No summary available.
ህዲር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡ …….ወ/ሮ ሐቢባ ሸምሱ ስሩር - ቀርበዋል ተጠሪ፡ ………….አቶ ቴዎድሮስ ገብሩ ብዙ- ቀርበዋል ይህ መዛገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የፍቺ ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች እና የአሁን ተጠሪ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.251802 ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከተጠሪ ጋር ግንቦት 12 ቀን 2001 ዓ.ም በግብጽ ሀገር ጋብቻ ፈጽመን አብረን ሲንኖር ህጻን ሉና ቴዎድሮስ የተባለችዉን ልጅ የወለድን ቢሆንም ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ግንኙነታችን ተቋርጦ በጋብቻ መቀጠል ስላልቻልን ጋብቻችን እንዱፈርስልን በማለት ዲኝነት ጠይቃለች።
የአሁን ተጠሪ በዘህ ክስ ላይ ባቀረበዉ መልስ ከአመልካች ጋር ጋብቻ አልፈጸምንም፣ በጋብቻ ሰነደ ላይም አልፈረምኩም፣ አመልካች ጋብቻ እንደላላቸዉ ስለመሆኑ ማስረጃ ተሰጥቷል፤
በግብጽ አገር ጋብቻ የሚፈጸመዉ በፍ/ቤት ነዉ፤ ከአመልካች ጋር በነበረን የግብረ ስጋ ግንኙነት የተጠቀሰችዉን ልጅ ከመዉለዲችን ዉጭ በጋብቻም ሆነ ጋብቻ ሳይፈጽም እንደባልና ሚስት አለመኖራቸዉን ገልጸዉ ጋብቻ በላለበት የቀረበዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በመስማት፣ ከሚመለከተዉ አካል በማጣራትና የቀረበዉን የሰነድ ማስረጃ በመመርመር ባሳለፈዉ ዉሳኔ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በግብጽ አገር ጋብቻ ስለመፈጸማቸዉ አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባለመረጋገጡ አመልካች የጋብቻ ፍቺ እንዱወሰን ያቀረበችዉ የዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም፤ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተፈጸመ ጋብቻ የለም፣ የሚሰጥ ፍቺ የለም በማለት ወስኗል። ይህ ጉዲይ በይግበኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.254606 በ20/4/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ግራ ቀኙን በማከራከር የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ አመልካች እና ተጠሪ መንግስትን ተቃዉመን ከአገር ተሰደን ለብዘ ጊዚ እንደባልና ሚስት አብረን ሲንኖር ዔድሜዋ 10 ዓመት የሆናትን ልጅ ሉና ቴዎድሮስ የተወለደች ሲሆን በግብጽ አገር የጋብቻ ዉል ያደረግን ሲሆን እኛ በግብጽ አገር በስደት የሚንኖርና ሕጋዊ ነዋሪዎች ባልሆንበት በአገሪቱ በሕጋዊ መንገድ እንደሚኖር ዚጋ የጋብቻ ዉለ በፍ/ቤት አልተመዖገበም በማለት የጋብቻ ዉል የለም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። አመልካች ይህን ክርክር ለማስረዲት የሰዉ ምስክሮችን ቆጥረን እያለ የሥር ፍ/ቤቶች ምስክሮቹን ሉቀበለን አልቻለም፣ ተጠሪ የጋራ ሀብት ነዉ በማለት በአመልካች ስም ለኮንድሚኒየም የተቆጠበዉን ገንዖብ ማሳገደ ጋብቻ መኖሩን እያመነ መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ ሳለ የሥር ፍ/ቤቶች ጋብቻ የለም በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በዛርዛር አመልክታለች።
ይህ ችልት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ባዖዖዉ መሰረት ሚያዘያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ አመልካች እና ተጠሪ በግብጽ አገር በስደተኞች ካምፕ ጋብቻ ስለመኖሩ የጋብቻ ሰነድ መፈረሙ ተረጋግጧል ይበለ እንጂ ሰነደ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በኢፋዳሪ የዉጭ ጉዲይ ሚኒስቴር ሕጋዊነቱ ተረጋግጦ የገባ ስላልሆነ ሕጋዊ ሆኖ የቀረበ ሰነድ አይደለም ተቀባይነት የለዉም፤ የሥር ፍ/ቤት ከግራ ቀኙ ክርክር አንጻር የሰዉ ምስክሮችን መስማት እንደማያስፈልግ ስላመነበት ማለፈ ትክክል ነዉ፤ አመልካች ከተጠሪ ጋር እንደባልና ሚስት አብረን ኖረናል ያለት በሥር ፍ/ቤት ያልተነሰ ክርክር ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም፤ ለኮንድሚኒየም የተቆጠበዉን ገንዖብ ያሳገድኩት የጋራ ሀብት ነዉ በሚል ሳይሆን በዘህ ክርክር ምክንያት ለሚደርስብኝ ወጪና ኪሳራ የሚወሰንልኝ ከሆነ ይህን ገንዖብ ለመዉሰድ እንዱችል ነዉ። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በአግባቡና ሕጋዊ ስለሆነ የቀረበዉ አቤቱታ ዉድቅ እንዱሆንልኝ ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልኝ በማለት በዛርዛር ተከራክሯል።
አመልካች የሰበር አቤቱታዋን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርባለች።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በዘህ ጉዲይ ምላሽ የሚሻዉ ፣ይህ ጉዲይ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት ነዉ ወይስ አይደለም? ጉዲዩ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ህግን የሚመለከት ከሆነ ክርክሩን ለማየት የሥረ-ነገር የዲኝነት ያለዉ የትኛዉ ፍ/ቤት ነዉ? የሚለት ነጥቦች መሆናቸዉን ተገንዛበናል። በዘህ መሰረት አመልካች ካቀረበችዉ ክርክር እና የሥር ፍ/ቤቶች በዉሳኔያቸዉ እንዲመለከቱት አመልካች ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ፈጽመናል የሚትለዉ በግብጽ አገር በስደተኞች ካምፕ መሆኑን ጠቅሳ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ጋብቻቸዉን በምስክሮች ፉት አስፈጽሟል ያለችበትን የጋብቻ የምስክር ወረቀት የሰጠ መሆኑን እና ተጠሪም ይህን ሰነድ መፈረሙን በፋዳራል ፖሉስ ኮሚሽን የፍረንሲክ ምርመራ ክፍል መረጋገጡን ነዉ። ተጠሪ ግን ከአመልካች ጋር በግብጽ አገር ጋብቻ አለመፈጻቸዉን፣ በግብጽ አገር ተጋቢዎች ጋብቻ መፈጸም ያለባቸዉ በፍ/ቤት መሆኑን፣ የተባለዉ የጋብቻ ሰነድ አግባብነት ባለዉ ሕግ መሰረት በኢትዮጵያ የዉጭ ጉዲይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ወደ አገር ያልገባ መሆኑንና ተቀባይነት ሉኖራዉ እንደማይገባ ገልጾ መከራከሩን መዛገቡ ያሳያል። በግራ ቀኙ መካከል ከሚነሳዉ የፍሬ ነገር እና የህግ ክርክር አንጻር ጉዲዩ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን [Private International Law] የሚመለከት ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ የዉጭ አካል ተካፊይ የሆነበትን የህግ ክርክር የሚመለከቱ መርሆዎችና ደንቦችን የሚያካተት ነዉ። የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ ወይም የሕግ ግጭት [Conflict of laws] የሚመለከተዉ በተያዖዉ የህግ ክርክር የትኛዉ ሕግ ተፈጻሚነት እንዲላዉ እና የትኛዉ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን እንዲለዉ የሚወስኑ የህግ መርሆችን ነዉ። የፋዳራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1፣ ሀ) እና 11 (1፣ ሀ) መሰረት የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን በሚመለከቱ የፍትሕ ብሓር ጉዲዮችን ለማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ስልጣን ያለዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መሆኑን ይደነግጋል።
በዘህ አግባብ አሁን የተያዖዉ ጉዲይ ሲታይ አመልካች ባቀረበችዉ ክርክር ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ፈጽመናል ያለችዉ በግብጽ አገር በሚገኘዉ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ካምፕ በከፍተኛ ኮሚሽንና በምስክሮች ፉት መሆኑን ገልጻ ተከራክራለች። ይሁን እንጂ አመልካች ከተጠሪ ጋር አድርገናል የሚትለዉ ጋብቻ እንዱፈርስላት ክስ አቅርባ ዲኝነት የጠየቀችዉ በኢትዮጵያ ፍ/ቤት መሆኑን ማየት ይቻላል። በዘህ መሰረት ከግራ ቀኙ ክርክር አንጻር በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በግብጽ አገር በሚገኘዉ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ካምፕ አመልካች ተፈጽሟል የሚትለዉ ጋብቻ በተመለከተ ሕጋዊ ጋብቻ ተፈጽሟል ለማለት የትኛዉ ሕግ ተፈጻሚነት ይኖረዋል? የሚለዉ ነጥብ ምላሽ የሚያስፈልገዉ ጉዲይ ሆኖ እናገኛለን።
እንዱሁም በግራ ቀኙ መካከል በግብጽ አገር በሚገኘዉ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ካምፕ ተፈጽሟል የተባለዉ ጋብቻ፣ በሕግ አግባብ የተፈጸመ ጋብቻ ነዉ የሚባል ከሆነና ጋብቻቸዉ በፍቺ ዉሳኔ እንዱፈርስ የሚወሰን እንደሆነ የፍቺ ዉጤት በምን አግባብ ይታያል?
የሚለዉ ነጥብ ሉነሳ እንደሚችል ላላዉ ጉዲይ ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ የግራ ቀኙን የጋብቻ ይፍረስልን ክርክር በተመለከተ ተፈጻሚነት ያለዉ ሕግ የትኛዉ ነዉ? የሚለዉን ነጥብ መወሰንን ይጠይቃል ማለት ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ የግራ ቀኙ ክርክር የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት ጥያቄ የሚያስነሳ ሆኖ እናገኛለን። ይህ ጉዲይ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት ከሆነ ደግሞ በኢትዮጵያ ዉስጥ የትኛዉ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን አለዉ? የሚለዉ አግባብነት ካለዉ ሕግ አንጻር ታይቶ ምላሽ ላሰጥበት የሚገባዉ ጉዲይ ነዉ። በዘህ መሰረት በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1፣ ሀ) እና 11 (1፣ ሀ) መሰረት የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከቱ የፍትሕ ብሓር ጉዲዮችን የማየት የመጀመሪያ ደረጃ የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መሆኑን ይደነጋገል። ስለሆነም ፍ/ቤት አንድን ጉዲይ ለማየት የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? የሚለዉን አስመልክቶ ተከራካሪ ወገኖች ከዘህ አንጻር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ባያነሱም ፍ/ቤት በራሱ ተነሳሽነት በማንሳት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ላሰጥበት እንዱሚገባዉ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.9 (1)፣ 231 (1፣ ለ)፣ 244 (3) እና 245 (2) ድንጋጌዎች ይዖትና ዓላማ መረዲት ይቻላል። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ይህ ጉዲይ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ ጥያቄን የሚያስነሳ መሆኑን እና ጉዲዩን ለማየት የመጀመሪያ ደረጃ የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መሆኑን በመገንዖብ የአሁን አመልካች ያቀረበችዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ ስልጣን ላለዉ ፍ/ቤት ጉዲዩን ማቅረብ እንደሚትችል በማመልከት መወሰን ሲገባቸዉ ይህን ባለማድረግ ያሳለፈት ዉሳኔ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት ሕጎች አንጻር ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ሳይኖረዉ ጉዲዩን አይቶ ያሳለፈዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህን ዉሳኔ ማረም ሲገባዉ በማጽናት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.251802 ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.254606 በ20/4/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
ይህ ጉዲይ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት ስለሆነ ጉዲዩን ለማየት የመጀመሪያ ደረጃ የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንጂ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አይደለም ብለናል።
ግራ ቀኛቸዉ ይህን ጉዲይ ስልጣን ላለዉ ፍ/ቤት ከማቅረብ ይህ ዉሳኔ የሚከለክላቸዉ አይሆንም ብለናል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ዉሳኔ ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ተነቧል።
መዛገቡ ተዖግቷል የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.