No summary available.
መስከረም 30/2009ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች (ቾች)፡- 1. አቶ ስማቸው ከበደ ጠበቃ - ስንደ ዓለሙ - ቀረቡ 2. ጂ.ኤች.ሲሚክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተጠሪ(ዎች) ፡- ኢንተርኮንቲኔታል ሆቴልስ ኮርፖሬሽን - ጠበቃ ኢዮብ ሐጎስ - ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
የጉዲዩ መነሻ የሆነው ክርክር የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት ተጠሪ ከሳሽ፤አመልካቾች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ይዖት ፤ በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 26 መሰረት በወቅቱ የንግድ ምልክት ምዛገባ ይሰጥ ከነበረው ከኢትዮጵያ ንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ከዘያም በኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት እስከ መሥከረም 21 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ ታድሶ የሚገኝ ለ3ኛ ወገን የሆቴል አገልግልት ለመስጠት የሚያችለው እና በኢትዮጵያ ግዙት ውስጥ ብቸኛ ባለቤት እና ተጠቃሚ የሚያደርገው ቁጥር 3741 የሆነ የንግድ ምልክት ሰርትፍኬት የተሰጠው መሆኑን፤
አመልካቾች በአዱስ አበባ ከተማ ኢንተርኮንቲኔንታል አዱስ አበባ ሆቴል በሚል ስም የሚታወቅ ሆቴል ያቋቋሙ እና ያስመዖገቡ መሆኑን፤ አመልካቾች በተጠሪው የንግድ ምልክት ስም በዖረጉት ድህረገጽ በአዱስ አበባ አለምዓቀፍ ኤርፖርት የውጭ እንግድች መግቢያ በር ላይ በመለጠፍ እና መጓጓዡ በማቅረብ በተጠሪው የንግድ ምልክት ከህግ ውጪ አላግባብ በመጠቀም ላይ መሆናቸውን ገልጾ አመልካች በንግድ ምልክቱ መጠቀም እንዱያቆሙ፤
በተለያዩ ዔቃዎች እና በየቦታው ያለትን የንግድ ምልክቶች እንዱያስወግደ፤ በተጠሪው የንግድ ምልክት ሥም የከፈቱትን ድሕረገጽ እንዱዖጉ እና ሆቴለ ከተቋቋመበት ጀምሮ ያገኙትን የተጣራ ትርፍ እንዱከፍለ እንዱወሰንባቸው ዲኝነት የጠየቀ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
አመልካቾች ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት መልስ ተጠሪው የሕግ ሰውነት ስለላለው ክስ ለመመለስ የሚያስችል መብት የለውም፤ በሁለት ዓመት ጊዚ ውስጥ ስላልቀረበ በይርጋ ይታገዲል፤ የንግድ ምልክቶቹም የተለያዩ ናቸው፤ ትክክለኛው የካሳ መጠንም በክሱ አልተመለከተም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል። በፍሬ ነገሩም ላይ ዛርዛር መልስ ሰጥተዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍ/ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ የንግድ ድርጅት ሕጋዊ ሰውነት ያገኝ ዖንድ መመዛገቡ አስፈላጊ ነው። ተጠሪው በንግድ መዛገብ ካልተመዖገበ በቀር የንግድ ምልክት ሰርተፍኬት መያዘ ብቻ ሕጋዊ ሰውነት ሉያሰጠው አይችልም ። ተጠሪው በክስ ማመልከቻው ላይ በተገለጸው አድራሻ ላይ በተመለከተው ሐገር ሕግ መሰረት ተመዛግቦ ሕጋዊ ህልውና ያገኘ መሆኑን ገልጾ ያቀረበው ክርክር ሆነ ማስረጃ የለም። በመሆኑም ተጠሪ የሕግ ሰውነት የላለው ድርጅት በመሆኑ መክሰስም ሆነ መከሰስ አይችልም በማለት ክሱን በብይን ውድቅ አድርጎታል።
ተጠሪ በዘህ ብይን ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቧል። አመልካቾችም በበኩላቸው በሥር ፍ/ቤት ያቀረብናቸው ላልች መቃወሚያዎች ያልተስተባበለ እና የሥር ፍ/ቤትም ላልች መቃወሚያዎች ላይ ብይን ሳይሰጥ ያለፈ በመሆኑ በላልቹ መቃወሚያዎች ምክንያት ክሱ ተቀባይነት የለውም እዱባልልን በማለት መስቀለኛ ይግባኝ አቅርበዋል።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የግራቀኙን አቤቱታ ከመረመረ እና ተጠሪ በውጪ አገር ሕጋዊ ሰውነት የተሰጠው መሆኑን የሚያረጋግጥለትን ማስረጃ በትዔዙዛ ካስቀረበ በኃላ ተጠሪ በውጪ አገር ሕግ መሰረት የህግ ሰውነት የተሰጠው በመሆኑ እና የንግድ ምልክቱንም በባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ያስመዖገበ በመሆኑ ከንግድ ምልክቱ ጋር በተያያዖ መብቱን ለማስከበር ክስ የማቀርብበት ምክንያት የለም በማለት የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ብይን ሽሮ የስር ፍ/ቤት በቀሪ መቃወሚያዎች ላይ ብይን በመስጠት ክሱ የሚቀጥል ሆኖ ካገኘው ግራቀኙን በፍሬ ጉዲይ ላይ አከራክሮ የመሰለውን ይወስናል በማለት ጉዲዩን መልሶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡- በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ወይም ያልተመዖገበ ንግድ ያለው እንደ ኢትዮጰያ ተቆጥሮ በንግድ ምልክት ምዛገባ ወረቀቱ ሉሰራበት የሚችለው ተመዛግቤበታለሁ ከሚለው ላላ ሀገር ጋር ኢትዮጵያ የእንካ ለእንካ ሥምምነት ከኖራት ወይም ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት ዓለም አቀፍ ውል ካለ ብቻ ነው። ተጠሪ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የእንካ ለእንካ ስምምነት አላቸው አላለም፤ የንግድ ማህበራት የሕግ ሰውነት ማግኘት ይችለ ዖንድ በንግድ መዛገብ መመዛገብ ይገባቸዋል፤ ተጠሪው በኢትዮጵያ ውስጥ የተመዖገበ የንግድ ሥራ የለውም፤ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ የሰጠው ውሳኔም የንግድ ምልክት ምዛገባን አስመልክቶ በንግድ ህጉ እና አግባብነት ባላቸው ላልች ሕጎች የጠጠቀሱት አንቀጾች ትርጓሜ ያላገኙበት ስለሆኑ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት የለውም። በመሆኑም የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አግባብነት ያላቸውን የሕጉን ድንጋጌዎች በመጣስ የሰጠው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፋመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዘህ ችልት መታየት የሚገባው ሆኖ ስለተገኘ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ግራ ቀኙ በጽሁፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጌዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምሮታል። እንደመረመረው የዘህንም ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው ዋነኛ ነጥብ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪው በውጪ አገር የተመዖገበ ድርጅት በመሆኑ እና የንግድ ምልክቱንም በባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ያስመዖገበ ድርጅት ምልክቱ ጋር በተያያዖ መብቱን ለማስከበር ክስ የማያቀርብበት ምክንያት የለም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ ሆኖ አግኝቶታል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ በውጪ አገር የተመዖገበ ድርጅት ለመሆኑ እና የንግድ ምልክቱንም በባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ተገቢውን መመዖኛ አሟልቶ ያስመዖገበ ለመሆኑ ፍሬ ነገርን ለማጣራት እና ማስረጃን የመመዖን ሥልጣን ባለው የበታች ፍ/ቤት ተረጋግጧል።
አምካቾች ተጠሪ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት የለውም በማለት በዋነኝነት የሚከራከሩት ተጠሪ በኢትዮጵያ ውሥጥ የጠመዖገበ የንግድ ድርጅት አይደለም ኢትዮጵያ እና ተጠሪው የተመዖገበበት አገርም የእንካ ግንኙ ነት የላቸውም በሚል ነው። የንግድ ምልክት እና ምዛገባ አዋጅ ቁጥር 501/98 የወጣበት አንደ ዓላማ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መልካም ሥም እና ዛና ለመጠበቅ በተመሣሣይ ዔቃዎች እና አገልግልቶች መካከል መሣከርን ለማስወገድ መሆኑ ከአዋጁ መግቢያ መገንዖብ ይቻላል። ተጠሪ አዋጁ በሚፈቅደው አግባብ የንግድ ምልክቱን ያስመዖገበ በመሆኑ እና ድርጅቱ በተመዖገበበት አገር ሕጋዊ ሰውነት የተሰጠው በመሆኑ በአዋጅ አንቀጽ 26/1 እና 2 ድንጋጌ መሰረት ላልች ወገኖች የንግድ ምልክቱን ወይም የንግድ ምልክቱን በሚመስል መለያ ሕዛብን ሉያሳስት በሚችል አኳሀን አላግባብ እንዲይጠቀሙበት ለማድረግ የሚያስችል መብት አለው። ከአዋጁ ዓላማ አኳያም ተጠሪ በኢትዮጵያ ውስጥ አለመመዛገቡን ምክንያት በማድረግ ክስ ሉያቀርብ አይችልም ልባል የሚችልበት አግባብ የለም። አመልካቾች በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ወይም ያልተመዖገበ ንግድ ያለው እንደ ኢትዮጵያዊ ተቆጥሮ በንግድ ምልክት ምዛገባ ወረቀቱ ሉሰራበት የሚችለው ተመዛግቤበታለሁ ከሚለው ላላ ሀገር ጋር ኢትዮጵያ የእንካ ለእንካ ሥምምነት ከኖራት ወይም ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት ዓለም አቀፍ ውል ካለ ብቻ ነው በማለት ክርክር ያቀረቡ እና ይህ የክርክራቸው ሐሳብም በአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 2/4 እና 3 ላይ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆንም የተጠሪ ክስ ጉዲዩ በቀረበለት ፍ/ቤት ተመርምሮ በአዋጁ መሰረት መብቱን ለማስጠበቅ የሚችል መሆን አለመሆኑ ውሣኔ የሚሰጥበት እንጂ ከወዱሁ ክስ ማቅረብ አይችልም ተብል ድምዲሜ የሚወሰድበት አይደለም።
በልላ በኩል አመልካቾች የንግድ ምዛገባ እና ፈቃድን አስመልክቶ የወጣው አዋጅ ቁጥር 686/2002 የንግድ ማህበራት የሕግ ሰውነት ማግኘት ይችለ ዖንድ በንግድ መዛገብ መመዛገብ እንዲለባቸው ይደነግጋል በማለት መከራከሪያ አቅርበዋል። ሆኖም ይህ አዋጅ የተደነገገው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራበት የንግድ ሥራ ምዛገባ ሥርአትን አስመልክቶ እንጂ የንግድ ምልክት ምዛገባን አስመልክቶ የተደነገገ አይደለም። በአዋጁም ሆነ በንግድ ህጉ ላይ በውጪ አገር የተመዖገበ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ ካልተመዖገበ በቀር ክስ ለማቅረብ አይችልም በማለት አልተደነገም።
አመልካቾች የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.23626 የሰጠው ውሣኔም የንግድ ምልክት ምዛገባን አስመልክቶ በንድግድ ህጉ እና አግባብነት ባላቸው ላልች ሕጏች የተጠቀሱት አንቀጾች ትርጓሜ ያላገኙበት ስለሆኑ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት የለውም በማለት ያቀረቡትን ክርክር ተጠቃሹን ውሣኔ መሰረት በማድረግ መርምረነወል። አመልካቾች በጠቀሱት የሰበር ውሣኔ የቀረበው ክርክር ከንግድ ምልክት ምዛገባ ጋር በተገናኘ የቀረበ ክርክር ሲሆን ፍ/ቤቱም ጉዲዩ የምዛገባ አስፈላጊ በኢትዮጵያ ውስጥየንግድ ስራን ለማካሓድ ነው፤ የንግድ ሥራ እና የነግድ ምልክት ማካሓድ የተለያዩ ተግባራ ናቸው፤ አመልካች በውጭ አገር ተመዛግቦ የህግ ሰውነት ያለው በመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ምዛገባ ጥያቄ ቢያነስ አስቀድሞ ያገኘውን የህግ ሰወነት የሚያሳጣው አይደለም በማለት አመልካች ክርክር ለማቅረብ መብት አለው በማት ውሳኔ መስጠቱን የሚያሳይ ነው። ይህ ውኔ የንገድ ሥራ ምዛገባ እና የንገድ ምልክት መዛገባ የተለያዩ ተግራ መሆናቸውን፤ የሕግ ሰውነት ያለው እና የንገድ ምልክቱን ያስመዖገበ ሰው ከንግድ ምልክት ጋር በተያያዖ ክስ ማቅረብ የሚችል መሆኑ የሚያሳይ፤ ተጠሪ ከንግድ ምልክት ምዛገባ ጋር አያይዜ ላቀረበ ክርክር አግባብነት ያለው ውሳኔ ነው ከሚባል በቀር አመልካቾች እንደገለጹት ለጉዲዩ አግባነት ያለው ውሳኔ አይደለም። ልባል አይገባም።
ሲጠቃለል የንግድ ምልክት እና ምዛገባ አዋጅ ቁጥር 501/98 እና የንግድ ምዛገባ እና ፈቃድን አስመልክቶ የወጣው አዋጅ ቁጥር 686/2002 የተደነገጉበት የየራሳቸው የሆነ ዓላማ ያላቸው በመሆኑ፤ ተጠሪ በውጪ አገር የሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በመሆኑ እና የንግድ ምልክቱንም በሚመለከተው ባለስልጣን መሥሪያ ቤት ያስመዖገበ በመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ ክስ ለማቅረብ የሚያስች መብት አለው በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ.98150 ሕዲር 11 ቀን 2007 ዓ.ም በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.134178 ታህሳስ 24 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠውን ብይን በመሻር የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348/1/ መሰረት ጸንቷል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
በ20/05/207 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው ዔግድ ተነስቷል። ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል። ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.