No summary available.
ህዲር 28 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተኽሉት ይመሰል 2. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 3. ቀነዓ ቂጣታ 4. ተሾመ ሽፈራዉ 5. ፀሐይ መንክር አመልካች፡ ……ዲሽን ባንክ አ.ማ - ነ/ፈ አለላ በሪሁን ቀረቡ ተጠሪ፡ ………...ሪቼል ተስፊዬ ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር - አልቀረቡም።
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ሁኖ ሲከራከሩ ነበር። ይህ ጉዲይ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.202150 በ06/07/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን አመልካች) ባቀረበዉ ክስ በግራ ቀኝ መካከል በተደረገዉ የቤት ኪራይ ዉል የቤቱን ኪራይ ከቅጣት፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በድምሩ 179,617.24 እንዱከፍለን እና ቤቱን እንዱያስረክበን በማለት ከሷል።
በዘህ ክስ ላይ በግራ ቀኝ መካከል ጥቅምት 9 ቀን 2008 ዓ.ም በተደረገዉ የቤት ኪራይ ዉል የቤቱን ኪራይ የከፈልን ስለሆነ የቀረበዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን በመመርመር በግራ ቀኛቸዉ መካከል በተደረገዉ የኪራይ ዉል በመካከላቸዉ ያለመግባባት ቢፈጠር ጉዲያቸዉን በእርቅ ወይም በግልግል ዲኛ ለመፍታት የተስማሙ በመሆኑ፣ ግራ ቀኛቸዉ አለመግባባታቸዉን በግልግል ዲኛ ከመፍታት በስተቀር ፍ/ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለዉም በማለት ትዔዙዛ ሰጥቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበዉን ይግባኝ ዉድቅ በማድረግ የሥር ትዔዙዛ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዘህ ትዔዙዛ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክርክር በተደረገዉ የቤት ኪራይ ዉል የቤቱን ኪራይ እንደከፈለ ከመከራከር ዉጪ ስለግልግል ዲኝነት በሁለቱም ወገኖች አልተነሳም። ስለግልግል ዲኝነት በግራ ቀኛችን ባልተነሳበት እና ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸዉ በፍ/ቤት መታየቱ ከማናቸዉም ወገን ተቃዉሞ ባልቀረበበት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ደግሞ ተከራካሪ ወገኖች በዛርዛር ባላቀረቡት ወይም በግልጽ ባላመለከቱት ጉዲይ ላይ ፍርድ መስጠት እንደማይችለ በሕግ በግልጽ ተደንግጎ እያለ የሥር ፍ/ቤቶች ጉዲዩ በግልግል ዲኝነት ከሚታይ በስተቀር ፍ/ቤቱ የማየት ስልጣን የለዉም በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልን እና በክሳችን መሰረት እንዱወሰንልን፣ በዘህ ምክንያት የደረሰብን ኪሳራ እንዱወሰንልን በማለት በዛርዛር ተከራክሯል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በተደረገዉ ስምምነት አለመግባባት ቢፈጠር በእርቅ ወይም በግልግል ዲኛ ለመፍታት የተስማሙ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለዉም በማለት በራሱ ተነሳሽነት የሰጠዉ ዉሳኔ በሕጉ አግባብ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ያዖዖ ቢሆንም ተጠሪ በአዱስ ዖመን ጋዚጣ ጥሪ ቢደረግለትም ባለመቅረቡ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት ይህን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ አመልካች እና ተጠሪ እ.ኤ.አ.ሚያዘያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም የቤት ኪራይ ዉል ማድረጋቸዉ የተካደ አይደለም። የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክስ በዘህ ዉል መሰረት ተጠሪ ያልከፈለዉን የቤት ኪራይ ዋጋ እና ከዘህ ጋር ተያያዣነት ያለዉን ክፍያዎች ተጠሪ እንዱከፍል እንዱወሰንልኝ የሚል ነዉ። የአሁን ተጠሪ በበኩለ በዉለ መሰረት የሚፈለግበትን የኪራይ ክፍያ መክፈለን እና ለአመልካች መክፈል ያለበት ክፍያ እንደላለበት በመግለጽ ተከራክሯል። በግራ ቀኛቸዉ መካከል የተደረገዉ የቤት ኪራይ ዉል ሕግ መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1731 (1) እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2945 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያስገነዛባለ። በመሆኑም ግራ ቀኛቸዉ በዉለ የተመለከተዉን መብት የመጠየቅና የመጠቀም፣ ግዳታቸዉን ደግሞ የመወጣት ኃላፉነት አለባቸዉ።
በዘህ አግባብ በግራ ቀኛቸዉ መካከል አለመግባባት የተከሰተ እንደሆነ ዉለ ምን ይላል?
No topics extracted.
የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ። የግራ ቀኛቸዉ የቤት ኪራይ ዉል አንቀጽ አምስት አለመግባባት የተከሰተ እንደሆነ አለመግባባቱ የሚፈታበትን አግባብ ይገልጻል። በዘህ መሰረት በግራ ቀኛቸዉ መካከል አለመግባባት የተከሰተ እንደሆነ በዉይይት ለመፍታት ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸዉ፣ ይህ ካልሆነ ግራ ቀኛቸዉ አንድ አንድ ሽማግላ በመምረጥ ለመስማማት ጥረት ያደርጋለ፣ ልዩነቱ በዘህ መልክ የማያልቅ ከሆነ ግራ ቀኛቸዉ በየበኩላቸዉ ሽማግላ በመምረጥ እና እንደ አስፈላጊነቱ የመሃል ዲኛ ተመርጦ በግልግል ዳኞች ጉዲያቸዉ ታይቶ እንደሚወሰን ያመለክታል። በዘህ አግባብ መስማማት ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.315 እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3325 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ተቀባይነት ያለዉ እንደሆነ ማየት ይቻላል። ይህ የዉል ድንጋጌ እንደሚያመለክተዉ ግራ ቀኛቸዉ ከቤት ኪራይ ዉለ ጋር በተያያዖ አለመግባባት የተፈጠረ እንደሆነ ጉዲዩ በመደበኛ ፍ/ቤት ቀጥታ ክስ ቀርቦ የሚታይ ሳይሆን ግራ ቀኛቸዉ በተስማሙበት የሙግት መፍቻ ዖዳን ተከትል በግልግል ዲኝነት ጉባኤ መሆን እንዲለበት ነዉ፣ ይህም ደግሞ መጀመሪያ በስምምነት ካልሆነ በግልግል ዳኞች ታይቶ ዉሳኔ ላሰጥበት የሚገባዉ ጉዲይ ነዉ። ይህ ማለት በመደበኛ ፍ/ቤት በዘህ ጉዲይ ቀጥታ ክስ የማይቀርብ መሆኑን ነዉ። ግራ ቀኛቸዉ ክርክሩን ለማየት ስልጣን ያለዉን አካል በስምምነተታቸዉ እስከወሰኑ ድረስ፣ ዉላቸዉን እስካላሻሻለ ድረስ ይህን የዉል ድንጋጌ ተግባራዊ በማድረግ ጉዲዩ በግልግል ዳኞች እንዱታይ ከሚደረግ በቀር የመደበኛ ፍ/ቤት ስልጣን እንዲላለዉ ግልጽ ነዉ። የአሁን አመልካች የቤት ኪራይ ዉለን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ተጠሪ የኪራይ ክፍያ እንዱፈጽምለት ዲኝነት እስከጠየቀ ድረስ፣ አለመግባባትን ለመፍታት በዉለ የተመለከተዉ ድንጋጌ ደግሞ አይመለከተኝም ተፈጻሚነት የለዉም በማለት ከፍል የዉለን ድንጋጌ መቀበልና ከፍለን አለመቀበል የሚቻልበት ሁኔታ የለም። ይህ ክስ በቤት ኪራይ ዉለ መሰረት ያልተከፈለዉ የኪራይ ክፍያ እንዱፈጸም እና ቤቱን እንዱያስረክብ ዲኝነት የተጠየቀበት በመሆኑ፣ መታየትና ተፈጻሚ መደረግ ያለበት የዉለ ከፍል ሳይሆን ሙለ ይዖቱ መሆን አለበት።
በዘህ መሰረት የአሁን አመልካች ዉለን መሰረት በማድረግ የቤት ኪራይ ዉል እንዱከፈለዉ ዲኝነት የጠየቀ በመሆኑ፣ የዉለ ሙለ ይዖት ሲታይ ዉለ አለመግባባት እንዳት መፈታት እንዲለበት የራሱን መፍቻ ዖዳ የዖረገ በመሆኑ በዙ አግባብ መታየት ይገባል። አመልካች የቤት ኪራይ ዉለን እንደማስረጃ አያይዜ አቅርቦ እያለ የሥር ፍ/ቤት የኪራይ መጠን ወይም ተመን የሚመለከተዉን አንቀጽ እንጂ የሙግት አፈታት ዖዳ የሚመለከተዉ ድንጋጌ ማንሳት የለበትም በማለት የሚያቀርበዉ ክርክር ከፍ ሲል የተመለከተዉን ዉል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ሕግ ነዉ የሚለዉን የህግ ድንጋጌ የሚቃረን ነዉ። በግራ ቀኛቸዉ መካከል የተደረገዉ የቤት ኪራይ ዉል ሕግ እስከሆነ ድረስ ፍ/ቤቱ ይህን ዉል መሰረት በማድረግ የቀረበዉን ክስ እልባት ለመስጠት የዉለን ሙለ ይዖት መፈተሹ አስፈላጊ በመሆኑ በግራ ቀኛቸዉ መካከል አለመግባባት ሲከሰት ምን መሆን እንዲለበት የተደረነገገዉን አንቀጽ ማየቱ ተገቢ ነዉ።
ስለሆነም ግራ ቀኛቸዉ የቤት ኪራይ ዉለን መሰረት በማድረግ እስከተከራከሩ ድረስ ስለግልግል የሚጠቅሰዉ የወለ ድንጋጌ የማይታይበት ምክንያት የለም። ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ረገድ ጉዲያችን በፍ/ቤት ሳይሆን በግልግል ዲኝነት መታየት አለበት በማለት ያቀረቡት ክርክር ባይኖርም የዉለ አንቀጽ ይኼንን እስካመለከተ ድረስ ፍ/ቤቱ በራሱ ጊዚ የማያነሳበት ምክንያት የለም። ከዘህም በላይ ግራ ቀኛዉ ክርክራቸዉን የሚያይ አካል ስልጣን የወሰኑ በመሆናቸዉ፣ ይህ ደግሞ የስረ ነገር ስልጣን የሚመለከት በመሆኑ፣ በዘህ ረገድ ተከራካሪ ወገኖች በያነሱትም ወይም የቀረበ መቃወሚያ ባይኖርም ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.9 (2)፣ 244 (2፣ ሀ) እና 245 (2) መሰረት በራሱ ተነሳሽነት በመንሳት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ መስጠት ይገባዋል። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት በራሱ ተነሳሸነት ግራ ቀኛቸዉ መካከል ዉለን መነሻ ያደረገ አለመግባባት ሲከሰት በግልግል ዲኝነት ከምፈቱት በስተቀር ፍ/ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለዉም በማለት የሰጡት ዉሳኔ በሕጉ አግባብ ነዉ ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች ግራ ቀኛቸዉ አለመግባባትን በግልግል ዲኝነት ጉባኤ ለመፍታት በተስማሙት መሰረት ከሚታይ በስተቀር ፍ/ቤት ቀጥታ ክስ ተቀብል ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለዉም በማለት የሰጡት ዉሳኔ በሕጉ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት ስለማይቻል የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.202150 በ6/7/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ጸንቷል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል።