No summary available.
የካቲት 28 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ታደሰ ዓለምሰገድ-- ጠበቃ ዉብሸት ደምሴ ቀረቡ ተጠሪ፡- ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማ -- ነ/ፈጅ ታደለ ቤዙ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፤
ተጠሪ ተከሳሽ ነበር። አመልካች ታህሳስ 01 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ ክስ በአመልካችና በአማራ ክልል የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ መካከል ነሀሴ 12 ቀን 2010 ዓ/ም የተደረገ የግንባታ ውል ያለ ሲሆን ለቅድመ ክፍያው አመላለስ ቅድመ ክፍያው ከግንባታው ሥራው ዓላማ ውጭ ከዋለ ወይም በግንባታ ውለ መሰረት ዋስትና የተገባለትን ቅድመ ክፍያ ካልመለሰ የሚከፈል የዋስትና ግዳታ ተጠሪ ለአሰሪው ሰጥቷል። የዋስትና ግዳታው ከግንባታው ውል አፈጻጸም ጋር ግንኙነት የላለው ነው። ተጠሪ በዋስትና ግዳታው ላይ የተመለከቱ ሁኔታዎችና መስፈርቶች መሟላት አለመሟላታቸውን ሳይመረምር አሰሪው የግንባታ ሥራው ባለመሰራቱና ሉሰራ ስለማይችል በሚል በዋስትና የተመለከተው ገንዖብ እንዱከፈለው ሲጠይቀው ተጠሪ ብር 20,551,492.40 ከፍሎል። ክፍያው የተፈጸመው ከዋስትና ሰነደ በማይስማማ ጥያቄና ከቅድመ ክፍያው ውል ድንጋጌ ውጭ በመሆኑ አመልካች የማይገደድበት ስለሆነ ውልና ተግባሩ ፈርሶና ተሰርዜ ለዋስትና ግዳታው ለተጠሪ ባንክ የተሰጠ ኮሚሽን እንዱመለስ፣ እንዱሁም በተሰጡ ዋስትናዎች አመልካች የማይገደድ ነው ተብል ዋጋ አልባ ወይም ፈራሽ ናቸው ተብል እንዱፈርሱ/እንዱሰረዘ እና ወደነበርንበት እንድንመለስ እንዱወሰን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች ክሱን ካቀረቡ በኋላ ታህሳስ 07 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የዋስትና ግዳታውን ባላከበረ መልኩ ክፍያውን ተጠሪ ከፈጸመ በኋላ ለዋስትና ግዳታው የተሰጡ መያዡዎችን ለመሸጥ የሐራጅ ማስታወቂያ ስላወጣ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 154 እና 155 እንዱታድ መጠየቁን ተከትል እግድ የተሰጠ ሲሆን ተጠሪ እግደ እንዱነሳ በመጠየቁ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ያወጣው ሀራጅ ሉቆም አይችልም በማለት የእግድ ትዔዙዘን አንስቷል። አመልካች በዘህ ዉሳኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡ ሲሆን፣ ይግባኝ ሰሚዉ ችልት የአመልካችን ይግባኝ ባለመቀበል ሰርዝል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዘህ ዉሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታው ይዖትም የዋስትና ግዳታው እንዱፈርስ ክስ አቅርበን እያለ፤ ለዘህ የዋስትና ግዳታ የተሰጠው ጠለፊ የንብረት ዋስትና የተሰጠ ይሁን አይሁን በራሱ የሚነሳ ክርክር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤
የጠለፊ ዋሱን ንብረት የሚሸጠው ቢሆን ያልተገባ የመዲረግ መብት ለአቶ የሱፍ ሰዑድ ስለመፍጠሩ ከወዱሁ ሉረጋገጥ በማይችልበት ተጠሪ በአግባቡ ቢከፍል ኖሮና ባይመለስለት በሚል በዋስትና የያዖውን ንብረት እንዲይሸጥ፣ ቢሸጥ የማይመለስ ጉዲት የሚያስከትል በመሆኑ እንዱታገድ ያቀረብነው ጥያቄ ውደቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም። የዋስትና ሰነድ መሰረት ያደረገው ክርክር በአዋጅ ቁጥር 97/1990 የሚገዙ አይደለም። አዋጅ ቁጥ 97/90 ለብድር ውል ተፈጻሚነት ያለው ነው። ስለሆነም በአመልካች ስም የወጣው ጨረታ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ እስኪታወቅ ማስታወቂያው እንዱታገድ እና የሥር ፍርድ ቤቶች ትዔዙዛ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
211 መሰረት እንዱሽር የሚል ነዉ።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ግዳታውን የተወጣው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ክርክር በሥር ፍርድ ቤት በመታየት ላይ ባለበት አመልካች ያቀረቡት የእግድ አቤቱታ ውድቅ መደረጉ አግባብነቱን ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ ጥሪ ተደርጎላታል። በዘህም መሰረት ተጠሪ ያቀረበው መልስ የዋስትና መስጫ ውለ አንቀጽ 3 ላይ ክፍያው እንዱከፈል በተጠየቀ ጊዚ ባንኩ ሳይከራከርና በባለዔዲውና በዋስትና ተጠቃሚው መካከል ያለውን አለመግባባት ሳይመለከት የዋስትና ገንዖቡን በሙለ ወይ በከፉል ለዋስትና ተጠቃሚው ለመክፈል ግዳታ መኖሩን ያሳያል። በአሰሪው በተጠየቀው መሰረት ተጠሪ ገንዖቡን ከፍሎል። ክፍያው የተፈጸመው በዋስትና ሰነደ ላይ የተቀመጡ ሁኔታዎች መሟላታቸውን በማረጋገጥ ነው።
አመልካች ያቀረቡት ክስ ባንኩ የከፈለው ገንዖብ መመለስ እንዲይችልና መብቱን ለመጉዲት ነው። አዋጅ ቁጥር 97/90 ለማንኛውም ዔዲ ተፈጻሚነት ያለው ሕግ ነው። ለዋስትና መስጫ ውል ግዳታ አፈጻጸም ዋስትና ይሆን ዖንድ ታህሳስ 06 ቀን 2011 ዓ/ም በተፈረመ የመያዡ ውል መሰረት ስመ ንብረቱን በአቶ የሱፍ ሰይድ የተመዖገበ መኖሪያ ቤት በመያዡ ይዖናል።
ያሲዘት ግለሰብ በሥር ፍርድ ባቀረቡት ጣልቃ ገብ አቤቱታ ለዔዲው አመላለስ ንብረቱን ማሲያዙቸውን አምነዋል። ባንኩ በሕግ ባለው ሥልጣን መሰረት የሐራጅ ማስታወቂያ ማውጣቱ ተገቢ ነው። ባንኮች የሐራጅ ማስታወቂያ ሲያወጡ ፍርድ ቤቶች ሂደቱን ማደናቀፍና እግድ መስጠት እንደላለባቸው ሰበር ችልት በተለያዩ መዛገቦች አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቷል። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች እግደን ማንሳታቸው የሚነቀፍ አይደለም በማለት ጸንቶ እንዱወሰንለት ዲኝነት ጠይቋል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የተሰጠው እግድ እንዱነሳ መወሰኑ ሕጋዊነቱን? በጭብጥነት በመያዛ መዛገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ በአመልካችና በአማራ ክልል የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ መካከል ነሀሴ 12 ቀን 2010 ዓ/ም የተደረገ የግንባታ ውል ያለ ሲሆን ለቅድመ ክፍያው አመላለስ ቅድመ ክፍያው ከግንባታው ሥራው ዓላማ ውጭ ከዋለ ወይም በግንባታ ውለ መሰረት ዋስትና የተገባለትን ቅድመ ክፍያ ካልመለሰ የሚከፈል የዋስትና ግዳታ ተጠሪ ለአሰሪው ሰጥቷል። ተጠሪ በዋስትና ግዳታው ላይ የተመለከቱ ሁኔታዎችና መስፈርቶች መሟላት አለመሟላታቸውን ሳይመረምር አሰሪው የግንባታ ሥራው ባለመሰራቱና ሉሰራ ስለማይችል በሚል በዋስትና የተመለከተው ገንዖብ እንዱከፈለው ሲጠይቀው ተጠሪ ብር 20,551,492.40 ከፍሎል። ክፍያው የተፈጸመው ከዋስትና ሰነደ በማይስማማ ጥያቄና ከቅድመ ክፍያው ውል ድንጋጌ ውጭ በመሆኑ አመልካች የማይገደድበት ስለሆነ ውልና ተግባሩ ፈርሶና ተሰርዜ ለዋስትና ግዳታው ለተጠሪ ባንክ የተሰጠ ኮሚሽን እንዱመለስ፣ እንዱሁም በተሰጡ ዋስትናዎች አመልካች የማይገደድ ነው ተብል ዋጋ አልባ ወይም ፈራሽ ናቸው ተብል እንዱፈርሱ/እንዱሰረዘ እና ወደነበርንበት እንድንመለስ እንዱወሰን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካች ታህሳስ 07 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የዋስትና ግዳታውን ባላከበረ መልኩ ክፍያውን ተጠሪ ከፈጸመ በኋላ ለዋስትና ግዳታው የተሰጡ መያዡዎችን ለመሸጥ የሐራጅ ማስታወቂያ ስላወጣ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 154 እና 155 እንዱታድ መጠየቁን ተከትል እግድ የተሰጠ ሲሆን ተጠሪ እግደ እንዱነሳ በመጠየቁ የሥር ፍርድ ቤቶች ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ያወጣው ሀራጅ ሉቆም አይችልም በማለት የእግድ ትዔዙዘን አንስተዋል።
እግድ በሰው የንብረት መብት አጠቃቀም ላይ ገደብ የሚፈጥር ነው። በኢፋዱሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 40(1) ላይ ጥበቃ የተደረገለት ንብረት መብት ላይ ገደብ ለማድረግ ደግሞ በሕግ በግልጽ በተመለከተ፣ ውስን ጉዲይና አፈጻጸሙም መብቱን መልሶ የመውሰድ ያህል ውጤት በማይፈጥር ሁኔታ ውስጥ ብቻ ላሆን ይገባል የሚለው ስለሰብዓዊ መብት ጥበቃ የተደረጉ የሥምምነት ድንጋጌዎች ሆነ በሕገ-መንግሥቱ ውስጥ የተቀረጸ የሕግ መርሕ ነው።
በፍትሐብሕር ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 154 እና 155 መሰረት የሚሰጥ እግድ፣ የፍትሐብሕር ጉዲዮችን በማየት ላይ ያለ አንድ ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት ከሚሰጣቸዉ የተለያዩ ጊዚያዊ የእግድ ትዔዙዜች አንደ ነዉ (የህጉ አንቀጽ 147-159 ይመለከቷል)። በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 154 ላይ እና በተከታዩ አንቀጽ 155 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዖብ እንደሚቻለዉ ክርክሩ በማናቸዉም ደረጃ ላይ ባለበት ጊዚ ላላዉን ተከራካሪ ወገን ሉጎዲ የሚችል አንድ የተወሰነ ተግባር እንዲይፈጸም በፍርድ ቤት የሚሰጥ ትዔዙዛ ነዉ። በእነዘህ ድንጋጌዎች መሰረት እግድ የሚሰጠዉ አንደኛ በንብረቱ ላይ የሚፈጸመዉ ተግባር ላላዉን ተከራካሪ የሚጎዲ ሲሆን (አንቀጽ 154)፣ ሁለተኛ ክርክሩ ከዉል ጋር የተያያዖ እንደሆነ ዉል እንዲይፈርስ ወይም አንድ ተግባር እንዲይፈጸም የሚያሰጋ ሆኖ ሲገኝ (አንቀጽ 155) ስለመሆኑ ከየድንጋጌዎቹ ይዖት የምንገነዖበዉ ነዉ።
ንብረትን በተመለከተ የሚሰጥ የእግድ ትዔዙዛም ነገሩ በፍርድ እስኪወሰን ወይም ላላ ትዔዙዛ እስኪሰጥ ድረስ ንብረቱ እንዲለ እንዱቆይ፣ ከመጥፊት እንዱድን ወይም እንዲይበላሽ፣ ለላላ ሰዉ ተላልፍ እንዲይሰጥ፣ ወደ ላላ ስፍራ እንዲይዙወር ወይም እንዲይባክን የሚሰጥ ነዉ። በዘህ መልኩ የሚሰጥ እግድ ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉን ንብረት የሚመለከት መሆኑንም ልብ ይሎል። በህጉ አንቀጽ 154(ለ) ላይ “ተከሳሹ የባለገንዖቦችን ጥቅም ለመጉዲት ሲል ንብረቱን ለማጥፊት፣ ለላላ ሰዉ አሳልፍ ለመስጠት ያቀደ፣ የዙተ፣ ወይም ያሰበ መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ነገሩ በፍርድ እስኪወሰን ድረስ ንብረቱ እንዲለ እንዱቆይ…..” በሚል የተገለጸዉ ላይ ላዩን ሲታይ፣ የተከሳሽን ማንኛዉንም ንብረት ማሳገድን የሚመለከት ይመስላል። ይሁንና የተከሳሽ ማናቸዉም ንብረት ሉከበር የሚችልበት ሁኔታ በህጉ አንቀጽ 151 ላይ ተመልክቶ እያለ፣ ህግ አዉጪዉ ለተመሳሳይ ዓላማ ተመሳሳይ ይዖት ያለዉ ላላ ድንጋጌ በዘህ አንቀጽ ስር በድጋሚ ይደነግጋል ተብል አይታሰብም። ይልቁንም በተጨባጩ ዓለም ሲታይ፣ አንዲንድ ባለዔዲዎች የሚጠበቅባቸዉን ዔዲ አለመክፈላቸዉን ተከትል ገና ለገና ንብረታቸዉ ለዔዲ ማስፈጸሚያ ይዉላል በሚል ሃሳብ ወይም በልላ ምክንያት ንብረቶቻቸዉን ሉያጠፈ፣ ለላላ አካል አሳልፍዉ ሉሰጡ የሚችለባቸዉ ሁኔታዎች ይኖራለ። ይህም ሲሆን፣ ባለገንዖቦች ያላቸዉ መፍትሓ ባለዔዲዉ ከዘህ ድርጊቱ እንዱታቀብ ለፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ እግድ እንዱሰጣቸዉ ዲኝነት መጠየቅ ነዉ። ይሁንና የቀረበዉ የእግድ ዲኝነት ጥያቄ ታይቶ ዉሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ንብረቱን የማሸሹ ወይም ለማጥፊት የመሞከሩ ስጋት የሚቀጥል ከሆነ በከሳሽ ላይ ከፍተኛ ወይም የማይመለስ ጉዲት ሉደርስ ይችላል ወይም እግድን አስመልክቶ የቀረበዉንም ዲኝነት ዉጤት አልባ ያደርጋል። በህጉ አንቀጽ 154(ለ) ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌም በዘህ መልኩ ማለትም ተከሳሽ በድንጋጌዉ ላይ የተመለከቱትን ድርጊቶች እንዲይፈጽም እግድ እንዱሰጥ የቀረበዉ ክስ ዉሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ተከሳሽ ከድርጊቱ እንዱታቀብ ለጊዚዉ እግድ እንዱሰጥ የሚቀርበዉን ጥያቄ የሚመለከት እንደሆነ መገንዖቡ ተገቢ ነዉ።
በአጠቃላይ በህጉ አንቀጽ 154 መሰረት የሚሰጥ እግድ ከክሱ ጋር ተያያዣነት ባላቸዉ ንብረቶች ወይም ጉዲዮች ላይ ሲሆን፣ ከሳሽ በቂ ምክንያት ያለዉ መሆኑ በቀረበዉ ክስ መብቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ሉካስ የማይችል ጉዲት እንዲይደርስበት ጥበቃ የሚያስፈልገዉ መሆኑንና እግድ ካልተሰጠ የበለጠ ጉዲት የሚደርስበት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ እንዱሁም የተጠየቀዉ የእግድ ትዔዙዘ ካልተሰጠ ከሳሹ በክሱ የጠየቀዉን ዲኝነት ያጣል፤ የክስ ዓላማም ዋጋ ያጣል የሚል እምነት ፍርድ ቤቱ ሲኖረዉ ስለመሆኑ በአንቀጹ ላይ እንደ ቅድመ ሁኔታ ከሰፈሩት ድንጋጌዎች ይዖትና መንፈስ መገንዖብ ይቻላል። የእግድ ትዔዙዛ በመርሕ ደረጃ የቀረበ ክስን መሰረት ያደረገ እና በሥነ-ሥርዓት ሕጉ አግባብ በተመለከቱት መስፈርቶች የሚሰጥ ነው።
ዓላማው ደግሞ ክሱ ያለውጤት እንዲይቀርና ፍርድ በሚሰጥበት ጊዚም የሚፈጸምበት ንብረት እንዱኖርና ዚጎች መብታቸውን ማስከበር የሚችለበትን ዔድል የሚፈጥርና በሂደቱም ፍርድ ቤቶች ላይ ያላቸውን እምነት የሚጨመር ነው።
ተጠሪ እግደ ሉነሳ ይገባል በማለት የሚከራከረው በዋስትና ግዳታው መሰረት ለግንባታ አሰሪው የቅድመ ክፍያ ዋስትና ገንዖቡን ከፈጸምኩ በኋላ ለዋስትና የተያዖው የመያዡ ንብረትን በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሰረት የመሸጥ ሥልጣን ያለኝ ስለሆነ ሐራጁ ሉቆም አይገባም በማለት ነው። ተጠሪ ባንክ በገባው ግዳታ መሰረት የዋስትና ቦንድ ግዳታውን ከፈጸመ ለተከፈለው ገንዖብ አመልካች ባለዔዲ ስለሚሆን በአዋጅ ቁጥር 97/1990 አንቀጽ 4 መሰረት ባለገንዖብ የሆነው ባንክ መያዡውን የመሸጥ ሥልጣን ይሰጠዋል። አዋጅ ቁጥር 97/1990 ለባንኮች በመያዡ የያዘትን ንብረት በራሳቸው ሽጠው ገንዖቡን ለማስመልስ የሚችለበትን ሥልጣንና ኃላፉነት የሚዖረዛር ሕግ ነው። አዋጅ ቁጥር 97/1990 መግቢያ ላይ እንደተመለከተው ባንኮች በመያዡ የያዘትን ንብረት ላይ በፍርድ ቤት ክስ አቅርበው ለማስወሰንና ለማስፈጸም የሚወስደው ጊዚ ረጀም ጊዚ በመሆኑና ይሕም ባንኮች ሥራ ላይ ተጽዔኖ በማሳደሩ፣ ለኢኮኖሚው እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ባንኮች ለተለያዩ የልማትና ንግድ እንቅስቃሴ የሚሰጧቸውን ብድሮችን በተቀላጠፈ መንገድ ለመሰብሰብ እንዱችለና ለወደፉቱ ጥሩ የንግድ አሰራር ባሕል እንዱዲብር ለማድረግ ለባንክ ብድር በመያዡ የተሰጡ የማይንቀሳቀሱና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ሽያጭ በሚመለከት በሥራ ላይ ያለ ሕጎችን በማሻሻል አዱስ ሥርዓት መዖርጋትን ዓላማ አድርጎ የወጣ ሕግ ነው። በዘህ ሕግ በመያዡ የተያዖን ንብረት ባንኮች በራሳቸው የመሸጥ መብት የተሰጣቸው ሲሆን መብቱ ገደብ የላለው (absolute right) ባለመሆኑ ንብረቱን ከመሸጥ ታግድ እንዱቆይ በፍርድ ቤት ትዔዙዛ እንዱሰጥ ጥያቄ ላቀርብበት ይችላል። በልላ በኩል የሚኖረው ገደብ ለፊይናንስ ተቋሞች በሕግ የተሰጠውን ሥልጣንና ሕጉ ሉያሳካ የፈለገውን ዓላማ ቀሪ በሚያደርግ አግባብ እንዲይሆን ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
የዋስትናን መሰረታዊ ሃሳብ ባለዔዲዉ ግዳታዉን ያልተወጣ እንደሆነ ይህን ግዳታ ለመወጣት በባለዔዲዉ ለባለገንዖቡ የሚሰጥ ማረጋገጫ ነዉ። ዋስትና በአጠቃላይ የሰዉ (personal security) እና የንብረት (real security) ተብል በሁለት የሚመደብ ሲሆን፣ የማይንቀሳቀስ ንብረትን መያዡ በማድረግ የሚሰጥ ዋስትና (mortgage) በንብረት ዋስትና ስር የሚመደብ ነዉ። በእኛ አገር የማይንቀሳቀስ ንብረት ዋስትና ምንጩ ዉል፣ ህግ አሉያም ደግሞ የፍርድ ቤት ዉሳኔ ላሆን እንደሚችል ከፍትሐብሕር ህጋችን አንቀጽ 3041 ቀጥተኛ ንባብ መገንዖብ እንችላለን። የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዡ እንደማንኛዉም ዓይነት ዋስትና ደባል ግዳታን (accessory obligation) የሚጥል ነዉ። በመሆኑም በህግ ፉት ተፈፃሚነት ይኖረዉ ዖንድ፤
ቅቡልነት ያለዉን ዋና ግዳታ (valid principal obligation) መሰረት ያደረገ፣ አመሰራረቱም ግልጽና የማያሻማ እንዱሁም የገንዖብ መጠኑን የሚገልጽና ከዋናዉ ግዳታ ያልከበደ ላሆን እንደሚገባ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1923፣ 1924፣ 1926 እና 3045 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች የምንገነዖበዉ ነዉ። በህግ አግባብ የተቋቋመ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዡ ዉጤቱ ለዋስትናዉ ምክንያት የሆነዉ ዔዲ እስከሚከፈል ድረስ ንብረቱን የመከታተል መብት (right in rem) ለዋስትና ተቀባዩ የሚሰጥ ሲሆን፣ ከዘህም ዉስጥ አንደ ዋስትና ተቀባዩ ከላልች ባለገንዖቦች የቅድሚያ መብት እንዲለዉ በህጉ አንቀጽ 3059(1) ላይ በግልጽ የተመለከተዉ ነዉ።
ተጠሪ የመያዡ መብቱን ያገኘው ከአመልካች ጋር ባለው የውል ግንኙነት ለሚመጣ ዔዲ አቶ ዮሴፍ ሰዑድ በአዱስ አበባ ከተማ ቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16 ያላቸውን ቤት መያዡ በማድረጋቸው ነው። የተጠሪ የመብት ምንጭ ውል እንደመሆኑ መጠን ውለ በአመሰራረት ጉድለት ሆነ በውል አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ጉዲዮች እንዱፈርስ ወይም እንዱሰረዛ ክርክር ላቀርብበት እንደሚችል ከፍ/ሕ/ቁ. 1808 እና 1771 እና ተከታይ ድንጋጌዎች የምንገነዖበው ነው። ባንክ ከላልች ተዋዋዮች በተለየ የገባሁት ውል ላይ ክስ ላቀርብበት አይችልም በሚል ሉከራከር አይችልም። አመልካችም ክስ ያቀረቡት ይህን መሰረት በማድረግ ነው። ለመያዡው መሰረት የሆነው ግዳታ ቀሪ ወይም ፍርስ የሚሆን ከሆነ ዋስትና/መያዡው አብሮ ቀሪ የሚሆን ነው። አመልካች ባቀረቡት ክስ መሰረት የሚወሰንላቸው ቢሆን ከተጠሪ ጋር ያላቸው ግዳታ/ዔዲ ቀሪ ስለሚሆን ለግዳታ ተያያዣ የሆነ የመያዡ ውልች አብረው ቀሪ ስለሚሆኑ የእግድ ጥያቄው ከክሱ ውጤት ጋር የተያያዖ ነው። ተጠሪ የመያዡ ንብረቱን ክሱ ውጤት ሳያገኝ አስቀድሞ የሚሸጠው ከሆነ አመልካች ያቀረቡት ክስ ያለውጤት እንዱቀር የሚያደርግና ፍርድ ቢያርፍበት እንኳን ውጤት የላለውና የማይፈጸም ያደርገዋል።
ዚጎች በፍትሕ ሥርዓቱ የሚጠቀሙት መብታቸውን ለማስከበር ነው። የመብት ማስከበር መሰረቱ ደግሞ ፍርድን ከማናቸውም መሰናክል ነጻ በማድረግ ማስፈጸም ነው። ፍርድ ቤቶች በዘህ አግባብ ኃላፉነታቸውን ካልተወጡ ዚጎች በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 ያገኙት ፍትሕ የማግኘት መብትን ማረጋገጥ እና ማስፈጸም አይቻልም። ውጤቱ ደግሞ መብት ካለመከበሩም በተጨማሪ ፍርድ ቤቶች ላይ እምነት (public trust) እንዲይኖር ያደርጋል።
ስለሆነም ፍርድ ቤቶች ሰብዓዊ መብቶችን ከማስከበር እና የሕግ የበላይነት እንዱኖር ያላቸውን የማይተካ ሚና የመወጣት ግዳታ ያለባቸው በመሆኑና አንደ መገለጫ የወሰኑትን ውሳኔ የሚፈጸም ስለመሆኑ በሕጉ የተዖረጉ ሥርዓቶችን በመከተል ፍርደ ያለውጤት ቀሪ እንዲይሆን መከላከል ነው። በዘህ አግባብ ከተዖረጉ ሥርዓቶች አንደ ደግሞ የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 154 እና 155 የተመለከተው ሲሆን የድንጋጌዎቹ ዋና ዓላማም ንብረቱን የማሸሹ ወይም የማጥፊት ሂደቶችን በማስቆም በከሳሽ ላይ ከፍተኛ ወይም የማይመለስ ጉዲት እንዲይደርስ መከላከልና የቀረበው ክስም ዉጤት አልባ እንዲይሆን ማድረግ በመሆኑ አመልካች ያቀረቡትን የእግድ ጥያቄ ከዘህ ማዔቀፍ መመልከቱ ተገቢ ነው።
ተጠሪ ቀድም ሲል በሰበር ችልት የተሰጡ ትርጉሞችን መሰረት በማድረግ የተከራከረ ሲሆን ሰበር ችልቱ በመዛገብ የተሰጡ ትርጉሞች ባንክ የገባው ውል ላይ እንዲይፈርስ ወይም እንዱሰረዛ ክስ በቀረበ ጊዚ፤ የውለ መፍረስ ውጤት የመያዡ ውለን ቀሪ የሚያደርገው ከሆነ ባንክ ያወጣው ሐራጅ እንዱቆም ትዔዙዛ ላሰጥ አይገባም በሚል የተሰጡ ትርጉሞች ባለመሆናቸው ለተዖያው ጉዲይ ተፈጻሚነት የላቸውም። በልላ በኩል ክስ የቀረበበት የዋስትና ውልና የዋስትና ግዳታ ሰነድ/ቦንድ በቅድመ ሁኔታ ወይስ ያለቅድመ ሁኔታ የተደረጉ ናቸው የሚለው ጉዲይ ክሱን በሚመረምረው ፍርድ ቤት እልባት የሚያገኙ ሲሆን የዋስትና ግዳታ ሰነድች የሦስትዮሽ ውል በመሆናቸው በዋነኛት ያለቅድመ ሁኔታ መሆኑ የሚጠቅመው የዋስትና ግዳታው የተገባለት ተጠቃሚን ነው። አሁን በተያዖው ጉዲይ የዋስትና ግዳታ ሰነደ ተጠቃሚው የአማራ ክልል የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ሲሆን ተጠሪ ክፍያውን የፈጸመለት በመሆኑ የዋስትና ገዳታው ሰነድ ያለቅድመ ሁኔታ የተደረገ ቢሆን እንኳን እግድ መሰጠቱ የሰነደ ውጤት ላይ የሚያመጣው ለውጥ ባለመኖሩ እግደ ሉነሳ የሚገባ አይደለም። በአጠቃላይ የሥር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የመያዡ መብት ያቋቋመበት ንብረት ላይ የተሰጠው እግድ ሉነሳ ይገባል በማለት የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ/ም እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ ቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16 ቤት ላይ ያወጣው ሐራጅ ታግድ ሉቆይ ይገባል ብለናል።
በዘህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ትዔዙዛ የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። በውሳኔው መሰረት እንዱፈጸም አዖናል።
ይጻፍ መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.