No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- መገል አይንትኦቨን ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ልጅስቲክ አገልግልት ድርጅት መዛገቡ ተመርምሮ ከዘህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በደረቅ ወደብ በተቀመጠ ንብረት ላይ ጉዲት ሲደርስ ኃላፉነት የሚያስከትለ እና ኃላፉነት የማያስከትለ ምክንያቶችን የሚመለከት ነዉ። አመልካች በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረተው ክስ ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነው የአመልካች ድርጅት በዱቮትራ ቢቪ ስም ከውጪ ሀገር አንድ ፍርክሉፍት በተጠሪ አማካኝነት አስጭኖ ወደ ሀገር ውስጥ እስከ ሞጆ ደረቅ ወደብ ድረስ አስገብቶ አስፈላጊውን የጉምሩክና ቀረጥ ሥነ ሥርዓት እስከሚፈፀም ድረስ የተጠሪ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በሆነው ሞጆ ደረቅ ወደብ በአደራ እንዱቀመጥ ተደርጓል። ተጠሪ ፍርክሉፍቱን በጥንቃቄ የመያዛ ሕጋዊ ግዳታ አለበት። ፍርክሉፍቱ በ12,000.00 የአሜሪካን ድላር የተገዙ ሲሆን በተጨማሪም አመልካች ብር 599,403.34 ቀረጥና ታክስ ከፍሎል።አመልካች ቀረጥና ታክስ ከፍል ፍርክሉፍቱን ከተጠሪ ለመረከብ ሲጠይቀው ፍርክሉፍቱ ፍፁም ጥንቃቄ በጎደለው አያያዛ በሜዲ ላይ ተጥል ተጠሪ ግዳታውን ሳይወጣ በመቅረቱ ምክንያት በፍርክሉፍቱ ላይ ጉዲት እንዱደርስ አድርጓል።የደረሰውን ጉዲት ለማስተካከል ለመለዋወጫ ብር 400,000.00 እና ለእጅ ሥራ ብር 350,000.00 በድምሩ ፍርክሉፍቱን ወደነበረበት ለመመለስ ብር 750,000 እንደሚያስፈልግ አመልካች በባለሙያ እንዱጣራ አድርጎ አረጋግጧል።በመሆኑ ተጠሪ ይህንን ገንዖብ እንዱከፍል እና ፍርክሉፍቱን እንዱያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪ በቀረበበት ክስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም በሰጠው መልስ ፍርክሉፍቱ ከወደብ መጋዖን እንዱቀመጥ የተደረገው ፍርክሉፍቱ በትርፍነት የተገኘ እንደሆነ ገልጾ ጉምሩክ ባለው አሰራር መሰረት የጉምሩክ ሥነ ሥርዓቶች እስኪጠናቀቁ ድረስ በጊዚያዊነት በሞጆ ደረቅ ወደብ እንዱቀመጥ በወሰነው መሰረት እንጂ አመልካች እንዲለው አመልካች በሕጋዊ መንገድ አምጥቶ በአደራ የተቀመጠ አይደለም። ፍርክሉፍቱ ከባህሪው የተነሳ እና የጉምሩክ ፍርማሉቲ እስኪያሟላ ድረስ እንዱቀመጥ የሚደረገዉ ግዚያዊ ማቆያ በደረቅ ወደብ ነዉ። ተጠሪ በዘህ መንገድ የተጣለበትን ግዳታ በጥንቃቄ ተወጥቷል። አመልካች በራሱ ጥፊት 3 ዓመት ከ6 ወር በላይ ፍርክሉፍቱን በወደብ መጋዖን በማቆየቱ በጊዚ እርዛማኔ ምክንያት በሂደት ለሚፈጠረው ለውጥ ተጠሪ ተጠያቂ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በአመልካች ምክንያት ለደረሰው ጉዲት በአዋጅ ቁጥር 588/2000 አንቀፅ 4/3 መሰረት ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም። ተጠሪ ኃላፉ ነው ቢባል እንኳ እቃው የተገዙው 12,000.00 የአሜሪካን ድላር በመሆኑ የተጠሪ ኃላፉነት በወቅቱ በነበረዉ የኢትዮጵያ ብር ምንዙሪ በብር 18.86 ሂሳብ ብር 226,320.00 ሲመነዖር በወቅቱ በነበረው ምንዙሬ ዋጋ ላሆን ይገባል።ፍርክሉፍቱ በተጠሪ ቁጥጥር ስር በመሆኑ በባለሙያ ሳይታይ እንደታየ ተደርጎ የቀረበዉ ማስረጃ ተገቢ ባለመሆኑ በገለልተኛ መርማሪ ሉመረመር ይገባል።ተጠሪ ኃላፉነት አለበት ከተባለ በፍርክሉፍቱ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ከላይ በገለጽነዉ መሰረት እንዱካስ ተደርጎ ፍርክሉፍቱ ለተጠሪ እንዱቀር እንዱወሰንልን።ፍርክሉፍቱ ለአመልካች ይመለስ የሚባል ከሆነ ደግሞ አመልካች ፍርክሉፍቱወደ ተጠሪ መጋዖን ከገባበት ከነሀሴ 27 ቀን 2005 ዓ/ም ጀምሮ ያለበትን የመጋዖን ኪራይ እንዱከፍል እንዱወሰንልን ሲል ተከራክሯል።እንዱሁም ፍርኪሉፍቱ እንዱቀመጥ ያዖዖዉ የጉምሩክ ባለስልጣን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 43 መሰረት በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ እንዱታዖዛለት ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የቀረበዉን ክርክርና የጉምሩክ ባለሥልጣን በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ የተጠየቀዉን ዉድቅ በማድረግ ፍሬ ነገሩን በተመለከት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎችን መርምሮ በቀን 18/10/2012 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ፍርክሉፍቱ አገር ዉስጥ ገብቶ ከቀን 25/06/2005ዓ/ም ጀምሮ በተጠሪ ዖንድ ለ3 ዓመት ያህል ጊዚ መቀመጡ ግራ ቀኙን አላከራከረም።ፍርክሉፍቱ አገር ዉስጥ በትርፍነት እንደገባ ተረጋግጦ አስፈላጊዉን ክፍያ በመፈጸም እንዱረከብ እና አስከዘያ በተጠሪ መጋዖን እንዱቀመጥ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን እንደሆነ የቀረበዉ ማስረጃ ያሳያል።ተጠሪ ፍርክሉፍቱን በጥንቃቄ የማስቀመጥ ኃላፉነት አለበት።አመልካች ፍርክሉፍቱ ተጠሪ በአግባቡ አላስቀመጠም ፍርክሉፍቱ ፀሐይና ዛናብ ስለተፈራረቀበት እንደተበላሸ ከመግለጽ ዉጪ ተጠሪ ፍርክሉፍቱን ማስቀመጥ የነበረበትን አላስረዲም።በአንጻሩ ተጠሪ ፍርክሉፉት እንደማንኛዉም መኪኖች የሚቀመጠዉ በግልጽ መጋዖን መሆኑን በማስረጃ አስረድቷል።ፍርክሉፍት በግልጽ መጋዖን የሚቀመጥ ከሆነ ፀሐይና ዛናብ የሚፈራረቅበት መሆኑ የሚታመን ነዉ።አመልካች የሚጠበቅበትን ግዳታ በመወጣት ፍርክሉፍቱን መረከብ ሲገባዉ የሚጠበቅበትን ግዳታ ባለመወጣቱ ለዖረጅም ጊዚ ፍርክሉፍቱ ፀሐይና ዛናብ እንዱፈራረቅበት እንዲደረገ ተረጋግጧል።በፍርክሉፍቱ ላይ ጉዲት የደረሰዉ አመልካች በክሱ ላይ እንደገለጸዉ ፀሐይና ዛናብ ስለተፈራረቀበት ቢሆንም ጉዲቱ የደረሰዉ ፍርክሉፍቱ በግልጽ መጋዖን በመቀመጡ ምክንያት ሳይሆን አመልካች ፍርክሉፍቱን በጊዚዉ ባለመዉሰደ ምክንያት በመሆኑ ለደረሰዉ ጉዲት ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም ሲል ወስኗል።እንዱሁም አመልካች የሚጠበቅበትን የመጋዖን ኪራይ ከፍል ፍርክሉፍቱን እንዱወስድ ወስኗል።
አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቢያቀርብም ችልቱ በመ/ ላይ በቀን 11/06/2013 ዓ/ም በሰጠው ትዔዙዛ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዜበታል።
አመልካች በቀን 10/09/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉም ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዖት በአጭሩ፡- የስር የከፍተኛው ፍርድ ቤት ለውሳኔዉ መሰረት ያደረገው በአዋጅ ቁጥር 588/2008 አንቀፅ 4/3/ን የተደነገገዉን ነው። ይህ የተጠቀሰው አንቀፅ እቃው የጠፊው ወይም ጉዲት ለደረሰበት ወይም እርክክብ የዖገየው በባለእቃው ምክንያት መሆኑ ከተረጋገጠ የደረቅ ወደቡ ተጠያቂነት አይኖርበትም የሚል ነው። ወደ አገር የሚገቡ እቃዎች አስፈላጊው የጉምሩክ ፍርማሉቲዎችና ክፍያዎች ተፈፅሞባቸው የእቃው ባለቤት እቃውን እስኪረከብ ድረስ እቃው በጉምሩክ ማቆያዎች እጅ እንደሚቆዩ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2008 አንቀጽ 2/10 እና 2/40 ስር ተደንግጓል። በዘህ መሰረት እቃው በተጠሪ እጅ በሚቀመጥበት ወቅት ተጠሪ እቃው ላይ ጉዲት ወይም ብልሽት እንዲይደርስበት በጥንቃቄ የመጠበቅ ግዳታ አለበት። ለባለእቃው የሚኖርበትን ኃላፉነት ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 588/2008 አንቀፅ 4/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት እቃዉ በደረቅ ወደብ ላይ እያለ…ጉዲት ቢደርስበት…በኃላፉነት እንደሚጠየቅ ተደንግጓል።ይህም የሚያሳየዉ የእቃዉ ባለቤት መክፈል ያለበት አስፈላጊዉን የጉምሩክ ክፍያዎችን ጉምሩክ አሳዉቆት ባለቤቱ ክፍያ ፈጸሞ እቃዉን እስከሚረከብ ድረስ እቃዉን በጥንቃቄ የመጠበቅ ግዳታ ያለበት መሆኑን ነው።ይህ እስከሚሆን ድረስ ተጠሪ ባለእቃዉን ለመረከብ ዖግይቷል የሚል ጥያቄ ሉያነሳ አይችልም።ተጠሪ በአደራ የሚጠብቀዉም በነፃ ሳይሆን ለጠበቀበት ለእያንዲንደ ቀን ክፍያ በማስከፈል ነው።በአዋጅ ቁጥር 588/2008 አንቀጽ 4/3 ላይ የተገለጸዉ መዖግየት በእቃዎቹ ላይ የሚፈጸመዉ የጉምሩክ ፍርማሉቲዎችና ክፍያዎች እስከሚጠናቀቁ ድረስ ያለዉን ጊዚ የሚመለከት ባለሆነበት የሥር ፍርድ ቤት ይህንን ድንጋጌ አለአግባብ ተፈጻሚ አድርጓል።በዘህ ድንጋጌ የተመለከተዉ ጊዚ መታየት ያለበት አመልካች የጉምሩክ ፍርማሉቲዎችንና ክፍያዎችን ፈጽሞ እቃዉን መረከብ ከሚችልበት ቀን በኋላ ያለዉን ጊዚ የሚመለከት ነዉ።ተጠሪ የአመልካችን ፍርክሉፍቱን በአደራ ለመጠበቅ ስለተረከበ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2718/1 እና 2720 መሰረት ፍርክሉፍቱን በተረከበበት ሁኔታ የማስረከብ እና በፍርክሉፍቱ ላይ ለደረሰበት ጉድለት ኃላፉነት ስላለበት በአመልካች ፍርክሉፍት ላይ የደረሰው ጉዲት በተጠሪ ቸልተኝነት ምክንት እንጂ ከአቅም በላይ በሆነ ሀይል የደረሰ ጉዲት አለመሆኑ እየታወቀ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም ሲል የሰጠዉ ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ይታረመልን በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ በአመልካች ፍርክሉፍት ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም የመባለን አግባብ ከአዋጅ ቁጥር 588/2008 አንቀፅ 4(1 እና 3) አላማና አተገባበር አንፃር ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትእዙዛ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 17/02/2014 ዓ/ም የተፃፈ መልሱን ያቀረበ ሲሆን ይዖቱ በአጭሩ፡- አመልካች ፍርክሉፍቱን በትርፍነት አገር ዉስጥ እንዲስመጣ የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቀን 04/13/2005ዓ/ም ባደረገዉ ፍተሻ አረጋግጧል።ፍርክሉፍቱ የመጣለት የአማራ ብሓራዊ ክልል መንግስት ቴኪኒክና የሙያ ኢንተርፕራይዛ ልማት ቢሮ በትርፍነት የመጣዉን ፍርክ ሉፍት የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 53 መሰረት አስፈላጊዉን ፍርማሉቲ አጠናቆ እንዱረከብ በጉምሩክ ኮሚሽን ቢገለጽለትም እንደማይረከበዉ ለባለስልጣኑ አሳዉቋል።በመሆኑም ባለቤት ያልወሰዲቸው የተተዉ እቃዎች በጊዚያዊነት የሚቆዩትበት ጊዚ ከ60 ቀናት መብለጥ እንደማይችል በአዋጁ 859/2006 አንቀፅ 51 ተደንግጓል።በዘሁ አዋጅ አንቀጽ 51/7፣57(2/ለ) እና 61 መሰረት ፍርክሉፍቱ በጊዖያዉ የጉምሩክ ክፍት መጋዖን እንዱቆይ ተደርጓል።ተጠሪ የአመልካችን ፍርክሉፍት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በደረቅ ወደብ አዋጅ 588/2008 መሰረት ባለስልጣኑ እንዱቀመጥ ባዖዖው መሰረት በእቃው ባህርይ መሰረት መሰል ማሽነሪዎች መቀመጥ የሚገባው ቦታ አስቀምጧል።ተጠሪ ከአመልካች ጋር የአደራ ዉል ግንኙነት ስለላለዉ የተጠሪ ኃላፉነት ሉወሰን የሚገባዉ በእነዘህ ልዩ ሕግጋት መሰረት ነዉ። አመልካች በአዋጅ ቁጥር 588/2008 አንቀጽ 4(2 እና 3) ላይ የተወሰነዉ ጊዚ የጉምሩክ ፍርማሉቲ ከመጠናቀቁ በፉት ያለዉን ጊዚ አያካተትም የገለጸዉ የተሳሳተ ነዉ።አመልካች ፍርክሉፍቱን በአዋጁ ከተቀመጠዉ መደበኛ ጊዚም አልፍ ለዓመታት የተወዉ በመሆኑ በግልጽ መጋዖን መቆየት ከሚገባዉ ጊዚ በላይ በመቆየቱ በቆየታዉ በሂደታዊ ለዉጥ የተነሳ የደረሰ ጉዲት ካልሆነ በስተቀር ተጠሪ የፈጸመዉ ጥፊት የለም በማለት የሥር ፍርድ ቤት ክሱን ዉድቅ በማድረጉ የተፈጸመ ስህተት የለም።ይህ ታልፍ የተጠሪ ኃላፉነት አለበት የሚባል ከሆነ የተጠሪ ኃላፉነት በአዋጅ ቁጥር 588/2008 አንቀጽ 5/1 በወቅቱ በነበረዉ ምንዙሪ መሰረት ብር 226,320.00 ነዉ እንዱባልልኝና አመልካች የመጋዖን ኪራይ እንዱከፍል የተወሰነዉ እንዱጸናልኝ በማለት ተከራክሯል።አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዘህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኙ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዖት የሚመለከት ሲሆን እኛም ሰበር አጣሪ ችልት የያዖዉን ጭብጥ ከግምት በማስገባት በፍርክሉፍቱ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም ተብል በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ፍርክሉፍት ከዉጭ አገር አገር ዉስጥ ገብቶ ከቀን 25/06/2005ዓ/ም ጀምሮ ከ3 ዓመት በላይ ለሆነ ጊዚ በሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ በተጠሪ ይዜታ ስር እያለ በፍርክሉፍቱ ላይ ጉዲት እንደደረሰበት ግራ ቀኙ አልተካካደም።በፍርክሉፍቱ ላይ ጉዲት ያደረሰዉ ምክንያት የፀሐይና የዛናብ መፈራረቅ እንደሆነም ግራ ቀኙ የተማመኑበት ነዉ። ግራ ቀኙን ያከራከረዉ አመልካች በፍርክሉፍቱ ላይ ጉዲት ሉደርስበት የቻለዉ ተጠሪ በጥንቃቄ ማስቀመጥ ሲገባዉ ፍርክሉፍቱን ሜዲ ላይ ጥል ፀሐይና ዛናብ እንዱፈራቅበት በማድረጉ ምክንያት ነዉ በማለት ያቀረበዉ ክርክር ነዉ።ከዘህ አንጻር ተጠሪ ደግሞ ፍርክሉፍት በባህርዉ በደረቅ ወደብ በጊዚያዊ ክፍት መጋዖን የሚቀመጥ እቃ እንደሆነ በመግለጽ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ፍርክሉፍቱ ከመነሻዉም በትርፍነት አገር ዉስጥ እንደገባ በፍተሻ በማረጋገጥ አመልካች አስፈላጊዉን የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት በማስፈጸምና የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ከፍል እስከሚያጠናቅቅ ድረስ ፍርክሉፍቱ በጉምሩክ ጊዚያዊ መጋዖን ዉስጥ እንዱቀመጥ የጉምሩክ ኮሚሽን በማዖዘና አመልካች ይህንን ግዳታዉን ሳይወጣ ስለቆየ በጊዚ ርዛማኔ ሂደት በፍርክሉፍቱ ላይ ጉዲት ሉደርስበት ችሎል እንጂ በተጠሪ አያያዛ ጉድለት የደረሰ ጉዲት አይደለም በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤት ከላይ እንደተመለከተዉ ፍርክሉፍቱ ሉቀመጥ የሚችለዉ በጊዚያዊ መጋዖን እንደሆነ፣ በፍርክሉፍቱ ላይ ጉዲት የደረሰዉ አመልካች የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አስፈጽሞ ፍርክሉፍቱን ሳይወስድ ለአመታት በመቆየቱ ምክንያት ፍርክሉፍቱ ፀሐይና ዛናብ ተፈራርቆበት እንጂ በተጠሪ የጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት አይደለም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።
ደረቅ ወደብ ለባለእቃዉ ስለሚኖረዉ ኃላፉነት ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 588/2000 አንቀጽ 4/1 ስር ማንኛዉም ዔቃ በደረቅ ወደብ አስተዲደሩ ቁጥጥር ሥር እያለ ቢጠፊ፣ጉዲት ቢደርስበት… በኃላፉነት እንደሚጠየቅ ደንግጓል። በዘህ አዋጅ አንቀጽ 4/3 ስር እንደተደነገገዉ ዔቃዉ የጠፊዉ ወይም ጉዲት የደረሰበት…በዔቃዉ ወይም በአጓጓዟ ጥፊት ወይም በዔቃዉ የተለየ ባህሪ ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑ ከተረጋገጠ የደረቅ ወደቡ ተጠያቂነት አይኖርበትም።በዘህ አዋጅ አንቀጽ 4/2 መሰረት የተለየ ዉል ወይም ደንብ ከላለ በስተቀር እቃ ማስረከብ ዖገየ የሚባለዉ በደረቅ ወደቡ በዉል ወይም በደንብ መሰረት በተመለከተዉ ጊዚ ዉስጥ ዔቃዉን እንዱያስረክብ ጥያቄ ከቀረበለት ጊዚ ጀምሮ በ3 ቀን ጊዚ ዉስጥ ማስረከብ ሳይችል ሲቀር እንደሆነ በግልጽ ተመልክቷል።በተያዖዉ ጉዲይ የክሱ ምክንያት ተጠሪ የፍርክሉፍት ርክክብ አዖግይቷል የሚል ባለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 4/2 ስር የተደነገገዉ የጊዚ ገደብ ለዘህ ጉዲይ አግባብነት ያለዉ አይደለም።በያዛነዉ ጉዲይ የክሱ ምክንያት በተጠሪ ጥፊት ምክንያት በደረቅ ወደብ እንዱቀመጥ በተደረገዉ ፍርክሉፍት ላይ ጉዲት ደርሷል የሚል ሲሆን በዘህ አዋጅ ላይ ደረቅ ወደቡ አንድ እቃ ለደረሰበት ጉዲት ኃላፉ የሚሆነዉ እቃዉ በወደቡ ምን ያህል ጊዚ ቢቆይ ነዉ ለሚለዉ ጥያቄ አዋጁ በግልጽ መልስ ስለማይሰጥ ለዘህ ነጥብ ምላሽ ለመስጠት የዘህን አዋጅ ተያያዣ የሆኑ ድንጋጌዎች ከጉምሩክ አዋጅ አግባብነት ካለዉ ድንጋጌ ጋር አገናዛቦ መመርመር ያስፈልጋል።በዘህ መሰረት ፍርክሉፍቱ ተጠሪ በሚቆጣጠረዉ ደረቅ ወደብ ላይ ከተቀመጠበት ከ2005ዓ/ም ጀምሮ በመሆኑ በዘህ ጊዚና እና ከዘህ ጊዚ በኋላ ፍርክሉፍቱ በተጠሪ ይዜታ ስር በቆየበት ጊዚ ተፈጻሚ ሲሆኑ የነበሩትን የጉምሩክ አዋጆች መሰረት በማድረግ መርምረናል።
በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 2(10/ሀ) ስር በተመለከተዉ ትርጓሜ መሰረት ጊዚያዊ የጉምሩክ ዔቃ ማከማቻ ማለት ገቢ ዔቃዎች የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም ተከናዉኖባቸዉ እስሚለቀቁ ወይም እንደሁኔታዉ ወደ ቦንድድ የጉምሩክ መጋዖን ወይም ወደ መንግስት የጉምሩክ መጋዖን እስኪዙወሩ… በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆነዉ የሚቆዩበት ዛግ ወይም ክፍት የእቃ ማከማቻ ሥፍራ ሲሆን ደረቅ ወደብን እንደሚጨምር ተመልክቷል።ለ”ጊዚያዊ የጉምሩክ ዔቃ ማከማቻ” ከዘህ አዋጅ በፉት ተፈጻሚ ሲሆን በነበረዉ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 2/29 ላይ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ትርጓሜ ተሰጥቶታል። በያዛነዉ ጉዲይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ፍርክሉፍት አገር ዉስጥ እንደገባ ተጠሪ ፍርክሉፍቱን በሞጆ ደረቅ ወደብ በጊዚያዊ ክፍት ማከማቻ ስፍራ እንዲስቀመጠና በባህሪዉም ፍርክሉፍት መቀመጥ ያለበት በክፍት የዔቃ መጋዖን(ማከማቻ ስፍራ) ነዉ በማለት ተከራክሯል። አመልካችም ተጠሪ ፍርክሉፍቱን በሜዲ ላይ ጥል ፀሐይና ዛናብ እንዱፈራረቅበት አድርጓል በሚል ከመግለጽ ባለፈ ፍርክሉፍቱ በክፍት የዔቃ ማከማቻ ስፍራ መቀመጥ አልነበረበትም በማለት መቀመጥ ያለበትን ስፍራ በመግለጽ በማስረጃ አስደግፍ ያቀረበዉ ክርክር የለም።በመሆኑም በዘህ ረገድ የስር ፍርድ ቤት የተጠሪን ክርክር በመቀበል ፍርክሉፍቱ ባለዉ አሰራር መሰረት በጊዚያዉ ክፍት የዔቃ ማከማቻ ስፍራ እንዱቀመጥ እንደሚደረግ አረገገጫለሁ ሲል የደረሰበት ድምዲሜ ተገቢ መሆኑን ተገንዛበናል።
ዔቃዎች በጉምሩክ መጋዖን (የጉምሩክ መጋዖን ማለት በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 2/9 ትርጓሜ መሰረት ጊዚያዊ የጉምሩክ ዔቃ ማከማቻን ይጨምራል) ዉስጥ ስለሚቆዩበት ጊዚ በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 28/1 እና በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 51/1 ስር ተደንግጓል።በእነዘህ ተጠቃሾቹ አዋጆች ድንጋጌዎች ስር እንደተመለከተዉ ማንኛዉም በባህር ወይም በየብስ ተጓጉዜ አገር ዉስጥ የገባ ዔቃ ጊዚያዊ የጉምሩክ ዔቃ ማከማቻ ከገባበት ቀን ጀምሮ በ2 ወር ጊዚ ዉስጥ (ይህ ጊዚ አዋጅ ቁጥር 859/2006ን ባሻሻለዉ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 ላይ 15(አስራ አምስት) ቀናት ሆኖ ተሻሽሎል) አስፈላጊዉ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ተከናዉኖበት ከማከማቻዉ ማዉጣት አለበት።በዘህ ጊዚ ዉስጥ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ከተከናወነ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 28/5 እና በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 51/6 መሰረት ከ7 የሥራ ቀናት በላይ (ይህ ጊዚ በአዋጅ ቁጥር1160/2011 ላይ 2 የሥራ ቀናት ሆኖ አጥሯል) በማከማቻ ስፍራ እቃዉ ሉቀመጥ እንደማይችል ተደንግጓል።ከዘህ መገንዖብ የሚቻለዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ፍርክሉፍት በተጠሪ በሚተዲደረዉ በሞጆ ደረቅ ወደብ ጊዚያዊ ክፍት የዔቃ ማከማቻ ስፍራ እንዱቀመጥ በተደረገበት በ2005 ዓ/ም እና ከዘህ በኋላ በተጠሪ ይዜታ ስር በቆየበት ጊዚ ተፈጻሚ ሲሆኑ በነበሩት የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 28/1 እና በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 51/1 መሰረት ዔቃዉ በማከማቻ ስፍራዉ ሉቀመጥ የሚችለዉ ለ60 ቀናት ብቻ እንደሆነ ነዉ።
ዔቃዉ(ፍርክሉፍቱ) በጊዚያዊ የጉምሩክ ዔቃ ማከማቻ ስፍራ(መጋዖን) የሚቀመጥበትም ዓላማ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት እንዱፈጸምበት እና ይህ ሥነ ሥርዓት ተፈጽሞ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዔቃዉ በጉምሩክ ባለስልጣን ቁጥጥር ሥር መሆን ስላለበት ነዉ።
እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 51/7 ስር ወደ ጊዚያዊ የጉምሩክ ዔቃ ማከማቻ… የገባ የጉምሩክ ዔቃ በዘህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1… ስር በተመለከተዉ ጊዚ ዉስጥ ካልወጣ ወደ መንግስት የጉምሩክ መጋዖን እንዱዙወር እንደሚደረግ ተደንግጓል።በዘህ አዋጅ አንቀጽ 2/13 ትርጓሜ መሰረት የመንግስት መጋዖን ማለት ደግሞ የጉምሩክ ሕግን በመተላለፍ የተያዘ ወይም የተወረሱ እንዱሁም የተተዉ ዔቃዎች በሽያጭ ወይም በልላ ሁኔታ እስከሚወገደበት ጊዚ ድረስ በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ሆነዉ የሚከማቹበት መጋዖን ነዉ።ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ፍርክሉፍት በጉምሩክ ኮሚሽን በተደረገ ፍተሻ በትርፍነት የተገኘ መሆኑ አከራካሪ አይደለም።እንዱሁም ፍርክሉፍቱ በትርፍነት የተገኘ መሆኑን በመግለጽ የጉምሩክ ኮሚሽን ፍርክሉፍቱ በሞጆ ደረቅ ወደብ እንዱቀመጥ ወስኗል በማለት ተጠሪ በማስረጃ አስደግፍ ያቀረበዉን ክርክር አመልካች ክድ አልተከራከረም። በትርፍነት የተገኘ እቃ በአዋጁ አንቀጽ 53 እና 143/2 ስር እንደተደነገገዉ የጉምሩክ ሕግ የመተላለፍ ድርጊት እንደተፈጸመበት የሚቆጠር በመሆኑ እቃዉ በጉምሩክ ባለሥልጣኑ እንዱያዛና ከዘህ እቃ የሚፈለግ ቀረጥና ታክስ ባለዔቃዉ ወዱያዉ እንዱከፍል የሚያስገድደዉ ነዉ።
በተጨማሪም ይህ ምክንያት ዔቃዉ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት በመተላለፍ እንደገባ የሚያስቆጥረዉ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆነ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 51/1 ስር በተመለከተዉ 60 ቀናት ጊዚ ዉስጥ አመልካች ለፍርክሉፍቱ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አስፈጽሞ እና የሚጠበቅበትን ቀረጥና ታክስ ከፍል ፍርክሉፍቱ እንዱሰጠዉ ሳይጠይቅ ከ3 ዓመት በላይ ለሆነ ጊዚ መቆየቱ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።ይህ የአመልካች አድራጎት በአዋጅ ቁጥር 588/2000 አንቀጽ 6/1 እና በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 51/7 እና 61(2/ሀ) መሰረት ፍርክሉፍቱን እንደተወ ጭምር ሉያስቆጥር የሚችል በመሆኑ፣የተተወ እቃ ደግሞ በሽያጭ ወይም በልላ በሕግ በተፈቀደዉ መንገድ ማስወገድ ያለበት የጉምሩክ ኮሚሽን በመሆኑ ኮሚሽኑ ይህንን ሳያደርግ በመቆየቱ ተጠሪ ተጠያቂ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት ባለመኖሩ፣ አመልካች በሕጉ በተመለከተዉ ጊዚ ዉስጥ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አስፈጽሞና ተገቢዉን ታክስና ቀረጥ ከፍል ሳይረከብ የተወዉን ፍርክሉፍት ላልተወሰነ ጊዚ ተጠሪ ፍርክሉፍቱ ጉዲት እንዲይደርስበት አድርጎ መጠበቅ የሚችልበት የሕግም ሆነ የዉል ግዳታ የለበትም።
እንዱሁም በግራ ቀኙ መካከል የተፈጠረዉ ግንኙነት የመልቲ ሞዲል ትራንስፖርት ግንኙነት ላይ የተመሰረተ የዉል ግንኙነት ቢሆንም የጊዚ ገደብ ለላለዉ ጊዚ እቃዉ ላይ ጉዲት እንዲይደርስበት ለመጠበቅ አመልካች የዉል ግዳታ እንዲለበት አመልካች ዉል ጠቅሶ ያቀረበዉ ክርክር የለም።የመልቲ ሞዲል ትራንስፖርት አዋጅ ቁጥር 548/1999ም ይህንን ግዳታ በተጠሪ ላይ አይጥልም።በግራ ቀኙ መካከል የዉል ግንኙነት መኖሩ አከራካሪ ባይሆንም የግራ ቀኙ ኃላፉነት የሚወሰነዉ ከላይ በተጠቀሱት ልዩ ሕግጋት በመሆኑ አመልካች በሰበር አቤቱታዉ ላይ ከተጠሪ ጋር የአደራ ዉል ግንኙነት አለን በማል የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2718 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎች ጠቅሶ ያቀረበዉ ክርክር ለተያዖዉ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያላቸዉ አይደለም ብለናል።
ሲጠቃለል በጉምሩክ አዋጁ ላይ በጊዚያዊ የጉምሩክ ዔቃ ማከማቻ ስፍራ አንድ ዔቃዉ ተቀምጦ ሉቆይ የሚችልበት ጊዚ ለዉስን ቀናት ብቻ እንዱሆን ከተደነገገበት ዓላማዎች ዉስጥ ዋናዎቹ ዓላማዎች ለረጅም ጊዚ ዔቃዉ በጊዚያዊ የጉምሩክ ዔቃ ማከማቻ በተለይም በክፍት መጋዖን ተቀምጦ የሚቆይ ከሆነ በዉጭ ምንዙሪ ተገዛቶ አገር ዉስጥ በገባ ዔቃ ላይ ጉዲት ስለሚደርስ በዔቃዉ ላይ የሚደርሰዉን ጉዲት ለመቀነስ እና ዔቃዉ በሕጉ በተመለከተዉ ጊዚ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ተፈጽሞበት ለታለመለት አገልግልት እንዱዉል በማድረግ ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታ እንዱሰጥ ለማስቻል ነዉ። ከዘህ ጊዚ በላይ ተጠሪ የመጋዖን ኪራይ ስለሚያስከፍል እቃዉን ከክፍት መጋዖን አንስቶ በዛግ መጋዖን ማስቀመጥ አለበት ተብል የሚገደድ ከሆነ ተጠቃሾቹ ዓላማዎች ከግብ እንዲይደርሱ የሚያደርግ ከመሆኑም በተጨማሪ የእቃዉ ዓይነት ምንም ይሁን ምን ዔቃዉን በዛግ መጋዖን ባለማስቀመጥህ እቃዉ ላይ ጉዲት ደርሷል ተብል ተጠሪ ካሳ እንዱከፍል የሚደረግ ከሆነ በጉምሩክ አዋጁ ላይ የተቀመጠዉ የጊዚ ገደብ ዉጤት እንዱያጣ የሚያደርግ ይሆናል፤በተጠሪም ላይ በሕግ ያልተመለከተ ግዳታ መጣል ስለሚሆን የሕግ ድጋፍ አይኖረዉም።ከዘህ አንጻር ሲታይ የሥር ፍርድ ቤት ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ ፍርክሉፍት ላይ ጉዲት ሉደርስበት የቻለዉ አመልካች በሕግ በተመለከተዉ ጊዚ ዉስጥ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት በማስፈጸም እና አስፈላጊዉን ቀረጥና ታክስ ከፍል መረከብ ባለመቻለ ፍርክሉፉቱ በተቀመጠበት ጊዚያዊ ክፍት ማስቀመጫ ቦታ ለፀሐይና ዛናብ በመጋለጡ ምክንያት እንጂ በተጠሪ የአያያዛ ጉድለት አይደለም በማለት የደረሰዉ ድምዲሜ የሕግ መሰረት ያለዉ ነዉ።በመሆኑም በፍርክሉፍቱ ላይ ጉዲት የደረሰዉ በአመልካች(በባለዔቃዉ) ጥፊት በመሆኑ ለደረሰዉ ጉዲት ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም ተብል በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ በዘህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 18/10/2012 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 11/06/2013 ዓ/ም የሰጠው ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንተዋል።
ግራ ቀኝ በዘህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ብለናል።
ትዔዙዛ የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዛገቡ ላይ የተሰጠ የዔግድ ትእዙዛ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ።መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.