No summary available.
የሰ/መ/ ሀምላ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ሚስ ሻሮን አና ኢሽተን ፡- አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ዶ/ር መላኩ መንግስቱ 2ኛ. ዋጋ ሜዱካል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጠበቃ ፊሲል አስናቀ -ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዘህ መዛገብ የተያዖው ጉዲይ የንግድ ማህበርን የሚመለከት ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 04/10/2011 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 09/09/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ስለጠየቁ ነው።
ክርክሩ የጀመረው በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ከሳሽ፤
ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች ነበሩ።
ከመዛገቡ መረዲት እንደሚቻለው አመልካች በቀን 16/05/2010 ዓ.ም ባቀረቡት የተሻሻለ አቤቱታ ከሳሽ እና 1ኛ ተከሳሽ ከላልች ሁለት ማህበርተኞች ጋር በመሆን ሰኔ 7/2002 ዓ.ም በብር 40,000,000 (አርባ ሚሉየን) ካፒታል 2ኛ ተከሳሽ ማህበርን አቋቁመን የህክምና ስራ ስንሰራ ቆይተናል። 1ኛ ተከሳሽ በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 8.1 መሰረት ስራ አስኪያጅ እንዱሆኑ ተሰይመዋል። ነገር ግን በስራ አስኪያጅነታቸው የማህበሩን ስራ ማከናወን ሲገባቸው የስራ ሀላፉነታቸውን ለከሳሽ አሳልፈው በመስጠት በቋሚነት ወደሚኖሩበት ካናዲ ሀገር ሄደዋል። ከሳሽም የ1ኛ ተከሳሽን ተግባር እና ኃላፉነት በመፈጸም ኩባንያው አሁን ያለበት ደረጃ ለማድረስ በቅተዋል። ከሳሽ ማህበሩን ስኬታማ ለማድረግ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ከግምት በማስገባት ጥቅምት 04/2007 ዓ.ም በተደረገ ድንገተኛ የባለ አክስዬኖች ስብሰባ መተዲደሪያ ደንቡ ተሻሽል ከሳሽ በምክትል ስራ አስኪያጅነት ተሰይመው ስራቸውን በትጋት ሲፈጽሙና ኩባንያውንም ከፍተኛ ስኬት እንዱያስመዖግብ በማድረግ ግዳታቸውን እየተወጡ ባለበት ሁኔታ 1ኛ ተከሳሽ ድርጅቱን እና ማህበርተኞችን የሚጎዲ በርካታ ህገወጥ ተግባራትን ፈጽመዋል።
ከዘህም ህገወጥ ተግባራት ውስጥ ባለቤታቸው እና እህታቸው ባለ አክስዬን የሆኑበትን የጃስፔራ ኃ/የተ/የግ/ማህበርን ህንጻ 2ኛ ተከሳሽ ድርጅት እንዱከራይ አድርገዋል፤ 1ኛ ተከሳሽ ድርጅቱ ከቀድሞ የስራ ቦታው ወደ ራሳቸው ህንጻ እንዱቀየር ካደረጉ በኋላ ህንጻው በአግባቡ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ጎርፍ ገብቶ በብዘ ሚሉየን በሚገመቱ የድርጅቱ ንብረቶች ላይ ጉዲት አድርሷል፤ ይህ ክስ እስከቀረበበት ጊዚ ድረስም የህንጻውን አስፈላጊ የማጠናቀቂያ ስራዎች ለመስራት ፈቃደኛ አልሆኑም፤ 1ኛ ተከሳሽ አቶ አቤል አሰፊ የተባለ የእህታቸውን ልጅና ሲስተር ጥሩወርቅ የተባለ የባለቤታቸውን እህት ግልጽነት በላለው መንገድ የድርጅቱ ተቀጣሪ አድርገዋቸዋል። ይህ በእንዱህ እንዲለ 1ኛ ተከሳሽ ህዲር 04/2010 ዓ.ም በድንገት ከካናዲ ሀገር በመምጣት በድሪም ላይነር ሆቴል ስብሰባ ይኖራል ብለው ከሳሽ ስብሰባውን በመጠባበቅ ላይ እያለሁ ወደ ስብሰባው የምሄድበትን መኪና እንዲይንቀሳቀስ በማድረግ ውክልና ተነስቷል የሚል ደብዲቤ በመጻፍ የድርጅቱን ማህተም እና ሰነድችን ነጥቀውኛል። ከሳሽ ከቼክ ፈራሚነት እንድነሳ በማድረግ የእህታቸውን ልጅ አቤል አሰፊን የጋራ ቼክ ፈራሚ አድርገዋል። ይህ ሳይበቃ 1ኛ ተከሳሽ አቶ በሪሁ የተባለ ግለሰብን ከህግና ከመተዲደሪያ ደንቡ ውጭ ተቀጣሪ ስራ አስኪያጅ አድርገዋቸዋል። አንድ የድርጅት ስራ አስኪያጅ በመደበኛነት መኖር የሚገባው ስራው በሚሰራበት ቦታ ቢሆንም 1ኛ ተከሳሽ ድርጅቱ ከተመሰረት ግዚ ጀምሮ የሚኖሩት ካናዲ ሀገር ነው። ከተዖረዖሩት ጥፊቶች አኳያ 1ኛ ተከሳሽ ድርጅቱን የጥቅም ግጭት በሚታይበት መልኩ እየመሩ የሚገኙ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን የስራ አስኪያጅነት የስልጣን ዖመን አንድ አመት ስለመሆኑ በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ ላይ ተመልክቶ እያለ 1ኛ ተከሳሽ በድጋሚ ሳይመረጡ በቋሚነት ስራ አስኪያጅ ሆነው ሉቀጥለ የሚችለበት አግባብ የለም። በመተዲደሪያ ደንቡ መሰረት ዋና ስራ አስኪያጅ በላለበት ምክትል ስራ አስኪያጅነት እንድሰራ በግልጽ በመተዲደሪያ ደንቡ ተቀምጦ እያለ 1ኛ ተከሳሽ ስራ እንዲልገባ በመከልከል ቅጥር ስራ አስኪያጁ በእጅ አዘር የዋናውን ስራ አስኪያጅ ተግባር በማከናወን ላይ የሚገኙ በመሆኑ ከሳሽ በ2ኛ ተከሳሽ ድርጅት ውስጥ ያለኝን አክስዮን ገበያ ዋጋ እንዱሁም እዲና ንብረት በማወቅ ለሽያጭ ማቅረብ እንድችል ገለልተኛ ገማች እንዱሰየም እፈልጋለሁ። በመሆኑም 1ኛ ተከሳሽ ድርጅቱን የጥቅም ግጭት በሚታይበት ሁኔታ እየመሩ በመሆኑ፤ የስልጣን ዖመናቸውም ያበቃ በመሆኑና በኩባንያ ውስጥ ለተፈጠረው ብርቱ ጭቅጭቅ መንስኤ በመሆናቸው ከስራ አስኪያጅነታቸው ተሽረው ባለ አክስዬኖች በፍ/ቤቱ ትዔዙዛ ላላ ስራ አስኪያጅ እንዱሰየም እንዱወሰንልኝ፤ 1ኛ ተከሳሽ የፈጸሙት ህገወጥ ቅጥር ውል እንዱሰረዛ እና ተቀጣሪዎች ከኩባንያው እንዱሰናበቱ፤ ዋጋ ገማች ባለሙያ በፍ/ቤት እንዱሰየምልኝ። ይህ የሚታለፍ ከሆነም 1ኛ ተከሳሽ ኩባንያውን የጥቅም ግጭት በሚታይበት አኳኋን እየመሩ በመሆኑ፤ በከሳሽም ላይ በርካታ ጉዲት እያደረሱ በመሆኑና በተፈጠረው ብርቱ ጭቅጭቅ ምክንያት አብረን መስራት ከማንችልበት ደረጃ ስለደረስን ኩባንያው ፈርሶ የንብረት ክፍፍል እንድናደርግ እንዱወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተከሳሾች በቀን 30/06/2010 ዓ.ም በሰጡት መልስ 1ኛ ተከሳሽ በስራ አስኪያጅነታቸው ሉፈጽሟቸው ሲገባቸው ያልፈጸሟቸው ተግባር እና ሀላፉነት ምን እንደሆነ በክሱ ላይ አልገለጹም፤ 1ኛ ተከሳሽ በቋሚነት ካናዲ አገር ቢኖሩም ኩባንያውን በስራ አስኪያጅነት እንዲይመሩ የሚከለክላቸው ህግ የለም፤ በኩባንያው መተዲደሪያ ደንብና መመስረቻ ጽሁፍ ላይ የስራ አስኪያጅ ስልጣናቸውን ለላላ ሰው ማስተላለፍ እንደሚችለ ተደንግጓል፤ 1ኛ ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር በኢሜል እና ላልች መገናኛ ዖዳዎች እየተገናኙ ድርጅቱን ሲመሩ ቆይተዋል፤
ከኩባንያው ጋር የህንጻ ኪራይ ውል የፈጸመው ጃስፔራ ቢዛነስ የሚባል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሆኖ እያለ 1ኛ ተከሳሽ ኩባንያውን ወደራሳቸው ህንጻ አዙውረው አከራይተዋል የተባለው ሀሰት ነው፤
የኪራይ ውለንም ከአከራዩ ጋር የፈጸሙትን ከሳሽ ራሳቸው የወከሎቸው ግለሰብ ናቸው፤ ከሳሽ በጎርፍ ምክንያት በኩባንያው ንብረት ላይ ጉዲት ደረሰ ቢለም ደረሰ የሚለት ጉዲት ካለ ህንጻ ያከራየውን ድርጅት ከሚጠይቁ በቀር 1ኛ ተከሳሽን ሉጠይቁ አይችለም፤ በኩባንያው ሰራተኞች ሲቀጠሩ የቅጥር ውል የፈረሙት ከሳሽ ራሳቸው ከመሆናቸውም በላይ የተቀጠሩ ሰራተኞች ለስራ ብቁ እስከሆኑ ድረስ ከመቀጠር የሚከለክላቸው ህግ የለም፤ 1ኛ ተከሳሽ ከሳሽ የሚጠቀሙበትን መኪና አግተው እንዲይንቀሳቀስ አደረጉ የተባለው ሀሰት ነው፤ 1ኛ ተከሳሽ እንደ ስራ አስኪያጅነታቸው ውክልና የመስጠትም ሆነ የመሻር ስልጣን ያላቸው ሲሆን ለከሳሽ የሰጡትን ውክልና መሻራቸው የሚነቀፍበት ምክንያት የለም፤ 1ኛ ተከሳሽ ከሳሽን ከምክትል ስራ አስኪያጅነት አልሻሩም ከማህበር አባልነትም አላሰናበቱም፤ ከሳሽ በኩባንያው ላይ በፈጸሙት ምክንያት ከስራ እንዱታገደ የተደረገ ሲሆን ይህም ለስራ አስኪያጁ በተሰጠ ስልጣን መነሻነት ነው፤ 1ኛ ተከሳሽ ሰነድም ሆነ ማህተም ከከሳሽ ላይ አልነጠቁም፤ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ መሰረት የተሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም ላላ ሰው ቼክ እንዱፈርም ውክልና መስጠታቸው የጥቅም ግጭት ስለመኖሩ የሚያመለክት አይደለም፤ በተሻሻለው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 8 መሰረት የስራ አስኪያጁ ስልጣን ላልተወሰነ ግዚ የተራዖመ በመሆኑ ከሳሽ የስራ አስኪያጅ ስልጣን ካበቃ በኋላ ይሰራል በሚል ያቀረቡት ተቀባይነት የለውም፤ 1ኛ ተከሳሽ ከማህበሩ መተዲደሪያ ደንብና መመስረቻ ጽሁፍ ውጭ የፈጸሙት ተግባር የለም፤ ህልውና ያለው ማህበር በፍ/ቤት ስራ አስኪያጅ እንዱሾምለት የሚደረግበት አግባብ የለም። ከሳሽ የኩባንያው አክስዬን ዋጋ እንዱገመትላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ለፍ/ቤት የማይቀርብ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ማስገመት ይችላለ። ከከሳሽ ጋር የተፈጠረው ግዚያዊ አለመግባባት ኩባንያውን ለማፍረስ የሚያስችል ብርቱ ጭቅጭቅ አለ ለማለት አያስችልም፤ የተፈጠረ የጥቅም ግጭት የለም እንጂ አለ ቢባል እንኳ ላላ ህጋዊ ውጤት ይኖረዋል እንጂ ማህበሩ እንዱፈርስ አያደርግም። ከሳሽ ጉዲት ደረሰብኝ የሚለ ከሆነ መብታቸው እንዱከበር ከመጠየቅ በቀር ማህበሩ እንዱፈርስ መጠየቅ አይችለም። በላልች የኩባንያው ባለአክስዬኖች መካከል የተፈጠረ አለመግባባት የለም፤ ከሳሽ ድርሻቸውን ለመሸጥ ገለልተኛ ገማች እንዱሰየምላቸው በጠየቁት ዲኝነት መሰረት ድርሻቸው ተገምቶ ተሰጥቷቸው ከማህበር አባልነት ቢሰናበቱ ተቃውሞ የለንም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በዘህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት ክርክሩንና ማስረጃ ከሰማ በኋላ 1ኛ ተከሳሽ ከስራ አስኪያጅነታቸው እንዱሻሩ የሚያደርግ በቂ ምክንያት ባለመኖሩ ከስራ አስኪያጅነታቸው ሉሻሩም ሆነ ግዚያዊ ስራ አስኪያጅ ሉሾም አይገባም፤ 1ኛ ተከሳሽ የፈጸሙት ህገወጥ የስራ ቅጥር የላለ በመሆኑ የስራ ቅጥር ውለ የሚሰረዛበት አግባብ የለም፤ ከሳሽ የአክስዬን ድርሻቸው እንዱገመት የጠየቁበት ምክንያት ምን እንደሆነ በግልጽ ባያስቀምጡም ተከሳሾች ከሳሽ በራሳቸው ወጪ ድርሻቸውን ማስገመት የሚችለ መሆኑን በመግለጻቸው ከሳሽ ያላቸው የአክስዬን ድርሻ ዋጋው ምን ያህል እንደሆነ የሚገምት ባለሙያ በፍ/ቤቱ ሬጅስትራር በኩል እንዱሾም እና ወጪውን ከሳሽ እንዱሸፍኑ፤ ከሳሽ 1ኛ ተከሳሽ ፈጽመዋቸዋል ያሎቸው ተግባራት 1ኛ ተከሳሽን ከስራ አስኪያጅነት ለማስነሳት በቂ አለመሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የእነዘህ ተግባሮች መፈጸም አለመፈጸም ብቻውን ማህበሩን ሉያስፈርስ የሚያስችል በቂ ምክንያት ተደርገው ሉወሰደ አይችለም፤ በክሱ ላይ የተገለጹት ተግባራት በስራ አስኪያጁ መፈጸማቸው ህገወጥ አለመሆናቸው ከተረጋገጠ ደግሞ በእነዘህ ተግባራት የሚፈጠር አለመግባባት የንግድ ማህበሩም ህልውና እንዱያጣ የሚያደርጉ አለመግባባቶች ተከስተዋል ወደፉትም ማህበሩ የተቋቋመበትን አላማ ማሳካት አይችልም የሚያስብል አይደለም፤ 2ኛ ተከሳሽ ማህበር እንዱፈርስ ቢወሰን ከሚያስገኘው ጥቅም ይልቅ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዲት የሚያስከትል በመሆኑ ከሳሽ በማህበር አባልነታቸው መቀጠል የማይፈልጉ ከሆነ ማህበሩን ከማፍረስ ይልቅ ድርሻቸውን በመውሰድ ከአባልነታቸው መውጣት የሚችለ በመሆኑ ከሳሽ 2ኛ ተከሳሽ ማህበር እንዱፈርስ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም፤ ማህበሩ ሉፈርስ አይገባም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ከሳሽ ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ውሳኔው ጸንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዘህ ነው።
አመልካች በቀን 07/12/2013 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር ማመልከቻ ተፈፀመ የሚለትን ስህተት ዖርዛረው የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ 2ኛ ተጠሪ ማህበር እንዱፈርስ፤ ይህ የሚታለፍ ከሆነ 1ኛ ተጠሪ በርቀት 2ኛ ተጠሪን ቋሚ ስራ ኖሮት መምራት የማይችል በመሆኑ እንዱሻር በማለት ማመልከቻቸውን አቅርበዋል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በዘህ ጉዲይ የጥቅም ግጭት መኖሩን አመልካች ስላየበትና 1ኛ ተጠሪ በሩቅ ሀገር ሆኖ ድርጅቱን መምራት እችላለሁ በማለት ያቀረበውን ሀሳብ የስር ፍ/ቤት ከንግድ ህጉ አላማ አንጻር የተቀበለበትን አግባብነት ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪዎች በቀን 19/06/2014 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ ክርክራቸውን አጠናክረው በስር ፍ/ቤቶች የተሰጡት ውሳኔዎች እንዱጸኑ ጠይቀዋል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
እንደመረመርነው የአመልካች ቅሬታና የዲኝነት ጥያቄ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ 2ኛ ተጠሪ ማህበር እንዱፈርስ፤ ይህ የሚታለፍ ከሆነም 1ኛ ተጠሪ በርቀት 2ኛ ተጠሪን ቋሚ ስራ ኖሮት መምራት የማይችል በመሆኑ እንዱሻር የሚጠይቅ በመሆኑ እነዘህን የቅሬታ ነጥቦች (ጭብጦች) በቅደም ተከተላቸው እንደሚከተለው መርምረናል።
የማህበሩ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱፈርስ አመልካች የጠየቁ ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸው ማህበሩ እንዱፈርስ4 የሚወሰንበት ምክንያት እንደላለ ተከራክረዋል። ከማህበርተኞቹ አንደ ማህበሩ እንዱፈርስ በሚያቀርበው አቤቱታ መነሻነት ፍርድ ቤት የማህበሩን መፍረስ ሉወስን እንደሚችል ሥራ ላይ ከነበረው የንግድ ህግ አንቀጽ 218፣ 258፣ 278፣ 303፣ 495፣ 542፣ 543 እና ተያያዣ ድንጋጌዎች መገንዖብ ይቻላል። ነገር ግን የንግድ ማህበሩ በፍርድ እንዱፈርስ ስለተጠየቀ ብቻ የሚፈርስ ሳይሆን ማህበሩን ለማፍረስ የሚያበቃ በቂና ትክክለኛ ምክንያት መኖሩ ሉረጋገጥ ይገባል። በማህበርተኞቹ መካከል ብርቱ ጭቅጭቅና አለመስማማት የተፈጠረ እንደሆነ ለማህበሩ መፍረስ ትክክለኛ ምክንያት እንደሚሆን በንግድ ህጉ አንቀጽ 218(2) ስር ተመልክቷል። ይሁንና በማህበርተኞች መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ሁለ ማህበሩን የሚያስፈርስ ብርቱ ጭቅጭቅና አለመስማማት ተደርጎ እንደማይወሰድ ከህጉ አቀራረጽ፣ ከይዖትና መንፈሱ መረዲት ይቻላል።
በተያዖው ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት በ2ኛ ተጠሪ ማህበር አባላት መካከል ጭቅጭቅና አለመግባባት ተፈጥሯል ወይስ አልተፈጠረም? በ1ኛ ተጠሪ ተፈፀመ የሚባለው የሥራ ጉድለትና አለመግባባት ማህበሩ እንዱፈርስ የሚያስችል ነው ወይስ አይደለም? ማህበሩስ ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለና ተያያዣ ነጥቦችን ከግራቀኙ ክርክርና ማስረጃዎች ጋር መርምሮ ማህበሩን ለማፍረስ የሚያስችል በቂና አሳማኝ ምክንያት ባለመገኘቱ ሉፈርስ እንደማይገባ፤ 2ኛ ተጠሪ የንግድ ማህበር እንዱፈርስ ቢወሰን ከሚያስገኘው ጥቅም ይልቅ ከፍተኛ ጉዲት የሚያስከትል መሆኑን በማረጋገጥ አመልካች በማህበር አባልነት መቀጠል የማይፈልጉ ከሆነ ድርሻቸውን በመውሰድ ከአባልነት መውጣት ስለሚችለ የማህበሩ ህልውና እንዱቀጥል የማድረጉን አስፈላጊነት ከአጠቃላይ ክርክሩ ተገንዛቦ በዘህ አግባብ ወስኗል። በዘህ መልኩ ማህበሩ ሉፈርስ አይገባም ተብል መወሰኑ ደግሞ የንግድ ህጉን ድንጋጌዎች የተከተለ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም።
ሁለተኛው ጭብጥ 1ኛ ተጠሪ በርቀት 2ኛ ተጠሪን ቋሚ ስራ ኖሮት መምራት የማይችል በመሆኑ እንዱሻር የቀረበውን ጥያቄ የተመለከተ ነው። እንደሚታወቀው የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠ ሰው በህጉ፣ በመመስረቻ ጽሁፈ እና መተዲደሪያ ደንቡ የተሰጠውን ሥልጣን (ኃላፉነት) በተገቢው ትጋት መወጣት፣ ጊዚውንም በሥራው ላይ ማዋል፣ ማህበሩንም በአግባቡ መምራትና ማስተዲደር ይጠበቅበታል። የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ በመሆን በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ የተሾመ ወይም በማህበርተኞች የተሾመም ቢሆን የስራ አስኪያጅን መሻር በተመለከተ አቤቱታ ሲቀርብ ፍርድ ቤት ሉቀበለው በሚችለው ተገቢ ምክንያቶች ሉሻር ይችላል። ማንኛውም ማህበርተኛ ቢሆን በሚገባ ምክንያት ሥራ አስኪያጅ እንዱሻር ለፍርድ ቤት ክስ ሉያቀርብ ይችላል። እነዘህን መሰረታዊ ሀሳቦች በክርክሩ ወቅት ሥራ ላይ ከነበረው የንግድ ህጉ አነቀጽ 527 ድንጋጌዎች መገንዖብ ይቻላል።
ስለሆነም ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥራ አስኪያጅ እንዱሻር ከማህበርተኞቹ አንደ ክስ ሉያቀርብ መቻለ እና በተገቢ ምክንያቶች በፍርድ ቤት ውሳኔ ከሥራ አስኪያጅነት ሉሻር መቻለ በህጉ ተቀባይነት ያለው ነው።
ሥራ አስኪያጁ እንዱሻር የሚያደርጉ ተገቢ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ በህጉ ተለይተው ተዖርዛረው ባይቀመጡም ለሥራ አስኪያጁ በህጉ ፣ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ፣ በመተዲደሪያ ደንብ፣ እንዱሁም በጠቅላላ ጉባኤዎች በሚተላለፈ ውሳኔዎች የተጣለበትን ኃላፉነት መወጣት ካለመቻል፤ የማህበሩን የዔለት ከዔለት ተግባራት በቅርበት በኃላፉነት አለመምራት፣ ማህበሩ የተቋቋመበትን አላማ ዲር ለማድረስ አለመቻል፣ የማህበሩንና የማህበርተኞችን መብትና ጥቅም የሚጎደ ተግባራት መፈፃም እና የመሳሰለት ምክንያቶች እንደ ሁኔታው ተገቢ ምክንያቶች ተብለው የሚወሰደ ናቸው።
በተያዖው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ በቋሚነት በካናዲ ሀገር የሚኖሩ መሆናቸውና ራሳቸው ቋሚ ሥራ ያላቸው መሆኑ ግራቀኙን አላከራከረም። 1ኛ ተጠሪ ይህን አምነው ይቀበለታል።
መከራከሪያቸው የሥራ አስኪያጁን በአገር ውስጥ በአካል መገኘት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች ሲኖሩ ወደ ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዚ የሚመጡ በመሆኑ እና በላልች ጉዲዮች ደግሞ በኢ-ሜይል የመልዕክት ልውውጥ እያደረጉ ማህበሩን የሚመሩ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ይሁንና በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 8(3) ስር የሥራ አስኪያጁ ስልጣንና ተግባራት ተብለው ከ8(3)(1) እስከ 8(3)(12) ድረስ ተዖርዛረዋል። በዘህ መሰረት የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ የዖርፍ ሥራ አስኪያጆችን መሾምና መቆጣጠር፣ ማህበሩን በመወከል መፈረም፣ ለማህበሩ ቴክኒካዊ እና አስተዲደራዊ ተግባሮች ኃላፉ መሆን፤ የጠቅላላ ጉባኤና የቦርደን ውሳኔዎች ሥራ ላይ ማዋል፤ ለማህበሩ የሚከፈል ገንዖብ መቀበል፣ ዔዲ መክፈል፣ የተለያዩ ዔለታዊ ሰነድችን መፈረም፤ ሰራተኛ መቅጠርና ማስተዲደር፤ የባንክ ሂሳብ ከፍቶ ገንዖብ ገቢ ማድረግና ሂሳቡን በፊርማው ማንቀሳቀስ፤ የግዣና ሽያጭ ማዖዡዋችን መወሰን፤ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ውል መዋዋል፤ በፍርድ ቤት ክርክር ማህበሩን በመወከል አስፈላጊውን መፈፀም፤
የሂሳብ ወጪና ገቢ መዛገብ በደንቡ እንዱያዛ ማድረግ እንዱሁም እነዘህን ተግባራት በተመለከተ ውክልና መስጠት ሥልጣንና ተግባር እንዲለው ተመልክቷል።
እነዘህ በመመስረቻ ጽሁፈ የተመለከቱ ዛርዛር ስልጣንና ተግባራት የማህበሩን የዔለት ተዔለት እንቅስቃሴ የሚመለከቱ በመሆናቸው 1ኛ ተጠሪ እንዲቀረቡት ክርክር አልፍ አልፍ ከውጭ ሀገር በመምጣት ሉከወን የሚችል አለመሆኑ ግልጽ ነው። ለረዣም ጊዚ በአሁን በአመልካች ድጋፍ እና በኃላም አመልካች በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተሰይመው ማህበሩን እንዱመሩ በመደረጋቸው ምክንያት ማህበሩ ሲመራና ሲተዲደር ቆይቷል ከሚባል በቀር ለሥራ አስኪያጁ በመመስረቻ ጽሁፈና መተዲደሪያ ደንቡ የተሰጡትን ኃላፉነቶች 1ኛ ተጠሪ በቋሚነት በሚኖሩበት ካናዲ ሀገር ሆነው ወደ ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዚ እየመጡ እና በኢ-ሜይል የመልዕክት ልውውጥ እያደረጉ ማህበሩን ይመሩ ነበር ለማለት አይቻልም። 1ኛ ተጠሪ በዘህ ሰበር ችልት ካቀረቡት መከራከሪያም መገንዖብ እንደሚቻለው አሁንም ማህበሩን ባለበት ሀገር ሆነው አልፍ አልፍ በመምጣት እና በመልዕክት ልውውጥ መምራት እንደሚፈልጉ የሚያሳይ ነው። ይህ ደግሞ በማህበሩ መመስረቻ እና ደንብ የተጣለባቸውን ዛርዛር ኃላፉነት መወጣት የማያስችል ነው።
ሥራ አስኪያጁ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍና በመተዲደሪያ ደንቡ የተጣለባቸውን ኃላፉነት መወጣት በማይችለበት ሁኔታና የማህበሩን የዔለት ከዔለት ተግባራትም በቅርበት በኃላፉነት መምራት እንደማይችለ ከተረጋገጠ ይኸው ሁኔታ 1ኛ ተጠሪን ከማህበሩ ሥራ አስኪያጅነት ለመሻር ተገቢ ምክንያት ተደርጎ ሉወሰድ የሚችል ነው።
ስለሆነም 1ኛ ተጠሪ የኪራይ ውል እርሳቸውና ባለቤታቸው ባለአክስዬን በሆኑበት ጃስፔራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር ህንጻው ሳያልቅ የኪራይ ውል እንዱፈጸም ተጽእኖ አድርገዋል መባለ፤
በዘህ ተግባር ጎርፍ ገብቶ ጉዲት ደረሰ መባለ፤ 1ኛ ተጠሪ ዖመድቻቸውን ግልጽነት በላለው መንገድ የቀጠሩ መሆኑ፤ የድርጅቱን ማህተም ከአመልካች የነጠቁ እና አላግባብ ያገዶቸው መሆኑ፤ እንዱሁም አመልካች ያለአግባብ ከቼክ ፈራሚነት በማገድ ላላ በስጋ ዖመድ የሆነ ሰው ቼክ ፈራሚ እንዱሆን ሰይመዋል የማህበሩንም ጥቅም ጎድተዋል የተባለ ምክንያቶች ሁለ በተለያየ ምክንያት በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ ቢደረጉም 1ኛ ተጠሪ የ2ኛ ተጠሪ ስራ አስኪያጅ ሆነው ቋሚ የመኖሪያ አድራሻው ካናዲ ሀገር ሆኖ እና ላላ ቋሚ ስራ ያላቸው ስለመሆኑ ባላከራከረበት ሁኔታ እና መመስራቻ ፅሁፍና በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ የተመለከቱ የሥራ አስኪያጂ የእለት ተዔለት ተግባራትና በፍሬ ነገር ደረጃ በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡ እውነታዎች 1ኛ ተጠሪ 2ኛ ተጠሪን በርቀት እንዱመሩ የማያስችላቸው በሆኑበት ሁኔታ ከሥራ አስኪያጅነት ሉሻሩ አይገባም ተብል መወሰኑ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ 1ኛ ተጠሪ ከስራ አስኪያጅነት ሉሻሩ ይገባል ተብል የቀረበው የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ መደረጉ በወቅቱ ሥራ ላይ የነበረውን የንግድ ህግ አንቀጽ 527(3) እና (5) ፤ የአዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 517(1)፣ እንዱሁም የማህበሩን መመስረቻ ጽሁፍና መተዲደሪያ ደንብ መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ውሳኔው የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። ተከታዩንም ወስነናል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 04/10/2011 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 09/09/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ ተጠሪ ማህበር ሉፈርስ አይገባም ተብል መወሰኑ፤ አመልካች በማህበር አባልነታቸው መቀጠል የማይፈልጉ ከሆነ ድርሻቸውን በመውሰድ ከአባልነታቸው መውጣት የሚችለ ስለመሆኑ፤ እንዱሁም አመልካች ከማህበሩ ያላቸው የአክሲዮን ድርሻ የገበያ ዋጋ የሚገምት ባለሙያ እንዱሾምና ድርሻቸው እንዱታወቅ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
1ኛ ተጠሪ ከዋጋ ሜዱካል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅነታቸው እንዱነሱና በምትካቸው ላላ ሥራ አስኪያጅ እንዱሾም ላደረግ አይገባም በማለት የተሰጠው ውሳኔ ተሸሯል።
1ኛ ተጠሪ ከዋጋ ሜዱካል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅነታቸው እንዱሻሩ ወስነናል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተዖጋውን መዛገብ በማንቀሳቀስ ላላ ሥራ አስኪያጅ የሚሾምበትን ሁኔታ ከግራቀኝ ክርክርና ከህጉ አንጻር ተመልክቶ በተቻለ ፍጥነት ተገቢውን እንዱወሰን ጉዲዩን መልሰናል።
የዘህ ውሳኔ ግልባጭ በአፊጣኝ ለስር ፍርድ ቤት ይድረሰው ብለናል።
በዘህ ፍርድ ቤት ስለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
የስር ፍርድ ቤት መዛገብ በመጣበት መልኩ ይመለስ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.