የተሽከርካሪን አካል ዔቃዎችን ለመደበቅ የሚያስችል እንዱሆን ለውጦ ወይም ሻግ ተሰርቶ የኮንትሮባንድ ዔቃ ጭኖ የተገኘ ተሽከርካሪ የባለቤቱ እውቅና ያለው አለመሆኑን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ተሽከርካሪው ውርስ ሆኖ ለመንግሥት ገቢ የሚደረግ ስለመሆኑ። ጉምሩክ አዋጅ ቁ.859/2006 አንቀጽ 1479(3)(ሀ)
No summary available.
የካቲት 28 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡ …….ኢንተርስቴት ኤክስፕሬስ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፡- የቀረበ የለም ተጠሪ፡ ………….የሚላ አዋሽ ጉምሩክ ጽ/ቤት ፡- የቀረበ የለም ይህ መዛገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የተሽከርካሪ ዉርስ ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ይግባኝ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር መልስ ሰጪ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር።
ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.190485 በ10/6/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የሥር ይግባኝ ባይ (የአሁን አመልካች) በፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ባቀረበዉ የይግባኝ ቅሬታ የይግባኝ ባይ ድርጅት ተሽከርካሪ የሆነዉ ኮድ 3- 35522/10862 ኢት የሆነዉ የነዲጅ ቦቴ የመኪናዉ አካል ዔቃዎችን ለመደበቅ እንዱያስችል ሆኖ ተለዉጦ ተሰርቶ የኮንትሮባንድ ዔቃ ጭኖ የተገኘ በመሆኑ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (3) መሰረት ተሽከርካሪዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ያሳለፈዉ ዉሳኔ ተገቢ አይደለም፤ ይግባኝ ባይ የተሽከርካሪዉ አካል ዔቃዎችን ለመደበቅ በሚያስችል ሁኔታ አድርጎ አልሰራም፤ ሹፋር የተሽከርካሪዉን ከሕግ ዉጭ ሳልቫትዮዉን በድብቅ አስቀድድ ለሕገወጥ ተግባር አዉሎል፤ ይግባኝ ባይ ይህን ጉዲይ ባላወቀበት ተሽከርካሪዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ መደረጉ ተገቢ አይደለም እንዱሻርልኝ በማለት አመልክቷል።
የሥር መልስ ሰጪ ባቀረበዉ መልስ የይግባኝ ባይ ተሽከርካሪ የመጠባበቂያ የነዲጅ መያዡ አካል ከመደበኛ አገልግልት ዉጭ የኮንትሮባንድ ዔቃ መሸሸግ እንዱያስችል ሆኖ የተለወጠ አካል መሰራቱን እና በዘህም የኮንትሮባንድ ዔቃን ጭኖ መገኘቱ በሰዉ እና በሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ ተሽከርካሪዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን በመልስ ሰጪ የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዱጸናልን በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ የፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ጉዲዩን በማጣራት ባሳለፈዉ ዉሳኔ የይግባኝ ባይ ተሽከርካሪ በሆነዉ የኮንትሮባንድ ዔቃዎች የተገኙበት ቦታ በተሽከርካሪዉ ፊብሪካዉ ለመጠባበቂያ ነዲጅ መያዡ ተብል የተሰራዉ ታንከር ከኋላ በኩል በአራት ማዔዙን በመቆራረጥና ፍሬም ብረት በማዖጋጀት ከቻንሲዉ ጋር በመበየድ የተቆጠረዉን ላሜራ በጠርዘ በኩል በብልን እንዱታሰርና እንዱፈታ ተደርጎ ከመደበኛ አገልግልት ዉጪ ሕገወጥ ዔቃዎችን ለመደበቅ እና ለማጓጓዛ በተለወጠዉ የመደበቂያ አካል ላይ መሆኑን በባለሙያ ሪፖርት የተደረገ በመሆኑ፤
በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (3፣ ሀ) መሰረት በተሽከርካሪ ላይ ሻግ በመገኘቱ ተሽርካሪዉን ዉርስ አድርጎ ለመንግስት ገቢ ለማድረግ የሚያበቃ ቢሆንም በይግባኝ ተሽከርካሪ ላይ የተደረገዉ ለዉጥ ይግባኝ ባይ በቁጥጥር የሚለያቸዉ ሳይሆን ጥንቃቄ የተሞላበትና ይግባኝ ባይ በቀላለ እንዲይለያቸዉ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን ጉባኤዉ ስለተገነዖበ፣ የይግባኝ ባይ ተሽከርካሪ ዉርስ የሆነዉ በአዋጁ ዉጪ ነዉ በማለት የመልስ ሰጪ በመሻር ወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበለትን ይግባኝ በትዔዙዛ በመሰረዛ የጉባኤዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የሥር መልስ ሰጪ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በማከራከር ባሳለፈዉ አከራካሪዉ ተሽከርካሪ በነዲጅ መጠባበቂያ ክፍል ዉስጥ ዔቃ መደበቂያ ሻግ መሰራቱን እና በዉስጡም የጉምሩክ ሥነሥርዓት ያልተፈጸመባቸዉ ዔቃዎች መያዙቸዉን ግራ ቀኙ ያልተካካደና በማስረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ ቢሆንም የሥር ጉባኤ ተሽከርካሪዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ መሆን የለበትም ያለዉ የሥር ይግባኝ ባይ ሻግ መሰራቱን እንደማያዉቅና ቀድሞ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ የለም የሚል ነዉ። ነገር ግን በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (3፣ ሀ) መሰረት ተሽከርካሪ ዉርስ ሆኖ ለመንግስተ ገቢ የሚሆነዉ በተሽከርካሪዉ አካል የዔቃ መደበቂያ /ሻግ/ የተሰራለት ወይም የተገጠመለት መሆኑን እንጂ የባለቤቱን እዉቀት ያለዉ መሆኑን ከግምት የማያስገባ በመሆኑ፤ ጉባኤዉ በድንጋጌዉ ያልተቀመጠዉን መስፈርት ዉጪ ሻግ መገጠሙን የሥር ይግባኝ ባይ አያዉቅም በማለት ተሽከርካሪዉ ሉወረስ አይገባም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ የህግ ስህተት በመሆኑ ዉሳኔዉ ተሽሯል፤ የሥር መልስ ሰጪ መ/ቤት ተሽከርካሪዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ ላሆን ይገባል በማለት ያሳለፈዉ ዉሳኔ ጽንቷል በማለት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልከች መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የአሁን አመልካች ለክርክር መነሻ በሆነዉ ተሽከርካሪ ላይ የተሰራዉን ሞዱፉኬሽን በቀላለ የሚለየዉ ወይም የሚቆጣጠረዉ ነዉ ተብል የማይገመት ሆኖ ሳለ፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በተሽከርካሪዉ ላይ የተሰራዉን መደበቂያ (ሻግ) መሰራቱን ባለቤቱ ያዉቀዋል የሚል ግምት ወስደናል በማለት ያሳለፈዉ ዉሳኔ ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ በመሆኑ፣ አመልካች ይህ መደበቂያ መሰራቱን የማያዉቅና መኪናዉን ለመዉረስ አስቀድሞ የተሰጠዉ ማስጠንቀቂያ ሳይኖር፣ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልን፤ የጉባኤዉና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ እንዱጸናልን በማለት በዛርዛር አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣የሥር ፍ/ቤት ተሽከርካሪዉ ሉወረስ ይገባል በማለት የሰጠዉን ዉሳኔ አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (3) አንጻር ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ባዖዖዉ መሰረት በ12/9/2013 ዓ.ም በጻፈ መልስ፡ የአመልካች ንብረት የሆነዉ አከራካሪዉ ተሽከርካሪ ላይ ዔቃዎችን ለመደበቅ እንዱያስችል ሆኖ የተለወጠ ወይም መደበቂያ አካል (ሻግ) የተሰራለበት ወይም የተገጠመለት መሆኑና በዘህ መደበቂያ አካል ዉስጥ የኮንትሮባንድ ዔቃ ጭኖ መገኘቱ በማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ የተሽከርካሪዉ ባለቤት እዉቀት እንደመስፈርት ያልተቀመጠ በመኖኑ፣ አመልካች ሻግ በሹፋሩ መሰራቱን በማስረጃ አላረጋገጠም፤ በመሆኑም የአመልካች ተሽከርካሪ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን የተወሰነዉ ዉሳኔ ሕግን የተከተለ ስለሆነ የዉርስ ዉሳኔዉ እንዱጸናልን በማለት በዛርዛር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ የአመልካች ድርጅት ተሽከርካሪ የሆነዉ ኮድ 3-35522/10862 ኢት የሆነዉ የነዲጅ ቦቴ ለመጠባበቂያ ነዲጅ መያዡ ተብል የተሰራዉ ታንከር ከኋላ በኩል በአራት ማዔዙን በመቆራረጥና ፍሬም ብረት በማዖጋጀት ከቻንሲዉ ጋር በመበየድ የተቆጠረዉን ላሜራ በጠርዘ በኩል በብልን እንዱታሰርና እንዱፈታ ተደርጎ ከመደበኛ አገልግልት ዉጪ ሕገወጥ ዔቃዎችን ለመደበቅ እና ለማጓጓዛ በተለወጠዉ የመደበቂያ አካል (ሻግ) የተሰራበት እና የኮንትሮባንድ ዔቃን በዘህ የዔቃ መደበቂያ ሻግ ዉስጥ ጭኖ ሲያጓጉዛ መያዘን ግራ ቀኙን ያላከራከረና በማስረጃም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። ግራ ቀኙን ያከራከረዉ ጉዲይ አመልካች ባቀረበዉ ክርክር በተሽከርካሪዉ የመጠባበቂያ ነዲጅ መያዡ በሆነዉ የመኪናዉ አካል ዉስጥ የተሰራዉ የዔቃ መደበቂያ ሻግ ከአመልካች እዉቀት ዉጭ በሹፋሪ የተሰራ ስለሆነ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (3፣ ሀ) መሰረት ተሽከርካሪዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን በቂ ምክንያት ላሆን አይችልም የሚል ሲሆን፤ ተጠሪ በበኩለ የአመልካች ንብረት የሆነዉ ተሽከርካሪ የዔቃዎች መደበቂያ ሻግ ተሰርቶለት የኮንትሮባንድ ዔቃዎች ጭኖ ሲያጓጉዛ መያዘ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ የአመልካች እዉቀት ከግምት ሳይገባ ተሽከርካሪዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ለማድረግ በቂ ምክንያት ነዉ በማለት ተከራክሯል። በመሆኑም እዘህ ላይ ምላሽ ማግኘት ያለበት ጉዲይ ፣የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (3፣ ሀ) መሰረት የኮንትሮባንድ ዔቃዎችን ለማጓጓዛ የዋለዉን ማጓጓዡ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ለማድረግ የኮንትሮባንድ ዔቃዎቹን ለመደበቅ እንዱያስችል ሆኖ የተሰራ፣ የተለወጠ ወይም መደበቂያ አካል የተገጠመለት መሆኑ ብቻ ሳይሆን የባለንብረቱ እዉቅት እንደመስፈርት ተቀምጧል ወይስ አልተቀመጠም?
የሚለዉ ነጥብ መሆኑን ተገንዛበናል።
በዘህ መሰረት ከአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (3፣ ሀ) ደንጋጌ መደረት እንደሚቻለዉ በዘህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1 ሥር ዉርስ ሆኖ ለመንግስተ ገቢ የሚደረጉትን ዔቃዎች የሚዖረዛር ሲሆን፣ እነዘህን የሚወረሱ ዔቃዎችን ለማጓጓዛ የዋለዉን ማንኛዉም ማጓጓዡ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንደ በዘህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 3 (ሀ) ሥር የተመለከተዉ ዔቃዎቹን ለመደበቅ እንዱያስችል ሆኖ የተሰራ፣ የተለወጠ ወይም መደበቂያ አካል የተገጠመለት እንደሆነ መሆኑን ይደነግጋል። ከዘህ ደንጋጌ ይዖትና ዓላማ መገንዖብ እንደሚቻለዉ ማጓጓዡዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን የሚያደርገዉ በማጓጓዡዉ አካል ላይ የዔቃዎች መደበቂያ ሻግ ተሰርቶለት/ተገጥሞለት መገኘቱ እንጂ ባለንብረቱ ይህን ጉዲይ ያዉቃል ወይስ አያዉቀዉም? የሚለዉን የእዉቀትን ሁኔታ እንደአንድ መስፈርት ያስቀመጠበት አግባብ የለም። የማጓጓዡዉ ባለንብረት ንብረቱን በተመለከተ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል በንብረቱ ላይ የሚደረገዉን ሁለ ተከታትል ሕጋዊ ማስተካከያ እርምጃ ይወስዲል ተብል ይታመናል። እነዘህ የሚወረሱ ዔቃዎች በአገርና በሕዛብ ላይ የሚያደርሱትን ዖርፈ ብዘ ችግሮችና ጉዲቶችን ለመከላከል እንዱቻል፣ የማጓጓዡ ባለንብረት በሚገባ ንብረቱን የመቆጣጠርና የመከታተል እንደነዘህ ዓይነት ዔቃዎችን ለማጓጓዡነት እንዲይዉል የማድረግ ግዳታ የጣለ ነዉ። ስለሆነም በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (3፣ ሀ) መሰረት በማጓጓዡዉ አካል ላይ የሚወረሱ ዔቃዎች መደበቂያ ሻግ ተሰርቶለት ወይም ተገጥሞለት በዘህ መደበቂያ ሻግ ዉስጥ ዔቃዎቹን ጭኖ መገኘቱ የተረጋገጠ እንደሆነ፣ ማጓጓዡዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ለማድረግ በቂ ምክንያት ነዉ እንጂ ባለንብረቱ ያዉቃል ወይስ አያዉቀዉም? ተብል ተጣርቶ፣ በዘህ መሰረት የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር መነሻ ተደርጎ ማጓጓዡዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን የሚያበቃ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ታይቶ ዉሳኔ የሚሰጥበት አግባብ የለም። በመሆኑም በዘህ ድንጋጌ መሰረት ማጓጓዡዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን የሚያስደርገዉ የመደበቂያ ሻግ የተሰርቶለት ወይም የተገጥሞለት ሆኖ፣ የሚወረሱ ዔቃዎችን በሻግ ዉስጥ ጭኖ መገኘቱ እንጂ የባለንብረቱ የእዉቀት ሁኔታ ታሳብ የሚደረግበት አግባብ አይኖርም ማለት ነዉ።
በዘህ መሰረት አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ የአመልካች ንብረት የሆነዉ ተሽከርካሪ በተሰራለት የዔቃዎች መደበቂያ ሻግ ዉስጥ የኮንትሮባንድ ዔቃዎችን ጭኖ ሲያጓጉዛ የተያዖ መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ያልተካደ ጉዲይ ስለሆነ፣ ተሽከርካሪዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስተ ገቢ እንዱሆን ለማድረግ በቂ ምክንያት በመሆኑ፣ የአመልካች እዉቀት ሁኔታ ማረጋገጥን የሚያስፈልግ ጉዲይ አይደለም። በመሆኑም የተጠሪ መ/ቤትም ሆነ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የአመልካች ተሽከርካሪ በዘህ ምክንያት ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ ላሆን ይገባል በማለት ያሳለፈት ዉሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢፋዳሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80 (3፣ ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 (1) መሰረት ከተሰጠዉ ስልጣን አንጻር አመልካች ያቀረበዉ ቅሬታ የተጠሪ መ/ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ መሆኑን የሚያመለክት ስላልሆነ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የአመልካች ተሽከርካሪ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ያሳለፈዉ ዉሳኔ በሕግ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.190485 በ10/6/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ጸንቷል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዘህ ችልት የደረሳባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.