No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዘያ 30 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) እንዲሻው አዲነ ተሾመ ሽፈራው መላኩ ካሳዬ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ተጠሪ፡- ኦሮሚያ ኢንሹራንስ አ.ማ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል
በዘህ መዛገብ የተያዖው ጉዲይ የመድን ዋስትና ውልን መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የጀመረው የአሁን ተጠሪ ባቀረቡት ክስ ሲሆን 1ኛ. ተከሳሽ አቶ ሽብሬ ሁንዳ፤ 2ኛ. ተከሳሽ አቶ መሪድ ባጫ እንዱሁም 3ኛ ተከሳሽ የአሁን አመልካች ነበሩ።
ከመዛገቡ እንደተረዲነው ተጠሪ ንብረትነቱ የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ አ/ማ ለሆነው የሰላዲ ቁጥር 3-A59886 ተሸከርካሪ የመድን ዋስትና ሽፊን የሰጠ ሲሆን የስር 1ኛ ተከሳሽ ንብረት በሆነው የሰላዲ ቁጥር 3-A03862 በ2ኛ ተከሳሽ ሲሽከረከር የተጠሪ ደንበኛ ተሸከርካሪ ተገጭቶ ጉዲት ደርሷል። ለግጭቱ መንስኤ የሆነውና በአደጋውም ጥፊተኛ በመሆን ኃላፉነት ያለባቸው የ1ኛ ተከሳሽን መኪና ሲያሽከረክሩ የነበሩት 2ኛ ተከሳሽ መሆናቸው ፖሉስ በሰጠው ማስረጃ ተረጋግጧል። ከሳሽ የደንበኛውን ተሸከርካሪ ለማስጠገን ብር 77,232.37 ወጪ አድርጎ ኃላፉነቱን ተወጥቷል፤ እንዱሁም ለክሱ ማስረጃዎችን ለማስተርጎም ብር 2,069.59 አውጥቷል። ከተከሳሾች የሚከፈለው የካሳ ክፍያ በአጠቃላይ ሲሆን ብር 79,301.96 ሲሆን በመድን ውለ መሰረት ደንበኛው የከፈለት የአደጋ መነሻ ዋጋ (excess) ብር 1,500.00 እና 2ኛ ተከሳሽ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነቱን በማመን ለከሳሽ የከፈለው ብር 10,000.00 ከካሳ ገንዖቡ ላይ ሲቀነሱ ከተከሳሾች የሚፈለገው ብር 67,801.96 (ስድሳ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ አንድ ብር ከ96/100) ነው። ይህን ገንዖብ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በንብረት ባለቤትነት እና በጥፊት፤
እንዱሁም 3ኛ ተከሳሽ ለጉዲት አድራሹ ተሸከርካሪ አስገዲጅ የሶስተኛ ወገን መድን ሽፊን የሰጠ በመሆኑ የመክፈል ኃላፉነት ስላለባቸው የክሱን ገንዖብ ከነወለደ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ይሁንና ከሳሽ በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ላይ ያቀረበው ክስ እንዱቋረጥ ጠይቆ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 278 መሰረት ከክሱ ውጪ እንዱሆኑ ተደርጓል።
3ኛ ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) ለክሱ የመጀመሪያ መቃወሚያ እና መልስ አቅርቧል። ባቀረበው መቃወሚያ ከሳሽ በክሱ እንደገለፀው የደንበኛው ተሸከርካሪ በቀን 24/03/1012 ዓ.ም በመገጨቱ ምክንያት ለደረሰው የንብረት ጉዲት ለማስጠገን የከፈለውን ከተከሳሾች ለማስመለስ አደጋው ከደረሰ ከ2 ዓመት ከ 3 ወራት በኃላ ክስ ያቀረበው በቀን 21/06/2014 ዓ.ም በመሆኑ፤
እንዱሁም በማስረጃነት ያቀረበው ደረሰኝ በግልጽ እንደሚያስረዲው ክፍያ የፈፀመው በ08/05/2012 ዓ.ም መሆኑንና የኢንሹራንስ የካሳ ክፍያው ጥያቄ የቀረበው ክፍያ ከተፈፀመ 2 ዓመት በኃላ በመሆኑ ክሱ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2143(1) እንዱሁም በንግድ ህግ ቁጥር 674(2) መሰረት በይርጋ ይታገዲል። ላልች ተከሳሾች ለከሳሽ ኃላፉነትን በማመን ክፍያ መፈፀም ጀምረው ቢሆን እንኳ ከ3ኛ ተከሳሽ ዔውቅና እና ፈቃድ ውጪ በመሆኑና ከመድን ውለ ጋር የተቃረነ ጭምር በመሆኑ በ3ኛ ተከሳሽ ላይ ይርጋ ጊዚውን የሚያቋርጥ አይደለም ብሎል።
በመቃወሚያው ላይ ተጠሪ ባቀረበው ክርክር 2ኛ ተከሳሽ የካቲት 20/2012 እና መጋቢት 8/2012 ዓ.ም ክፍያ በመፈፀማቸው ይርጋውን ያቋርጣል፤ 3ኛ ተከሳሽ ለተሸከርካሪው የመድን ሽፊን ስለሰጠ 2ኛ ተከሳሽ በፈፀመው ድርጊት ምክንያት ይርጋው ይቋረጣል በማለት ተከራክሯል።
የስር ፍርድ ቤት ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ጭብጥ በመያዛ የመቃወሚያ ክርክሩን መርምሮ የከሳሽ ክስ ምክንያት የሚመነጨው ካሳ ሲከፍል በመሆኑ ከዘህ አንፃር የካሳ ክፍያ የፈፀመው በ08/05/2012 ዓ.ም መሆኑን የክፍያው ደረሰኝ የሚያስረዲ በመሆኑ ከዘህ ጊዚ ጀምሮ ሲታሰብ በቀን 21/06/2014 ዓ.ም የቀረበው ክስ 2 ዓመት እንዲለፈው መገንዖብ ይቻላል። ይሁንና 2ኛ ተከሳሽ የካቲት 20 እና መጋቢት 8/2012 ዓ.ም ክፍያ ፈጽመዋል። በፍ/ብ/ህ/ቁ 1901 መሰረት ባለዔዲ የሆኑ ሁለ ዔዲው በሙለ ወይም በከፉል ተከፍሎል ወይም በይርጋ ታግዶል በማለት ባለገንዖቡን መከራከር እንደሚችለና ከተከሳሾች በአንደ የተነሳ የይርጋ መቃወሚያ በሁለም ተከሳሾች ላይ ክሱን የማዖጋት ውጤት የሚኖረው በመሆኑ የይርጋ ጊዚን የማቋረጥ ውጤት ያለው ተግባር ያልተነጣጠለ ኃላፉነት ካለባቸው ባለዔዲዎች በአንደ ከተፈፀመ ዔዲውን የማመን ተግባር ባይፈፀም እንኳ በላልች ተከሳሾች ላይ ተፈፃሚ የማይሆንበትና ይርጋው የማይቋረጥበት ምክንያት የለም። በመሆኑም በፍ/ብ/ህ/ቁ 1851(ሀ) በተመለከተው መልኩ 2ኛ ተከሳሽ ዔዲውን በማመን ክፍያ መጋቢት 8/2012 ዓ.ም የፈፀሙ በመሆኑ ከዘህ ጊዚ ጀምሮ ሲታሰብ ክሱ 2 ዓመት ባልሞላ ጊዚ ውስጥ የቀረበ በመሆኑ በ3ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበው ክስ በይርጋ አይታገድም በማለት ብይን ሰጥቷል።
No topics extracted.
የስር ፍርድ ቤት የፍሬ ነገር ክርክርና ማስረጃውን መርምሮም 3ኛ ተከሳሽ ብር 65,732.37 ከወለድና ወጨና ኪሳራ ጋር ለከሳሽ እንዱከፍል በማለት ወስኗል። የአሁን አመልካች በዘህ ብይንና ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ጉድለት የለበትም ተብል ይግባኙ ተሰርዝል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዘህ ነው።
አመልካች ህዲር 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረበው የሰበር ማመልከቻ ተፈፀመ የሚለውን ስህተት በመዖርዖር የስር ፍርድ ቤቶች ያሳለፈት ብይንና ውሳኔ ተሽሮ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው ተብል እንዱወሰን ጠይቋል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በአመልካች የተነሳው የይርጋ ክርክር የታለፈው ህጉ በአግባቡ ተተርጉሞ ስለመሆኑ ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ተደርጓል። ተጠሪ በሰጠው መልስ የስር ፍርድ ቤት የፍ/ብሓር ህጉን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የተፈፀመው ክፍያ በሁለም ተከሳሾች ላይ እንደ ይርጋ ማቋረጫ ምክንያት ሉወሰድ ይገባል በማለት የይርጋ መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ የህግ ትርጉም ስህተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ ውሳኔው ሉፀና ይገባል ብሎል።
አመልካችም የመልስ መልስ አቅርቧል። መዛገቡ ለምርመራ የተቀጠረው በዘህ ሁኔታ ነው።
በበኩላችን የአመልካች የይርጋ ክርክር የታለፈው በአግባቡ መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር እና በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንደተመለከተው ተጠሪ ክሱን ያቀረበው በቀን 21/06/2014 ዓ.ም ሲሆን ለክሱ ምክንያት የሆነውን የካሳ ክፍያ ለደንበኛው የፈፀመው ደግሞ በ08/05/2012 ዓ.ም መሆኑ፤ ይህ ጊዚ ሲታሰብ የቀረበው ክስ 2 ዓመት እንዲለፈው አላከራከረም። የስር ፍርድ ቤትም ተቀብልታል። ይህ በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው እውነታ ሲሆን እውነታው ከየትኛው ህግ ጋር ሲገናዖብ ነው ለይርጋው ክርክር አወሳሰን አግባብነት የሚኖረው የሚለውን ደግሞ ቀጥለን እንመለከታለን።
ተጠሪ ክሱን ያቀረበው በኢንሹራንስ ገቢው መብት በመዲረግ ነው። በንግድ ሕጉ አንቀጽ 683 መሰረት ኢንሹራንስ ሰጪው በከፈለው ካሣ መጠን ጉዲት እንዱደርስ ባደረጉ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ክስ ለማቅረብ ኢንሹራንስ ለገባው ሰው በተከፈለው ገንዛብ መጠን፣ ባለት መብቶችና ክሶች ኢንሹራንስ ሰጪው ምትክ ሆኖ እንደሚገባ ተመልከቷል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ እና ላልችም ተመሳሳይ መዙግብት በሰጠው ትርጉም መሰል የኢንሹራንስ የካሳ ክፍያ ጥያቄ ክፍያ ከተፈፀመበት ጀምሮ በ2 ዓመት ውስጥ ክስ ካልቀረበ ጉዲዩ በይርጋ ቀሪ ይሆናል። ስለሆነም ተጠሪ ለክሱ ምክንያት የሆነውን የካሳ ክፍያ ለደንበኛው ከከፈለ ከ 2 ዓመት በኃላ በአመልካች ላይ ያቀረበው ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው።
ይህም ሆኖ የስር ፍርድ ቤት የይርጋ መከራከሪያውን ውድቅ ያደረገው የስር 2ኛ ተከሳሽ ይርጋውን የሚያቋርጥ ክፍያ ለተጠሪ በመፈፀሙና ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1901 እና 1851(ሀ) ንባብ አንፃር የይርጋ መቃወሚያ በሁለም ተከሳሾች ላይ ክሱን የማዖጋት ውጤት የሚኖረውን ያህል የይርጋ ጊዚን የማቋረጥ ውጤት ያለው ተግባር ያልተነጣጠለ ኃላፉነት ካለባቸው ባለዔዲዎች በአንደ ከተፈፀመ በላልች ተከሳሾች ላይ ተፈፃሚ የማይሆንበትና ይርጋው የማይቋረጥበት ምክንያት የለም በሚል ነው።
የፍ/ብ/ህ/ቁ 1901 የባለዔዲዎችን ዔዲ በተመለከተ በመካከላቸው ስላለው የማይከፊፈል አንድነት በሚደነግገው የህጉ ክፍል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የዘህ የህጉ ክፍል አላማ ባለገንዖቡ ስለ ግዳታው አፈፃፀም እንደፈቀደው ኃላፉዎች የሆኑትን ሁለ ወይም አንደን ለማስገደድ እንዱችል ለማስቻል ነው። ከዘህ በቀር ያልተነጣጠለ ኃላፉነትን ካስከተለው ጉዲይ ውጪ የሆኑ በአንደኛው ባለዔዲ የተፈፀሙ ተግባራት ሁለ የላልችን ባለዔዲዎች መብት ለማጣበብ ወይም ዔዲቸው ቀሪ እንዲይሆን እንዱያደርጉ ታስቦ የተደነገገ አይደለም። የፍ/ብ/ህ/ቁ 1901 በግልጽ የሚደነግገው ባለዔዲዎች ስለሚኖርባቸው ግዳታ ሳይሆን ባለዔዲ የሆኑት ሁለ ዔዲው ተከፍሎል ወይም በይርጋ ታግዶል በማለት ባለገንዖቡን መከራከር ስለመቻላቸው ብቻ ነው።
በልላም በኩል አንድን ክስ ለማቅረብ በህጉ የተመለከተው የይርጋ ጊዚ ካለፈ በኋላ ክስ ለማቅረብ የማይቻል ቢሆንም ህጉ ለይቶ ባስቀመጣቸው ምክንያቶች የይርጋው ጊዚ ሉቋረጥ የሚችል እና አዱስ የይርጋ ጊዚ መቆጠር እንደሚጀምር በፍ/ብ/ህ/ቁ 1852(1) ሥር የተመለከተ ሲሆን ይርጋ ከሚቋረጥባቸው ምክንያቶች መካከል ደግሞ ባለዔዲው በራሱ ዔዲውን ሲያምን ፤
ይልቁንም ወለድ ወይም ከዔዲው ላይ በከፉል መስጠቱ እንደሚገኝበት ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1851 (ሀ) መገንዖብ ይቻላል። ከዘህ ድንጋጌ በግልጽ መገንዖብ የሚቻለውም ዔዲን አምኖ ከዔዲው ላይ በከፉል መክፈል ይርጋውን የሚያቋርጠው በዘሁ ባለዔዲ ላይ ብቻ ነው። ከመሰረቱም ይርጋን የተመለከቱ ድንጋጌዎች ሉተረጎሙ የሚገባው ህጉን እንደ አቀራረጹ በጥብቅ በመከተል (strict construction) ነው።
ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ህ/ቁ 1901 እና 1851(ሀ) መሰረት የይርጋ ጊዚን የማቋረጥ ውጤት ያለው ተግባር ያልተነጣጠለ ኃላፉነት ካለባቸው ባለዔዲዎች በአንደ ከተፈፀመ በላልች ተከሳሾች ላይ ተፈፃሚ የማይሆንበትና ይርጋው የማይቋረጥበት ምክንያት የለም በሚል የደረሰበት መደምደሚያ እና ያሳለፈው ብይን በድንጋጌዎቹ በግልጽ የተመለከተውን ያልተከተለና ከተደነገጉበት አላማ የራቀ ነው። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈው ብይን የህግ መሰረት ያለው አይደለም ብለናል።
በአጠቃላይ ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ ያቀረበው በህጉ በይርጋ ቀሪ ከሆነ በኋላ ሲሆን አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ያሳለፈት ብይንና ውሳኔ በህጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 89181 ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና ግንቦት 19/2014 ዓ.ም ያሳለፈው ውሳኔ፤ እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ኮ/መ/ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ያሳለፈው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ በአመልካች ላይ የመሰረተው ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ወስነናል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሣራ የራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መ/ቤት ይመለስ።
አፈጻጸም የሰ.መ.
ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ ኪነጥበብ አዲነ ተጠሪዎች፡-