No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ ወርቅነሽ ጀቤሳ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አክስዮን ማህበር - የቀረበ የለም 2ኛ. አቶ ሚካኤል ማሙዬ - የቀረበ የለም መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ክርክሩ ከባንክ ለተወሰደ ብድር በመያዡነት የተያዖ ቤት ሽያጭ ውል ይፍረስልኝ ክስ በፍርድ ቤት ላቀርብ የሚችልበትን ሁኔታ የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩ በተጀመረበት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፤ ተጠሪዎች እንደየቅደም ተከተላቸው 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች ነሐሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ በአመልካች እና በአቶ በቀለ ገመዲ ዱኖ መካከል የነበረው ጋብቻ ጥር 30 ቀን 2008 ዓ.ም በፍቺ የፈረሰ ሲሆን በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 14 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥሩ አዱስ፤ የካርታ ቁጥሩ 10/80/50-2917/11 የሆነን ቤት እኩል እንድንካፈል እና ቤቱን አስይዖን ከ1ኛ ተጠሪ የተበደርነውን ገንዖብ እንድንከፍል የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ በጥቅምት 03 ቀን 2009 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዘሁ መሰረት በመዛገብ የአፈጻፀም ክስ አቅርቤ ቤቱ በሐራጅ ተሽጦ የባንኩ እዲ ከተከፈለ በኋላ የሚቀረውን ገንዖብ እኩል እንድንካፈል ትዔዙዛ ተሰጥቷል። የቀድሞ ባለቤቴ በ2007 ዓ.ም የወሰደት በ3 ዓመት ነሐሴ 2010 ዓ.ም ተከፍል የሚያልቅ ብድርን በየወሩ ሳናቋርጥ ስንከፍል የቆየን ቢሆንም ተጠሪዎች በተጠቀሱት መዛገቦች የተሰጡትን ውሳኔዎች ወደ ጎን በመተው፤ 1ኛ ተጠሪ ለአመልካች ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ቤቱን በጥቅምት 15 ቀን 2009 ዓ.ም ለ2ኛ ተጠሪ በብር 4,250,000.00 መሸጡን ታህሳስ 6 ቀን 2009 ዓ.ም በፍርድ ቤት ችልት ላይ ለማወቅ ችያለው። የሽያጭ ውለ 1ኛ አመልካች ስልጣኑን ያለአግባብ በመጠቀም የተፈጸመ፤ ለሕግ እና ሞራል ተቃራኒ ስለሆነ ውለ ፈርሶ ቤቱን በአንድነት እና በነጠላ ለአመልካች እንዱያስረክቡ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
1ኛ ተጠሪ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው መልስ አመልካች እና የቀድሞ ባለቤታቸው የወሰደትን ብድር ባለመክፈላቸው መጋቢት 24 ቀን 2008 ዓ.ም በቁጥር ኦኢባ/የቅ/አዋ/405/08 የተፃፈ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀፅ 3 እና በውለ አንቀፅ 15 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለ3ኛ ጊዚ በጋዚጣ በወጣ የሀራጅ ማስታወቂያ ቤቱን ለ2ኛ ተጠሪ መሸጡ ህጋዊ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን ስልጣን የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል።
2ኛ ተጠሪም መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ፅፈው ባቀረበው መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም፤ 1ኛ ተጠሪ በሕግ እና በውል በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቤቱን የሸጠ ስለሆነ 2ኛ ተጠሪ ልከሰስ አይገባም፤ ክሱ የክስ ምክንያት የለውም በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም መቃወሚያውን መርምሮ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ባንኮች ለብድር አመላለስ በዋስትና የያዘትን ንብረት በሀራጅ መሸጥ የሚችለ መሆኑ ተመላክቷል። ሽያጩ የሐራጅ ስርዓቱን አልተከተለም የሚባል ከሆነ ካሳ ከሚጠየቅ በቀር በመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ የሚቀርብበት አለመሆኑን በሰ/መ/ ውሳኔ የተሰጠበት ስለሆነ ጉዲዩ ላይ ለመወሰን ስልጣን የለኝም በማለት ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ይግባኛቸውን ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዝል።
አመልካች ህዲር 14 ቀን 2014 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡት ይህን የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአቤቱታው ይዖት ባጭሩ በአመልካች እና በቀድሞ ባለቤቴ አቶ በቀለ ገመዲ መካከል በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ በነበረው ክርክር ጥቅምት 3 ቀን 2009 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ የባንኩ እዲ ተከፍል ቤቱን እኩል እንድንካፈል ውሳኔ የተሰጠ በመሆኑ የመያዡ ውለ በሁኔታ ስለፈረሰ 1ኛ ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 90/97 መሰረት ተጠቃሚ ላሆን ስለማይገባ ጉዲዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት ላታይ ይገባል። የ1ኛ ተጠሪ መብት ቀሪ አልሆነም ቢባል እንኳ የብድር ውለን ሳናቋርጥ በየወሩ እየከፈልን እያለ፤ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠን የክፍያ ጊዚው ከማብቃቱ ነሐሴ 2010 ዓ.ም በፉት ጥቅምት 15 ቀን 2009 ዓ.ም እና በፍርድ ቤት ውሳኔ ካረፈበት በኋላ መሸጡ በአዋጅ ቁጥር 97/90 ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ስለሆነ ጉዲዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚታይ ነው።
የአመልካች ዋና የዲኝነት ጥያቄ ሀራጁ የሀራጅ ስርዓትን አልተከተለም የሚል ሳይሆን ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች ከጅምሩ የሽያጭ ውለ መከናወኑ አግባብ አይደለም ሉፈርስ ይገባል የሚል በመሆኑ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚል ነው።
አቤቱታው በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ አመልካች ተጠሪ ጨረታ ሳያወጣ የሸጠው የቤት ሽያጭ ውል እንዱፈርስ ያቀረቡትን ክስ የስር ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 97/90ን በመጥቀስ ጉዲዩን ለመዲኘት ስልጣን የለኝም በማለት ውድቅ ያደረገበትን አግባብ ከአዋጅ ቁጥር 97/90 እና ከቀረበው የክርክር ጭብጥ አኳያ ሉመረመር ይገባዋል በማለት ተጠሪዎች መልሳቸውን እንዱያቀርቡ አዝል።
1ኛ ተጠሪ ጥር 13 ቀን 2014 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው መልስ በአመልካች፣ የቀድሞ ባለቤታቸው እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል መስከረም 19 ቀን 2007 ዓ.ም በተፈረመ የብድር ውል ቤቱን በመያዡነት በመያዛ በየ3 ወሩ ተከፍል መስከረም 18 ቀን 2010 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ብር 800,000 ያበደረ ቢሆንም ብድሩን መክፈል አልቻለም። በዘህም ምክንያት በተለያዩ ጊዚያት ብድሩን እንዱከፍለ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ መክፈል ባለመቻላቸው በመጨረሻ መጋቢት 24 ቀን 2008 ዓ.ም በቁጥር ኦኢባ/አዋ/405/08 የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ በጋዚጣ የሀራጅ ማስታወቂያ አስነግሮ ለ3ኛ ጊዚ የወጣው የሀራጅ ማስታወቂያም 30 ቀን አየር ላይ ከቆየ በኋላ ቤቱን በሐራጅ መሸጡ ተገቢ ነው። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃ መርምሮ በጨረታ ሑደቱ የተፈጸመ ጉድለት አለመኖሩን አረጋግጦ 1ኛ ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 3 እና በብድር ውለ አንቀጽ 15 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተደረገ ሽያጭ ስለሆነ ጉዲዩን ለማየት የስረ ነገር ስልጣን የለኝም ማለቱ ተገቢ ነው። ለብድር አመላለስ የተያዖን ንብረት የሀራጅ አሻሻጥን እና የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ የሚቀርብ ክስን መደበኛ ፍርድ ቤቶች የመዲኘት ስልጣን የላላቸው መሆኑን የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዛገብ ቅፅ 14 ላይ ውሳኔ የሰጠበት ስለሆነ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተገቢ ነው። 1ኛ ተጠሪ ጨረታ ሳያወጣ ቤቱን ቢሸጥ እንኳ አመልካች ካሳ ከሚጠይቁ በቀር የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ ሉጠይቁ አይችለም። በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ ጥቅምት 3 ቀን 2009 እንዱሁም በመዛገብ ታህሳስ 6 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዔዙዛ የ1ኛ ተጠሪን የቅድሚያ መብት እውቅና የሚሰጥ እንጂ የመያዡ ውለን የሚያፈርስ ባለመሆኑ አቤቱታው ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
2ኛ ተጠሪ በበኩለ ጥር 13 ቀን 2014 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው መልስ አመልካች እና ባለቤታቸው ከ1ኛ ተጠሪ ለተበደሩት ገንዖብ አከራካሪ የሆነው ቤት በዋስትና ያስያዘ ሲሆን ብድሩን መክፈል ባለመቻላቸው ምክንያት 1ኛ ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 97/90፤98/90 እና 216/98 በተሰጠው ስልጣን መሰረት እንደአስፈላጊነቱ በፍሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 394-449 ድንጋጌዎች መሰረት የጨረታ ሑደቱ ተከናውኖ ቤቱን የገዙውት ስለሆነ የሽያጭ ውለ ሉፈርስ አይገባም። ባንኩ ሕጉን አልተከተለም ቢባል ባንኳ አመልካች ካሳ ከሚከፈላቸው በቀር በፍርድ ቤት ሀራጁ ሉቆም ስለማይገባ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል።
አመልካች በበኩላቸው የካቲት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠውን ውሳኔ አግባብነት በስር ፍርድ ቤት ከተደረጉ ክርክሮች፤ በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዱሁም ለጉዲዩ ተገቢነት ካለው የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
እንደመረመርነውም አመልካች በዋናነት የሚከራከሩት በአመልካች እና የቀድሞ ባለቤታቸው መካከል ያለው ጋብቻ ከፈረሰ በኋላ ቤቱን እኩል እንድንካፈል እና ብድሩን እንድንከፍል በመወሰኑ የመያዡ ውለ በሁኔታ ፈርሷል፤ አልፈረሰም ቢባል እንኳ የብድር ገንዖቡን በውለ መሰረት በየወሩ እየከፈልን እያለ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠን ከብድሩ ማብቂያ ጊዚ ነሐሴ 2010 ዓ.ም በፉት ቤቱ በሀራጅ የተሸጠ ስለሆነ ውለ እንዱፈርስ የቀረበውን ክስ የስር ፍርድ ቤት ስልጣን የለኝም በማለት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም የሚል ነው። 1ኛ ተጠሪ በበኩለ አመልካች እና የቀድሞ ባለቤታቸው በብድር ውለ መሰረት ክፍያውን ባለመፈጸማቸው ክፍያውን እንዱፈጽሙ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ባለመፈጸማቸው በመያዡነት የተያዖውን ንብረት በሐራጅ መሸጡ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በውለ አንቀፅ 15 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ነው፤ ጨረታው ጉድለት ቢኖርበት እንኳ ካሳ ከሚጠይቁ በቀር ውለ ሉፈርስ አይገባም በማለት ተከራክሯል። 2ኛ ተጠሪም ይህን የ1ኛ ተጠሪን ክርክር በሚያጠናክር መልኩ መልሳቸውን አቅርበዋል።
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በዋስትና የያዖ ባለገንዖብ ባንክ የሚፈልገው እዲ እንዱከፈል በተወሰነው ጊዚ ሳይከፈለው ቢቀር ከ30 ቀናት ያላነሰ ማስጠንቀቂያ ለባለእዲው በመስጠት በመያዡነት የያዖውን የማይንቀሰቀስ ንብረት በሐራጅ ለመሸጥ እና ባለቤትነቱን ለገዠው ማስተላለፍ የሚችል ስለመሆኑ ይህንንም ሲያደርግ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 394-449 የተመላከቱ ድንጋጌዎችን ተግባራዊ ማድረግ ያለበት እና እነኚሕንም ድንጋጌዎች በመተላለፍ ለሚደርስ ጉዲት ለባለንብረቱ ካሳ የመክፈል ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀፅ 3 እና 6 ላይ ተመላክቷል።
በተያዖው ጉዲይ በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 14 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥሩ አዱስ የካርታ ቁጥሩ 10/80/50-2917/00 የሆነውን ቤት አመልካች እና የቀድሞ ባለቤታቸው የጋራ ንብረት መሆኑ፤
ይህንንም ቤት በመያዡነት ለ1ኛ ተጠሪ አስይዖው መስከረም 19 ቀን 2007 ዓ.ም በተደረገ የብድር ውል ከ1ኛ ተጠሪ ባንክ ገንዖብ መበደራቸው እና 1ኛ ተጠሪ ብድሩ አልተከፈለም በሚል በሐራጅ ጨረታ ቤቱን ለ2ኛ ተጠሪ መሸጡ ግራ ቀኙን አላከራከረም። አመልካች ክስ ያቀረቡት ቤቱ በእዲ ምክንያት የተሸጠው የእዲው የመጨረሻ የመክፈያ ጊዚ ሳይደርስ እና ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ በመሆኑ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያደረጉት የሽያጭ ውል ይፍረስልኝ በሚል ነው።
በመሰረቱ ባንክ በመያዡ የያዙቸውን ንብረቶች በሐራጅ መሸጥ እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ፣ 98/9ዐ እና 216/92 ተመላክቷል። በአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ አንቀጽ 3 እና 4 መሰረት እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 216/92 በተደረገው ማሻሻያም ባንኮች ለሰጡት ብድር አከፊፈል በመያዡነት የተቀበለትን ንብረት የብድር እዲው እንዱከፈለው በተወሰነው ጊዚ ሳይከፈል ከቀረ ከ3ዐ ቀናት ያላነሰ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የመያዡ ንብረቱን በሐራጅ ለመሸጥና ባለቤትነቱንም ለገዣው ለማዖዋወር ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። ባንኮች ይህንን በሚያደርግቡት ጊዚም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ.394-449 ያለትን ድንጋጌዎች እንደአስፈላጊነታቸው ተግባራዊ ማድረግ ያለባቸው መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ በአንቀጽ 6 ላይ ተመላክቷል። ከአዋጁ ድንጋጌዎችም መረዲት የሚቻለው በአበዲሪው ባንክ በዋስትና የተያዖው ንብረት በሀራጅ ከመሸጡ በፉት የብድር ገንዖቡ በመክፈያ ጊዚው ያልተከፈለ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲለበት እንዱሁም ይህን ተከትል ባንኩ ተበዲሪው የብድር ገንዖቡን እንዱመልስ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ የሰጠ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲለበት ነው። ይህ መሆኑ ከተረጋገጠ ባንኩ ያለማንም ጣልቃ ገብነት አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን በመከተል በሐራጅ ሽጦ ለእዲው ክፍያ ማዋል የሚችል ሲሆን በአሻሻጡ ሂደት ባንኩ ሕጉን ባለመከተል የፈፀመው ስህተት ቢኖር እና በዘህም ባለዔዲው ላይ ጉዲት ቢደርስ ለዘህ ጉዲት ባንኩ ለባለእዲው ካሣ የመክፈል ኃላፉነት አለበት። ባለእዲው ባንኩ ያከናወነው የሐራጅ ጨረታ ጉድለት አለበት የሚል ከሆነም ካሳ እንዱከፈለው ክስ ለማቅረብ መብት እና ጥቅም ያለው ሲሆን የሀራጅ ጨረታው ወይም የሽያጭ ውለ ይፍረስልኝ በሚል ክስ ለማቅረብ ግን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33/3 እና 231/1/ሀ መሰረት የክስ ምክንያት አይኖረውም። ከዘህ ጋር በተያያዖም የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዛገብ በቅጽ 14 እንደታተመው የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ የክስ ምክንያት አለው ወይስ የለውም? ከሚለው አንጻር መመርመር ሲገባው ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም በሚል ምክንያት ክሱን ውድቅ ማድረጉ ሉታረም የሚገባው መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው።
በመቀጠል የአመልካች ክስ የክስ ምክንያት አለው የለውም የሚለውን ስንመለከት አበዲሪ ባንክ በመያዡ የያዖውን ንብረት በእዲው ምክንያት ከመሸጡ በፉት የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ መስጠት እንዲለበት እና እዲውም የበሰለ ወይም የመክፈያ ጊዚው የደረሰ መሆን እንዲለበት በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 3 እና 4 ላይ ተመልክቷል። ይህም ማለት ባንኩ በመያዡ በያዖው ንብረት ላይ የሐራጅ ጨረታ በማውጣት ከመሸጡ በፉት ይህንን በህግ የተጣለበትን ግዳታ መወጣት ይኖርበታል። ነገር ግን ባንኩ የእዲው መክፈያ ጊዚ ከመድረሱ በፉት ንብረቱን በጨረታ የሸጠ ከሆነ የውል ጥሰት ተግባር እንደፈጸመ ይቆጠራል። ባንኩ በመያዡ የያዖውን ንብረት በጨረታ ሸጦ እዲውን የመሰብሰብ መብት የሚኖረው ውለን ካከበረ እና ተበዲሪው በብድር ውለ በተመለከተው አግባብ የሚጠበቅበትን እዲ መክፈል ካልቻለ ነው። ከዘህ ውጪ ባንኩ መያዡ ሰጪው በውለ መሰረት እዲውን የሚከፍልበት ጊዚ እና ሁኔታ አለማክበሩን ወይም መጣሱን ሳያረጋግጥ በመያዡ የያዖውን ንብረት በሀራጅ የሸጠ እንደሆነ ይህ ተግባር የውል ጥሰት ስለሚሆን እና መያዡ ሰጪው ከህግ ውጪ የባለቤትነት መብቱን ሉያጣ ስለማይገባ በመደበኛ ፍርድ ቤት የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ ክስ የማቅረብ መብት እና ጥቅም ይኖረዋል። በተያዖው ጉዲይ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ካደረጉት ክርክር እና ካቀረቡት የሰበር አቤቱታ መገንዖብ የሚቻለው ዋና የዲኝነት ጥያቄያቸው በአመልካች፣ በቀድሞ ባለቤታቸው እንዱሁም በ1ኛ ተጠሪ መካከል በተደረገው የብድር ውል መሰረት በየወሩ ክፍያ እየፈፀምን ቢሆንም የብድር መክፍያ ጊዚው ከሚጠናቀቅበት ነሐሴ 2010 ዓ.ም በፉት 1ኛ አመልካች ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ ቤቱን በሐራጅ መሸጡ ተገቢ አይደለም የሚል ነው። ይህም የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ከመነሻው ብድሩን እየከፈልኩ ባለሁበት ቤቱ በጨረታ መሸጡ አግባብ አይደለም የሚል እንጂ 1ኛ ተጠሪ ጨረታውን ሲያካሑድ በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀፅ 6 እንዱሁም አዋጁን ባሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 መሰረት የጨረታ ስርዓቱን አልተከተለም ወይም በፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ በተደነገገው አግባብ አልተከናወነም የሚል አይደለም። በመሆኑም ዋናው የክርክሩ ጭብጥ ቤቱ በሀራጅ የተሸጠው አመልካች እዲቸውን ያለማቋረጥ እየከፈለ ባለበት ነው ወይስ አይደለም? 1ኛ ተጠሪ ቤቱን በሐራጅ የሸጠው የእዲው መክፈያ ጊዚ ሳያልቅ ነው የሚባል ከሆነ የሽያጭ ውለን ለማፍረስ በቂ ምክንያት ነው ወይስ አይደለም? የሚለው በፍሬ ነገር ደረጃ በሚደረግ ክርክር እና በሚቀርቡ ማስረጃዎች በማረጋገጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባ (justiciable matter) እና የክስ ምክንያት ያለው ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት ለተያዖው ጉዲይ ተገቢነት የላለውን የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ጠቅሶ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠውን ውሳኔ ይግባኝ ሰሚው ችልት ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ አፈጻጸም እና አተረጓጎም ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
1.የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዛገብ ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽሯል።
2.የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሆነውን መዛገብ አንቀሳቅሶ ከላይ በፍርደ ውስጥ በተገለጸው አግባብ በተጠሪዎች መካከል የተደረገው የሽያጭ ውል ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን አከራክሮ ተገቢውን እንዱወስን መዛገቡን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1) መሰረት በነጥብ መልሰንለታል። ይፃፍ።
3.በዘህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.