No summary available.
ጥር 24 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡-
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የሐራጅ ሽያጭ እንዱፈርስና እንዱታገድ የቀረበ ክስን መነሻ ያደረገ ክርክር ሲሆን፣ ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.177079 ግንቦት 8 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት የአሁን አመልካች ያቀረበዉን የሰበር አቤቱታ ምርመሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ በፋዳራል መጀመሪያ ደራጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪዎች የሥር ከሳሾች፣ የአሁን አመልካች የሥር 1ኛ ተከሳሽ፣ በዘህ ችልት የክርክሩ ተከፊይ ያልሆነዉ የሥር 2ኛ ተከሳሽ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሁኖ ሲከራከሩ የነበረ ሲሆኑ፤ ከሳሾች ባቀረቡት ክስ ከሳሾች ባልና ሚስት መሆናቸዉን በመግለጽ በ1ኛ ከሳሽ የይሳኮር ኮንስትራክሽን ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ሲሆን፣ 1ኛ ከሳሽ በድርጅቱ አማካይነት በባላ ዜን ዉስጥ የጎሮ ሆስፒታል እና በአርሲ ዜን ዉስጥ ቀርሳ ሆስፒታል ለመገንባት ስምምነት ያደረገ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ ለዘህ ዉል አፈጻጸም የቅድመ ክፍያ ዋስትና ብር 11,600,000 ሰጥቷል። 2ኛ ተከሳሽ ለዘህ ዋስትና ሲባል በ2ኛ ከሳሽ ስም ተመዛግቦ የሚገኝ ሁለት ካርታ፣ በ1ኛ ከሳሽ ስም ተመዛግቦ የሚገኙ ሶስት መኪኖች በመያዡነት ይዝል። 2ኛ ተከሳሽ የግንባታ ዉለን አቋርጧል።
ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር የተደረገዉ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ዉል ባለመታደሱ እና ጊዚዉ በማለቁ ቀሪ ሆኗል። ይህ ሆኖ ሳለ ተከሳሾች በፍ/ቤት ሲያደርጉ የነበረዉን ክርክር አቋርጠዉ መዛገቡን በማዖጋት የከሳሾችን ንብረት በሕገ ወጥ መንገድ ሸጠዉ፣ ልልቹን ለመሸጥ እየተንቀሳቀሱ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.445 መሰረት ሽያጩ እንዱፈርስ ወይም እንዱታገድ ወይም በ1ኛ ከሳሽ እና በ2ኛ ተከሳሽ አማካይነት እንዱጣራ እና ለማቀናነስ ወይም ለማቻቻያ እንዱዉል በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ይህን ክስ በተመለከተ የሥር 1ኛ ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ ፍ/ቤቱ ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን የለዉም፣ በተመሳሳይ ጉዲይ ክስ የቀረበ ስለሆነ ክሱ ድጋሚ ላቀርብ አይችልም፣ ተከሳሽ በመያዡ የያዙቸዉን ንብረቶች ዔዲዉ ካልተከፈለ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በሐራጅ በመሸጥና የባለቤትነት መብቱን በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 3 መሰረት ማዖዋወር ይችላል በማለት ተከራክሯል። 2ኛ ተከሳሽ በበኩለ ባቀረበዉ መልስ የተለያዩ መከራከሪያ ነጥቦችን በማቅረብ፣ ተከሳሽ በሐራጅ ሽያጭ ዉስጥ ስላልተሳተፍን ክሱ ስለማይመለከተን በነጻ እንዱንሰናበት በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ ፍ/ቤቱ በሰጠዉ ብይን ከሳሽ ያቀረበዉ ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.445 መሰረት ጨረታዉ በአግባቡ እየተካሄደ አይደለም የሚል ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት የፍ/ቤቱ ስልጣን ነዉ፣ ይህ ጉዲይ በድጋሚ የቀረበ ነዉ በማለት የቀረበዉ መቃወሚያ ተቀባይነት የለዉም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዉን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።
የሥር 1ኛ ተከሳሽ በዘህ ብይን ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ትዔዙዖ በመቃወም ለማለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ አራት ገጽ አቤቱታ አቅርቧል።
የአቤቱታዉም ይዖት፡--የአሁን ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ የመያዡ ዉል ግምቱ ብር 11,600,000 ስለሆነ በዘህ ግምት መሰረት ተገቢዉን የዲኝነት ክፍያ ፈጽመዉ ክስ ማቅረብ ሲገባቸዉ፣ በዘህ አግባብ ዲኝነት ሳይከፈል ፊይል መከፈቱ ከፍተኛ የሕግ ስህተት ነዉ። ለክሱ መመስረት ምክንያት የሆነዉ የመያዡ ዉል ግምት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስልጣን ነዉ።
ተጠሪዎች በተመሳሳይ ጉዲይ የተለያዩ ክሶችን አቅርበዉ ሶስት መዙግብቶችን አስከፍተዉ ክርክር ላይ ያለ ሆኖ ሳለ ጉዲዩ በድጋሚ የቀረበ አይደለም በማለት የተሰጠዉ ብይን እንዱታረም በማለት በዛርዛር ቅሬታዉን አቅርቧል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታዉ የሚጣራ ጉዲይ አለዉ በማለት የስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ በታዖዖዉ መሰረት ሐምል 4 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ ሶስት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዖት፡--አመልካች የሥር ፍ/ቤት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ የሰጠዉን ብይን በመቃወም በመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.320 /3/ መሰረት በሥረ ነገሩ ላይ ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት በዘህ ብይን ላይ ይግባኝም ሆነ የሰበር አቤቱታ ለማቅረብ ስለማይቻል የቀረበዉ አቤቱታ ከሥነ ሥርዓት ዉጭ ነዉ። አመልካች የዲኝነት ክፍያን በተመለከተ በሥር ፍ/ቤት ያቀረበዉ መቃወሚያ በላለበት በክርክር መሐል ሉያቀርብ አይችልም። ተጠሪ ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዲኝነት የተጠሪዎችን ንብረት ያለአግባብ ለመሸጥ የወጣዉ ጨረታ ትክክል ባለመሆኑ ተገቢ ዲኝነት ተከፍል ክሱ ቀርቧል። ተጠሪዎች የብር 11.6 ሚሉዮን ዲኝነት ወይም መብት ለማስከበር ዲኝነት አልጠየቁም። አመልካች በተመሳሳይ ጉዲይ ክሶችን አቀርቧል ያለዉን በተመለከተ እነዘህ ክሶች በባህሪያቸዉና በጭብጥም ደረጃ የተለያዩና የማይገናኙ ስለሆኑ የቀረበዉ አቤቱታ ተቀባይነት የለዉም። የሥር ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ስላለዉ አመልካች ያቀረበዉ አቤቱታ ተሰርዜ የሥር ዉሳኔ እንዱጸናልን በማለት ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የመልስ መልስ አናቀርብም በማለቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር ለሰበር አቤቱታዉ መነሻ ከሆነዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም የአመልካች ባንክ በመያዡ የያዙቸዉን ንብረቶች ለመሸጥ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ለሚፈጽመዉ የሐራጅ ሽያጭ መደበኛዉ ፍ/ቤት የማየት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? የሚለዉን ነጥብ እንደጭብጥ በመያዛ እንደሚከተለዉ መርምሮታል። መዛገቡን እንደመረመርነዉ የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ አመልካች በመያዡነት የያዙቸዉን ንብረቶች ያለአግባብ ከሕግ ዉጭ በሐራጅ ስለሸጠ እና ለመሸጥም እየተንቀሳቀሰ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.445 መሰረት ሽያጩ እንዱፈርስ ወይም እንዱታገድ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸዉን ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ማየት ይቻላል። የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክርክር ባንኩ በመያዡ የያዙቸዉን ንብረቶች በሐራጅ ለመሸጥ እና ለገዡም ባለቤትነቱን ለማዙወር ስልጣን እንዲለዉ እና ፍ/ቤቱም ጉዲዩን ለማየት ስልጣን እንደላለዉ በመግለጽ ተከራክሯል። ግራ ቀኛቸዉ የሚከራከሩበት ጉዲይ የአመልካች ባንክ በመያዡነት የያዙቸዉ ንብረቶች የሐራጅ ሽያጭ ጋር የተያያዖ መሆኑን የተካዲ አይደለም። ይህን የግራ ቀኛቸዉን ክርክር በተመለከተ አግባብነት ወይም ተፈጻሚነት ካለዉ ሕግ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምረነዋል።
እንደተመለከተዉ የአሁን አመልካች በዋስትና መያዡነት የያዙቸዉን የተጠሪዎችን የማይንቀሳቀስ እና ልዩ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን በሐራጅ ከመሸጥ ጋር የሚያያዛ መሆኑ ግልጽ ነዉ። በመሆኑም ለዘህ ጉዲይ አግባብነት ያለዉ ሕግ ‹‹በባንክ በመያዡ ስለተያዖ ንብረት የወጣ አዋጅ ቁጥር 97/90›› እንደሆነ የሚያከራከር ጉዲይ አይደለም። በዘህ አዋጅ መሰረት ባንክ በመያዡነት የያዙቸዉ ንብረቶች ለመሸጥ ያለዉ ስልጣን፣ ከዘህ ሽያጭ ጋር በተያያዖ መደበኛ ፍ/ቤት ያለዉ ስልጣን፣ በዘህ አዋጅ አግባብ ለተፈጸመ የሐራጅ ሽያጭ ጋር በተያያዖ በምን አግባብ ለመደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩ ላቀርብ እንደሚችል መታየት ያለባቸዉ ነጥቦች ናቸዉ።
የዘህን አዋጅ ዓላማ ከአዋጁ መግቢያ /preamble/ መገንዖብ የሚቻል ሲሆን፣ በመግቢያ ከተመለከቱት መካከል ባንኮች በመያዡ የያዘትን ንብረቶች ለመሸጥ መደበኛ ሥነ ሥርዓት ተክትል ለመደበኛ ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ለማስወሰንና ዉሳኔዉን ለማስፈጸም ረጅም ጊዚ በመዉሰደ፤ ባንኮች ገንዖብ አበድረዉ ወለድ በመሰብሰብ ገቢ የማግኘት ሥራቸዉ ላይ ከፍተኛ ተጽዔኖ በማሳደሩ፣ ባንኮች የሚሰጡትን ብድሮች በተቀላጠፈ መንገድ መሰብሰብ እንዱችለ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር አዋጁ ማስፈለጉን ያመለክታል። ከዘህም በላይ በአዋጁ አንቀጽ 3 እና 4 እንደተመለከተዉ ባንኮች በመያዡነት የያዘአቸዉን ንብረቶች ተፈላጊዉ ዔዲ ያልተከፈለ እንደሆነ በድንጋጌዎቹ የተመለከተዉን ሥርዓት ተከትል ንብረቶቹን በሐራጅ የመሸጥ እና ለገዡዉ ባለቤትነቱን የማዙወር እና ሁለት ጊዚ ሐራጅ ወጥቶ ያልተሸጠ እንደሆነ ንብረቱን በመያዡ ስምምነቱ ላይ በተመለከተዉ ግምት መዉሰድ እንደሚችለ እና ወደ ስሙ ለማዙወር ስልጣኑ የባንኮች እንደሆነ ማየት ይቻላል። ባንክ ይህን የሐራጅ ሽያጭ ሲያካሄድ እንደአግባብነቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.394--449 ተፈጻሚ ማድረግ እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 6 ሥር ተመልክቷል። ከዘህ ሁለ መገንዖብ እንደሚቻለዉ ባንክ ለዔዲ በመያዡ የያዖዉን ንብረት በሐራጅ በመሸጥ ዋናዉን ገንዖብ እና ወለድ ለመሰብሰብ ለሚያካሄደዉ የሐራጅ ሽያጭ ሂደት ጋር በተያያዖ ስልጣኑ የባንኩ መሆኑን እና መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ማየት እንደማይችል ነዉ።
መደበኛ ፍ/ቤት ባንክ ያካሄደዉ የሐራጅ ሽያጭ በአግባብ ነዉ ወይስ አይደለም? የሐራጅ ሽያጩ ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለትን ነጥቦች አይቶ ለመወሰን ስልጣን እንደላለዉ መገነዖብ ይቻላል። መደበኛ ፍ/ቤቶች እነዘህን ነጥቦች በማየት የሐራጅ ሽያጩ የተካሄደዉ በአግባብ ነዉ ወይስ አይደለም? በዘህ ምክንያት ሽያጩ ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም?
የሚለትን በመመርመር የሚወስኑ ከሆኑ ከላይ የተመለከተዉን የአዋጁን ዓላማ ሙለ በሙለ ዋጋ ሚያሳጣ እና የአዋጁንም ተፈጻሚነት የሚገድብ ይሆናል። በመሆኑም ሕግ አዉጭዉ ባንክ በመያዡ የያዖዉን ንብረት በሐራጅ በመሸጥ ያበደረዉን ገንዖብ መሰብሰብ እንዱችል በአዋጁ የዖረጋዉን ሥርዓት መደበኛ ፍ/ቤቶች በማክበር ተፈጻሚ ማድረግ ይገባቸዋል እንጂ አዋጁ ለባንክ የሰጠዉን ስልጣን በመንጠቅ ጉዲዩን የማየት ስልጣን አለን በማለት የአዋጁን ዓላማ ዋጋ ማሳጣት የለባቸዉም። ስለሆነም መደበኛ ፍ/ቤት አንድ ባለዔዲ የሐራጅ ሽያጭ ያለ አግባብ የተደረገ ስለሆነ እንዱፈርስልኝ ወይም እንዱታገድልኝ በማለት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.445 በመጥቀስ ያቀረበዉን ክስ በመቀበል ክርክር በማካሄድ አዋጁ የወጣበትን ዓላማ መና ማስቀረት የለበትም።
በልላ በኩል ባለዔዲዉ የሐራጅ ሽያጭ በአግባቡ አልተደረገም የሚል ከሆነ በዘህ ምክንያት የደረሰበትን ጉዲት ለይቶ ክስ ማቅረብ እንዲለበት አወጁ ያሳያል። የአዋጁ አንቀጽ 7 ስለባንክ ተጠያቂነት ሲደነግገዉ ‹‹ባንክ በዘህ አዋጅ አንቀጽ 6 የተጠቀሱትን አግባብ ያላቸዉን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ሽያጩን በመፈጸሙ በባለዔዲዉ ላይ ለሚደርሰዉ ጉዲት በኃላፉነት ተጠያቂ ይሆናል›› በማለት ይደነግጋል። የእንግሉዛኛዉ ቅጅ Liability of of the Bank በማለት <<The Bank shall be liable for any damage it causes to the debtor in the process of selling by auction in violation of the relevant provisions of the civil procedure code specified under Article 6 of this Proclamation>> በማለት ይደነግጋል። ከዘህ ድንጋጌ መገንዖብ እንደሚቻለዉ አንድ ባለዔዲ ከሐራጅ ሽያጭ ጋር በተያያዖ ጉዲዩን ለመደበኛ ፍ/ቤት ማቅረብ የሚችለዉ የሐራጅ ሽያጩ ያለ አግባብ ከሕግ ዉጭ የተደረገ ነዉ የሚል ከሆነ፣ በዘህ ምክንያት የደረሰበት ጉዲት ካለ አግባብነት ባለዉ ማስረጃ በማስደገፍ ክስ አቅርቦ ካሳ እንዱከፈለዉ ዲኝነት ከመጠየቅ ዉጭ የሐራጅ ሽያጩ እንዱፈርስ ወይም እንዱታገድለት የሚጠይቅበት የሕግ አግባብ የለም። በዘህ ድንጋጌ ደረሰብኝ የሚለዉን ካሳ አግባብነት ባለዉ ማስረጃ በማስደገፍ ስልጣን ላለዉ መደበኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ከመጠየቅ በስተቀር ሐራጁ እንዱፈርስ ክስ ማቅረብ አይችልም። በመሆኑም መደበኛ ፍ/ቤት በዘህ አዋጅ አግባብ የሚቀርብ ክስ የካሳን ጥያቄ የሚመለከት ካልሆነ በስተቀር ክሱን ተቀብል ግራ ቀኛቸዉን አከራከሮ ተገቢ ዉሳኔ ለመስጠት ስልጣን የለዉም።
ይህን አዋጅ መሰረት በማድረግ ባንክ ያካሄደዉ ሐራጅ እንዱፈርስ ወይም ለማከሄድ ያለዉ ሐራጅ እንዱታገድ የሚል ክስ የቀረበ እንደሆነ፣ ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሕ/ቁ.9 /1/ እና 231 መሰረት ክሱን ተቀባይነት የለዉም በማለት ለባለጉዲዩ መመለስ ይጠበቅበታል። ነገር ግን ፍ/ቤቱ ክሱን ተቀብልም ቢሆን ጉዲዩን ለማየት የሥረ ነገር ስልጣን የላለዉ በመሆኑ፣ በላለ ተከራከሪ ወገን መቃወሚያ ቢቀርብም ባይቀርብም፣ ፍ/ቤቱ ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን እንደላለዉ በተገነዖበ ጊዚ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.9(2) 244 /2/ /ሀ/ እና 245 /2/ መሰረት ክሱን ዉድቅ በማድረግ መዛገቡን መዛጋት አለበት። መደበኛ ፍ/ቤት በዘህ አግባብ የቀረበዉን ክስ ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ ስልጣን አለኝ በማለት ጉዲዩን ማየት የቀጠለ እንደሆነ ይግባኝ ልባልበት የሚል ጉዲይ ነዉ ወይስ በክርክሩ ላይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አንድ ላይ ይግባኝ የሚቀርበበት ጉዲይ ነዉ? የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ።
ከዘህ አንጻር የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.320 /1/ እና /2/ እንደሚያመለክተዉ ይግባኝ ልባልበት የሚችለዉ የመጨረሻ ፍርድ ባገኘ ጉዲይ ላይ እንደሆነ እና ጊዚያዊ አገልግልት ባለዉ በማናቸዉም ትዔዙዛ ላይ ከሥረ ነገሩ ፍርድ በፉት ይግባኝ ልባልበት እንደማይችል እና በክርክሩ የመጨረሻ ፍርድ እንደተሰጠ ከሥረ ነገሩ ጋር አጠቃል ይግባኝ ማቅረብ እንደሚቻል ነዉ። ነገር ግን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር እንደመረመረዉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.320 /2/ ድንጋጌ ከአዋጅ ቁጥር 97/90 አንጻር መተርጎም እንዲለበት ተገንዛቧል። በዘህ መሰረት ባንክ በመያዡ የያዖዉን ንብረት በሐራጅ ከመሸጥ ጋር በተያያዖ፣ የካሳ ጥያቄ ካልሆነ ሐራጁ እንዱፈርስ ወይም እንዱቆም ዲኝነት ለመጠየቅም ሆነ ፍ/ቤት ተቀብል ለማየት ስልጣን እንደላለዉ በግልጽ ተደንግጎ እያለ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለኝ በማለት ክርክሩን ማየት የሚቀጥል እንደሆነ፣ የአዋጁን ዓላማ ዋጋ የሚያሳጣዉ በሆኑ በሥረ ነገሩ ላይ ፍርድ እስከሚሰጥ ድረስ ሉጠበቅ የሚገባ ጉዲይ አይደለም። ስለሆነም መደበኛ ፍ/ቤት ሕግ አዉጭዉ አዋጅ ቁጥር 97/90 ያወጣበትን ዓላማ መና በሚስያቀር ሁኔታ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለኝ በማለት ክርክሩን ማየት የሚቀጥል እንደሆነ የአዋጁን ዓላማ ከማሳካት አንጻር ጊዚያዊ አገልግልት ያለዉ ትዔዙዛ ነዉና ይግባኝ ልባልበት አይችልም ልባል አይገባም።
መደበኛዉ ፍ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በግልጽ ከተደነገገዉ ዉጭ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለኝ በማለት ክርክሩን ማየት የሚቀጥል እንደሆነ ክርክሩ ከመፍጀዉ ጊዚ የተነሳ ባንክ ያበደረዉን ገንዖብ በመሰብሰብ በወለድ መልክ ማግኘት የሚገባዉን ገቢ የሚያሳጠዉ በመሆኑ እና ያበደረዉን ገንዖብ በተቀላጠፈ መንገድ እንዲይሰበስብ በማድረግ የባንኩን ጠቅም የሚጎዲ መሆኑ ግልጽ እስከሆነ ድረስ በዘህ ጉዲይ ይግባኝ የማይባልበት ምክንያት የለም። ስለዘህ ይህ ጉዲይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.320 /2/ ሥር የሚወድቅ አይሆንም። ነገር ግን በሥረ ነገሩ ላይ ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት ይግባኝ ልባልበት የሚችል ጉዲይ ነዉ ብለናል።
በዘህ አግባብ አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ አመልካች በመያዡ የያዙቸዉን ንብረቶች ያለአግባብ ከሕግ ዉጭ በመሸጡ እና ለመሸጥም እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ የሐራጅ ሽያጭ እንዱፈርስ ወይም እንዱታገድ የሚል ደኝነት የጠየቁ በመሆኑ፣ ከላይ በተመለከተዉ መሰረት ተጠሪዎች ይህን ክስ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የማቅረብ መብት የላቸዉም። ተጠሪዎች ይህን ክስ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ ክሱን ሳይቀበል ለተጠሪዎች መመለስ ነበረበት። ፍ/ቤቱ ክሱን መቀበል አልነበረበትም እንጂ ከተቀበለም አመልካች ባቀረበዉ መቃወሚያ መሰረት ጉዲዩን አከራከሮ ለመወሰን የሥረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ መዛገቡን መዛጋት ሲገባዉ ክርክሩን ለማየት ስልጣን አለኝ በማለት ክርክሩን ማየት መቀጠለ የሕግ ድጋፍ የለዉም። የሥር ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት የሥረ ነገር ስልጣን ሳይኖረዉ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለኝ በማለት ብይን በመስጠቱ፣ አመልካች ይህን ብይን በመቃወም ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማቅረብ ስለሚችል፣ ፍ/ቤቱ የሥር ፍ/ቤት ብይን በመሻር የሥር ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለዉም በማለት አስተካክል መወሰን ሲገባዉ ይህን ሳያደርግ በመቅረት የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት መወሰኑ የሕግ አግባብ የለዉም።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች ይህን ጉዲዩ አይቶ ለመወሰን የሥረ ነገር ስልጣን ሳይኖራቸዉ፣ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለን በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.233769 በ13/8/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ብይን እና ይህን ብይን በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.177079 ግንቦት 8 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
የአሁን ተጠሪዎች የአመልካች ባንክ ለዔዲ ማስከፈያነት በመያዡ የያዙቸዉን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት በሐራጅ ከመሸጥ ጋር በተያያዖ የሐራጅ ሽያጩ ያለ አግባብ በሕገ ወጥ መንገድ የተደረገ ነዉና እንዱፈርስልን ወይም እንዱታገድልን በማለት ያቀረቡትን ክስ የሥር መደበኛ ፍ/ቤት ክሱን ተቀብል ዉሳኔ ለመስጠት ስልጣን የለዉም። የሥር መደበኛ ፍ/ቤት በዘህ አግባብ የቀረበዉን ክስ ለማየት ስልጣን ሳይኖራዉ ስልጣን አለኝ በማለት ብይን የሰጣ በመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.320 /2/ ሥር የሚወድቅ ሳይሆን ከሥረ ነገሩ ፍርድ በፉት ይግባኝ ልባልበት የሚቻል ጉዲይ ነዉ ብለናል። የአሁን ተጠሪዎች የሐራጅ ሽያጩ ሂደት ያለ አግባብ ከሕግ ዉጭ በመደረጉ የደረሰባቸዉ ጉዲት ያለ እንደሆነ የአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 7 በሚደነግገዉ አግባብ በመደበኛ ፍ/ቤት ክስ በማቅረብ ካሳ ከመጠየቅ ይህ ዉሳኔ የሚከለክላቸዉ አይሆንም ብለናል።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
በ25/9/2008 ዓ.ም የተሰጠዉ እግድ በዘህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዲኖች ፊርማ አለበት
No topics extracted.