No summary available.
ቀን ፡- ግንቦት 26 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- የቡራዩ ከተማ አስተዲደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ተጠሪ፡- አቶ ከበደ አበበ መዛገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከሥር ፍርድ ቤት የመዛገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ። ተጠሪ በአመልካች፣ በሥር 2ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ገሥጥ መታፈሪያ እና በሥር 3ኛ ተከሳሽ አቶ ወርቁ ገብረጻዱቅ ላይ ያቀረቡት ክስ በቡራዩ ከተማ በለኩ ከታ ቀበላ የቤት ቁጥር 102 የሆነ ቤቴንና ንብረቴን አመልካች ከሥር 2ኛና 3ኛ ተከሳሾች ጋር በመሆን አፍርሶ ጉዲት ስላደረሰብኝ ካሣ ብር 288,000.00 እንዱከፍለኝ እና የሥር 2ኛና 3ኛ ተከሳሾች ይዜታውን እንዱለቁልኝ የሚል ነው። አመልካች ያቀረበው መልስ ተቋሙ ከመቋቋሙ በፉት ለተከናወነ ተግባር ኃላፉነት የለብኝም። ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው። ተጠሪ የንብረቱ ባለቤት ስለመሆኑ ማስረጃ አላቀረቡም የሚል ነው። የሥር 3ኛ ተከሳሽ በበኩላቸው አመልካችና እኔ ኦሮሚያ ክልል ስለምንኖር እና ጉዲዩ ኦሮሚያ ክልል ስለተነሳ በፋደራል ፍርድ ቤት ጉዲዩ ሉዲኝ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን በመመርመር የአመልካች፣ የተጠሪና የሥር 3ኛ ተከሳሽ አድራሻ ኦሮሚያ ክልል ቢሆንም የሥር 2ኛ ተከሳሽ መኖሪያ አድራሻ አዱስ አበባ ከተማ በመሆኑ በተለያዩ ክልል ነዋሪዎች መካከል የሚደረግ ክርክር የፍደራል ጉዲይ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አለው በማለት ላልች መቃወሚያዎችን በማለፍ አመልካች ተጠሪ ላይ ላደረሰው ጉዲት ብር 180,200.00 እንዱከፍልና ለተወሰደው ይዜታ ምትክ እንዱሰጥ ሲወስን የሥር 2ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ገሥጥ መታፈሪያ እና የሥር 3ኛ ተከሳሽ አቶ ወርቁ ገብረጻዱቅ ላይ የቀረበውን ክስ ወድቅ አድርጓል።
አመልካች ይግባኙን ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ቅሬታውን ባለመቀበል ሰርዝል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዘህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዖትም አመልካችና ተጠሪ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ ነን፤ ቤቱም የሚገኘው ኦሮሚያ ክልል ሆኖ እያለ ጉዲዩ በፋደራል ፍርድ ቤት መታየቱ ስህተት ነው። የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤትም የፍደራል ጉዲዩን የማየት ውክልና አለው። የሥር ፍርድ ቤቶች ሥልጣን የላቸውም። በሉዛ ሕግ መሰረት ከይዜታዬ አፈናቀለኝ ካለ መደበኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ማየት አይችልም። አመልካች ተቋም ከመቋቋሙ በፉት ለተከናወነ ተግባር ኃላፉነት የለብኝም የሚል ነው። የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በውክልና የማየት ሥልጣን እያለው በፋደራል ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ መታየቱ ሕጋዊነቱን ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ አዝል። ተጠሪ ያቀረቡት መልስ የተከራካሪዎች መኖሪያ አድራሻ ኦሮሚያ ክልል እና አዱስ አበባ ከተማ በመሆኑ ጉዲዩ የፍደራል ነው። ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በውክልና የማየት ሥልጣን ቢኖረውም አዱስ አበባ ከተማ የሚያስችል በመሆኑ ጉዲዩ በፋደራል ፍርድ ቤቶች መታየቱ ተገቢ ነው። በሉዛ ሳይሆን ገበሬ ማህበር እያለ ይዢው የተጠናልኝ ይዜታ ነው። የማፈናቀል ተግባር ሳይሆን ከሕግ ውጭ ጉዲት ስላደረሱብኝ ነው በፍርድ ቤት ክስ ያቀረብኩት፤ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ተብል ሉጸና ይገባል ብለዋል።
አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩ በፋደራል ፍርድ ቤቶች መታየቱ ሕጋዊ መሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዛ መዛገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው ተጠሪ በአመልካች፣ በሥር 2ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ገሥጥ መታፈሪያ እና በሥር 3ኛ ተከሳሽ አቶ ወርቁ ገብረጻዱቅ ላይ ያቀረቡት ክስ በቡራዩ ከተማ በለኩ ከታ ቀበላ የቤት ቁጥር 102 የሆነ ቤቴንና ንብረቴን አመልካች ከሥር 2ኛና 3ኛ ተከሳሾች ጋር በመሆን አፍርሶ ጉዲት ስላደረሰብኝ ካሣ ብር 288,000.00 እንዱከፍለኝ እና የሥር 2ኛና 3ኛ ተከሳሾች ይዜታውን እንዱለቁልኝ የሚል ነው። አሁን አከራካሪ ሆነው ክሱ የክልል ፍርድ ቤት በውክልና ሉመለከተው የሚችል የፍደራል ጉዲይ ነው ወይስ በፋደራል ፍርድ ቤት የሚታይ ክርክር ነው የሚለውን የሚመለከት ነው።
በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 78(2) መሰረት የሕዛብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2/3ኛ ድምጽ የፍደራል ከፍተኛ ሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዱደራጅ እስካልወሰነ ድረስ የፍደራል ከፍተኛና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን በውክልና ለክልል ፍርድ ቤቶች ተሰጥቷል። ምላሽ የሚያስፈልገው ጉዲይ በውክልና በተሰጠ ሥልጣን ላይ የፍደራል ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም? ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዱስ አበባ ከተማ ከፋደራል ፍርድ ቤት ማስቻያ ከተማ ላይ መገኘቱ በውክልና የተሰጠውን ሥልጣን ከመመልከት አኳያ ያለው ውጤት ምንድን ነው?
የሚለት ጉዲዮች ናቸው።
ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፉነት ሲሆን በዘህ ሂደት ከሚመረምራቸው ጉዲዮች መካከል ጉዲዩ ላይ ለመወሰን ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑ ዋነኛው ነው። የፍርድ ቤት ሥልጣን ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን (judicial jurisdiction)፣ የሥረ-ነገር ሥልጣን (material jurisdiction) እና የግዙት ወይም ከበባዊ ሥልጣን (local or territorial jurisdiction) በሚል የተከፊፈለ ነው። ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን ከሀገሮች ለዓላዊነት፣ የሚሰጠው ፍርድ በላልች ሀገሮች ዔውቅና ሉሰጠውና ሉፈጸም የሚችል መሆን አለመሆኑ እና ከተከሳሽ መብት ጋር የተያያዖ መሰረቱ ዓለምአቀፍ ሕግና የታወቁ የሕግ መርሆዎች ሆኖ የአንድ ሀገር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመመልከት ከተከሳሹ ወይም የክርክሩ ምክንያት የሆነው ተግባር ከተፈጸመበት ወይም አከራካሪ የሆነው ንብረት ከሚገኝበት ቦታ ጋር በቂ የሆነ ግንኙነት ያለው ሆኖ ሲገኝ ወይም ተከሳሽ የሆነው ወገን በሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች ለመዲኘት ያለው ፈቃድ ላይ መሰረት በማድረግ የሚወሰን ነው። የሥረ-ነገር ሥልጣን በአንድ ሀገር ጉዲዩን ለመዲኘት ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች መካከል በዋነኛነት ይሕ የሥልጣን ዓይነት ታሳቢ የሚያደርገው የፍርድ ቤቱን አቅም ፣ ፍትሐዊነትን፣ ኢኮኖሚንና የሥራና ሀብትወይም ችልታ (competence of the court) ክፍፍልን መሰረት አድርጎ በገንዖብ ግምት (pecuniary jurisdiction) ወይም በጉዲዩ ዓይነት (subject matter jurisdiction) ወይም ጉዲዩን በመጀመሪያ ሆነ በይግባኝ ደረጃ (original and appellate jurisdiction) የሚያዩት ሥለመሆኑ በፍርድ ቤቶች መካከል የሚመለከቱት ጉዲዩችን የሥልጣን ድልድል የሚደረግበት ነው። የግዙት ክልል ሥልጣን ደግሞ አንድን ጉዲይ ተቀብል ለመስማት እና ለመወሰን ዐቅም ካላቸው ፍርድ ቤቶች መካከል በየትኛው ፍርድ ቤት ቀርቦ ተመሳሳይ የሥረ-ነገርመታየት እንዲለበት የሚያመለክት ነው። ያስፈለገበትም ዓላማም ሥልጣን ያላቸው ግን በተለያዩ ማስቻያ ቦታ ላይ በሚያስችለ ፍርድ ቤቶች መካከል ለዚጎች ፍትሕ የማግኘት መብትን በቅርብ ለማረጋገጥና ለተከራካሪ ወገኖች ይልቁንም ለተከሳሹና ሥልጣኑም በተከራካሪዎች አድራሻ፣ ንብረቱለምስክሮቹ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል ነው።
በሚገኝበት ቦታ፣ ውለ በተመሰረተበት ወይም በሚፈፀምበት ወይም ጉዲቱ በደረሰበት ቦታ ወይም ተመሳሳይ ምክንያቶችን በመያዛ የሚመለከቷቸውን ጉዲዮች የሚለዩበት ነው። ይሕ ኢትዮጵያ የፍደራል ሥርዓትን ሳትከተል በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተቀረጸ የፍርድ ቤቶች የሥልጣን ክፍፍል ሥርዓት ነው።
ኢትዮጵያ የፍደራል የመንግሥት አወቃቀር ሥርዓትን በ1987 ዓ/ም በወጣው የኢፋዱሪ ሕገመንግሥት መከተሎን ተከትል ሥልጣን በክልልችና በፋደራል መንግሥት የተከፊፈለ ስለመሆኑ በሕገ-መንግሥቱ ከአንቀጽ 50-52 ላይ ተመልክቷል። በዘህም ክልልች በሥልጣናቸው ሥር ባለ ጉዲዮች ለዓላዊ ሥልጣን አላቸው። ክልልች እንደ ፋደራል መንግሥት ሕግ-አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና የዲኝነት አካል ያደራጃለ። በኢፋዱሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 78 መሰረት የዲኝነት አካለ በፋደራል እና በክልል መንግሥት ደረጃ መቋቋሙ እና በአንቀጽ 80(1)(2) ላይ በፋደራል ጉዲዮች የፍደራል ፍርድ ቤት፤ በክልላዊ ጉዲዮች የክልል ፍርድ ቤት የመጨረሻ ሥልጣን ያለው መሆኑ መመልከቱ በፋደራልና በክልል መንግሥታት መካከል የፍርድ ቤት የሥልጣን ክፍፍል እንዲለ ያሳያል። የፍደራል ወይም የክልል ጉዲዮች የሚለው በጉዲይ ዓይነት የተከፊፈለ ሥልጣን ስለሆነ የፍርድ ቤቶች ሥልጣን የተለየው የሥረ-ነገር ሥልጣንን መሰረት ያደረገ ቢመስልም ጉዲዩ ከለዓላዊ ሥልጣን እና ክልላዊ ጉዲይ በፋደራል ፍርድ ቤት ቢታይ ከጣልቃገብነት ጋር የተያያዖ በመሆኑ ጉዲዩ የብሓራዊ ዲኝነት ሥልጣንን የሚያስነሳ ነው። በፋደራል መዋቅር የብሓራዊ የዲኝነት ሥልጣን መሰረቱ ዓለምአቀፍ ሕግ ሳይሆን ሕገ-መንግሥት ነው። ሕገ-መንግሥቱ የፍደራልን ሆነ የክልልን ፍርድ ቤቶች ያቋቋመና አክብረው ለማስከበርም ግዳታ የጣለ ነው። ውጤቱም እንደ ሀገር የሚመረመረው የብሓራዊ የዲኝነት ሥልጣን ከላላ ሀገር ዚጋ ጋር በተያያዖ እና ላልች ሀገሮች ጋር የዱፕልማቲክ ቅራኔንም ሉፈጥር የሚችል ሲሆን በፋደራልና በክልል መንግሥታት መካከል ያለው ግን በአንድ ሀገር ያለና በሕገ-መንግሥቱ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማሕብረሰብ ለመፍጠር በሚሰሩ ተቋማትና ዚጎች ላይ፣ የተለያየ ሥልጣን ቢሆንም የጋራ የሆኑ ጉዲዮች ደግሞ ባላቸው መካከል የሚነሳ ስለሆነ የተለየ ነው። በፋደራል መዋቅር የፍደራል መንግሥት ለዓላዊነቱ በመላው የኢትዮጵያ ግዙት ነው። ነገር ግን በግዙቱ ሥር ሁለንም በፈቃደ መወሰንና መፈጸም የማይችል መሆኑን የሚመለከት ነው። ለክልል ፍርድ ቤት ሥልጣን መሰረቱ ግን በግዙት ክልል ሥር ያለ ሰውና ንብረት መሆን አለመሆኑን መሰረት ያደረገ (limited sovereignty) ነው።
በሕገ-መንግሥቱ የሥልጣን ክፍፍለም የክልል ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የፍደራል ጉዲዮችን በውክልና ማየት የሚችለ ሲሆን ክልላዊ ጉዲዮች በክልልች ለዓላዊ ሥልጣን ክልል ውስጥ (exclusive jurisdiction of state courts) ያለ በመሆኑ በመርሕ ደረጃ የፍደራል ፍርድ ቤቶች ማየት አይችለም። ይሕም ክልላዊ ጉዲዮች ላይ የፍደራል ፍርድ ቤቶች የመዲኘት ሥልጣን (judicial jurisdiction) የላላቸው መሆኑን ሲያሳይ በውክልና እና በጣምራ ሥልጣናቸው ከሚመለከቱት በሥተቀር የክልል ፍርድ ቤቶች የፍደራል ጉዲዮችን ማየት አይችለም። ከዘህ ጋር ተያይዜ መመርመር ያለበት በሕገ-መንግሥቱ የተመለከተው የፍርድ ቤቶች የጣምራነት ሥልጣን (concurrent jurisdiction) እና የፍደራል ጉዲዮች የሚወሰኑበት ሥርዓት ነው። የፍደራል ጉዲዩች ምን እንደሆኑ በሕገ-መንግሥቱ ያልተወሰነ ቢሆንም በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 3 መሰረት የፍደራል ጉዲዮች ሕገመንግሥቱን፣ የፍደራል መንግሥት ሕጎችንና ዓለም አቀፍ ሥምምነቶችን መሰረት ያደረጉ ጉዲዮች (based on laws)፤ በፋደራል ሕግ ተገልጸው በተወሰኑ ባለጉዲዮች (parties) እና በሕግ በተገለጹ ቦታዎች (places) ላይ የሚነሱ ጉዲዮች ናቸው። በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 4 እና 5 መሰረት የተዖረዖሩት የፍደራል ፍርድ ቤት በብቸኝነት ሥልጣኑ የሚመለከታቸው ሕግንና ባለጉዲዮችን መሰረት አድርጎ የተለዩ የፍደራል ጉዲዮች ሲሆን በላልች ሕጎች በግልፅ ለፋደራል ፍርድ ቤት የተሰጡ ጉዲዮችን ይጨምራል። የአዋጁን አንቀጽ 11 እና ተከታዮችን ሥንመለከት ደግሞ ቦታን መሰረት በማድረግ አዱስ አበባና ድሬዲዋ ከተሞች ላይ የሚነሡ ጉዲዮች የፍደራል ፍርድ ቤት የሚመለከታቸው የፍደራል ጉዲዮች ስለመሆናቸው ተደንግጓል።
በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 3 መሰረት ሕግን መሰረት አድርጎ የተለዩት የፍደራል ጉዲዮች ውስጥ የፍደራል መንግሥት ሕጎችን መሰረት ያደረጉ ጉዲዮች ያለበት በመሆኑና በአዋጁ የትርጉም ክፍል አንቀጽ 2(3) ላይ የፍደራል መንግሥት ሕጎች ማለት በሕግ በተሰጠው ሥልጣኑ ክልል ሥር ያለ ነባር ሕጎችን የሚጨመር መሆኑ ሲታይ በሕግ በግልጽ የፍደራል ፍርድ ቤት ሥልጣን ሥር ከተመለከቱት ሕግን መሰረት ያደረጉ ጉዲዮች እና በፋደራል ሥልጣን ሥር እንዱታዩ ከተወሰኑት ባለጉዲዮች ውጭ ያለ የፍደራል ሕግን መሰረት ያደረጉ ጉዲዮች የፍደራልና የክልል ፍርድ ቤቶች በጣምራ ሥልጣናቸው የሚመለከቷቸው ናቸው። ሥለሆነም የፍደራል ሕግን መሰረት ያደረጉ ላልች ጉዲዮች እንደተነሱበት ቦታ የፍደራል ፍርድ ቤት ወይም የክልል ፍርድ ቤት በክልላዊ ሥልጣኑ ሉመለከተው ይችላል።
በኢትዮጵያ የፍደራል ሥርዓት መሰረት አድርጎ የተዋቀረው የዲኝነት ሥልጣን የፍደራል እና የክልል ፍርድ ቤቶች ካላቸው የጣምራነት ሥልጣን ባለፈ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 78(2) እና 80(4-6) የፍደራል ፍርድ ቤት በብቸኝነት ሥልጣኑ የሚመለከታቸውን ጉዲዮች የክልል ጠቅላይና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በውክልና እንዱመለከቱ ሥልጣን ሰጥቷል። ይህም ሕገመንግሥቱ የክልል ፍርድ ቤቶችን ማብቃትን (empowerment)፣ የክልልችን ተሳትፍ ማሳደግ ላይ ዓላማ ያለውና ተቋሞቻቸው ላይ አመኔታ ያለው መሆኑን ያረጋግጣል። በሕገ-መንግሥቱ የዲኝነት አካል በፋደራልና በክልል ደረጃ በየእርከኑ መዋቀሩ ሲታይ አደረጃጀቱ በተዋረደ ያለ አቀራረጽ (dual system) ያለው ቢሆንም የፍደራልና የክልል ጉዲይን የክልል ፍርድ ቤቶች መመልከታቸው የተደባለቀ (integrated system) እንደሚከተልም ያሳያል።
የክልል ፍርድ ቤቶች በጣምራ ሥልጣናቸው በክልል ግዙታቸው የተነሱ ጉዲዮች የመመልከት ሥልጣን ያላቸው በመሆኑ የፍደራል ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አይኖረውም። ጉዲዩ በክልል ፍርድ ቤት የሚታየው ጉዲዩ የተነሳበትን ቦታና ተከራካሪውን መሰረት በማድረግ ነው።
የጣምራነት ሥልጣን መሰረቱ የፍደራል መንግሥት ሕግን መሰረት ያደረገ የፍደራል ጉዲይ በመሆኑ የፍደራል ፍርድ ቤት በፋደራል ጉዲይ ላይ ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን የለውም ልባል አይችልም። ነገር ግን በፋደራል ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 25/1988 አቀራረጽ መሰረት ከተለዩት ውስን የፍደራል ፍርድ ቤት ሥልጣኖች ውጭ ያለ በክልል ግዙት የሚነሱ ጉዲዮችን የክልል ፍርድ ቤቶች እንዱመለከቷቸው የተተወ በመሆኑ ጉዲዩ የሥረ-ነገር ሥልጣን ጥያቄ የሚያስነሳ ይሆናል።
በተመሳሳይ የክልል ፍርድ ቤቶች በፋደራል ፍርድ ቤት በብቸኝነት እንዱታዩ የተለዩ ጉዲዮችን (exclusive jurisdiction) በግዙታቸው ባለ ሰዎቸ ወይም ንብረቶች ጋር የሚነሱ ሲሆን በውክልና (delegation) እንዱመለከቱ በሕገ-መንግሥት ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። በክልል የሚነሱ የፍደራል ጉዲዮች ላይ ጉዲዩ የፍደራል በመሆኑ የፍደራል ፍርድ ቤቶች ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን አላቸው። በፋደራል ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 4 እና 5 የተመለከቱት የፍደራል ጉዲዮችን በተከታዮቹ ድንጋጌዎች ለፋደራል ፍርድ ቤቶች የሥረ-ነገር ሥልጣናቸውን ያከፊፈለ በመሆኑ ይህን ሕግ መሰረት ተደርጎ ሲታይ የፍደራል ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመዲኘት የሥረ-ነገር ሥልጣን እንዲለው ያሳያል። የአፊር፣ የቤንሻንጉል/ጉሙዛ፣ ጋምቤላ፣ ሶማላና የደቡብ ብሓሮች፣ ብሓረሰቦችና ሕዛቦች ክልልች በሕገ-መንግሥቱ ያላቸው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ሥልጣን በውክልና በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማየት ሥልጣን በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማደራጃ አዋጅ ቁጥር 322/1995 ሲነሳ በእነዘህ ክልልች የፍደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት መደራጀቱ ታወጀ እንጂ በአምስቱ ክልልች ግዙቶች የሚነሱ ጉዲዮችን የመመልከት የሥረ-ሥልጣን እንደ አዱስ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አለመሰጠቱ ቀድሞውንም በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 መሰረት የሥረ-ነገር ሥልጣን ተወስኖ ያደረ መሆኑን ያረጋግጣል። የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከአዱስ አበባና ድሬዲዋ ከተሞች ውጭ በእነዘህ ክልልች ሲደራጅ የማስቻያ ቦታው የተወሰነ በመሆኑ ጉዲዮችን ለማየት የግዙት ክልል ሥልጣን ያገኛል። ይሕም የክልል ፍርድ ቤቶች በግዙታቸው ባለ ሰዎቸ ወይም ንብረቶች ጋር የሚነሳ በውክልና የሚመለከቱትን የፍደራል ጉዲይ ውክልናቸው ሳይነሳ ጉዲዩ ለፋደራል ፍርድ ቤት ቀርቦ ከታየ የግዙት ክልል ሥልጣን ክርክር የሚያስነሳ መሆኑን ያስገነዛባል።
ነገር ግን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ከተመለከተው የግዙት ክልል የተለየ ውጤት ያለው ነው። ሥነ-ሥርዓት ሕጉ በሚቀረጽበት ጊዚ የፍደራል ሥርዓት አወቃቀር ባለመኖሩ ተመሳሳይ የሥረ-ነገር ሥልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች በተለያዩ የፍደራልና የክልል መንግሥታት ሥልጣን ክልል ውስጥ በሚሆንበት ጊዚ የሚያስነሳውን ክርክር የሚመለስ አይደለም። የሥነ-ሥርዓት ሕጉ አቀራረጽም ከፋደራል ሥርዓቱ ጋር ተጣጥሞ መተርጎም ይኖርበታል። ጉዲዩ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ እንደተቀረጸው የግዙት ክልል ሥልጣን በዋነኛነት አመቺነትን ብቻ መሰረት ያደረገ ነው፤ አመቺ እስከሆነ ድረስ በፋደራል ፍርድ ቤት ላታይ ይችላል ከተባለ፤ በሕገ-መንግሥቱ የክልል ፍርድ ቤቶች ውክልና ሉነሳ የሚችለው በሕዛብ ተወካዮች ምክር ቤት 2/3ኛ ድምጽ ብቻ ስለመሆኑ በአንቀጽ 78(2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፤ የክልል ፍርድ ቤቶች በሕገ-መንግሥቱ የተሰጣቸውን የውክልና ሥልጣን በሕጉ በተገለጸው አግባብ ሳይነሳ በፍርድ ቤቶች ውክልናውን የማንሳት ውጤት ያስከትላል። ሕገ- መንግሥቱ የፍደራል ጉዲይን በውክልና በክልል ፍርድ ቤቶች እንዱታይ የወሰነበትንና ሉያሳካው የፈለገውን ዓላማና ግብ ላይ እንዲይደርስ ያደርጋል። ጉዲዩን የሚመለከተው ፍርድ ቤት የሚወሰነው በሕግ ሆኖ እያለ በክልል ፍርድ ቤት በውክልና ላታይ የሚችል ሥልጣን በፋደራል ፍርድ ቤት የሚቀርብ ከሆነ ተከራካሪዎች ክሱን የሚያቀርቡበት ፍርድ ቤት የፍደራል ወይስ የክልል ፍርድ ቤት ስለመሆኑ በራሳቸው ምርጫ እንዱያቀርቡ (forum shopping) የሚያደርግ ተገቢ ያልሆነ የዲኝነት አሰጣጥ ሥርዓት እንዱፈጠር ዔድል ይሰጣል።
ሥለሆነም በእነዘህ ምክንያቶች የክልል ጠቅላይና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በሕገ-መንግሥቱ የፍደራል ጉዲዮችን በውክልና እንዱመለከቱ የተሰጣቸውን ሥልጣን መሰረቱ የፍደራል አወቃቀር በመሆኑ ውክልናቸው በሕግ እስካልተነሳ ድረስ ጉዲዮቹ ለፋደራል ፍርድ ቤት ሉቀርቡ አይችለም። ጉዲዮቹ ቀርበው በፋደራል ፍርድ ቤቶች ከታዩ ውጤቱም አስገዲጅነት ያለውን የፍርድ ቤት ሥልጣን ክፍፍል የሚጥስ ስለሆነ ጉዲዩ በየትኛውም ደረጃ ፍርድ ቤት ሲደርስ በተከራካሪዎች ሆነ በፍርድ ቤቱ የሥልጣን ጥያቄው ተነስቶ ክሱ ውድቅ ላደረግ የሚገባው ነው።
ወደ ያዛነው ጉዲይ ስንመለስ ክሱ መሰረት ያደረገው ከውል ውጭ ኃላፉነትን ሲሆን ጉዲት የደረሰበት ንብረት የሚገኘው ሆነ ጉዲቱ የደረሰበት ቦታ ኦሮሚያ ክልል ቡራዩ ከተማ ውስጥ ነው። በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ጉዲት በደረሰ ጊዚ ክሱ የሚቀርበው ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ መሆኑን ስለግዙት ክልል የሚደነግገው የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 25(1)(መ) ላይ ተመልክቷል።
ይሕም ክሱ ኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤት እንደሚታይ ያስረዲል። በልላ በኩል የተከራካሪዎችን አድራሻ ስንመለከት አመልካች፣ ተጠሪ፣ እና የሥር 3ኛ ተከሳሽ ኦሮሚያ ክልል ነዋሪ ሲሆን የሥር 2ኛ ተከሳሽ የአዱስ አበባ ከተማ ነዋሪ ናቸው። በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5(2) መሰረት መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልልች ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል በሚነሱ ክርክሮች ላይ የመዲኘት ሥልጣን ያለው የፍደራል ፍርድ ቤት ነው።
በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 47(1) ከተዖረዖሩት ክልልች ውስጥ አዱስ አበባ ከተማ ራሷን ችላ ክልል ባትሆንም ከአንድ ክልል በላይ የሚሻገር ጉዲይ የፍደራል መንግሥት ፍላጎትና ጥቅም (federal interest) ያለበት መሆኑን ታሳቢ ተደርጎ የተቀረጸ ሕግ በመሆኑ ጉዲዩ የፍደራል ነው። የፍደራል ጉዲይ ቢሆንም ጉዲዩ የተነሳው በኦሮሚያ ክልል በመሆኑ በሕገመንግሥቱ በተሰጠው ውክልና መሰረት መታየት ያለበት በክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።
የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዱስ አበባ ወይም ላላ ከተማ ላይ ማስቻለ ጉዲዩ በውክልና የሚመለከተው ሥልጣን ክልል ውስጥ እስከሆነ ድረስ ልዩነት የለውም። የኦሮሚያ ክልል በሕገ-መንግሥቱ የተሰጠው የውክልና ሥልጣን ያልተነሳ ስለሆነ የፍደራል አወቃቀሩን መሰረት ያደረገው አስገዲጅነት ያለውን የፍርድ ቤት የግዙት ክልል ሥልጣን ክፍፍል በሚጥስ መልኩ በፋደራል ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ ቀርቦ መታየቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ሐምል 15 ቀን 2011 ዓ/ም እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ ጥር 13 ቀን 2011 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለውም በማለት ወስነናል።
በዘህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ትዔዙዛ የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
አፈጻጸሙ ላይ የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.