No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- መዓዙ አሸናፉ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ አመልካች፡- ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ተጠሪ፡- የፋዳራል ፖሉስ የምሥራቅ ቀጠና ወንጀል ምርመራ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር መዛገብ ተከፍቶ ላቀርብ የቻለው አመልካች በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ድሬደዋ ምድብ ችልት ባስከበርኩት ንብረት ላይ የተሰጠ እግድ ይነሳልኝ በሚል አቅርቦት የነበረው አቤቱታ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ እና በይግባኝም አለመታረሙ በተሰጠው ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲል አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ ላየው ፍ/ቤት አመልካች አቀርቦት የነበረው አቤቱታ እንደሚያሳየው አቶ ዖሪሁን ላቀው መኮንን ለተባለ ግለሰብ ነሐሴ 29 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም በተፈፀመ የመያዣ ውል መሰረት የሰ.ቁ ኢት 3-755ዐዐ የሆነ ተሽከርካሪን ግለሰቡ በሙስና ወንጀል በወንጀል በተከሰሱ ጊዚ ተጠሪ ይህን መኪና ያሳገደ በመሆኑ በታገደው ንብረት ላይ የቀዲሚነት መብት ስላለው እግደ እንዱነሳለት አመልክቷል።
ፍ/ቤቱም የታገደው ንብረት በሙስና ወንጀል የተገኘ ወይም በወንጀል በተገኘ ንብረት የተፈራ መሆን አለመሆኑ ገና ውሣኔ ያላረፈበት በመሆኑ በሙስና የተገኘ ወይም በሙስና በተገኘ ንብረት የተፈራ ከሆነ ደግሞ የተከሣሹ ንብረት ነው ለማለት ስለማይቻል ከወዱሁ ለባንኩ ዔዲ መክፈያ ይሸጥ በሚል የዔግድ ትዔዙዘን ለማንሳት አይቻልም በሚል አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ ትዔዙዛ ሰጥቷል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ትዔዙዛ ቅር ተሰኝቶ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቅሬታውን ያቀረበ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ግራ ቀኙን አስቀርቦ እና ጉዲዩን መርምሮ ንብረቱ በሙስና ወንጀል ወይንም በወንጀል የተፈራ በሚል ጥርጣሬ የታገደ ከመሆኑ አኳየ የሙሰና ወንጀል ክርክሩ የመጨረሻ እልባት ባላገኘበት የንብረቱ እግድ የሚነሳበት አግባብ የለም በማለት የስር ፍ/ቤት ትዔዙዛን በማጽናት ወስኗል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት በተሰጠው ፍርድ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ይታረምልኝ ሲል ነሐሴ 2ዐ ቀን 2ዐ11 ዓ.ም. የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። የአቤቱታው ይዖትም በአጭሩ፡- ባንኩ ለግለሰቡ ለሰጠው የብር 715ዐዐዐ.ዐዐ ብድር ተመላሽ የሰ.ቁ. ዐ3-755ዐዐ የሆነው ተሽከርካሪ በመያዣነት ይዝል።ተሽከርካሪው በመያዣ የተያዖው የብድር ገንዖቡ ባይመለስ መኪናውን ሽጦ ገንዖቡን ለማስመለስ በመሆኑ፣ ብድሩን ሲሰጥ ንብረቱን አሳግድ የቀዲሚነት መብት በንብረቱ ላይ ያለው በመሆኑ ሸጦ ለብድር መክፈያ እንዱያውለው እግድ እንዱነሳለት ጠይቋል።
ንብረቱን እንዱመዖግብልን የፋዳራል ት/ባ/የአ/አ/ት/ቅ/መ/ቤት አቃቂ ቃሉቲ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት አመልክተንም ቅ/ጽ/ቤቱ የባንኩን የመያዛ መብት በቀዲሚነት በዐ2/13/2ዐዐ7 ዓ.ም. አረጋግጦ የመዖገበ በመሆኑ ገንዖቡን በብድር ሰጥቷል።
የስር ፍ/ቤት እግደ አይነሳም ሲል የሰጠው ትዔዙዛ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 16/ 3/ ስር ከተቀመጠው የእግድ ትዔዙዛ እንዱነሳ ወይም እንዱሻሻል ላደረግ እንደሚችል ከተደነገገው ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ጉዲዩ የመጨረሻ እልባት ባያገኝም በበቂ ምክንያት ላይ የተመሰረተ ከሆነ ፍ/ቤቱ ሉወስን እንደሚሽል የሚደነግግ ስለሆነ ከዘህ አንፃር ሉመለከትልን ሲገባ፣ የፍ/ቤቱ ትዔዙዛ አስቀድሞ ትርጉም ከተሰጠበት የሰ/መ/ቁ/ 81215 ጋር የሚቃረን በመሆኑ፣ አመልካች የመያዡ መብቱን ያስመዖገበው ጰጉሜን ዐ2 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም. ሆኖ ፍ/ቤቱ እግድ የሰጠው ደግሞ ግንቦት 28 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. በመሆኑና ንብረቱን አስቀድሞ አመልካች ካሳገደ በኋላ መሆኑ፣ ባንኩ ንብረቱን ሲያሳግድ ከማንም አካል በንብረቱ ላይ እግድ የላለ መሆኑ ሰበር አስቀድሞ ትርጉም ከሰጠበት የሰ/መ/ቁ/ 16218 ጋር ተገናዛቦ መወሰን ሲገባው እግድ አይነሳም ተብል መወሰኑ ስህተት በመሆኑ ሉታረምልን ይገባል ሲል ጠይቋል።
አቤቱታው በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ አመልካች አቶ ዖሪሁን ላቀው ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዡ ውል መሰረት ተበዲሪ ያስያዖው ተሽከርካሪ ላይ የተሰጠው የእግድ ትዔዙዛ እንዱነሳለት አመልካች ያቀረበው አቤቱታ በስር ፍ/ቤት ውድቅ የተደረገበትን አግባብነት ከሰ/መ/ቁ/ 81215 ከተሰጠው ትርጉም አንፃር ለመመርመር ሲባል መልስ ሰጪን ያስቀርባል ተብል ጭብጥ በመያዘ መነሻነት መዛገቡ ለችልቱ ላቀርብ ችሎል።
አቤቱታው ከማስቀረቢያ ነጥቡ ጋር ለተጠሪ ደርሶት መለሰ እንዱያቀርብ መጥሪያ ቢላክለትም ሳይቀርብ በመቅረቱ መለሰ የማቅረብ መብቱ ታልፎል። የፋ/ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በክርክሩ ጣልቃ ልግባ ሲል አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም በስር ፍ/ቤት ተከራካሪ ያልነበረ በመሆኑ በሰበር ደረጃ ጣልቃ ልግባ ሲል ያቀረበውን አቤቱታ ችልቱ ስላልተቀበለው ውድቅ አድርጏታል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበውን አቤቱታ ከስር ፍ/ቤት ትዔዙዛ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች አቀርቦት የነበረው አቤቱታ እንደሚያሳየው አቶ ዖሪሁን ላቀው መኮንን ለተባለ ግለሰብ ነሐሴ 29 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም በተፈፀመ የመያዣ ውል መሰረት የሰ.ቁ ኢት 3-755ዐዐ የሆነ ተሽከርካሪን ግለሰቡ በሙስና ወንጀል በወንጀል በተከሰሱ ጊዚ ተጠሪ ይህን መኪና ያሳገደ በመሆኑ ከመከሰሱና ተጠሪ ንብረቱን ከማሳደ አስቀድሞ በታገደው ንብረት ላይ የቀዲሚነት መብት ስላለው እግደ እንዱነሳለት አመልክቷል።
ከማስቀረቢያ ነጥቡ አንፃር አመልካች በተሽከርካሪው ላይ የተሰጠው የእግድ ትዔዙዛ እንዱነሳለተ ያቀረበው አቤቱታ በስር ፍ/ቤት ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው ወይንስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ በሰበር ደረጃ በጭብጥነት ተይዜ ሉመረመር የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
በአንድ በማይንቀሳቀስ እና ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ በሕግ አግባብ የተቋቋመ የመያዡ መብት በሕግ ጥበቃ የሚደረግለት ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር የፍ/ሕ/ቁጥር 2828፣2857/1/ እና 3059 ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዖት ያሳያለ። በሕግ አግባብ የተቋቋመው የመያዡ ውል መኖሩ ከተረጋገጠ ደግሞ ይኼው መብት ያለው ሰው ከላላው ሰው የቀደመ መብት ያለው መሆኑን የድንጋጌዎቹ ጣምራ ንባብ ያስረዲል። በባንክ በመያዡ ስለተያዘ የማይንቀሳቀሱ የሚንቀሳቀሰ ንብረቶችን አስመልክቶ በወጣው አዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 3 ሲታዩ ደግሞ ባንክ በመያዡ የያዙቸውን ንብረቶች እዲው ሳይከፈለው በቀረ ጊዚ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ለተበዲሪው በመስጠት ያለማንም ጣልቃ ገብነት በመያዡ የያዖውን ንብረት በመሸጥ ገንዖቡን ገቢ ማድረግ እና ከዘህም ላላ መያዡ የተቀበለ ባለገንዖብ ከመያዡው ሽያጭ ዋጋ ከላልች ባለገንዜቦች ቀድሞ የመቀበል መብት እንዲለውም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2857/1/ ላይ ተደንግጓል። ከእነዘህ ድንጋጌዎች አንጻር አመልካች ለብድር አከፊፈል በመያዡነት በያዖው ንብረት ላይ የቀደምትነት መብት እንዲለው መገንዖብ ይቻላል።
ወደያዛነው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ አቶ ዖሪሁን ላቀው መኮንን የተባለ ግለሰብን በሙስና ወንጀል የከሰሰ ሲሆን ለንብረት ማካካሻ ይሆን ዖንድ በግለሰቡ ስም ተመዛግቦ የሚገኘውን እና አመልካች አስቀድሞ ግለሰቡ ለተበደሩት 715,ዐዐዐ.ዐዐ የዔዲ አመላለስ በሚል በመያቸዡነት የያዖውን የሰ.ቁ. ዐ3-755ዐዐ ኢት ተሽከርካሪን በፍ/ቤት አሳግዶል።
የአመልካች ጥያቄም ለዔዲ መክፈያነት የያዛኩትን ንብረት ዔግድ የተሰጠበት በመሆኑ ዔግደ ተነስቶልኝ ሸጨ ዔዲውን ተመላሽ ላድርግ የሚል ነው።
አመልካች ለግለሰቡ ብድሩን የሰጠው ለእዲው መልካም አመላለስ ይረዲው ዖንድ ተሽከርካሪውን በመያዡ የያዖው በንብረቱ ላይ ምንም ዓይነት ዔዲ እና እገዲ የላለበት መሆኑን አጣርቶ ከመሆኑም በላይ በግለሰቡ ላይ ተጠሪ ክስ የመሰረተውም ብድሩ ከተሰጠ በኋላ መሆኑ የሚያከራክር ሆኖ አልተገኘም።
በዘህ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 81215 መዛገብ ላይ በባንክ በመያዡነት የተያዖ ተሽከርካሪ በልላ በኩል የጉምሩክ ደንብ በመተላለፍ ወንጀል ባለቤቱ ጥፊተኛነቱ ተረጋግጦበት ተሽከርካሪውም በመንግስት እንዱወረስ ውሣኔ የተሰጠበት እንደሆነ በህግ ፉት ቅድሚያ ተሰጥቶት ሉፈፀም ስለሚገባው ጉዲይ. በባንክ በመያዡነት የተያዖ ተሽከርካሪ ከመያዡው በኋላ በኮንትሮባንድ ወንጀል ምክንያት ለመንግስት ውርስ እንዱሆን በፍ/ቤት የመጨረሻ ፍርድ ባረፈበት ጊዚ ባለመያዡው ንብረቱን በመያዡነት የያዖው አካል የቀዲሚነት መብት ያለው መሆኑን በመግለጽ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።
ይህ ከሆነ ደግሞ ከላይ እንደተመለከትነው የፍ/ብ/ሕ/ ድንጋጌዎቹ ስለመያዡ መብት የደነገጉትን ስንመለከት እና ሰበር ከሰጠው ትርጉም አኳያ ባንኩ በያዖው ንብረት ላይ የቀዲሚነት መብት ያለው መሆኑን የሚያሳዩ በመሆኑ የሰላዲ ቁጥሩ በተጠቀሰው ንብረት ላይ አመልካች የቀደምትነት መብት ይኖረዋል። በመሆኑም አስቀድሞ አመልካች/ ባንኩ/ ለዔዲው መልካም አመላለስ ሲል በንብረቱ ላይ ላላ ጠያቂ የላለበት መሆኑን አረጋግጦ ብድር ያበደረ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ አንድ ጊዚ ንብረቱን በመያዡነት ከመዖገበ እና ገንዖቡን ወጪ አድርጏ ለተበዲሪው ከከፈለ በኋላ ላላ ገንዖብ ጠያቂ ካለ በህግ በተሰጠው የቀደምትነት መብት ደረጃ መሰረት ከሚጠይቅ በቀር ባንኩ ባስከበረው ንብረት ላይ ዔግድ በማሰጠቱ ብቻ ባንኩ የቀደምትነት መብቱን የሚያጣበት ህጋዊ ምክንያት የላለ በመሆኑ ባንኩ ተሽከርካሪው በሙስና በተገኘ ገንዖብ የተገዙ መሆኑን አስቀድሞ ያውቅ እንደነበረ ካልተረጋገጠ በቀር በስር ፍ/ቤቶች በንብረቱ ላይ የተሰጠው ዔግድ ሉነሳ አይገባም ሲለ የደረሱበት መደምደሚያ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው ብለን ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/171ዐ66 በ12/11/2ዐ11 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 12782 ታህሳስ 15 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ለብድር ዔዲ መያዡነት በያዖው የአቶ ዖሪሁን ላቀው መኮንን ንብረት የሰ.ቁ. ኢት-3- 75599 በሆነው ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ላይ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክር እየተደረገበት ባለው የመ/ቁ/ 12782 በሆነው መዛገብ ላይ የተሰጠው ዔግድ ሉነሳ ይገባል ብለን ወስነናል።
የሚያከራክረው መኪና በሙስና የተገኘ ነው የሚባል ከሆነ መኪናው ተሽጦ አመልካች ከሚፈልገው የዔዲ ተመላሽ ተራፉ ገንዖብ ካለ እና በግለሰቡ ላይ የወንጀል ጥፊተኝነት ውሣኔ ከተሰጠ ተጠሪ የተረፈውን ገንዖብ የመጠየቅ እንዱሁም የተሽከርካሪውን ቀሪ ዋጋ ያክል ከተሽከርካሪው ባለንብረት ላላ ንብረት ላይ የመጠየቅ መብቱን ይህ ውሣኔ አያግደውም ብለናል።
ግራ ቀኙ በዘህ ሰበር ሰሚ ችልት ያወጡት ወጪ ካለ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
መዛገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፉሪማ አለበት
No topics extracted.