No summary available.
ሐምል 23 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡
ተጠሪ፡ ..........አቶ ኤፍሬም ኤርሚያስ - ጠበቃ አቶ ሙለጌታ ብሰማ ቀርበዋል።
ይህ መዛገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ እና በዘህ ችልት የክርክሩ ተካፊይ ያልሆነች ወ/ሮ አምሮት ደግፋ 2ኛ ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.147071 በ23/2/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረበዉን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ዉሳኔ ለመስጠት ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ባቀረበዉ ክስ 1ኛ ተከሳሽ ከአሜሪካን ሀገር ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ፈለገዉ ገንዖብ እንዲበድረዉ በስልክ ደዉል በጠየቀኝ መሰረት 20,000 (ሀያ ሺህ) ድላር 2ኛ ተከሳሽ መተማመኛ ፈርማ ወስዲ ለ1ኛ ተከሳሽ የሰጠች ቢሆንም ይህ ገንዖብ ስላልተከፈለኝ፣ ፍ/ቤቱ ከእነዘህ ተከሳሾች ኃላፉነቱ የማን እንደሆነ ለይቶ ገንዖቡን ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለኝ እንደወሰንልኝ በማለት ከሷል።
በዘህ ክስ ላይ 1ኛ ተከሳሽ በሰጠዉ መልስ ይህን ያህል የዉጪ ምንዙሪ ያለፈቃድ ማበደር በወንጀል የሚያስጠይቅ ስለሆነ ዉለ ሕገ ወጥ ነዉ፣ ከሳሽ በ2ኛ ተከሳሽ በኩል ለ1ኛ ተከሳሽ ሰጥቻለሁ የሚለት ድላር በብድር ሳይሆን ለሙዘቃ ኮንሰርት ሥራ የተከፈለ የቅድሚያ ክፍያ ነዉ፣ 2ኛ ተከሳሽ የፈረሙት ሰነድ ብድር መሆኑን በግልጽ አያሳይም፣ የብድር ዉል የለም፣ ከሳሽ ብድሩን በሰዉ ምስክሮች ለማስረዲት ያቀረበዉ ጥያቄ የሕግ አግባብነት የለዉም በማለት ተከራክሯል። 2ኛ ተከሳሽ በበኩሎ ባቀረበችዉ መልስ እኔ ገንዖቡን ከከሳሽ ተቀበዬ ለተከሳሽ የማድረስ ስራ ብቻ እንጂ ላላ ሚና የለኝም በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር የሰዉ ምስክሮች በመስማት፣ የሰነድ ማስረጃ በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ 1ኛ ተከሳሽ በክሱ የተመለከተዉን 20,000 (ሀያ ሺህ) ድላር ከከሳሽ መቀበለን አልካደም፣ ነገር ግን ከሳሽ ገንዖቡ በብድር የተሰጠ ነዉ በማለት ሲከራከር፣ 1ኛ ተከሳሽ ደግሞ ገንዖቡ በብድር ሳይሆን ለሙዘቃ ኮንሰርት የቅድሚያ ክፍያ የተከፈለ ነዉ በማለት የተከራከሩ ሲሆን፣ ከቀረበዉ ማስረጃ መገንዖብ የሚቻለዉ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2472 (2) መሰረት የብድር ዉል የሚያቋቁም ማስረጃ የለም፣ ይህ ገንዖብ ለሙዘቃ ኮንሰርት የቅድሚያ ክፍያ የተከፈለ በመሆኑ፣ ከኮንሰርቱ የሚገኘዉን ገቢ በተመለከተ በመ.ቁ.95218 ላይ በተጀመረዉ ክርክር መሰረት በጋራ ሂሳባቸዉ በባለሙያ እንዱሰራ በማድረግ መከፊፈል ይችላለ በማለት የቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።
የሥር ከሳሽ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ ይግባኝ ባይ በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት የሰነድ እና የሰዉ ማስረጃ መልስ ሰጪ ይህን ገንዖብ በብድር ዉል መዉሰዲቸዉን ሚዙን በሚደፊ መልኩ የሚያስረዲ በመሆኑ፣ መልስ ሰጪ ደግሞ ገንዖቡን የወሰደት ለሙዘቃ ኮንሰርት ሥራ የቅድሚያ ክፍያ መሆኑን ያቀረቡት ማስረጃ ስለላለ፣ መልስ ሰጪ 20,000 (ሀያ ሺህ) ድላር ወይም ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ) ለይግባኝ ባይ እንዱከፍለ በማለት የሥር ዉሳኔ በመሻር ወስኗል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይህን ዉሳኔ በማጽናት ትዔዙዛ ሰጥቷል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ህዲር 27 ቀን 2010 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ አመልካች ከተጠሪ ጋር ምንም ዓይነት የብድር ዉል ባላደረኩበት፣ ተጠሪ በሐዋላ ወረቀት ገንዖብ የላኩት ለሥር 2ኛ ተከሳሽ እንጂ ለአመልካች ገንዖብ ባልላከበት፣ ተጠሪ ይህን ገንዖብ ለሥር 2ኛ ተከሳሽ የሰጠዉ አመልካችና ተጠሪ በጋራ ለማከናወን ላቀድነዉ የሙዘቃ ኮንሰርት የቅድሚያ ክፍያ እንጂ በብድር መልክ አይደለም። በአመልካችና በተጠሪ መካከል በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2472 መሰረት የብድር ዉል መኖሩን የሚያስረዲ ማስረጃ የለም። በሥር ፍ/ቤት የቀረበዉ ማስረጃ የገንዖብ መቀበያ ደረሰኝ እንጂ የብድር ዉል የሚያቋቁም አይደለም። በሥር ፍ/ቤት የቀረቡት የሰዉ ምስክሮች በሰጡት የምስክርነት ቃል ገንዖቡ ከኮንሰርት ሥራ ጋር የሚገናኝ መሆኑን መስክሯል። የሥር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሕጉ አግባብ ጉዲዩን በመመርመር የብደር ዉል የለም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ዉሳኔ ሰጥቶ እያለ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሥር ዉሳኔ በመሻር የብድር ዉል አለ በማለት በክሱ የተመለከተዉን ገንዖብ ለተጠሪ እንዱከፍል የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህን ዉሳኔ ማረም ሲገባዉ በማጽናት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልኝ፣ ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብቴ እንዱጠበቅልኝ በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣በአመልካችና በተጠሪ መካከል የብድር ዉል አለ የመባለን አግባብነት፣ ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ባዖዖዉ መሰረት በ6/6/2010 ዓ.ም የተጻፈ ስምንት ገጽ መልስ አቅርቧል። በዘህ ጉዲይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበዉን ማስረጃ በመመርመር የብድር ዉል መኖሩን እንደሚያረጋገጥ በመገንዖብ አመልካች በክሱ የተመለከተዉን ገንዖብ ለተጠሪ እንዱከፍል የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የጸደዉ ዉሳኔ ምንም ዓይነት የሕግ ስህተት የማይገኝበት ስለሆነ ዉሳኔዉ በአግባቡ ነዉ እንዱባልልን፣ አመልካች በዘህ ክርክር ምክንያት የደረሰብን ወጪዎችና የጠበቃ አበል እንዱተካ እንዱወሰንልኝ በማለት በዛርዛር ተከራክሯል።
የአሁን አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ ከፍ ሲል እንደተጠቀሰዉ የአሁን ተጠሪ ለክርክር ምክንያት የሆነዉን ገንዖብ ለአመልካች የሰጠሁት በብድር ነዉ፣ የብድር ዉል አለ ስለዘህ በዉለ መሰረት አመልካች ይህን ገንዖብ ስላልከፈለኝ እንዱከፍለኝ የሚል ዲኝነት መጠየቁን መገንዖብ ይቻላል። አመልካች በበኩለ ይህን ገንዖብ መዉሰደን ሳይክድ ገንዖቡ የተከፈለዉ በጋራ ለሚናዖጋቸዉ የሙዘቃ ኮንሰርት የቅድሚያ ክፍያ ነዉ እንጂ ብድር አይደለም፣ የብድር ዉል የለም በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኛቸዉ ክርክር ይህ ከሆነ በዘህ ጉዲይ ምላሽ የሚሸዉ በሕጉ አግባብ የተቋቋመ የብድር ዉል አለ ወይስ የለም? የሚለዉ ነጥብ ነዉ። ከዘህ አንጻር የአሁን ተጠሪ የብድር ዉል መኖሩን ለማስረዲት በሥር ፍ/ቤት ያቀረበዉ የሰነድ ማስረጃ ሲታይ ሚያዘያ 6 ቀን 2000 ዓ.ም የሥር 2ኛ ተከሳሽ የፈረሙት የገንዖብ መቀበያ ደረሰኝ፣ በሥር 2ኛ ተከሳሽ ስም በሐዋላ የተለካ ገንዖብ የሚያሳይ ሰነድ እና የሰዉ ምስክሮች መሆናቸዉን የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። የአሁን አመልካች በበኩለ ባቀረበዉ ክርክር ይህን ገንዖብ በብድር የወሰደ ሳይሆን ለሙዘቃ ኮንሰርት የቅድሚያ ክፍያ የተከፈለ ነዉ በማለት ይህንኑ ለማስረዲት የሰዉ ምስክሮችን የቆጠረ መሆኑን የሥር ዉሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። ከግራ ቀኛቸዉ ክርክር አንጻር የአሁን ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.259 (1) መሰረት በሕጉ አግባብ የተቋቋመ የብድር ዉል መኖሩን በቅድሚያ የማስረዲት ሸክም እንዲለበት የሚያከራክር አይሆንም። አመልካች ደግሞ በሕግ አግባብ የተቋቋመ የብድር ዉል እንደላላ አለኝ የሚለዉን ማስረጃ አቅርቦ የማስረዲት ሸክም እንዲለበት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.259 (2) ሥር ተመልክቷል። በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር በሕጉ አግባብ የተቋቋመ የብድር ዉል መኖሩን የሚያረጋግጥ መሆን አለመሆኑን መፈተሹ አስፈላጊ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ የሚያልቅ ነገር ብድር በተመለከተ እንደአግባብነቱ ተፈጻሚነት ያለዉ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2471-2489 ድንጋጌዎች መሆናቸዉን ማየት ይቻላል። ስለሆነም የሚያልቅ ነገር የብድር ዉል አለ ለማለት በእነዘህ የህግ ድንጋጌዎች የተመለከቱትን አስገዲጅ ድንጋጌዎች ባከበረ መልኩ መፈጸሙ ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ። በዘህ መሰረት የገንዖብ ብድር ዉል መኖሩን እና ክፍያ መፈጸሙን ለማረጋገጥ አግባብነት ያለዉን ማስረጃ ምን እንደሆነ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2472 ሥር ተደንግጎ እናገኛለን። በዘህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 1 ሥር እንደተመለከተዉ ከ500 (አምስት መቶ) ብር በላይ የተደረገዉን የገንዖብ ብድር ዉል ለማስረዲት የሚቻለዉ የብድር ዉለን ጽሐፍ በማቅረብ ወይም በፍ/ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም መሒላ እንደሆነ ነዉ። የዘህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 2 ደግሞ ለብድር ዉል ማናቸዉም ላላ ዓይነት ማስረጃ ለማቅረብ እንደማይቻል ደንግጓታል። እንዱሁም ከብር 500 (አምስት መቶ) በላይ የመክፈል ነገር ማስረዲት የሚቻለዉ በዘሁ አግባብ መሆን እንዲለበት የዘህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 3 ያመለክታል። በመሆኑም ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸዉ የገንዖብ ብድር ዉል ለማድረግ መፈለጋቸዉን ሙለ ፈቃዲቸዉን ተከትል የተፈጸመ መሆን እንዲለበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1678 (ሀ) እና 1679 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያስገነዛባለ። ተዋዋይ ወገኖች በዘህ አግባብ የገንዖብ ብድር ዉል ለማድረግ ፈቅደዉ አዉቀዉ ገብቷቸዉ ዉል ያደረጉ እና ዉለም ደግሞ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የፍትሒ ብሓር ሕግ ቁጥር 2472 አግባብ የተደረገ መሆን እንዲለበት መገንዖብ ያስፈልጋል።
በዘህ አግባብ አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ አመልካች እና ተጠሪ በክስ የተመለከተዉን ገንዖብ ብድር ዉል ለማድረግ ፈልገዉ እና አዉቃዉ የብድር ዉል ማድረጋቸዉን እና ይህም የብድር ዉል መኖሩን በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2472 (1) መሰረት የሚያስረዲ አግባብነት ያለዉ ማስረጃ መቅረቡን የሚያመለክት ነገር የለም። የአሁን አመልካች የተጠቀሰዉ ገንዖብ የብድር ዉል የለም በማለት ክድ እስከተከራከረ ድረስ ተጠሪ 20,000 (ሀያ ሺህ) ድላር ብድር መኖሩን ለማስረዲት አግባብነት ያለዉ ማስረጃ ማለትም በጽሐፍ የተደረገ የብድር ዉል ወይም በፍ/ቤት የተሰጠ የእምነት ቃል ወይም መሒላ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ነገር ግን አመልካች በዘህ አግባብ ያቀረበዉ ማስረጃ መኖሩን የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ አያመለክትም። ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ መገንዖብ የሚቻለዉ ተጠሪ የብድር ዉል መኖሩን ለማስረዲት ያቀረበዉ ማስረጃ በሥር 2ኛ ተከሳሽ በሐዋላ የተላከ ገንዖብ፣ የሥር 2ኛ ተከሳሽ የፈረመችዉ መተማመኛ እና የሰዉ ምስክሮች ናቸዉ። እነዘህ ማስረጃዎች ደግሞ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የሕግ ድንጋጌ ከብር 500 በላይ የሆነዉን የገንዖብ ብድር ዉል ለማስረዲት አግባብነት ያለዉ ማስረጃዎች አይደለም። የግራ ቀኛቸዉ የሰዉ ምስክሮች ቃል ሲታይ በግራ ቀኛቸዉ መካከል የሙዘቃ ኮንሰርት የሥራ ግንኙነት እንደነበረ እና ገንዖቡም የሰጠዉ ከዘህ ግንኙነት ጋር በተያያዖ መሆኑን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። በመሆኑም የአሁን ተጠሪ ከአመልካች ጋር በሕጉ አግባብ የተቋቋመ የ 20,000 (ሀያ ሺህ) ድላር የብደር ዉል ማድረጋቸዉን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ማስረዲቱን የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ግልባጭ የማያመለክት ሆኖ ሳለ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የብድር ዉል አለ በማለት የሰጠዉን ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህን ዉሳኔ ማረም ሲገባዉ በዉሳኔ በማጽናት የሰጡት ዉሳኔ ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን የሕግ ድንጋጌ የሚጥስ ነዉ ብለናል።
ሲጠቃለል የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በግራ ቀኛቸዉ መካከል በሕጉ አግባብ የተቋቋመ የ 20,000 (ሀያ ሺህ) ድላር የብድር ዉል መኖሩን የሚያስረዲ አግባብነት ያለዉ ማስረጃ ሳይቀርብ የብድር ዉል አለ በማለት አመልካች ይህን ገንዖብ ለተጠሪ እንዱከፍል የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ በመሆኑ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.182820 በ5/11/2009 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን ዉሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.147071 በ23/2/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.92571 በ12/3/2009 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ጸንቷል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በሕጉ አግባብ የተቋቋመ የ 20,000 (ሀያ ሺህ) ድላር ብድር ዉል የለም ብለናል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከላቸዉ በነበረዉ የሙዘቃ ኮንሰርት የሥራ ግንኙነት ጋር በተያያዖ በመ.ቁ.95218 ላይ ክርክር እንደነበር የተገለጸ በመሆኑ ያንን ክርክር ይህ ዉሳኔ የሚያግደዉ አይሆንም ብለናል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም የተሰጠዉ የአፈጻጸም እግድ ትዔዙዛ በዘህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.