No summary available.
ጥቅምት 20 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡ ...1. ዲኜ መላኩ 2. ተፈሪ ገብሩ 3. ቀነዓ ቂጣታ 4. ተሾመ ሽፈራዉ 5. ፀሐይ መንክር አመልካች፡- ........የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሞጆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተጠሪዎች፡- .......1. ዲሽን ባንክ አ.ማ 2. ኤ.አይ.ኤል.ኤፍ.ኤ. ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጣልቃ ገብ፡-......የኢትዮጵያ ፋዳራል ፖሉስ ኮሚሽን ይህ መዛገብ የተቀጠረዉ ለምርመራ ሲሆን ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የአፈጻጸም ክርክር የሚመለከት ሲሆን ለችልቱ ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የምስራቅ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.50115 በ22/6/2009 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበዉን አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዲዩ መነሻ ሲታይ በኦሮሚያ ክልል በለሜ ወረዲ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች አመልካች፣ የአሁን 1ኛ ተጠሪ የፍ/ባለመብት እና የአሁን 2ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለዔዲ እንደነበሩ የሥር ዉሳኔ ያሳያል። የሥር ወረዲ ፍ/ቤት በፍ/ባለመብት እና በፍ/ባለዔዲ መካከል የነበረዉን የአፈጻጸም ክርክር በመመርመር በሰጠዉ ትዔዙዛ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሞጆ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍርድ ባለዔዲ ንብረት ላይ የሰጠዉ የእግድ ትዔዙዛ እያለ ትዔዙዘ ሳይነሳ ለፋዳራል ፖሉስ ኮሚሽን ተወስኗል በሚል ምክንያት ንብረቱን በጨረታ የሸጠ ስለሆነ ኃላፉነት ስላለበት የፍ/ባለዔዲዉ ንብረት ከተሸጠበት ገንዖብ ብር 396,893.37 ወጪ በማድረግ ለፍ/ባለመብት እንዱከፍል በማለት ትዔዙዛ ሰጥቷል። የአሁን አመልካች ይህን ትዔዙዛ በመቃወም አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ አመልካች አቤቱታዉን ማቅረብ የነበረበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.418 መሰረት ሆኖ ሳለ በዘህ አግባብ ስላላቀረበ ተቀባይነት የለዉም በቀደመዉ ትዔዙዛ መሰረት ፈጽሞ እንዱቀርብ አዝል። የአሁን አመልካች ይህን ትዔዙዛ በመቃወም ይግባኝ ለምስራቅ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን ዉድቅ በማድረግ የስር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ ለማሳራም ነዉ።
የአሁን አመልካች በ27/6/2009 ዓ.ም የተጻፈ ሶስት ገጽ አቤቱታ አቅርቧል። የአቤቱታዉ ይዖት በአጭሩ፡--ለፍርድ አፈጻጸም እንዱዉል የታዖዘት ዔቃዎች የፍ/ባለዔዲ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ንብረት ሳይሆን የአልፊ ጠቅላላ የንግድ ማህበር ሆኖ ሳለ፣ የአሁን አመልካች የክርክሩ አካል ሳይሆን ሳይከሰስ እና ሳይከራከር ጥፊተኛ ነዉ ተብል ለደረሰዉ ጉዲት ኃላፉ ነዉ የተባለበት አግባብ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረምልን ይገባል። እነዘህ ንብረቶች ደግሞ የፖሉስ የደንብ ልብስ በመሆናቸዉ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ለፍርድ ማስፈጸሚያ ሉይዙቸዉ እንደማይችል ዉሳኔ ተሰጥቶበታል። ስለዘህ የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ እንዱታረምልን በማለት በዛርዛር አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣የሥር ፍ/ቤት በጨረታ የተሸጠዉ ንብረት የፍ/ባለዔዲ ንብረት ስለመሆኑ ባልተጣራበት በዉሳኔ የተመለከተዉን ገንዖብ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱከፍል የመወሰኑን አግባብነት፣ ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ ትዔዙዛ በሰጠዉ መሰረት 1ኛ ተጠሪ ሚያዘያ 30 ቀን 2009 ዓ.ም የተጻፈ አምስት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዖት በአጭሩ፡--የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመባቸዉ አመልካች ያቀረበዉ አቤቱታ የፍሬ ነገርና የማስረጃ ምዖና ጉዲይ ስለሆነ ዉድቅ ሆኖ የሥር ዉሳኔ እንዱጸናልን አመልካች ያካሄደዉ ጨረታ ተሰርዜ ካፖርቶቹ እንደገና ተሽጠዉ ለፍርድ ማስፈጸሚያነት እንዱዉለልን እንዱወሰንልን በማለት አመልክቷል። የአሁን አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል። የአሁን 2ኛ ተጠሪ በአዱስ ዖመን ጋዚጣ ጥሪ ቢደረግለትም ባለመቅረቡ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
ይህ በእንዱህ እንዲለ የአሁን ጣልቃ ገብ በ22/7/2009 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ በጣልቃ ገብ እና በ2ኛ ተጠሪ ድርጅት መካከል በተደረገዉ ዉል መሰረት 8,000 የፖሉስ አባላት ካፖርቶች ለማቅረብ ባለመቻላቸዉ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ መስረተን ዉሳኔ ተሰጥቶን በአፈጻጸም ላይ እያለን የአሁን 1ኛ ተጠሪ መብት አለኝ በማለት በአፈጻጸም ላይ ክርክር አቅርቦ አቤቱታዉ ዉድቅ ተደረጓል። ስለዘህ በእነዘህ ካፖርቶች ላይ መብት ያለን ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.41 መሰረት ወደ ክርክሩ ገብተን እንዱንከራከር በማለት አመልክቷል። በዘህ አቤቱታ ላይ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም በተጻፈ መልስ ጣልቃ ገብ ያቀረበዉ አቤቱታ ተቀባይነት የለዉም ዉድቅ እንዱደረግን በማለት በዛርዛር መልስ አቅርቧል። አመልካች ደግሞ በ1/10/2009 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። የአሁን 2ኛ ተጠሪ በጋዚጣ ጥሪ ተደርጎለት ስላልቀረበ አስተያየት የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
እንደመረመረዉ በዘህ ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ጉዲይ የለሜ ወረዲ ፍ/ቤት በተሰጠዉ በፍርድ አፈጻጸም የዉክልና ስልጣን የሰጠዉን ትዔዙዛ የምስራቅ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ የማየት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? የአሁን ጣልቃ ገብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.41 መሰረት ያቀረበዉ አቤቱታ በዘህ ችልት ሉስተናገድ የሚችል ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለትን ነጥቦች እንደጭብጥ በመያዛ መርምሮታል።
በዘህ መሰረት የመጀመሪያዉ ጭብጥ በተመለከተ በ1ኛ ተጠሪ እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል በነበረዉ የፍትሒ ብሓር ክርክር የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ገንዖብ እንዱከፍል ዉሳኔ በመስጠት፣ ፍርደን ለማስፈጸም ደግሞ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.372 /1/ በሚደነግገዉ መሰረት የፍ/ባለዔዲ ንብረት በአመልካች ጽ/ቤት ዖንድ ታግድ ይገኛል በሚል ምክንያት የለሜ ወረዲ ፍ/ቤት እንደፍርደ እንዱያስፈጽም ያስተላለፈለት መሆኑን መገንዖብ ይቻላል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍርድ አፈጻጸም የለሜ ወረዲ ፍ/ቤትን በመወከለ የወረዲዉ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን ማግኘቱን ማየት ተችሎል። ስለሆነም በዘህ አግባብ የተወከለዉ የወረዲዉ ፍ/ቤት ያለዉ ስልጣን ምን እንደሆነ ማየቱ አስፈላጊ ነዉ። በዘህ ረገድ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.374 /1/ እንደሚደነግገዉ ፍርድ አስፈጻሚዉ ፍ/ቤት ስለፍርድ አፈጻጸም የሚሰጠዉ ትዔዙዛና በትዔዙዘም ላይ ይግባኝ ስለሚባልበት ሁኔታ ያለዉ ስልጣን ዋናዉን ፍርድ ከወሰነዉ ፍ/ቤት ሥልጣን ጋር እኩል ሆኖ ይቆጠራል በማለት ደንግጓታል።
በመሆኑም የለሜ ወረዲ ፍ/ቤት ይህን የአፈጻጸም ክርክር በተመለከተ የሚሰጠዉ ትዔዙዛና በትዔዙዘም ላይ ይግባኝ ስለሚባልበት ሁኔታ ልክ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንደሰጠዉ ይቆጠራል ማለት ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ የለሜ ወረዲ ፍ/ቤት በፍርድ አፈጻጸም የተሰጠዉን ዉክልና መሰረት በማድረግ በሰጠዉ ትዔዙዛ ላይ የአሁን አመልካች ይግባኝ ማቅረብ ያለበት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠዉን ትዔዙዛ በይግባኝ አይቶ ለማረም ስልጣን ወደአለዉ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ነዉ። በዘህ መሰረት የአሁን አመልካች ያቀረበዉን አቤቱታ የለሜ ወረዲ ፍ/ቤት ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉን ትዔዙዛ በመቃወም ይግባኝ ማቅረብ የነበረበት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ነዉ እንጂ ለምስራቅ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት አይደለም።
የምስራቅ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ በይግባኝ የማየት ስልጣን የለዉም። በዘህ ምክንያት የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ በይግባኝ የማየት ስልጣን ሳይኖራዉ አመልካች ያቀረበዉን ይግባኝ በመቀበል የሥር ዉሳኔ በማጽናት የሰጠዉ ትዔዙዛ ከስልጣኑ ዉጭ የተሰጠ ትዔዙዛ ስለሆነ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል። የአሁን አመልካች ከፈለገ የለሜ ወረዲ ፍ/ቤት የሰጠዉን ትዔዙዛ በተመለከተ ይግባኙን ሥልጣን ላለዉ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል ብለናል።
ሁለተኛዉን ጭብጥ በተመለከተ የአሁን ጣልቃ ገብ ለክርክር መነሻ በሆኑት የፖሉስ አባላት የደንብ ልብስ ላይ የፍ/ባለዔዲዉን ከሰን ዉሳኔ ተሰጥቶን በፍርድ አፈጻጸም ላይ እያለን የአሁን 1ኛ ተጠሪ መብት አለኝ በማለት አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታዉ ዉድቅ ተደርጎ ካፖርቶቹን እንዱንረከብ ዉሳኔ ስለተሰጠን ወደ ክርክሩ ገብተን እንዱንከራከር በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.41 መሰረት አቤቱታ አቅርቧል። በዘህ አቤቱታ ላይ የአሁን አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የየራሳቸዉን መልስ አቅርቧል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.41 ድንጋጌ ይዖትና ዓላማ ሲታይ በላልች ተከራካሪ ወገኖች መካከል በሚደረግ ክርክር ወደ ክርክሩ ገብቸ ሳልከራከር ዉሳኔ የሚሰጥ ከሆነ መብቴ ይነካል የሚል ሶስተኛ ወገን ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት አቤቱታዉን ለፍ/ቤቱ ማቅረብ እንደሚችል ያመለክታል። የድንጋጌ ይዖትና ዓላማ ሲታይ የፍሬ ነገርና የማስረጃ ጉዲይ በዉስጡ ያዖለ ሁኖ እናገኛለን። ይህ ከሆነ ደግሞ ይህ ችልት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ከሚያርም በስተቀር ፍሬ ነገር የማጣራት እና ማስረጃ የመመዖን ስልጣን ስለላለዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.41 መሰረት የሚቀርብ አቤቱታን ተቀብል ለማስተናገድ የሚያስችለዉ ስልጣን የሚያገኝበት የሕግ አግባብ የለም።
የአሁን ጣልቃ ገብ ደግሞ በግልጽ ከአቤቱታዉ ጋር አያይዜ ያቀረበዉ የተለያዩ ዉሳኔዎችን እንደሰነድ ማስረጃዎች በማድረግ እንደሆነ መገንዖብ ተችሎል። ስለሆነም ጣልቃ ገብ ያቀረበዉ አቤቱታ ተቀባይነት አለዉ ወይስ የለዉም? ለማለት እነዘህን የሰነድ ማስረጃዎች መመርመር አስፈላጊ ስለሚሆን ይህ ደግሞ የዘህ ችልት ስልጣን ስር የሚወድቅ ጉዲይ አይሆንም። ይህ ጉዲይ በአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ መጠን የአሁን ጣልቃ ገብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.41 በመጥቀስ አቤቱታ ያቀረበዉ ሲታይ አግባብነት ያለዉን የህግ ድንጋጌ ከመጥቀስ አንጻር ለሚነሳ ጥያቄ ለጊዚዉ በማለፍ፣ አሁን ግን በአቤቱታዉ የተጠቀሰዉ ፍሬ ጉዲይና ተያይዜ ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃዎችን ለመመርመር ከዘህ ችልት ስልጣን ዉጭ ስለሆነ ችልቱ አቤቱታዉን ለማስተናገድ የሕግ ስልጣን የለዉም። ስለሆነም የአሁን ጣልቃ ገብ ከፈለገ አግባብነት ባለዉ የሕግ ድንጋጌ መሰረት ለለሜ ወረዲ ፍ/ቤት አቤቱታዉን ከሚያቀርብ በስተቀር ለዘህ ችልት ያቀረበዉ አቤቱታ ተቀባይነት የለዉም ብለን ዉድቅ አደርገናል።
ሲጠቃለል የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት፣ የለሜ ወረዲ ፍ/ቤት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠዉ የፍርድ አፈጻጸም ዉክልና ስልጣን መሰረት የሰጠዉን ትዔዙዛ፣ በይግባኝ የማየት ስልጣን ሳይኖረዉ የሥር ትዔዙዛ በማጽናት የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱሁም ይህ ችልት የአሁን ጣልቃ ገብ ያቀረበዉን አቤቱታ ለማየት ስልጣን የላለዉ ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.50115 በ22/6/2009 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ ከስልጣኑ ዉጭ የሰጠ ስለሆነ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
የአሁን አመልካች የለሜ ወረዲ ፍ/ቤት የሰጠዉ ትዔዙዛ ላይ ቅሬታ ያለዉ እንደሆነ ይግባኙን ስልጣን ላለዉ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ለማቅረብ ይችላል ብለናል።
ይህ ችልት የአሁን ጣልቃ ገብ ያቀረበዉን አቤቱታ የማየት ስልጣን የለዉም፤ ጣልቃ ገብ ከፈለገ አቤቱታዉን አግባብነት ባለዉ የሕግ ድንጋጌ መሰረት ለለሜ ወረዲ ፍ/ቤት ለማቅረብ ይችላል ብለናል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ ብለናል።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.