅ ንብረቱ የበርካታ ሰዎች ያልተከፋፈለ የጋራ ሀብት ከሆነ እና ከእነዚህ የጋራ ባለድርሻዎች ውስጥ አንዱ በሀራጁ ከተሳተፈ ዋናው የፍርድ ባለእዳ እንደቀረበ ተቆጥሮ በሀራጁ ለተሳተፈው የጋራ ባለሃብት በቀዳሚነት የመግዛት መብት ይጠበቅለታል የሚል ነው።
ከመነሻውም ቢሆን የቀደምትነት መብት ምንጩ መሰረታዊ ህግ እንጂ የሥነ ሥርዓት ህግ አይደለም። የሥነ ሥርዓት ህግ መሰረታዊ ዓላማም በመሰረታዊ ህግ የተቋቋመ መብት የሚፈፀምበትን ሥርዓት ማበጀት ነው። ከዚህ ውጪ በመሰረታዊ ህግ የተቋቋመ መብት እና ጥቅም በሥነ ሥርዓት ህግ ቀሪ የሚሆንበት የህግ አስተምህሮ የለም። ከዚህ አንፃር በፍ/ብ/ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 443 ስር የተመለከተው ድንጋጌ ንብረትን የማስመለስ የቀደምትነት መብትን የሚመለከት ባለመሆኑ ለቀረበው ጉዳይ አግባብነት ያለው ድንጋጌ አይደለም።
ሲጠቃለል የአሁን ተጠሪዎች በአፈፃፀም ምክንያት በተሸጠው ንብረት ላይ የጋራ ባለሃብቶች በመሆናቸው እና ንብረቱንም የማስመለስ ከህግ የመነጨ የቀደምትነት መብት ያላቸው በመሆኑ በንብረቱ ሽያጭ ሂደት በተጫራችነት መካፈል ሳያስፈልጋቸው ንብረቱ ከተላለፈለት ከማናቸውም ሰው የሽያጩን ዋጋ ከፍለው የማስመለስ መብት አላቸው።
ከዚህ አኳያ የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ሰበር ሰሚ ችልት ጉዳዩን የተረዱበት እና ክርክሩን የመሩበት ሁኔታ በፍ/ብ/ህጉ ስለ ንብረት ማስመለስ የቀደምትነት መብት (Right of Recovery) የተመለከተውን ድንጋጌ መንፈስ የተከተለ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ሉፀና ይገባ ነበር በማለት ከስራ ባልደረቦቻችን የተለየ አቋም ይዘናል።