No summary available.
የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- አቶ ሰይድ ተስፊ - ጠበቃ ታምራት ቸርነት ቀርቧል ተጠሪ- ወ/ሮ ለባባ ጀማል ቀርቧል መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርደ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ውልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዜን አንፆኪያ ወረዲ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ የአመልካች እና የተጠሪ ጋብቻ በፍቺ እንዱፈርስ ከተወሰነ እና የሀብትና ንብረት ክፍፍል ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ከተጠሪ ጋር የጋራ እዲ ብር 380,000.00 እንዲለብን ተማምነን የድርሻዋን ብር 190,000.00 ለመክፈል የተስማማች ቢሆንም ልትከፍል ስላልቻለች በውለ መሰረት እንድትፈፅም ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቆ ተከራክሯል።
ተጠሪ በበኩሎ በሰጠችው መልስ ጉዲዩ በፍርድ ያለቀ ስለሆነ በድጋሚ ክስ ላቀርብብኝ አይገባም፤ በስር ፍርድ ቤት በክርክር ላይ እያለን በአመልካች በኩል ያለት ሽማግላዎች የንብረት ክፍፍለን በስምምነት እንጨርስ በማለት አሳስተው አስፈረሙኝ እንጂ በማላውቀው እዲ ልጠየቅ አይገባም፤ ስምምነቱ ህጋዊ ቢሆን ኖሮ በፍርድ ቤት ሉፀድቅ ይችል ነበረ፤
እንዱሁም የስምምነቱ ርዔስ የንብረት ክፍፍል መሆኑን ሲገልጽ ይዖቱ ደግሞ እዲ አለ የሚል ሆኖ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነው የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርባ ክሱ ውድቅ እንዱደረግላት ጠይቃለች።
ጉዲዩ የቀረበለት የስር ወረዲ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ጉዲዩ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው በማለት የአመልካችን አቤቱታ በብይን ውድቅ አድርጎታል።
በዘህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው አመልካች ይግባኙን ለዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ከዘህ በፉት ግራ ቀኙ ያደረጉትን ስምምነት መሰረት አድርጎ ቀረበ ክርክርም ሆነ የተሰጠ ውሳኔ የለም፤ የግልግል ስምምነቱም ለፍርድ ቤት ቀርቦ መጽደቅ አያስፈልገውም በማለት የወረዲ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሽሮ በፍሬ ጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ የመሰለውን እንዱወስን ጉዲዩን በፍ/ብ/ስ/ህ/ቁ. 341(1) መሰረት መልሶ ልኮለታል።
የወረዲ ፍርድ ቤቱም መዛገቡን እንደገና አንቀሳቅሶ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ግራ ቀኙ የጋራ እዲ አለባቸው ከተባለ መጠየቅ ያለበት ብድር አበድረናቸዋል የሚለው ወገን እንጂ አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ ሉያቀርብ አይችልም በማለት ወስኗል። አመልካች አሁንም በዘህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ጉዲዩን ያስቀርባል ብል ግራ ቀኙን ካራከረ በኋላ የወረዲ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ጉዲዩን በመለሰበት ነጥብ መሰረት አጣርቶ አልወሰነም፤ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ስምምነት ፀድቋል ወይስ አልፀደቀም ከሚለው ጭብጥ ወጥቶ በግልግል ስምምነቱ ላይ ግራ ቀኙ ያነሷቸውን ክርክሮች በአግባቡ አዲምጦና አከራክሮ የመሰለውን ውሳኔ ይስጥበት በማለት በድጋሚ ጉዲዩን መልሶ ልኮለታል።
ጉዲዩ በድጋሚ የተመለሰለት የወረዲ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረና የማጣሪ ምስክሮችን ጠርቶ ካደመጠ በኋላ በግራ ቀኙ መካል የተደረገው ስምምነት በሁለቱም ነፃ ፈቃድ የተፈፀመ ነው፤ በስምምነቱ መሰረት አመልካች ግዳታዋን ያልተወጣች በመሆኑ ብር 190,000.00 ትክፈል በማለት ወስኗል። ተጠሪ በበኩሎ በዘህ ውሳኔ ባለመስማማት ለዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብታቀርብም አቤቱታዋ ውድቅ ተደርጎባታል።
በመቀጠል የሰበር አቤቱታዋን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርባ ግራ ቀኙ ከተከራከሩበት በኋላ ሰበር ሰሚ ችልቱ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው የግልግል ስምምነት ፍርድ ቤት ቀርቦ ያልፀደቀ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት በወረዲው ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀናውን ውሳኔ በመሻር በተጠሪ ላይ የቀረበው ክስ ተገቢነት የለውም ሲል ወስኗል። ለዘህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ በአመልካች የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው የግልግል ስምምነት የፍርድ ቤት ክርክር ካበቃ በኋላ የተፈፀመ ሆኖ እያለ በፍርድ ቤት ካልፀደቀ ተቀባይነት የለውም ተብል መወሰኑ፤ ስምምነቱ በፍርድ ቤት ቀርቦ መጽደቅ እንደማይጠበቅበት የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ተጠሪ ይግባኝ ያላቀረበችና ይህንን ውሳኔ ባላሻረችበት ስምምነቱ አልፀደቀም ተብል ክሱ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገበዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለም ተጠሪ በተደረላት ጥሪ መሰረት ቀርባ በሰጠችዉ መልስ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበባቸው ነጥቦች በክልለ ፍርድ ቤቶች የፍሬ ነገር እና የማስረጃ ምዖና ያደረጉባቸው እና የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዲዮ ስለሆኑ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10(ሐ) እና (መ) መሰረት ይህ ሰበር ችልት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም፤ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ሰበር ሰሚ ችልት መጋቢት 28 ቀን 2009 ዓ.ም በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው ስምምነት ፍርድ ቤት ቀርቦ ባለመጽደቁ ህጋዊ ውጤት የለውም፣ እንዱሁም አመልካች በስምምነቱ መሰረት የተጣለበትን ተነፃፃሪ ግዳታ አልተወጣም ሲል አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ መወሰኑ ህግን መሰረት ያደረገ ስለሆነ ውሳኔው ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክራለች።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ የክርክር ይዖት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በዘህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን ያለመሆኑን በጭብጥነት በመያዛ መዛገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም አመልካች ያቀረበዉን ክስ መሰረት በማድረግ ጉዲዩን የተመለከተዉ የወረዲዉ ፍርድ ቤት በመካከላቸዉ የነበረዉ ጋብቻ ከመፍረሱ በፉት ብር 380,000.00 ዔዲ ያለባቸዉ ስለመሆኑ ተጠሪ በነፃ ፍቃዶ ከአመልካች ጋር ባደረገችዉ ስምምነት አምና ለመክፈልም የተስማማች በመሆኑ በስምምነቱ መሰረት ግማሹን ለአመልካች ብር 190,000.00 ልትከፍል እንደሚገባ የወሰነዉ ዉሳኔ በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት በትዔዙዛ የጸና ቢሆንም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ይህን ዉሳኔ ሽሮታል። ሰበር ሰሚዉ ችልት ዉሳኔዉን ሲሽር መሰረት ያደረገዉም በግራ ቀኝ መካከል የተደረገዉ እና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የእርቅ ስምምነት ፍርድ ቤት ቀርቦ መጽደቅ እንዲለበት በዉለ ላይ የተመለከተ ቢሆንም ለፍርድ ቤት ቀርቦ ያልጸደቀ መሆኑን፣ የእርቅ ስምምነቱ ቀደም ሲል በፍርድ ቤት የተሰጠዉን ዉሳኔ ለማስቀረት የተደረገ በመሆኑ እና እንደዘህ ዓይነት ስምምነት ደግሞ በፍርድ ቤት ቀርቦ ካልጸደቀ ህጋዊ ዉጤት የላለዉ ነዉ እንደሆነ በዘህ ረገድ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን አስገዲጅ የህግ ትርጉም በዋቢነት በመጥቀስ ስለመሆኑ የዉሳኔዉ ይዖት ያሳያል።
እንደሚታወቀዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉን ዉሳኔዎች በማረም ላይ የተገደበ ስለመሆኑ በኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ሀ) ላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ መገንዖብ ይቻላል። መሰረታዊ የህግ ስህተት ማለት ምን ማለት ነዉ? ወይም አንድ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት የሚቻለዉ መቼ ነዉ? የሚለዉን ጽንሰ ሃሳብ አስመልክቶ፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በበርካታ መዙግብት ላይ በሰጠዉ ዉሳኔ አመላካች መስፈርቶችን ለማስቀመጥ የሞከረ ቢሆንም፣ እስከ ቅርብ ጊዚ ድረስ በህግ ደረጃ ወጥ የሆነ ትርጓሜ አልተሰጠዉም ነበር። ይሁንና ከጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለዉ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረታዊ የህግ ስህተት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትርጓሜ ይሰጣል። የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ተግባራቸዉን ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ ዉጤታማ፣ ቀልጣፊ፣ ተደራሽ እና ተገማች በሆነ ሁኔታ እንዱያከናዉኑ ማድረግን አንደ ዓላማዉ ያደረገዉ ይህ አዋጅ ካካተታቸዉ አዲዱስ ድንጋጌዎች ዉስጥ አንደ መሰረታዊ የህግ ስህተት ለሚለዉ ጽንሰ ሃሳብ ትርጓሜ መስጠቱ እና በክልልች ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠ ዉሳኔ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ላታይ የሚችልበትን ሁኔታ አስመልክቶ የተለየ ድንጋጌ ማካተቱ ነዉ። በአዋጁ በትርጉም ክፍል አንቀጽ 2(4) ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዖብ እንደሚቻለዉ አንድ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት የሚቻለዉ የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎች የሚቃረን፣ ህግ ያላግባብ የሚተረጉም ወይም ለጉዲዩ አግባብነት የላለዉን ህግ የሚጠቅስ፣ ለክርክሩ አግባብነት ያለዉ ጭብጥ ሳይያዛ ወይም ከክርክሩ ጋር የማይዙመድ አግባብነት የላለዉ ጭብጥ ተይዜ የተወሰነ፣ በዲኝነት ታይቶ ሉወሰን የሚገባዉን ጉዲይ ዉድቅ በማድረግ የተወሰነ፣ በፍርድ አፈፃፀም ሂደት ከዋናዉ ፍርድ ጋር የማይገናኝ ትዔዙዛ የተሰጠበት፣ ጉዲዩን አይቶ የመወሰን የዲኝነት ስልጣን ሳይኖር የተወሰነ፣ የአስተዲደር አካል ወይም ተቋም ከህግ ዉጭ የሰጠዉ ዉሳኔ፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትን አስገዲጅ ዉሳኔ በመቃረን የተወሰነ ሲሆን ነዉ።
በመሆኑም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በሚል የሰበር አቤቱታ ሲቀርብለት ለአቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ጉዲይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት የሚቻለዉ ዉሳኔዉ/ትዔዙዘ/ብይኑ ከላይ በዛርዛር ከተመለከቱት ሁኔታዎች ዉስጥ ቢያንስ አንደን ያሟላ ሆኖ ሲገኝ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 10 ላይ ከተመለከቱት ድጋጌዎች የምንገነዖበዉ ነዉ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠ ዉሳኔ/ትዔዙዛ/ብይን ሲሆን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታዉን ተቀብል በሰበር የማየት ስልጣን የሚኖረዉ ዉሳኔዉ/ትዔዙዘ/ብይኑ የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎች፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትን አስገዲጅ ዉሳኔ የሚቃረን ሲሆን እንዱሁም አግባብነት የላለዉን ህግ በመጥቀስ ወይም ህግን ያላግባብ በመተርጎም የተሰጠ ዉሳኔ/ትዔዙዛ/ብይን ሆኖ ጉዲዩም አገራዊ ፊይዲን የሚመለከት ሲሆን ብቻ ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 10 (1/ሐ/ እና /መ) ድንጋጌዎች ያስገነዛባለ። ከዘህም የምንረዲዉ የሰበር አቤቱታ የቀረበበት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ዉሳኔ ከእነዘህ ሦስቱ ሁኔታዎች ዉጪ ባለት ሁኔታዎች፣ መሰረታዊ የህግ ስህተትን መስፈርት አስመልክቶ በአዋጁ አንቀጽ 2(4) ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ዉስጥ አንደን የሚያሟላ ሆኖ ቢገኝ እንኳን፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን በሰበር የማረም ስልጣን የላለዉ መሆኑን ነዉ። ስለሆነም ይህ የፋዳራል ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችልት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትን ዉሳኔ/ትዔዙዛ/ብይን በመቃወም የቀረበለት አቤቱታ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ከሆነ ዉሳኔዉ/ትዔዙዘ/ብይኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን ያለመሆኑን በመወሰን ረገድ እነዘህኑ ልዩ ሁኔታዎች ማለትም በአዋጁ አንቀጽ 10(1/ሐ) ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ከግምት ዉስጥ የማስገባት ኃላፉነት ይኖርበታል።
ከዘህ አንፃር የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ከፍ ሲል በተመለከተዉ መልኩ የሰጠዉ ዉሳኔ በአዋጁ ቁጥር 1234 አንቀጽ 10 (1/ሐ/ እና /መ) ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች አግባብ ህገ መንግስቱን የሚጥስ፣ አገራዊ ፊይዲ ያለዉን የህዛብ ጥቅም የሚጎዲ ወይም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉን አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሚጥስ ይዖት የላለዉ በመሆኑ በዘህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አይቻልም። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁጥር 03-907110 ላይ ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍትሐብሕር ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዘህ ችልት የተደረገ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.