No summary available.
ህዲር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነጻነት ተገኝ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ ከግልግል ዲኝነት ስልጣን ጋር በተያያዖ የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በሚል በቀረበ አቤቱታ መነሻ የተደረገ ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረዉ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን አመልካቾች ከሳሾች የነበሩ ሲሆን የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበረ። ከግራ ቀኝ ክርክርና ከስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ መረዲት እንደቻልነዉ ተጠሪ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዱስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዘት ፕሮጀክት ለመገንባት በአማካሪነት ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር በዋና አማካሪነት፣ከአመልካቾች ጋር ደግሞ በቀን 25/10/2004ዓ/ም እና በቀን 25/04/2006ዓ/ም የንኡስ አማካሪነት ዉልች መዋዋለን፤ 2ኛ አመልካች የ1ኛ አመልካች ስራ አስኪያጅ እንደሆኑና 1ኛ አመልካች 2ኛ አመልካችን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ በባቡር መንገድ እስፔሻሉስትና ሪዛደንት ኤንጂነርነት የማማከር ሙያ በፕሮጀክቱ ለማገልገል እና ተጠሪ በዉልቹ ላይ የተመለከተዉን ክፍያ ለ2ኛ አመልካች ለመክፈል እንደተስማሙ፤ ተጠሪ በዉልቹ መሰረት መክፈል የሚገባዉን ከአሰሪዬ ክፍያ ስላልተፈጸመልኝ ነዉ ላላ ጊዚ ደግሞ ተቀንሶ ስለተከፈለኝ ነዉ በሚል እዲዉ መሆኑን ያመነዉን በድምሩ 121,723.69 የአሜሪካን ድላር ወይም የኢትዮጵያ ምንዙሬዉን ብር 2,735,253.03 በዉለ በተመለከተዉ የአመልካቾች የባንክ ሂሳብ ገቢ እንዱያደርግ ወይም እንዱከፍላቸዉ እንዱወሰንላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪ ለቀረበበት ክስ ባቀረበዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከዉል የመነጨ ማንኛዉም አለመግባባት መጀመሪያ በስምምነት ለመፍታት ይህ ካልተቻለ በግልግል ታይቶ እንዱያልቅ በዉለ አንቀ ጽ 9.1 ስር በግልጽ ስለተስማማን ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የመዲኘት ስልጣን የለዉም በሚል ተቃዉሟል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርክር ሰምቶና መርምሮ በመ/ ላይ በቀን 18/11/2010 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ ግራ ቀኝ በዉላቸዉ ላይ ከዉለ የሚመነጭ ማንኛዉም አለመግባባት በሽምግልና እንዱታይ በዉለ ስለተስማሙ ይህ ስምምነታቸዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1731 መሰረት የሕግ ያህል አስገዲጅነት ያለዉ በመሆኑ በዘህ መሰረት መስማማታቸዉ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ተቀብል እንዲይዲኝ መስማማታቸዉን ስለሚያሳይ እንዱሁም እንዱህ አይነት ስምምነት ከተደረገ መደበኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ተቀብል መዲኘት እንደላለባቸዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ አስገዲጅ ትርጉም መስጠቱን በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ ጉዲየን የመዲኘት የሥረ ነገር ሥልጣን የለዉም በሚል ወስኗል። አመልካች በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ችልቱ በመ/ ላይ በቀን 20/03/2011 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዙዛ ይግባኙን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዝል።አመልካቾች በዘህ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል በቀን 14/06/2011 ዓ/ም ጽፈዉ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዖት በአጭሩ ከዘህ የሚከተለዉ ነዉ።
ተዋዋዮች የዉጭ አገር ህጎች ተፈጻሚ እንዱሆኑ መስማማታቸዉ፣ተዋዋዮች ኢትዮጵያዊ አለመሆናቸዉ፣ የመጀመሪያዉን ዉል በኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚሰራ ሥራ ከኢትዮጵያ ዉጭ መፈራረማቸዉ፣ ለጉዲዩ አወሳሰን የሚገለግለ ማስረጃዎች በኢትዮጵያ ዉስጥ መገኘታቸዉ፣ተጠሪ በኢትዮጵያ ዉስጥ የተመዖገበ ድርጅት መሆኑ ጉዲዩ ከኢትዮጵያ ጋር ከፍተኛ ግንኙት ያለዉ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ሉመለከት የሚገባዉ እንደ አገር ዉስጥ ጉዲይ (Domestic Matter) ሳይሆን የአለም አቀፍ የግለሰቦች ሕግ (Private International Law Matter) መርህ መሰረት በማድረግ መሆን ሲገባዉ እንደ አገር ዉስጥ ጉዲይ በመመልከት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1731፣ 3307፣3345 እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 244 እና 315 ስር በኢትዮጵያ የዲኝነት ስልጣንና ሕግ ስር ስለተደረጉ የግልግል ስምምነቶች የተደነገገዉን እና በሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠዉን ትርጉም መሰረት በማድረግ ጉዲዩ የግለሰብ አለም አቀፍ ህግ ጥያቄን የሚያስነሳ ሆኖ እያለ በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 11(2/ሀ) እና 5 የተሰጠዉን ስልጣን የሚያሳጣዉን ዉሳኔ መወሰኑ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ የሰጠዉን አስገዲጅ ትርጉም ጭምር የሚቃረን በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንደሆነ፤
ዋናዉ ወል አለም አቀፍ ባህርይ ያለዉ እንደመሆኑ በዘህ ዉል ላይ ያለዉ የግልግል ስምምነት የጸና የግልግል ስምምነት ላሆን የሚችለዉ (valid arbitration agreement) በግልጽ የግልግል ዲኝነቱ የሚታይበት ቦታ/አገር( Seat of Arbitration)፣ የግልግል ዲኝነቱን የሚመለከተዉ አካል፣የግልግል ጉባኤዉን ማን እና የትኛዉ ፍርድ ቤት እንደሚያቋቁም፣የዘህ አካል ሞያ (Profession)፣ የዳኞች ብዙት፣በግልግል ጉባኤዉ የሚሰጠዉን ዉሳኔ ለመቃወም ቅሬታ እንዳትና የት እንደሚቀርብ፣ጉባኤዉ የሚሰጠዉን ዉሳኔ(award) የት የሚገኘዉ ፍርድ ቤት ያስፈጽማል፣አፈጻጸሙን እንዳት መቃወም እና ቅሬታ ማቅረብ ይቻላል የሚለ መሰረታዊ የጸና የግልግል ስምምነት ጉዲዮች በግልጽ ሲቀመጡ ሲሆን የግልግል ስምምነቱ እነዘህን ዛርዛሮች የማያሟላ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት ገዲዩን እንደተለመደዉ የአገር ዉስጥ ጉዲይ ተመልክቶ ከላይ የተመለከቱትን መሰረታዊ ጉዲዮች የግልግል ስምምነቱ የሚያሟላ መሆን አለመሆኑን ሳይመረምር የግልግል ስምምነቱን፣የኢትዮጵያን ህግና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ዉሳኔ በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የመዲኘት ስልጣን የለዉም ሲል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንደሆነ፤
በዉለ አንቀጽ 9.1 ስር በተመለከተዉ የግልግል ስምምኑ መሰረት ወደ ግልግል ዲኝነት ሉሄድ የሚችለዉ የዉለን አተረጓጎም በተመለከተ አለመግባባት ካለ ለመሆኑ በአንቀጹ የመጀመሪያ ፓራግራፍ ለይ በግልጽ ተመልክቶ እያለ የስር ፍርድ ቤት ራሱን ችል የማይቆመዉን የአንቀጹን ሁለተኛ ፓራግራፍ ብቻ መሰረት በማድረግ ማንኛዉም ጉዲይ በግልግል ዲኝነት ይታያል ሲል የሰጠዉ ትርጉም በዉለ አንቀጽ 9.1 ስር የተመለከተዉ ያላገናዖበና ክርክሩም የዉለን አተረጓጎም የሚመለከት ሳይሆን በማስረጃ ተጣርቶ የሚወሰን በመሆኑ ለግልግል እንዱቀርብ የሚያስገድድ ክርክር ሳይኖር የስር ፍርድ ቤት በተሳሳተ ሁኔታ በመተርጎም ጉዲዩን ማየት ያለበት የግልግል ጉባኤ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የስረ ነገር ስልጣን የለዉም ሲል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ ተብል እንዱታረምላቸዉ በመጠየቅ አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን መርምሮ ግራ ቀኙን ያከራከረዉ ነጥብ በግራ ቀኙ ስምምነት አንቀጽ 9/1 ስር እንደተመለከተዉ በግልግል ዲኝነት አማካኝነት እንጂ በፍርድ ቤት ሉዲኝ የሚችል ጉዲይ አይደለም ከሚል ትርጉም የሚያደርስ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ ይታይ ዖንድ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ የሰጠዉን ትእዙዛ ተከትል ተጠሪ በቀን 29/08/2011 ዓ/ም የተጻፈ መልስ ያቀረበ ሲሆን ይዖቱ በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
አመልካች ዉለ አይጸናም ያለዉ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሕግ የተሰጠዉን ዓለም አቀፍ የግለሰብ ሕግን የሚመለከቱ ጉዲዮችን በዉል ሉወሰድበት አይችልም ከሚል መነሻ ቢሆንም አመልካችና ተጠሪዎች ጉዲያቸዉ የሚታይበትን ስርዓት መምረጥ አይችለም ተብል በሕግ እንዲልተከለከለ፤ አለም አቀፍ የግለሰብ ሕግን የሚመለከቱ ጉዲዮችን የመዲኘት ስልጣን የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣን ቢሆንም ይህ ማለት ግን ማንኛዉም የግለሰብ ዓለም ዓቀፍ ሕግን የሚመለከቱ ጉዲይ በግዳታ በዘህ ፍርድ ቤት ብቻ መታየት አለበት ማለት እንዲልሆነ፤ ተዋዋይ ወገኖች በመዋዋል ነጻነታቸዉ ተጠቅመዉ ጉዲያቸዉን የሚዲኝላቸዉን አካል ከወሰኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩ ዓለም ዓቀፍ የግለሰብ ሕግን ይመለከታልና ማየት አለብኝ ለማለት የሚያስችለዉ የሕግ ስርዓት እንደላለ፤ ጉዲዩ በግዳታ መታየት ያለበት በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብቻ ነዉ የሚለዉ የአመልካቾች ክርክር የዚጎችን የመዋዋል ነጻነትና የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3325-3346 የተደነገገዉን የሚጥስ እንደሆነ፤ አመልካች የጠቀሳቸዉ የሰበር ዉሳኔዎችም ዓለም አቀፍ የግለሰብ ሕግን የሚመለከቱ እንጂ ከግልግል ጉባኤ ስምምነት ጋር ተያይዜ የተሰጡ ዉሳኔዎች እንዲልሆኑ፤ በዉለ አንቀጽ 9.1 ስር ከዉል በመነጨ ወይም ከዉለ ጋር በተያያዖ በአማካሪዉ እና በንኡስ አማካሪዉ መካከል የሚነሳ ማናቸዉም አለመግባባት (ክርክር) በግልግል ጉባኤ ታይቶ እንደሚወሰን በግልጽ መስማማታቸዉን፤ክስ የቀረበበት ጉዲይም የዉለን አንቀጽ መተርጎምን የሚጠይቅ ሆኖ እያለ ክርክሩ ዉልን መተርጎም የሚጠይቅ ባለመሆኑ የዉለ አንቀጽ 9.1 ተፈጻሚነት የለዉም እንዱባል የቀረበዉ ክርክር ተገቢ እንዲልሆነ፤
እንዱሁም በአለም ዓቀፍ የንግድ ምክር ቤት የግልግል ደንብ መሰረት በአለም ዓቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት በግልግል ጉባኤ እንዱታይ ስምምነት ስለተደረገ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1733 ስር በተደነገገዉ መሰረት ዉለ በዘህ ልክ ግልጽ በሆነበት የተዋዋዮች ፈቃድ ምን እንደነበር መተርጎም ስለላለበት የፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የመዲኘት ስልጣን የለኝም ማለቱ ተገቢ እንደሆነ፤ በግራ ቀኝ የዉል ስምምነት ላይ አለመግባባትን የመፍታት ስልጣን ለግልግል ጉባኤ ሲሰጥ ጉዲዩ በአለም አቀፍ የንግድ ምክር ቤት የግልግል ጉባኤ ደንብ (International Chamber of Commerce Rules of Arbitration) መሰረት የሚመራ መሆኑ በዉለ ቁጥር 9.1 እና በአባሪ ቁጥር 1 ላይ በግልጽ የሰፈረ በመሆኑ አንድ ተዋዋይ ወገን ይህን ደንብ ለግልግል ጉባኤዉ ስነስርዓት መመሪያ እንደሚሆን በዉለ ላይ ሲያሰፍር የዓለም ዓቀፍ የግልግል ዲኝነት ፍርድ ቤት (International Court of Arbitration) ጉዲዩን የማየት ስልጣን እንደተቀበለ እንደሚቆጠር በደንቡ አንቀጽ 6/2 ላይ በግልጽ ስላሰፈረ በዘህ ደንብ የዲኝነት ቦታዉ የዘሁ ጉባኤ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦታ ሲሆን የባለሙያዎች አመዲደብም ሆነ የግልግል ዳኞች ቁጥር አወሳሰን ምን እንደሚመስል በግልጽ በደንቡ ዉስጥ ሰፍሮ ስለሚገኝ አመልካቾች ይህንን እያወቁ የግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ጉድለት አለበት በማለት ፍርድ ቤቱ ዉለን እንዱያሻሽልላቸዉ ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለዉም ተብል የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱጸናለት በመጠየቅ ተከራክሯል።
አመልካቾች ተጠሪ ለሰጠዉ መልስ በቀን 14/09/2011ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥና የክርክሩ ይዖት ከዘህ በላይ የተመዖገበዉ ሲሆን እኛም ሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለዘህ ችልት ያስቀርባል ብል ከያዖዉ ጭብጥ አንጻር ጉዲዩ በግልግል ዲኝነት አካል ላታይ የሚገባ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚል ጭብጥ በመያዛ ከግራ ቀኝ ክርክር፣ በዉለ ከተመለከተዉ የግልግል ዲኝነት ስምምነት፣ ከስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ እና አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
ጉዲዩን መርምረን እንደተረዲነዉም በጉዲዩ ላይ ተገቢዉን ዉሳኔ ለመስጠት ይረዲ ዖንድ በመጀመሪያ የግልግል ዲኝነት ምንነትና አቋቋም፣ የግልግል ዲኝነት ስምምነት መያዛ ያለበትን ነገሮች፣ በግልግል ዲኝነት ሉታዩ የሚገባቸዉና በግልግል ዲኝነት መታየት የማችይለ ጉዲዮች ምንነት በአገራችንና በዓለም አቀፍ ደራጃ ተፈጻሚነት ካላቸዉ ሕጎች አንጻር መመርመር ያስፈልጋል።
ሰዎች በመካከላቸዉ ከፈጠሩት ሕጋዊ ተግባራት (juridical acts) በመነጨ ወይም ከዘህ ጋር በተያያዖ ለወደፉት በመካከላቸዉ የሚፈጠረዉን አለመግባባት ወይም ተፈጥሮ ያለዉን አለመግባባት ከመደበኛ ፍርድ ቤት ዉጭ በግልግል ዲኝነት በኩል ለመፍታት የመዋዋል ነጻነታቸዉን በመጠቀም መስማማት ይችላለ። የግልግል ዲኝነት በስምምነት የሚቋቁሙበት ዋነኛ ዓላማም ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በመሄድ የሚያጠፈትን ጊዚ፣ ጉልበትና ገንዖብ ለመቀነስ እንዱሁም ክርክራቸዉ በመደበኛ ፍርድ ቤት በግልጽ ችልት እየታየ ግላዊ የሆነ ጉዲያቸዉ (ምስጢራቸዉ) ወደአደባባይ እንዲይወጣ ለማድረግ ካላቸዉ ፍላጎት እንደሆነ ይታመናል።
በዘህ መልኩ በጽሁፍ በተዋዋለት በዋናዉ ዉላቸዉ የሚያደርጉት የግልግል ዲኝነት ስምምነት ቃል ( Arbitration Clause) ተብል የሚታወቅ ሲሆን አስቀድሞ በመካከላቸዉ ተከስቶ ያለዉን አለመግባባት በግልግል ዲኝነት ለመፍታት ራሱን በቻለ የጽሁፍ ስምምነት የሚያደርጉት የግልግል ዲኝነት ስምምነት ደግሞ Submission Agreement ተብል የሚታወቀዉ ነዉ። እነዘህ ሁለት አይነት ገጽታ ያላቸዉ አለመግባባትን በግልግል ዲኝነት ለመፍታት የሚደረጉ ስምምነቶች በጠቅላላዉ የግልግል ዲኝነት ስምምነት (Arbitration Agreement) ተብለዉ እንደሚታወቁ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3325/1 እና 3328 እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 315 ስር የተደነገገዉን አጣምሮ በማንባብ መገንዖብ ይቻላል። እንዱሁም በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ስር በሚገኝ የአለም አቀፍ የንግድ ሕግ ኮሚሽን (United Nations Commission on International Trade Law /UNCITRAL) አገራት እንደ ተምሳላት ሕግ (Model Law) እንዱጠቀሙበት ባወጣዉ አንቀጽ 7 እና በዉጭ አገር የግልግል ዲኝነት አካል ታይቶ ለተወሰነ ዉሳኔ(Award) እዉቅና ለማሰጠት እና ለማስፈጸም እ.ኤ.አ በ1958 በወጣዉ የኒዉ ዮርክ ቃል ኪዲን (ይህንን ቃል ኪዲን አገራችን እስካሁን አለማጽደቋን ልብ ይሎል) አንቀጽ 2 ስር ለግልግል ዲኝነት ስምምነት (Arbitration Agreement) ተመሳሳይ ትርጉም መሰጠቱን መረዲት ይቻላል።
በአገራችን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 315 (2 እና 3) ስር እንደተደነገገዉ በግልግል ዲኝነት ሉዲኙ የማይችለ ጉዲዮች ናቸዉ ተብል በሕግ በግልጽ ከተደነገገዉ እና ከአስተዲደር ዉልች ጋር ከተያያዖዉ ዉጭ የሆኑ ሕጋዊ ተግባራትን መነሻ ያደረጉ አለመግባባቶች (Arbitrability) በግልግል ዲኝነት ታይተዉ እልባት እንዱያገኙ ለማድረግ ማናቸዉም ችልታ ያላቸዉ ተዋዋይ ወገኖች የመዋዋል ነጻነታቸዉን በመጠቀም የግልግል ዲኝነት ስምምነት መዋዋል ይቻላለ።
በአለም አቀፍ የግልግል ዲኝነት ሕግጋት መሰረት (በሞዳል ሕግ አንቀጽ 1 ግርጌ ላይ የተመለከተዉ ትርጉም እና በኒዉ ዮርክ ቃል ኪዲን አንቀጽ 2.1 ስር እንደተመለከተዉ) ተዋዋዮች የመዋዋል ነጻነታቸዉን በመጠቀም በአገራዊ ሕግ (Domestic Law) በግልግል ዲኝነት ሉታዩ አይገባም ተብል ገደብ የተጣለባቸዉን ሳያካትቱ በግልግል ዲኝነት ሉታዩ የሚችለ ጉዲዮችን (በአብዙኛዉ ከንግድና ከኢንቨስትመንት ጋር የተያያዘትን) መነሻ ያደረጉ አለመግባባቶች በግልግል ዲኝነት ለመዲኘት ስምምነት ማድረግ ይችላለ።
በተጨማሪም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3346 ስር በጥቅለ እንደተገለጸዉና በዘህ ዘሪያ ከተጻፈት የህግ አስተያየቶች መረዲት እንደሚቻለዉ የግልግል ስምምነት ግልጽና በቀላለ ተፈጻሚ መሆን እንዱችል እንደሁኔታዉ የሚከተለትን ጉዲዮች የያዖ ላሆን ይገባል።ተዋዋዮች በስምምነታቸዉ የግልግል ዲኝነትን ሲመርጡ ጉዲያቸዉን የሚዲኝ ተቋማዊ ህልዉና የላለዉ/የላላቸዉ/ ገላጋይ ዲኛ/ዳኞች (Ad hoc Arbitration) በስምምነታቸዉ ላይ መምረጣቸዉን አሉያም በተቋም ደረጃ የተደራጀ የግልግል ዲኝነት አካል (Institutional Arbitration /Administered Arbitration) በመምረጥ ጉዲያቸዉ ከሁለቱ በአንደ አካል ታይቶ እልባት እንዱያገኝ መስማማታቸዉን ማሳየት አለባቸዉ። ተቋማዊ ህልዉና የላለዉን ገላጋይ ዲኛ (Ad hoc Arbitration) ከመረጡ ገላጋይ ዲኛ መሰየም፣ ወይም ገላጋይ ዲኛዉ የሚሾምበትን መንገድ መግለጽ፣ የግልግል ዲኝነቱ የሚታይበትን ቦታ፣ የግልግል ዲኝነቱ የሚጠቀምበትን ቋንቋ፣ የግልግል ዲኝነቱ የሚመራበትን ስነ ስርዓት ሕግ፣ ለግልግል ዲኛዉ ስለሚከፈለዉ ገንዖብ…ወዖት አስቀድመዉ በስምምነታቸዉ ላይ እንዱገልጹ ይጠበቃል። በዘህ አግባብ በተለይም ገላጋይ ዲኛ በስምምነታቸዉ ላይ ካልሾሙ ወይም የሚሾምበትን መንገድ ካልገለጹ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3331/3 እና በተከታዮቹ ድንጋጌዎች እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ከቁጥር 316-319 ስር በተደነገጉ ድንጋጌዎች መሰረት እንዱሁም በስምምነታቸዉ ላይ በሚመርጡት የግልግል ዲኝነት ደንብ መሰረት እንደሚወሰን ስርዓት ተዖርግቷል።
በልላ በኩል የመረጡት በተቋም ደረጃ የተደራጀ የግልግል ዲኝነት አካል (Institutional Arbitration /Administered Arbitration) ከሆነ ተዋዋዮች በስምምነታቸዉ ላይ ከላይ የተጠቀሱትን ዛርዛር ነገሮች እንዱገልጹ አይገደደም።ይህም ማለት ገላጋይ ዲኛ የሚሰየመዉ፣ ገላጋይ ዲኛ የሚሾምበት መንገድ ፣ የግልግል ዲኝነቱ የሚታይበት ቦታ፣ የግልግል ዲኝነቱ የሚጠቀምበት ቋንቋ፣ የግልግል ዲኝነቱ የሚመራበትን ስነ ስርዓት ሕግ፣ ለግልግል ዲኛዉ ስለሚከፈለዉ ገንዖብ…ወዖት በመረጡት ተቋም ደንብና አሰራር መሰረት ይወሰናል ማለት ነዉ።
የግልግል ስምምነት እንደማንኛዉም የዉል ስምምነት ልዩ ባህሪዉን ባገናዖበ ሁኔታ በተለያዩ ምክንያቶች ከመነሻዉ ዋጋ አልባ(void) ወይም ፈራሽ (የማይጸና /invalid) ላሆን ይችላል።
እነዘህም ምክንያቶች የተዋዋዮች የመዋዋል ችልታ ማጣት፣ የፈቃድ ጉድለት፣ ዓላማዉ የግብረ ገብነት ጉድለት ያለበት መሆን፣ ዓላመዉ ከሕግ ዉጭ ወይም ሕገወጥ መሆንን (immoral, illegal and unlawful object) ፣ በህግ የተቀመጠለትን የአጻጻፍ ስርዓት ያልተከተለ(የፍርማሉቲ ጉድለት ያለበት) ከመሆን ጋር የሚያያዘ ናቸዉ።
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3330(1 እና 2) ስር ከግልግል ዲኝነት ስምምነት አተረጓጎም ጋር የተያያዖ ክርክር ቢነሳ አከራካሪዉ ነጥብ ላይ ዉሳኔ መስጠት እንዱችል በግልግል ስምምነቱ ላይ ለግልግል ዲኛዉ ስልጣን ሉሰጠዉ እንደሚችል እና በተለይ የራሱን ሥልጣን አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮች በራሱ እንዱወስን በግልግል ስምምነቱ ላይ ሉፈቀድለት እንደሚችል ተደንግጓል። ይህም ከላይ በተጠቀሰዉ ተምሳላታዊ ሕግ (UNCITRAL Model Law እ.ኤ.አ በ1985 ወጥቶ በ2006 እንደተሻሻለዉ) አንቀጽ 16 ስር ከተደነገገዉና በዖመናዊዉ የግልግል ዲኝነት የህግ ዖርፍ The Rule of Competence-Competence ተብል ከሚታወቀዉ መርህ ጋር ከሞላ ጎደል የሚመሳሰል ነዉ። ይህ መርህ የግልግል ዲኛዉ የግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ዋጋ ያለዉ መሆን አለመሆኑን (ፈራሽ ነዉ ተብል የሚቀርብ ክርክር /validity of arbitration agreement) በተመለከተ የሚነሳ ክርክር ጭምር ሰምቶ መወሰን እንዱችል ስልጣን የሚሰጠዉ ቢሆንም ይህ መርህ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3330/3 ስር እንደተመለከተዉ በአገራችን በከፉል ተቀባይነት ባለማግኘቱ በዘህ ድንጋጌ መሰረት በአገራችን የግልግል ዲኛ የግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ዋጋ የለዉም በሚል የሚነሳ ክርክር ሰምቶ በራሱ መወሰን እንዱችል ሥልጣን አልተሰጠዉም። ስለሆነም በአገራችን የግልግል ዲኝነት ስምምነት ዋጋ የለዉም በሚል የሚቀርብ ክርክር ሰምቶ የመወሰን ስልጣን ያለዉ ገላጋይ ዲኛዉ ወይም የግልግል ዲኝነት አካለ ሳይሆን መደበኛ ፍርድ ቤት ነዉ።
ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመጣ ከላይ በዛርዛር እንደተመለከተዉ ግራ ቀኙን ያከራከረዉ ጉዲይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ጉዲይ የመዲኘት ስልጣን ያለዉ መደበኛ ፍርድ ቤት ነዉ ወይስ የግልግል ዲኝነት አካል ነዉ የሚለዉ ነዉ። አመልካቾች በዉለ የተመለከተዉ የግልግል ዲኝነት ስምምነት የግልግል ዲኝነቱ የሚታይበት ቦታ/አገር( Seat of Arbitration)፣ የግልግል ዲኝነቱን የሚመለከተዉን አካል፣የግልግል ጉባኤዉን ማን እና የትኛዉ ፍርድ ቤት እንደሚያቋቁም፣የዘህ አካል ሞያ (Profession)፣ የዳኞች ብዙት፣በግልግል ጉባኤዉ የሚሰጠዉን ዉሳኔ ለመቃወም ቅሬታ እንዳትና የት እንደሚቀርብ፣ ጉባኤዉ የሚሰጠዉን ዉሳኔ(award) የት የሚገኘዉ ፍርድ ቤት ያስፈጽማል፣አፈጻጸሙን እንዳት መቃወም እና ቅሬታ ማቅረብ ይቻላል የሚለ መሰረታዊ የጸና የግልግል ስምምነት ጉዲዮች በግልጽ ያልያዖ በመሆኑ የግልግል ስምምነቱ ከመጀመሪያዉ ፈራሽ እና ተፈጻሚነት የላለዉ ነዉ በሚል ተከራክረዋል።
የስር ፍርድ ቤት መዛገብ አስቀርበን እንደተመለከትነዉ የግልግል ስምምነት የሚገኝበት ዋናዉ ዉል የተፈረመዉ በቀን 25/10/2004ዓ/ም (እ.ኤ.አ ጁላይ 12/2012) ሆኖ ዉለ የተደረገዉም በአሁን ተጠሪና በአሁን 1ኛ አመልካች መካከል ሆኖ የአሁን ተጠሪ ከአዱስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዘት(ቀባት) የምድር ባቡር ፕሮጀክት ለመገንባት ለፕሮጀክቱ ኢፒሲ ዉል በማድረግ የአሰሪዉ ተወካይ በመሆን የማማከር አግልግልት ለመስጠት ዉል ማድረጉን ተከትል የአሁን 1ኛ አመልካች የማማከር ስራዉን እንዱሰራ የፈጸሙት ንኡስ የማማከር አገልግልት ዉል ነዉ።
ይህ ዉል በእንግሉዛኛ ቋንቋ የተዖጋጀ ሲሆን በዘህ ዉል በአንቀጽ 9 ስር ስለግልግል ዲኝነት የሚከተለዉን ስምምነት አድርገዋል፡- 9. ARBITRATION 9.1. ARBITRATION PROCEDURES The parties shall make every attempt to resolve in an amicable way any dispute concerning the interpretation of this agreement.
Any dispute arising between the consultant and the Sub-Consultant in connection with or arising out of this agreement, which can not be resolved between them in accordance with the terms of this Agreement, shall be finally settled by arbitration in accordance with the rules stated in schedule 1.
Sechedule 1 Project and Agreement Particulars Clause 9. ARBITRATION - Clause 9.1 ARBITRATION Any arbitration proceedings in accordance with clause 9.1 shall be in accordance with the rules of the International Chambers of Commerce. የእነዘህ ድንጋጌዎች የአማርኛ ትርጉሞ የሚከተለዉ ነዉ፡- 9. የግልግል ዲኝነት - 9.1 የግልግል አካሄድ የዘህ ስምምነት አተረጓጎም በተመለከተ ማንኛዉም አለመግባባት ቢኖር ተዋዋይ ወገኖች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁለንም ጥረቶች ያደርጋለ።
ከዘህ ስምምነት ጋር በተያያዖ ወይም በተነሳ በአማካሪዉና በንኡስ አማካሪዉ መካከል የተከሰተ ማንኛዉም አለመግባባት በዘህ ስምምነት በተመለከተዉ መሰረት በተዋዋይ ወገኖች መፈታት ካልቻለ በመጨረሻም በዘህ ዉል ሰንጠረዣ 1 ስር በተመለከተዉ ደንብ መሰረት በግልግል ዲኝነት እልባት እንዱያገኝ ይደረጋል።
ሰንጠረዣ 1 ፕሮጀክትና የስምምነቱ ዋና ጉዲዮች አንቀጽ (Clause) 9. የግልግል ዲኝነት Clause -አንቀጽ (Clause) 9.1 የግልግል ዲኝነት ማንኛዉም በአንቀጽ 9.1 መሰረት የሚከናወን የግልግል ዲኝነት አካሄድ በዓለም ዓቀፈ የንግድ ምክር ቤት ደንብ መሰረት እንዱከናወን ይደረጋል የሚል ነዉ።
ከላይ በተመለከተዉ መሰረት 1ኛ አመልካች እና ተጠሪ ባደረጉት ስምምነት መሰረት የስምምነታቸዉን አተረጓጎም በተመለከተ የሚነሳ አለመግባባት በራሳቸዉ በመነጋገር ለመፍታት እንዱሁም ከዘህ ስምምነት ጋር በተያያዖ ወይም በተነሳ ማንኛዉንም አለመግባባት ቢከሰትና ሁለቱም ወገኖች በመነጋጋር መፍታት ካልቻለ በግልግል ዲኝነት እልባት እንዱያገኝ ለማድረግ ተስማምተዋል። ሆኖም የመረጡት የግልግል ዲኝነት ተቋማዊ ህልዉና ከላለዉ ገላጋይ ዲኛ (Ad hoc Arbitration) እና በተቋም ደረጃ ከተደራጀ የግልግል ዲኝነት አካል (Institutional Arbitration /Administered Arbitration) የትኛዉን እንደመረጡ በግልግል ስምምነታቸዉ(Arbitration Clause) ላይ ስም በመጥቀስ በግልጽ አላመለከቱም። ከላይ እንደተመለከተዉ ተቋማዊ ህልዉና የላለዉ ገላጋይ ዲኛ ሲመረጥና በተቋም ደረጃ የተደራጀ የግልግል ዲኝነት አካል ሲመረጥ የግልግል ዲኝነት ስምምነት ይዖት መሰረታዊ ልዩነት አለዉ።
ከዘህ አንጻር ግራ ቀኝ ስለግልግል ዲኝነት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት የተስማሙት ምን ያመላክታል የሚለዉን እንደመረመርነዉ በዉለ ሰንጠረዣ 1 ስር ባለዉ አንቀጽ 9.1 ስር "ማንኛዉም በአንቀጽ 9.1 መሰረት የሚከናወን የግልግል ዲኝነት አካሄድ በዓለም ዓቀፈ የንግድ ምክር ቤት ደንብ መሰረት እንዱከናወን ይደረጋል።" በሚል የተገለጸዉን ማጤን ጠቃሚ ይሆናል።
ተሻሽል ከየካቲት 22 ቀን 2009 ዓ/ም (እ.ኤ.አ. ከማርቻ 01 ቀን 2017) ጀምሮ ተፈጻሚ በሆነዉ በዓለም ዓቀፈ የንግድ ምክር ቤት የግልግል ዲኝነት ደንብ (International Chamber of Commerce (ICC) Arbitration Rules) አንቀጽ 6/2 ስር የሚከተለዉ ተደንግጎ ይገኛል።
ARTICLE 6- Effect of the Arbitration Agreement 2. By agreeing to arbitration under the Rules, the parties have accepted that the arbitration shall be administered by the court. ይህም ወደ አማርኛ ሲለወጥ ፡- ተዋዋይ ወገኖች የግልግል ዲኝነቱ በዘህ ደንብ መሰረት እንዱከናወን ሲስማሙ የግልግል ዲኝነቱ በዓለም አቀፈ የንግድ ምክር ቤት ስር በሚገኘዉ ነጻ በሆነዉ የዓለም ዓቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት (The International Court of Arbitration of the International Chamber of Commerce) እንዱመራ(እንዱተዲደር) እንደፈቀደ ይቆጠራል እንደማለት ነዉ።
ይህ የደንቡ ድንጋጌ ከላይ ከተጠቀሰዉ የዉለ ሰንጠረዣ 1 አንቀጽ 9.1 ድንጋጌ ጋር ተጣምሮ ሲነበብ ግራ ቀኝ በግልግል ስምምነታቸዉ የመረጡት አማራጭ ተቋማዊ ህልዉና የላለዉ ገላጋይ ዲኛ (Ad hoc Arbitration) ሳይሆን በተቋም ደረጃ የተደራጀ የግልግል ዲኝነት አካል (Institutional Arbitration /Administered Arbitration) መሆኑን የሚያሳ ነዉ። ይህም አካል በዓለም ዓቀፍ የግልግል ዲኝነት ፍርድ ቤት (The International Court of Arbitration of the International Chamber of Commerce) አደራጅነት (አስተዲዲሪነት) በዘህ ተቋም የግልግል ዲኝነት ደንብ በተለይም በአንቀጽ 12 እና 13 በተደነገገዉ መሰረት የሚሰየም/የሚሾም/ ገላጋይ ዲኛ/ዳኞች ይዜ የሚቋቋም የግልግል ዲኝነት አካል(Arbitral Tribunal) ነዉ።
የገላጋይ ዳኞች አሰያየም(አሿሿም) እና ብዙታቸዉ(Nomination/Appointment and number/s of Arbitrator/s) ፣ የግልግል ዲኝነት አካለ መቀመጫ(Place of the Arbitration)፣ የግልግል ዲኝነቱ የሚመራበት ደንብ (Rules Governing the Proceedings)፣ የግልግል ዲኝነቱ የሚከናወንበት ቋንቋ(Language of the Arbitration) ፣ፍሬ ነገሩ ላይ ተፈጻሚነት ስለሚኖረዉ ሕግ (Applicable Rules of law) እና የመሳሳለትን ጉዲዮች በተመለተ በግራ ቀኝ በተፈጸመ የግልግል ዲኝነት ስምምነት ላይ በግለጽ ስምምነት ተደርጎ ባይገለጽም ግራ ቀኝ በስምምነታቸዉ ላይ ተጠቃሹ የግልግል ዲኝነት ደንብ ተፈጻሚ እንዱሆን እስከተስማሙ ድረስ እነዘህ ጉዲዮች የሚወሰኑት በደንቡ አንቀጽ 12፣13 እና 18-21 በዛርዛር በተመለከተዉ መሰረት በግልግል ዲኝነት ፍርድ ቤት መሆኑን ከደንቡ ይዖት መረዲት ችለናል።
ስለሆነም አመልካቾች እነዘህ ጉዲዮች በግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ላይ ባለመጠቀሳቸዉ ምክንያት የግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ፈራሽ ነዉ በሚል ያቀረቡት ክርክር በዉላቸዉ ሰንጠረዣ 1 ስር ባለዉ አንቀጽ 9.1 ስር "ማንኛዉም በአንቀጽ 9.1 መሰረት የሚከናወን የግልግል ዲኝነት አካሄድ በዓለም ዓቀፈ የንግድ ምክር ቤት ደንብ መሰረት ይከናወናል" በሚል የተስማሙትንና የዘህን ደንብ አንቀጽ 6/2ን ያላገናዖበ ክርክር መሆኑን አረጋግጠናል። ይህም ክርክር የግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ዋጋ የለዉም (ፈራሽ) ነዉ በሚል የቀረበ በመሆኑና እንዱህ አይነት ክርክር በግልግል ዲኝነት አካለ ታይቶ እንዱወሰን የሚፈቅደዉ The rule of Competence- Competence ተብል የሚታወቀዉ መርህ በአገራችን በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3330/3 ስር እንደተመለከተዉ እዉቅና ስለላለዉ የግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ፈራሽ ነዉ ተብል የቀረበዉ ክርክር /validity of arbitration agreement) ሉወሰን የሚገባዉ በመደበኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ከዘህ አንጻር የቀረበዉን ክርክር ሰምቶ ተንትኖ ባይወስንም የግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ፈራሽ እንዲልሆነ በመቁጠር የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም።
በተጨማሪም አመልካቾች ለክሱ መነሻ የሆነዉን ጉዲይ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን (private international law) የሚመለከት በመሆኑ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11(2/ሀ) መሰረት ጉዲዩን መዲኘት ያለበት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነዉ በሚል ተከራክረዋል። ተጠሪ በበኩለ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ አለመግባባት ቢፈጠር በግልግል ዲኝነት ታይቶ እልባት እንዱያገኝ ስለተስማማንና እንዱህ አይነት ስምምነት እንዲናደርግ የሚከለክል ሕግ ስለላለ ጉዲዩ መታየት ያለበት በግልግል ዲኝነት አካል እንጂ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን እንደሚመለከት ጉዲይ ተቆጥሮ ጉዲዩን መዲኘት ያለበት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነዉ ልባል አይገባም ሲል ተከራክሯል።
ከዘህ አንጻር የቀረበዉም ክርክር እንደተመረመረዉ በግልግል ዲኝነት ሉታዩ የሚችለ ጉዲዮችን (Arbitrability) በሚመለከት በአገራችን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 315 (2 እና 3) ስር እንደተደነገገዉ በግልግል ዲኝነት ሉዲኙ የማይችለ ጉዲዮች ናቸዉ ተብል በሕግ በግልጽ ከተደነገገዉ እና ከአስተዲደር ዉልች ጋር ከተያያዖዉ ዉጭ የሆኑ ሕጋዊ ተግባራትን መነሻ ያደረጉ አለመግባባቶች በግልግል ዲኝነት ታይተዉ እልባት እንዱያገኙ ለማድረግ ማናቸዉም ችልታ ያላቸዉ ተዋዋይ ወገኖች የመዋዋል ነጻነታቸዉን በመጠቀም የግልግል ዲኝነት ስምምነት መዋዋል እንደሚችለ በግልጽ ተደንግጓል። በአገራችን የዉል ሕግ መሰረት የሕጉን አግባብ ተከትለዉ የተቋቋሙ ዉልች በቋቋሟቸዉ ሰዎች ላይ መብትና ግዳታን ስለሚጥለ እንደ ሕግ ያህል ተፈጻሚነት እንዲላቸዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1731/1 ስር ተደንግጓል።
እንዱሁም ተዋዋይ ወገኖች ሕግ ከወሰናቸዉና ከከለከላቸዉ ነገሮች በቀር የሚዋዋለበትን ጉዲይ እንደመሰላቸዉ የመወሰን መብት እንዲላቸዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1711 ስር በግልጽ ተደንግጓል።
በተያዖዉ ጉዲይ ላይ በ1ኛ አመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገዉ የግልግል ስምምነት ከማማከር ንኡስ ዉለ የሚነጭ እና ከማማከር ዉለ ጋር የተያያዖ የስምምነት አተረጓጎም መነሻ ያደረገ አለመግባባት(ክርክር) ጭምር በግልግል ዲኝነት እንዱታይና እልባት እንዱያገኝ ስምምነት እንዲደረጉ የዉለ አንቀጽ 9.1 በግልጽ ያሳያል። ምንም አንኳን የግለሰብ ዓለም ዓቀፍ ሕግ ጉዲይ የሚመለከቱ ክርክሮችን ተቀብል በመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ስልጣን እንዱዲኝ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11(2/ሀ) መሰረት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰልጣን የተሰጠዉ ቢሆንም የግለሰብ ዓለም ዓቀፍ ሕግ ጉዲይ የሚመለከቱ ክርክሮች በግልግል ዲኝነት ሉታዩ አይገባም ተብል በአገራችን ሕጎች የተጣለ ክልከላ የለም።
ክስ የቀረበበት ጉዲይም ከአስተዲደር ዉል ጋር የተያያዖ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 315/2 ስር የተመለከተዉ ክልከላ ለዘህ ጉዲይ ተፈጻሚነነት ያለዉ አይደለም። ስለሆነም አመልካቾች ጉዲዩ የግለሰብ ዓለም ዓቀፍ ሕግን የሚመለከት በመሆኑ በግልግል ዲኝነት ላታይ አይገባም በሚል ያቀረቡት ክርክር የሕግ መሰረት ያለዉ ባለመሆኑ አልተቀበልንም።
ሲጠቃለል የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግልግል ዲኝነት ስምምነቱን መሰረት በማድረግ ጉዲዩን የመዲኘት ስልጣን የለኝም ሲል በመወሰኑና ይህንን ዉሳኔ በመቃወም አመልካቾች ያቀረቡትን ይግባኝ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በትእዙዛ በመሰረዘ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም። ስለሆነም ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 18/11/2010 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 27/02/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዙዛ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል።
ግራ ቀኝ በዘህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
የዘህ የፍርድ ዉሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ።
ዉሳኔዉ ይታተም ዖንድ ለሚመለከተዉ የፍርድ ቤቱ ክፍል ይተላለፍ።
በትእዙዛ የቀረበዉ መዛገብ ይመለስ። መዛገቡ ተዖግቷል ፤ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.