No summary available.
መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ- ነ/ፈጂ ኤልሳቤጥ ጌታቸው ተጠሪዎች-
ጉዲዩ ቼክን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች ተከሳሽ፣ እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ እና ላልች ሁለት ሰዎች ጣልቃ ገብ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ባቀረበው ክስ በአመልካች ባንክ ቦላ መድኃኒዓለም ቅርንጫፍ ካስከፈትኩት ሂሳብ ውስጥ ብር 221,054.40 ቁጥሩ EG 23310195 በሆነ ቼክ ለተክለኃይማኖት ደረጃ ሶስት የጭነት ትራንስፖርት ባለቤቶች እንዱከፈል ያዖዛኩ ቢሆንም ማህበሩ ቼኩን ለክፍያ ለአመልካች ሲያቀርብ ለክፍያ ከቀረበው ቼክ ጋር ተመሳሳይ ቁጥር ለያዖ እና 1ኛ ተጠሪ አውጥቶታል በተባለ ቼክ በቀን መጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ.ም ብር 1,800,000.00 ኃይለመለኮት አርያም ለተባለ ግለሰብ ክፍያ ፈጽሚያለሁ በማለት ክፍያ እንዱፈፀምለት ትዔዙዛ ለሰጡለሁለት ማህበር ክፍያ ሳይፈጽም ቀርቷል፤ አመልካች ክፍያ ፈፅሜለታለሁ የሚለው ቼክ በ1ኛ ተጠሪ እጅ የሚገኘው የቼክ ጥራዛ አካል አይደለም፤
ሰነደንም አላውቀውም፤ ስለሆነም አመልካች የቀረበት ቼክ ላይ ያለው ፊርማ የሂሳቡ ባለቤቶች መሆኑን ሳያረጋግጥ፣ በዲበረው አሰራርም ክፍያው እንዱፈፀም የማረጋገጫ እና የጽሁፍ ማሳወቂያ ደብዲቤ እንዱደርሰኝ ሳያደርግ ያለአግባብ የከፈለውን ገንዖብ ወጪ ከተደረገበት ጊዚ አንስቶ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍል ተብል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
አመልካች በበኩለ በቀን ጥር 22 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፍ በሰጠው መልስ የቼኩ ክፍያ የቀረበው ለወጋገን ባንክ ቦላ ቅርንጫፍ ሲሆን በቅድሚያ የታዖዖው ኃይለማርያም አርያም ለተባለ ግለሰብ ነው፤ በኋላም ተላልፍ ወይም በጀርባ ተፈርሞ የተከፈለው ከድጃ አብደራህማን ለተባለች ግለሰብ ወጋገን ባንክ ቦላ መድኃኒዓለም ቅርንጫፍ በከፈተችው 49230101 በሆነ ሂሳብ አማካኝነት ነው፤ ወጋገን ባንክ የላከው ቼክ ትክክለኛ እና ለክፍያ ብቁ ስለመሆኑ በቼኩ ጀርባ ላይ በባንኩ ሰራተኞች ፊርማ ለክፍያ ማረጋገጫ የሚሆነውን ለማስገባት ተቀብለናል የሚል ማህተም ቼኩ ላይ ተመቶበት ነበር፤ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ቼክም ሆነ የክፍያ ማረጋገጫ ሰነደን የተለያዩ ቅፆችን በመሙላት ጥርጣሬዎችን በመዛጋት በደንበኛው ጉዲይ ላይ እምነት እንዱኖረን በማድረግ ክፍያውን እንድንፈጽም ያደረገ በመሆኑ ኃፉነት ያለበት ወጋገን ባንክ ነው፤ 1ኛ ተጠሪ ሂሳቡን እንዱያንቀሳቅሱ የፈቀደላቸውን ግለሰቦች ያሳወቀን ሲሆን በቼኩ ላይ ያለው ፊርማ እና ግለሰቦቹ የሰጡት ናሙና የፊርማ ተመሳሳይ ነው፤ ፊርማውን በእይታ ብቻ ከማመሳከር ባለፈ የምናረጋግጥበት የተለየ የቴክኒክ መሳሪያ የለንም፤ ክፍያውን የፈፀምነውም የተለመደውን አሰራር ተከትለን ሲሆን ክፍያውን ለማረጋገጥ ለአመልካች ስልክ ለመደወል ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ የሂሳብ እንቅስቃሴውን የሚያሳይ የሂሳብ መግለጫ ለ1ኛ ተጠሪ የተላከለት ቢሆንም በ15 ቀን ውስጥ ቅሬታውን አልገለፀም፤
ይህም በወጪና ገቢው ላይ የተስማማ መሆኑን ያሳያል፤ ስለሆነም ከሳሽ ራሱ ኃላፉ ነው ወይም ጣልቃ ገቦችን ከሶ መጠየቅ አለበት ከሚባል በስተቀር ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክሯል።
በአመልካች ጠያቂነት 2ኛ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብቶ ባቀረበው መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቼክ 1ኛ ተጠሪ በአመልካች ባንክ በከፈቱት ሂሳብ ላይ የተሰጠ ሲሆን በተለመደው አሰራር የቼኩን ትክክለኛነት እና የፈራሚዎቹን ማንነት ማረጋገጥ ያለበት አመልካች ነው፤ እኛ የቼኩን ትክክለኛነት እና ለክፍያ ብቁ መሆኑን ልናረጋግጥ የምንችልበት አግባብ የለም፤
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ የተከፈለው Real Time Gross Settlement በተባለ እና በኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ በተቀረፀ ስርዓት ነው፤ ስርዓቱ እንድ ቼክ እንዱከፈለው የታዖዖለት ሰው ሂሳብ ወደ ከፈተበት ባንክ በመቅረብ ክፍያው ወደ ሂሳቡ እንዱከፈል ቼኩን ለባንኩ የሚያስረክብበት እና ቼኩን የተቀበለው ባንክ ደግሞ እንዱከፈል ለታዖዖው ባንክ በመስጠት ከፊዩ ባንክ የቼኩን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኋላ ክፍያ የሚፈፀምበት ስርዓት ነው፤ ቼኩን የተቀበለው ባንክ በቼኩ ጀርባ ላይ ማህተም የሚያደርግ እና ቼኩን ከተከፊዩ ላይ የተቀበለ ስለመሆኑም የማረጋገጫ ሰነድ መስጠቱ ብቻውን የቼኩን ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ አይደለም፤ ስለሆነም ኃለፉነት የለብንም በማለት ተከራክሯል። ላልቹን ጣልቃገቦች በሚመለከት ሉቀርቡ ባለመቻላቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱቀጥል ትዔዙዛ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዘህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች በቼኩ ላይ የተመለከተዉን ገንዖብ ለአቅራቢዎቹ ከመክፈለ በፉት ለክፍያ በቀረበዉ ቼክ ላይ የሰፈረዉ ፊርማ 1ኛ ተጠሪን በመወከል በሚፈርሙት ፈራሚዎች የተፈረመ መሆን ያለመሆኑን የማረጋገጥ ኃላፉነት ያለበት ሲሆን፣ ይህም ለማድረግ የተለየ ሳይንሳዊ አካሄድ አመልካች እንዱከተል ባይጠበቅበትም በቼኩ ላይ የተመለከተዉን ፊርማ የቼኩ ፈራሚዎች ከሰጡት የፊርማ ናሙና አንፃር በዓይን አይቶ ተመሳሳይ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚቻል፤ በዘህ ረገድ ለክፍያ በቀረበዉ ቼክ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ በሲስተም ዉስጥ ካለዉ የፈራሚዎች ፊርማ ናሙና ጉዲዩን በያዖዉ ዲኛ ሲታይ የማይመሳሰል መሆኑን መረዲት እንደሚቻል፤ በዓይን እይታ የማይመሳሰል መሆኑን መረዲት እየተቻለ በቸልተኝነት ክፍያዉን በመፈጸም የአመልካች ባንክ በፈጸመዉ ጥፊት ለ1ኛ ተጠሪ ኃላፉነት አለበት። 2ኛ ተጠሪ የክፍያ ማረጋገጫ ደብዲቤ ለአመልካች የላከለት 2ኛ ተጠሪ ስለመሆኑ ባያከራክርም 2ኛ ተጠሪ የ1ኛ ተጠሪን ገንዖብ በአደራ አስቀምጦ በቀጥታ ክፍያ የፈፀመ ባለመሆኑ የቼኩን ትክክለኛነት የማረጋገጥ ግዳታ የለበትም፤ ላረጋግጥ ቢልም የቼኩ ፈራሚዎች የፊርማ ናሙና ስለላለው አይችልም፤ 2ኛ ተጠሪ የማይመለከተውንና የማይችለውን ነገር ለምን አላደረግክም ተብል ኃላፉነት አለብህ ልባል የሚችልበት የህግ ወይም የውል ምክንያትም የለም፤ የስር 2ኛ እና 3ኛ ጣልቃ-ገቦች አከራካሪውን ገንዖብ የወሰደት በሃሰት የተዖጋጀ ቼክ እና የክፍያ ማረጋገጫ ደብዲቤዎችን ተጠቅመው ስለመሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን ግለሰቦቹ ቀርበው አላስተባለም፤ አመልካችም በንግድ ህግ ቁጥር 898(1) እና በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2786(1) መሰረት ገንዖቡን የመክፈል ኃላፉነት አለበት፤ የኃላፉነቱን ሁኔታ በሚመለከት ሶስቱም ማለትም አመልካች፣ የስር 2ኛ እና 3ኛ ጣልቃ-ገቦች በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት አለባቸው በማለት ወስኗል። አመልካች በዘህ ውሳኔ ባለማስማማት ይግባኙን ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው ተሰርዜበታል። ለዘህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች በጳጉሜን 03 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው 06 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈጽመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዖርዖር በዘህ ችልት እንዱታረሙለት ጠይቋል። የአቤቱታው ይዖትም በአጭሩ ገንዖቡን ስንከፍል በተለመደው አሰራር እና በህጉ መሰረት የቼኩን ትክክለኛነት በማረጋገጥ፣ በቼኩ ላይ ያለውን ፊርማ የ1ኛ ተጠሪ ፈራሚዎች ከሰጡት ናሙና ጋር በአይን እይታ በማመሳከር ከፍለን እንዱሁም ይህንኑ የሚሳይ የሰነድ ማስረጃ አቅርበን እያለ ማስረጃ እንዲልቀረበ ተደርጎ ውሳኔ መሰጠቱ፤ 2ኛ ተጠሪ የደንበኛዬን አድራሻ እና ማንነት አረጋግጫለሁ በማለት መሃተብ መትቶ ለአመልካች ልኮ እያለ የአንደኛ ተጠሪን ገንዖብ በአደራ አስቀምጦ በቀጥታ የከፈለ ባለመሆኑ የቼኩን ትክክለኛነት የማረገገጥ ግዳታ ስለላበት ኃላፉነት የለበትም መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርመሮ የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተጠሪን ከኃላፉነት ነፃ ያደረገበት አግባብ መጣራት አለበት ተብል ለዘህ ሰበር ችልት ቀርቧል። በዘሁም መሰረት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ 1ኛ ተጠሪ በቀን 22/05/2011 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ የሰበር አመልካቹ የቼክ ሰነደ ከ1ኛ ተጠሪ እጅ ጠፍቶ ነበረ በማለት በስር ፍርድ ቤት ያላነሳውን የፍሬ ነገር መከራከሪያ ነጥብ በማንሳት መከራከሩ ስነ-ስርዓታዊ አይደለም፤
ያነሳቸው የቅሬታ ነጥቦችም ፍሬ ነገርን እና ማስረጃን የሚመለከቱ በመሆኑ ይህ ሰበር ችልት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም፤ ገንዖቡን ለ1ኛ ተጠሪ የመተካት ሙለ ኃላፉነት ያለበት አመልካች ራሱ ነው ሲል የተከራከረ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ በበኩለ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያላነሳውን ክርክር በማንሳት መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ሲል ያቀረበው ክርክር ተገቢነት የለውም፤ አመልካች ባቀረበው አቤቱታ በብሓራዊ ባንክ የወጣውን መመሪያ ቁጥር 46/2010 የትኛውን ድንጋጌ እንደጣሰ ያቀረበው ክርክር የለም፤ በአከራካሪ ቼክ ክፍያ የተፈፀመላትን ግለሰብ ሂሳብ ስንከፍት በመመሪያው መሰረት ሁለንም ቅድመ ሁኔታዎች አሟልተን ነበር፤ በቼኩ ጀርባ ላይ ማህተም ማድረጋችን ብቻውን ዋስትና እንደሰጠን የሚያስቆጥርብን ካለመሆኑም በላይ በብሓራዊ ባንክ መመሪያ ውስጥ የላለ ሃሳብ ነው የሚለ እና ላልች በስር ፍርድ ቤት ያነሳቸውን መከራከሪያዎች በመድገም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቶ ተከራክሯል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዖት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መዛገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም 1ኛ ተጠሪ ባቀረበዉ ክስ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ ተገቢዉን ጥንቃቄ የማድረግ ግዳታዉን ባለመወጣት ተመሳስል ተዖጋጅቶ በቀረበዉ ተመሳሳይ ቁጥር ባለዉ ቼክ ከሂሳቡ ወጪ አድርጎ ለሦስተኛ ወገን የከፈለዉን ገንዖብ አመልካች የመተካት ኃላፉነት ያለበት መሆኑን በመጥቀስ ሲሆን፣ አመልካች የሚከራከረዉ ለክፍያዉ ምክንያት በሆነዉ ቼክ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ በባንክ በዲበረዉ የክፍያ አሰራር መሰረት በዓይን ሲታይ ከ1ኛ ተጠሪ ድርጅት ቼክ ፈራሚዎች የፊርማ ናሙና ጋር ተመሳሳይ መሆኑን በማረጋገጥ እንዱሁም ቼክ አቅራቢዉ (ተከፊዩ) ከ2ኛ ተጠሪ ቼኩንና የክፍያ ማረጋገጫ ይዖዉ ቅጽ ሞልተዉ በማቅረባቸዉ ምክንያት ደንበኛዉን በመተማመን በመሆኑ ኃላፉነቱ የ2ኛ ተጠሪ ነዉ በማለት ይከራከራል። አመልካች ኃላፉነቱ የ2ኛ ተጠሪ መሆኑን ጠቅሶ ወደ ክርክሩ እንዱገባ ባቀረበዉ ጥያቄ መሰረት 2ኛ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ገብቶ ኃላፉነት የለብኝም የሚልባቸዉን ምክንያቶች በዛርዛር በመጥቀስ የተከራከረ ሲሆን፣ ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም በሚል የወሰነ ሲሆን ለዘህ የሰጠዉ ምክንያትም ክፍያዉ የቀረበዉ ለአመልካች ባንክ እንጂ ለ2ኛ ተጠሪ ባንክ በመሆኑ በቼኩ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ የ1ኛ ተጠሪ ፈራሚዎች መሆን ያለመሆኑን አረጋግጦ ክፍያዉን የመፈጸም ኃላፉነት የአመልካች እንጂ የ2ኛ ተጠሪ ኃላፉነት ካለመሆኑም በላይ የቼኩ ፈራሚዎች የፊርማ ናሙና የሚገኛዉ በአመልካች ዖንድ እንጂ በእርሱ ዖንድ ባለመሆኑ 2ኛ በቼኩ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ ከ1ኛ ተጠሪ ቼክ ፈራሚዎች ፊርማ ጋር ተመሳሳይ መሆን ያለመሆኑን ሉያረጋግጥ የሚችልበት ሁኔታ የለም በማለት ነዉ። ከዘህ ሁለ በመነሳት የዘህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልጋቸዉ ጭብጦች፡- 2ኛ ተጠሪን ከኃላፉነት ነፃ በማድረግ የተሰጠዉ ዉሳኔ በአግባቡ ነዉ ወይስ አይደለም?
ለክፍያዉ ምክንያት በሆነዉ ቼክ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ ከ1ኛ ተጠሪ ቼክ ፈራሚዎች ፊርማ ናሙና ጋር አይመሳሰልም የሚል ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የደረሰበት ድምዲሜ የማስረጃ አቀባበል መርህን መሰረት ያደረገ ነዉ ወይ? የሚለ ናቸዉ።
ከመጀመሪያዉ ጭብጥ ስንነሳ፣ እንደሚታወቀዉ አንድ ሰዉ ለላላ ሰዉ በፍትሐብሕር ኃላፉነት የሚኖርበት በህግ ወይም በዉል የተጣለበትን ግዳታ በመጣስ ወይም የተጣለበትን ኃላፉነት ባለመወጣቱ ምክንያቱ ጉዲት ያደረሰ መሆኑ ሲረጋገጥ ነዉ። የፍትሐብሕር ኃላፉነት አለበት በሚል በልላ ሰዉ ላይ ክስ ወይም ክርክር የሚያቀርብ ሰዉ፣ ክሱ ወይም ክርክሩ የቀረበበት ሰዉ ከህግ ወይም ከዉል የመነጨ ኃላፉነት ያለበት መሆኑን የማስረዲት ግዳታ ይኖርበታል።
በዘህ ረገድ አመልካች 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነት አለበት በማለት አጥብቆ የሚከራከረዉ ቼክ አቅራቢዉ ቼኩን እና የክፍያ ማረጋገጫ ሰነደን በመያዛ ተገቢዉን እና ላልች ተያያዣ ቅጽ ሞልቶ ክፍያ እንዱፈጸም ወደ አመልካች ባንክ ለክፍያ ያቀረበዉ 2ኛ ተጠሪ በመሆኑ እና ይህ መሆኑም ጥርጣሬዎችን በመዛጋት በደንበኛዉ ላይ አመልካች እምነት እንዱኖረዉ በማድረግ ለገንዖቡ መከፈል ምክንያት የሆነዉ 2ኛ ተጠሪ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ። ከግራ ቀኝ ክርክር ሂደት መገንዖብ እንደሚቻለዉ 2ኛ ተጠሪ ቼኩን ከደንበኛዉ በመቀበል ለአመልካች ባንክ ሉያስተላልፍ የቻለዉ ብሓራዊ ባንክ በዖረጋዉ Ethiopian Automated Transfer System (EATS) በሚባል ሥርዓት ሲሆን በዘህ ሥርዓት መሰረት የቼኩ ተከፊይ የተሰጠዉን ቼክ ሂሳብ ወዲለዉ እና በዘህ ሥርዓት ዉስጥ ለታቀፈ ባንክ በማቅረብ በቼኩ ላይ የተፃፈዉን ገንዖብ ወደ ሂሳቡ እንዱከፈልለት ቼኩን ሂሳብ ወዲለዉ ባንክ (Requesting Bank) የሚያስረክብበት እና ቼኩን የተቀበለዉም ባንክ ቼኩን ትክክለኛ እና ለክፍያ ብቁ መሆኑን ወይም ክፍያ ለመፈጸም የማያስችል ላላ ማንኛዉም ምክንያት መኖር አለመኖሩን በማረጋገጥ ክፍያ የሚፈጸምበትን ሥርዓት መሰረት በማድረግ ሲሆን በዘህ የክፍያ ሥርዓት መሰረት ቼኩ በተከፊይ የቀረበለት ባንክ ቼኩን ከደንበኛዉ ከመቀበል እና ለከፊይ ባንክ ከማስተላለፍ ዉጪ ቼኩ ትክክለኛና ለክፍያ ብቁ መሆኑን ወይም ክፍያ የማይፈጸምበት ምክንያት መኖር ያለመኖሩን የማረጋገጥ ኃላፉነት እንደላለበት እንዱሁም ቼክ አዉጪዉ የከፊዩ ባንክ ደንበኛ በመሆናቸዉ 2ኛ ተጠሪ የቼኩን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሚችልበት ምንም ዓይነት እድል የላለዉ ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ሙያዊ የምስክርነት ቃል መረጋገጡን 2ኛ ተጠሪ ለዘህ ችልት ባቀረበዉ መልስ የሚከራከር ሲሆን፣ አመልካች በመልስ መልሱ ይህን የተጠሪን ክርክር ክድ አይከራከርም። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ 2ኛ ተጠሪ ቼኩን ከደንበኛዉ በመቀበል ለክፍያ ብቁ መሆኑን አረጋግጦ ለአመልካች ባንክ ማስተላለፈ፣ አመልካች ለቼክ አቅራቢዉ ክፍያ ከመፈጸሙ በፉት ለክፍያ በቀረበዉ ቼክ ላይ የሰፈረ ፊርማ የቼክ አዉጪዉ ፊርማ መሆኑን ለማረጋገጥ ያለበትን ኃላፉነት የሚያስቀር አይደለም። በመሆኑም አመልካች በቼኩ ላይ እንዱተማመን ወይም እንዲይጠራጠር ያደረገዉ 2ኛ ተጠሪ ሞልቶ የላከለት የክፍያ ሰነድ ነዉ በማለት አመልካች የሚያቀርበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም። ስለሆነም 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም።
በሁለተኛነት ወደ ተያዖዉ ጭብጥ ስንመለስ፣ እንደሚታወቀዉ ቼክ የንግድ ወረቀት ከሚባለ አንደ ሲሆን እንደቀረበ የሚከፈል፣ በባንክ ተቀማጭ ሂሳብ ያለዉ ሰዉ ገንዖቡ ለእራሱ ወይም ለላላ ወገን እንዱከፈል ሐተታ የላለዉ ትዔዙዛ የሚሰጥበት፣ ገንዖብን ተክቶ ክፍያን የሚያቀላጥፍ የንግድ ወረቀት ወይም ሰነድ ስለመሆኑ ከንግድ ህጉ አንቀጽ 732፣ 827፣ 828 እና 854 ድንጋጌዎች ይዖት የምንገነዖበዉ ነዉ። በዘህም መሰረት ቼክ የተሰጠዉ ሰዉ ቼኩን ለባንክ በማቅረብ ክፍያ እንዱፈጸምለት የመጠየቅ መብት ያለዉ ሲሆን፣ በቼክ የክፍያ ጥያቄ የቀረበለት ባንክም ቼኩን ያወጣዉ ሰዉ ፊርማን ጨምሮ በቼክ ላይ መገለጽ የሚገባቸዉ ላልች ሁኔታዎች ተሟልቶ የቀረቡ መሆናቸዉን በማረጋገጥ ቼኩ እንደቀረበለት የመክፈል ኃላፉነት እንዲለበት በንግድ ህጉ አንቀጽ 827 እና 854 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዖብ ይቻላል። በቼክ የክፍያ ጥያቄ የቀረበለት ባንክ ክፍያዉን ለአምጪዉ የሚፈጽመዉ በንግድ ህጉ አንቀጽ 896 እና ተከታዮቹ መሰረት በተደረገዉ የአደራ ዉል መሰረት በባንኩ ከተከፈተዉ የደንበኛዉ ሂሳብ በመቀነስ በመሆኑ ክፍያዉን ከመፈጸሙ በፉት ቼኩ ፊርማን ጨምሮ ላልች አስፈላጊ ሁኔታዎችን አሟልቶ የቀረበ መሆን አለመሆኑን በጥንቃቄ በማረጋገጥ የደንበኛዉን መብት እና ጥቅም የመጠበቅ በዉል የተጣለበት ኃላፉነት አለበት። ስለሆነም ባንኩ በአንድ በኩል ቼክ እንደቀረበለት ወዱያዉኑ ክፍያ በመፈጸም የቼክን መሰረታዊ ዓላማ ያገናዖበ አገልግልት የመስጠት ኃላፉነት ሲኖርበት በልላ በኩል ደግሞ ገንዖቡ ከደንበኛዉ ሂሳብ ተቀንሶ ደንበኛዉ ላልታዖዖለት ሰዉ ክፍያ እንዲይፈጸም የማድረግ የደንበኛዉን ጥቅም የመጠበቅ ከዉል የመነጨ ኃላፉነት ይኖርበታል። ይህም ማለት ባንኩ ማድረግ የሚገባዉን ጥንቃቄ ባለማድረግ በቼክ ክፍያ ፈጽሞ ከተገኘ በተከፈለዉ ገንዖብ ልክ ለደንበኛዉ (ለባለ ሂሳቡ) ኃላፉነት ይኖርበታል ማለት ነዉ።
1ኛ ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ ሉያቀርብ የቻለዉም በዘሁ መነሻነት ሲሆን፣ አመልካች ከሂሳቡ (ከ1ኛ ተጠሪ ሂሳብ) ወጪ ተደርጎ ለላላ ሰዉ የተከፈለዉን ገንዖብ ለ1ኛ ተጠሪ ለመተካት ኃላፉነት የሚኖርበት ክፍያዉን የፈጸመዉ በቼኩ ላይ የተመለከተዉን ፊርማ በሲስተሙ ላይ ከተመለከተዉ ፊርማ አንፃር በጥንቃቄ አይቶ እና አመሳክሮ ፊርማዉ 1ኛ ተጠሪን ወክል በቼኩ ላይ የሚፈርም ሰዉ ፊርማ መሆኑን አረጋግጦ መክፈል ሲገባዉ ይህን ሳያደርግ ክፍያዉን መፈጸሙ ሲረጋገጥ ነዉ። በባንክ በተለመደዉ አሰራር መሰረት ባንኩ በቼክ ላይ የተፈረመዉ ፊርማ የቼክ አዉጪዉ ፊርማ መሆኑን የሚያረጋግጠዉ በዓይን እይታ እንጂ ልዩ የፊርማ መመርመሪያ መሣሪያዎችን በመጠቀም አለመሆኑም የሚታወቅ ነዉ። ይህም ማለት ባንኩ በቼኩ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ በዓይን እይታ በሲስተሙ ላይ ካለዉ የፊርማ ናሙና ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን አረጋግጦ መክፈለ ከተረጋገጠ ምንም እንኳ ክፍያዉ የተፈጸመዉ ለማይገባዉ ሰዉ ወይም ተመሳስል በቀረበ ፊርማ መነሻነት መሆኑ ቢረጋገጥም ኃላፉነት አይኖርበትም። “መቃወሚያ ሳይቀርብበት፣ በቅን ልቦና እና ለስራ አፈፃፀም በተለመደዉ አኳያ ቼክ የከፈለ ከፊይ በሚገባ ነፃ እንደወጣ ይቆጠራል (A drawee who in the absence of objection pay a cheque in good faith and in accordance with normal business practice shall be deemed to be validly discharged)” በሚል በንግድ ህጉ አንቀጽ 861 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌም ይህንኑ የሚያስገነዛብ ነዉ።
የስር ፍርድ ቤት አመልካች ኃላፉነት አለበት በሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰዉ በአመልካች ባንክ ሲስተም ዉስጥ የሚገኘዉን የ1ኛ ተጠሪ ቼክ ፈራሚዎችን የፊርማ ናሙና ክፍያዉ በተፈጸመበት ቼክ ላይ ከሰፈረዉ ፊርማ ጋር የሚመሳሰል መሆኑ አለመሆኑን ዲኛዉ እራሳቸዉ በዓይን በማየት ፊርማዎቹ አይመሳሰለም በማለት ስለመሆኑ ከዉሳኔዉ ይዖት መገንዖብ ይቻላል። በእርግጥ ከላይ እንደተገለጸዉ አመልካች በቼክ በቀረበለት የክፍያ ጥያቄ መሰረት ክፍያዉን ከመፈጸሙ በፉት በቼኩ ላይ የሰፈረዉ ፊርማ በሲስተሙ ላይ ከተመለከተዉ የአዉጪዉ የፊርማ ናሙና ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑ የሚረጋገጠዉ በአይን እይታ እንጂ በልላ የመመርመሪያ ማሽን አይደለም። ክፍያዉን የሚፈጽም ባንክ በቼኩ ላይ ያለዉን ፊርማ ከናሙናዉ ፊርማ ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑን በማረጋገጥ ባንኩ ክፍያዉን የፈጸመዉ ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ መሆን አለመሆኑ የሚረጋገጠዉ በምክንያታዊ ሰዉ እይታ ነዉ። ጥያቄዉ ጉዲዩን የተመለከተዉ ዲኛ በእራሱ እይታ ፊርማዉ የሚመሳሰል መሆን ያለመሆኑን መለየት የመቻለ ጉዲይ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ በክርክር ሂደት የተያዖ የፍሬ ነገር ጭብጥ የሚረጋገጠዉ በማስረጃ ነዉ።
ማስረጃ ሳይቀርብበት ፍርድ ቤቶች በአንድ የፍሬ ነገር ድምዲሜ ላይ መድረስ የሚችለት የፍሬ ነገር ጭብጡ በባህርዉ ፍርድ ቤቶች ግንዙቤ ሉወስደበት የሚችለ (judicial notice) ዓይነት ሲሆን ብቻ ስለመሆኑ ከማስረጃ አቀራረብ እና ምዖና አጠቃላይ መርህ እንዱሁም በፍርድ ቤቶች ከዲበረዉ ልምድ የምንገነዖበዉ ነዉ። በተያዖዉ ጉዲይ አከራካሪዉ ጭብጥ በቀረበዉ ቼክ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ በሲስተሙ ላይ ከተመለከተዉ ፊርማ ጋር ተመሳሳይ አለመሆኑን በዓይን አይቶ መለየት የሚቻል መሆን አለመሆኑ ነዉ። በመሰረቱ የሰነድ ማስረጃ ማለት በላዩ ላይ የተፃፈበት፣ የተሳለበት፣ ወይም ማናቸዉም ዓይነት ምልክት የተደረገበት ወይም ድምጽ የተቀዲበት ወይም ድምጽና ምስል የተቀረጸበት ሆኖ ለአስረጅነት የሚቀርበዉም እንደሁኔታዉ የተፃፈዉ ጽሐፍ፣ የተሳለዉ ስዔል፣ ወይም የተደረገዉ ምልክት ወይም የተቀረጸዉ ድምጽ ወይም ምስል ወይም ማናቸዉም ነገር ላሆን ይችላል። ማስረጃዉን የሰነድ ማስረጃ የሚያሰኘዉም ወረቀትነቱ ወይም ካሴትነቱ ሳይሆን ለማስረጃነት ተፈልጎ ለፍርድ ቤት የሚቀርበዉ እና ፍርድ ቤት የሚመለከተዉ ፍሬ ነገር በወረቀት፣ ካሴት እና ወዖተ ላይ ሰፍሮ መገኘቱ ነዉ። ከዘህም የሰነድ ማስረጃ ሁለት መሰረታዊ ባህርያት ያለት መሆኑን መገንዖብ ይቻላል። የመጀመሪያዉ ወረቀቱ ወይም ካሴቱ ተፈላጊዉን ፍሬ ነገር መያዛ አለመያዘ ሲሆን፣ ሁለተኛዉ ሰነደ የሚይዖዉ ፍሬ ነገር ፍርድ ቤቱ ለያዖዉ ጭብጥ አግባብነት ያለዉ እና የማስረዲት ብቃቱ ነዉ። ይህ በመሆኑም ከሰነድ ማስረጃ ጋር በተያያዖ አንድም የሰነደን ይዖት (ሰነደ የተፈለገዉን ፍሬ ነገር በእርግጥም የያዖ መሆን አለመሆኑ) ሁለትም በሰነደ ላይ መኖሩ የተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር በፍርድ ቤቱ የተያዖዉን ጭብጥ ሉያስረዲ የሚችል መሆን አለመሆኑ ነዉ። ስለሆነም ክርክሩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የያዖዉን የፍሬ ነገር ጭብጥ የሚያስረዲ መሆን አለመሆኑን የሰነድ ማስረጃዉ መመርመር እና የመመዖን ኃላፉነት እንዲለበት ሁለ ከሰነደ ይዖት ጋር በተያያዖ ክርክር ሲኖርም ይህንኑ በጭብጥነት በመያዛ (የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 248/ለ/ ይመለከቷል) መርምሮ እና መዛኖ ሰነደ የያዖዉን ፍሬ ነገር ትክክለኛነት አረጋግጦ ከድምዲሜ ላይ የመድረስ ኃላፉነትም የፍርድ ቤት ሲሆን ይህን የሚያደርገዉም የተለያዩ ማስረጃዎችን በመመርመር እንጂ እራሱ ግምት በመዉሰድ አይደለም። በማስረጃ መረጋገጥ የሚገባዉን ነገር በእራስ ግምት መዉሰድ ፍርድ ቤቱን እራሱ አስረጂ እራሱ ፈራጅ እንደሆነ የሚያስገምተዉ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ይህን እንዱያደርጉ አይጠበቁም።
ከዘህ አንፃር የተያዖዉን ጉዲይ ስንመለከት አመልካች በቼኩ ላይ የተፈረመ ፊርማ በፊርማ ናሙናዉ ላይ ከተመለከተዉ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን በማረጋገጥ ክፍያ ፈጽማለሁ በማለት የሚከራከር ከመሆኑ አንፃር በቼኩ ላይ የተፈረመዉ ፊርማ በእርግጥም ከፊርማ ናሙናዉ ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለመሆኑ በጉዲዩ ላይ ዉሳኔ ለመስጠት በማስረጃ መረጋገጥ የሚገባዉ ጭብጥ ነዉ። ይህን ለማረጋገጥ በአስረጅነት የቀረበዉ እራሱ ክፍያ የተፈጸመበት ቼክ ሲሆን በቼኩ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ ከናሙና ፊርማ ጋር የሚመሳሰል መሆን አለመሆኑ ገለልተኛ በሆነ አካል ታይቶ የሚረጋገጥ እንጂ ዲኛዉ እራሳቸዉ አይተዉ ግምት ሉወስደበት የሚገባ አይደለም። በመሆኑም በቼኩ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ ከተጠሪ ከተወሰደዉ የፊርማ ናሙና ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለመሆኑን አመልካች በጥንቃቄ የማረጋገጥ ግዳታዉን አልተወጣም በሚል ድምዲሜ ላይ ሉያደርስ የሚያስችል አሳማኝ ምክንያት በላለበት ሁኔታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪ የጠየቀዉን ገንዖብ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ የማስረጃ አቀራረብ እና የምዖና መርህን ያገናዖበ ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዘህ ሁለ ምክንያትም ተከታዩ ዉሳኔ በአብላጫ ድምጽ ተሰጥቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 206237 በቀን ሐምል 22 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽለዋል።
2ኛ ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም በማለት የተሰጠዉ የዉሳኔ ክፍል ጸንቷል፤ ከክርክሩ ዉጪ እንዱሆን ተወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዖግቶ የነበረዉን መዛገብ በማንቀሳቀስ ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ ቼክ ላይ የተመለከተዉ ፊርማ ከ1ኛ ተጠሪ ቼክ ፈራሚዎች የፊርማ ናሙና ጋር በአይን እይታ ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑ በፍርድ ቤቱ ወይም በግራ ቀኝ ወይም በተቻለ መጠን ከአመልካች ባንክ ዉጪ በላልች ባንኮች ከቼክ ክፍያ ጋር በተያያዖ ልምድ ባላቸዉ የባንክ ባለሙያዎች እንዱታይ ካደረገ በኋላ የቀረበለትን ዉጤት መሰረት በማድረግ አመልካች ኃላፉነት ያለበት መሆን አለመሆኑን በተመለከተ የመሰለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 343(3) መሰረት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
ይህ ችልት ህዲር 15 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ እግድ ተነስቷል።
በዘህ ችልት የተደረገው ክርከር ያስከተለውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
ስሜ በተራ ቁጥር 5 ላይ የተጠቀሰው ዲኛ በአብላጫው ድምጽ ከ2ኛ ተጠሪ አንጻር በተሰጠው ውሳኔ የምስማማ ቢሆንም ከ1ኛ ተጠሪ አንጻር የስር ፍርድ ቤት በቼክ ላይ ያለውን ፊርማ በባንክ ለናሙና ከሚገኘው ፊርማ ጋር በራሱ ይመሳሰላል አይመሳሰልም የሚለውን ሰነድቹን በማየት ብቻ ውሳኔ መስጠት አይችልም በሚል እንደገና ሰነድቹ ላይ የሚገኙት ፊርማዎች ከአመልካች ባንክ ውጪ ባለ ላልች ባንኮች ውስጥ በሚሰሩ ሰራተኞች ታይቶ ውጤቱ እንዱቀርብ ከተደረገ በኋላ ወይም በልላ ማስረጃ ተጣርቶ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩ ለስር ፍርድ ቤት ሉመለስ ይገባል በመባለ ባለመስማማት የሚከተለውን የልዩነት ሃሳብ አስፍሬአለው።
አንድ ባንክ ቼክ ለክፍያ ሲቀርብለት ቼኩ በቼክ አውጭው ለክፍያ የታዖዖ ትክክለኛ ቼክ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ክፍያ ከመፈጸሙ በፉት የማጣራት ግዳታ እንዲለበት አከራካሪ አይደለም። አንድ ሰነድ ቼክን ጨምሮ ትክክለኛ መሆኑ የሚጣራው በሰነደ ላይ የሰፈሩትን ጽሁፍች፣ ምልክቶች፣ፊርማዎች እና ላልች በሰነደ ላይ የሰፈሩ ምልክቶችን ትክክለኛነት በማጣራት ነው። በባንክ የተለመደ አሰራር ቼክ ለክፍያ ሲቀርብ የባንኩ ሰራተኛ በቼኩ ላይ ያለውን ፊርማ የቼክ አውጪው መሆኑን በባንኩ በሲስተም ውስጥ ከሚገኘው የቼክ አውጪው የፊርማ ናሙና ጋር በማስተያየት አንድ አይነት መሆኑን ወይም አለመሆኑን በአይን እይታ በማጣራት ክፍያ እንደሚፈጸም ይታወቃል። በተያዖው ጉዲይ አመልካች ለክርክሩ መሰረት የሆነውን ክፍያ በቼክ የፈጸመው ቼኩ ላይ የሚገኘው ፊርማ በባንኩ ከሚገኘው የተጠሪ የፊርማ ናሙና ጋር ተመሳሳይ መሆኑን በአይን እይታ በማጣራት መሆኑን በመግለጽ ክርክር አቅርቧል። አመልካች የሚጠበቅበትን ጥንቃቄ አድርጓል ወይስ አላደረገም ለሚለው እልባት ለመስጠት ጉዲዩን ያየው የስር ፍርድ ቤት አንድም ማጣራት የሚጠበቅበት በቼኩ ላይ የሚገኘው ፊርማ እና በአመልካች ባንክ ውስጥ የሚገኘው የፊርማ ናሙና በአይን ሲታይ ተመሳሳይነት አለው ወይስ የለውም የሚለው ነው። በሁለቱ ሰነድች ላይ የሚገኙት ፊርማዎች ተመሳሳይነት አላቸው ወይስ የላቸውም የሚለውን ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት እራሱ በህግ በተሰጠው ማስረጃን የመመዖን ስልጣን ሰነድቹን በመመልከት እና በመመዖን የሚደርስበት ድምዲሜ እንጂ ከፍርድ ቤት ውጪ ያለ አካል ማስረጃዎቹን መዛኖ ይመሳሰላለ ወይም አይመሳሰለም በሚል የሚሰጠውን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ላሆን አይገባም።
በእርግጥ በሰነድቹ ይዖት ላይ ክርክር ከቀረበ ወይም ፍርድ ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ሰነድቹ የባለሙያ ምርመራ ወይም በፖሉስ የፍረንሲክ ምርመራ እንዱደረግባቸው የማዖዛ ሃላፉነት እንዲለበት ከፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 136 ድንጋጌ መገንዖብ ይቻላል። ይሁን እንጂ በባንክ አሰራር ፊርማ በፍረንሲክ ምርመራ እየተጣራ ክፍያ የመፈጸም አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ የማይቻል በመሆኑ የፍረንሲክ ምርመራ ውጤቱ አመልካች ተገቢውን ጥንቃቄ አለማድረጉን የሚያሳይ ላሆን አይችልም። ይህ የፍረንሲክ ምርመራ ውጤት ለጉዲዩ ተገቢነት ያለው ማስረጃ አይደለም ከተባለ ደግሞ ፍርድ ቤቱ በልላ ባለሙያ ፊርማው እንዱጣራ የማድረግ ሃላፉነት የለበትም።
በአይን እይታ ብቻ በሁለት የተለያዩ ሰነድች ላይ የሚገኙ ፊርማዎች አንድ አይነት መሆኑን ወይም አለመሆኑን ከፍርድ ቤት ውጪ ባለ ሰው እንዱረጋገጥ ማድረግ ፍርድ ቤቱ በህግ የተሰጠውን ማስረጃን የመመዖን ስልጣን ለላላ ማስረጃን ለመመዖን በህግ ስልጣን ለላለው አካል አሳልፍ እንደመስጠት የሚያስቆጥር ነው የሚል እምነት አለኝ። የቀረቡትን ሰነድች በአይን በመመልከት ፊርማው ይመሳሰላል ወይም አይመሳሰልም የሚለውን መመርመር የፍርድ ቤቱ ከማስረጃ ምዖና ጋር የተያያዖ ሃላፉነት የተወጣ መሆኑን ከሚያሳይ በስተቀር ፍርድ ቤቱ እራሱ ምስክር እራሱ ፈራጅ እንደሆነ የሚያስቆጥረው ነው የሚል እምነት ስለላለኝ የስር ፍርድ ቤት እራሱ በቼኩ ላይ ያለው ፊርማ አመልካች ባንክ ውስጥ ከሚገኘው የ1ኛ ተጠሪ ፊርማ ናሙና ጋር በማገናዖብ ተመሳሳይነት የለውም ማለቱ የማስረጃ ምዖና መርህን የተከተለ ነው። በመሆኑም በስር ፍርድ ቤት በአከራካሪው ቼክ ላይ ያለውን ፊርማ በአመልካች ባንክ ከሚገኘው የ1ኛ ተጠሪ ፊርማ ናሙና ጋር በማገናዖብ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የማስረጃ ምዖና መርህ ጥሰት ተፈጽሞበታል የሚያስብል ሆኖ ስላላገኘሁት ውሳኔው ሉጸና ይገባ ነበር በሚል ከአብላጫው ድምጽ በሃሳብ ተለይቻለሁ።
የማይነበብ አንድ ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.