No summary available.
የሰበር መዛገብ ሚያዛያ 28 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ወ/ሪት ነስሪያ ተካ ተጠሪ፡- ረጀቦ ከድር ለምርመራ የተቀጠረው መዛገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
አመልካች ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ለመፈፀም በአካል ቀርባ ወይንም በቤተሰብ ሕጉ በተቀመጠው አግባብ በእንደራሴ ፈቃዶን ሳትሰጥ የሸርዓ ሕጉ በሚደነግገው መሰረት በአባቷ ተወክላ ፈቃዶን ስለሰጠች በግራቀኙ መካከል የሸርዓ ሕጉን መሰረት በማድረግ የተመሰረተው ጋብቻ ሉፈርስ ይጋበል በማለት በየደረጃው ያለት የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ጋብቻ በተጋቢዎች ነፃና ሙለ ፈቃድ ብቻ ይመሰረታል በማለት ሕገ መንግስቱ እና የቤተሰብ ሕጉ በአስገዲጅነት የተመለከተውን ሰብአዊ መብት የሚፃረር መሰረታዊ የሕግ ስህት የተፈፀመበት ነው በማለት በሰበር ለማሳረም ጳጉሜ 4 ቀን 2013 ዓ/ም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል ተብል መዛገቡ ለችልት ቀርቧል።
ጉዲዩ የጋብቻ ፍቺን የሚመለከት ሆኖ ተጠሪ በምዔራብ አዖርነት በርበሬ ወረዲ ፍርድ ቤት መስከረም 13 ቀን 2012 ዓ/ም ያቀረቡት ክስ ይዖት፡- ግራቀኙ በ2009 ዓ/ም በእስልምና ሃይማኖት መሰረት ጋብቻ መስርተው ንብረት ያፈሩ ቢሆንም በግንኙነቱ ለመቀጠል የሚያስችል ሁኔታ በመካከላቸው መፈጠሩን ገልፀው ፤ የግራቀኙ ጋብቻ ፈርሶ ለፍቺው መንስኤ አመልካች በመሆኗ የሞራል ካሳ እንድወሰንለት ጠይቋል። ክርክሩ አመልካች በላለችበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ተሸሮ አመልካች የክርክሩ ተካፊይ እንድትሆን ያቀረበችው አቤቱታ በስልጤ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቀባይነት በማግኘቱ ለክሱ በሰጠችው መልስ፡- ከተጠሪ ጋር የፈፀሙት የሚፈርስ ጋብቻ አለመኖሩ ፤ ተጠሪ በግራቀኙ መካከል ጋብቻ ተፈጽሟል በሚለበት ወቅትም ሆነ የፍቺ ጥያቄው በቀረበበት ጊዚ አመልካች በሀገር ውስጥ የላለች ነዋሪነቷ አረብ ሀገር መሆኑን ፤ ተጠሪ ጋብቻ በላለበት የፍቺ ጥያቄ ያቀረበው አመልካች በሰው ሀገር የቤት ሰራተኛ ሆና ባገኘችው ገንዖብ የገዙችውን ቤት ለመቀማትና አላግባብ ለመበልግ ካለው ፍላጎት የተነሳ በመሆኑ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ምንም ጋብቻ ሳይኖር የቀረበው የፍቺ ክስ ውድቅ ሆኖ ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንላት ጠይቃለች።
የምዔራብ አዖርነት በርበሬ ወረዲ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ምስክሮች ሰምቶ መዛገቡ እንደሚከተለው መርምሯል። የቤተሰብ ሕጉ በመርህ ደረጃ ሁለቱ ተጋቢዎች በተገኙበት ጋብቻ የሚፈፀም መሆኑን ሲደነግግ በየትኛውም የአፈፃፀም ሥርዓት የተደረገ ጋብቻ እኩል መሆኑን በልዩ ሁኔታ የሚያስገነዛብ በመሆኑ ፤ ግራቀኙ በላለበት በውክልና ኒካ መታሰሩ በምስክሮች በመረጋገጡ ፤ በእስልምና ሃማይኖት አንዱት ሴት ለመጋባት በወላጅ አባቷ ፣ አባት ከላላት በወንድም እያለ በቤተሰብ በኩል በውክልና ኒካ ከታሰረ በኋላ ባልና ሚስት እንደሆኑ ስለሚገመትና የአመልካች ፈቃድ በአባቷ በኩል ተረጋግጦ እሷ በላለችበት ጋብቻ መደረጉን በቤተሰብ ሕጉ የተደነገገውን ቅድመሁኔታ በሸርዓ ሕጉ የግድ የሚል አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ከሸርዓ ፍርድ ቤት ጠይቆ የተረዲ በመሆኑ ፈቃዳን ባልሰጠሁበት እና በላለሁበት ጋብቻ ላደረግ አይችልም የሚለው የአመልካች ክርክር የቤተሰብ ሕጉ እሳቤ የሸርዓ ሕጉ የግድ የሚል ባለመሆኑ ከአከባቢው በሕልና ልማድ ፤ እንዱሁም ከሃይማኖት አንፃር ሲታይ ኒካ ከታሰረ ቀን ጀምሮ ባልና ሚስት እንደሆኑ ስለሚገመት በቤተሰብ ሕጉ የተቀመጠው ቅድመሁኔታ መሟላት ግዳታ አይደለም በማለት የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዛቦች ክልላዊ መንግስት የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/96 አንቀጽ 13 እና 91(4) መሰረት ጋብቻ መኖሩ ስለተረጋገጠ የአመልካች መቃወሚያ ውድቅ ነው በማለት የፍቺ ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በውሳኔው ባለመስማማት ያቀረበችውን ይግባኝ የሥልጤ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 337 በመሰረዘ ጉዲዩን የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችልት በእስልምና ሃይማኖት ሥርዓት መሰረት ጋብቻ መፈፀሙን ተጠሪ በቂና አሳማኝ በሆነ መልኩ ያስረዲ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች በግራቀኙ መካከል መኖሩን ያተረጋገጡትን ጋብቻ እንዱፈርስ መወሰናቸው በአግባቡ ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካች በየደረጃው ያለት የሥር የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዛቦች ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች የሰጡት ፍርድ ፣ ውሳኔ እና ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት በሰበር ለማሳረም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዖት፡- ጋብቻን ለመፈፀም በሕጉ የተመለከተው ቅድመ ሁኔታ በሃይማኖት መሰረት የሚፈፀመውን ጋብቻ ጭምሮ ሁለንም የጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓቶችን የሚመለከት ሆኖ ከቅደመ ሁኔታዎቹ አንደ በደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዛቦች ክልላዊ መንግስት የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/1996 አንቀጽ 22(1) ሥር የተመለከተው ጋብቻ ሲፈፀም ተጋቢዎች በአካል ተገኝተው ፈቃዲቸውን በማያሻማ ሁኔታ መግለጽ አስፈላጊነት በየትኛውም ሥርዓት ለሚፈገፀም ጋብቻ በውክልና ጋብቻ እንዲይፈፀም ሕጉ የሚከለክል ሆኖእያለና ጋብቻው ተፈጽሟል በተባለበት ጊዚ አመልካች በሀገር ውስጥ ያልነበረች በግንባር በአካል ቀርባም ሆነ በአባቷ ተወክላ የሰጠችው ፈቃድ ሳይኖር እና አመልካች በአባቷ መወከሎን የሚያስረዲ አግባብነት ያለው ማስረጃ ጉዲዩ ከሚመለከተው አካል ሳይቀርብ ፤ ህጉ በሃይማኖታዊ ሥርዓት ለሚፈፀም ጋብቻ ዔውቅና የሚሰጠው ጋብቻው ማሟላት ያለበትን በሕጉ የተመለከተውን መሰረታዊ መስፈርቶችን አሟልቶ ሲገኝ ሆኖሳለ ፤
የግራቀኙ ጋብቻ በእስልምና ሃይማኖት ሥርዓት የተፈፀመ በመኆኑና ሥርዓቱ ደግሞ በውክልና ጋብቻ መፈፀምን ስለመፈቅድ ፤ ክልከላው በዘህ ሥርዓት የተፈፀመ ጋብቻን አይመለከት በማለት የሕገ መንግስቱንና የቤተሰብ ሕጉን ግልጽ ድንጋጌዎች ወደጎን በማለት ሃይማኖታዊ ሕግን መሰረት በማድረግ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው ጋብቻ ሳይኖር ጋብቻ እንዲለ ተወስድ እንዱፈርስ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ የሚፈርስ ጋብቻ የለም ተብል እንዱወሰን ጠይቀዋል።
አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልቱ፡- አመልካች በአባቷ ወኪልነት በሸሪዓ ሕግ መሰረት የፈፀመችው ጋብቻ ይፍረስ በማለት የመወሰኑን አግባብነት ለአመልካች አባት በክልለ የቤተሰብ ሕግ አንፃር የተሰጠ ውክልና ስለመኖሩ ተረጋጦ መሆኑን ለማጣራት መዛገቡ ለሰበር ሰሚ ችልቱ ያስቀርባል ተብል ተጠሪ በሰጡት መልስ፡- በአመልካች እና ተጠሪ መካከል በእስልምና ሃይማኖት መሰረት የተደረገ ጋብቻ መኖሩን አመልካች ሳይክደ በግራቀኙ መካከል የተደረገው ጋብቻ ሳይሆን መተጫጫት ነው በማለት ስከራከሩ የቆዩ ሲሆን ፤ በግራቀኙ መካከል የተደረገው ጋብቻ በሀገሪቱ በሚልዮን በሚቆጠሩ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዖንድ በተመሳሳይ መልኩ የሚፈፀም በመሆኑና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችልት በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 ቁጥር 10(3) የተሰጠውን ሥልጣን መሰረት አድርጎ የሚሰጠው ውሳኔ በየትኛውም ደረጃ ባለው ፍርድ ቤት ላይ አስገዲጅነት ያለው በመሆኑ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ጋብቻ የለም ከተባለ ተመሳሳይነት ባለው መልኩ የተፈፀሙ በሚሉዮኖች የሚቆጠሩ ተጋቢዎች ጋብቻ እንዲልተፈፀመ ተቆጥሮ ትልቅ ማኀበራዊ ቀውስ ሉፈጥር ስለሚችል ችልቱ ጉዲዩን በጥሞ እና በጥንቃቄ እንዱመለከተው ጠይቀዋል። አመልካች የተፈፀመ ጋብቻን እንዲልተፈፀመ በማድረግ ስለእስልምና ወይንም ስለሸርዓ በቂ እውቀት የላለውን የሰበር ሰሚ ችልቱን በማደናገር ህብረተሰቡ እየኖረበት ያለውን ማኀበራዊ እሴት በመናድ በማኀብረሰቡ መካከል መተማመን እንዲይፈጠር ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የላለው መሆኑን ፤ የቤተሰብ ህጉ በሃይማኖት ሥርዓት ጋብቻ እንዱፈፀም ፈቅድ በሰጠው እውቅና መሰረት በእስልምና ሃይማኖት ተጋቢዎቹ በአካል ኖሩም አልኖሩ ኒካ የሚታሰረው የሴቷ ፈቃደኝነት በቤተሰቧዋ( አባት ፣ አባት ከላለ በወንድም ፣ ወንድም ከላለ አጎት) ተጠይቆ በመሆኑ ፤ አመልካችን ወክለው ኒካ በሚያስሩ የአመልካች አባት ፈቃዲኛ መሆናቸው ተረጋግጦ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ተከትል ጋብቻ የተፈፀመ መሆኑ በምስክር የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች በእስልምና ሃይማኖት ሥርዓት ለተፈፀመ ጋብቻ አግባብነት የላለውን የቤተሰብ ህጉን የውክልና ጽንሰ ሃሳብ በማንሳት በግራቀኙ መካከል ጋብቻ እንዲልተፈፀመ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ሆኖ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዱፀና ጠይቀዋል። አመልካችም ለአባቷ በእሷ ስም ጋብቻ መመስረት የሚያስችለው የውክልና ሥልጣን ያልሰጠች መሆኗንና ግራቀኙ ጋብቻ መሥርተው አብረው አለመኖራቸውን በማንሳት የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑ ለጉዲዩ አግባነት ካለው ሕግ አንፃር እንደሚከተለው ተመርምሯል። ኀብረተሰብ ሆነ መንግስት ያለቤተሰብ አይኖሩም። ቤተሰብ የኀብረተሰብ የተፈጥሮ መሰረታዊ መነሻ ነው። የቤተሰብ መሰረት ደግሞ ጋብቻ ፤ የባልና ሚስት ትዲር ነው። ጋብቻ ተራ ውል ባለመሆኑ መንግስትም ሆነ ኀብረተሰቡ ጋብቻንና የጋብቻ ውጤትን በልዩ ዓይን ይመለከቷቸዋል። ስለዘህም መንግስት ለጋብቻ ዔውቅና ከመስጠት ጀምሮ ጋብቻ እንዳት እንደሚመሰረት ፣ የጋብቻ ውጤትን ፣ ፍቺን ፣ የባልና ሚስት ግዳታና መብትን ፣ ልጆችንና የመሳሰለትን በሚመለከት የሕግ ድንጋጌዎችን በማውጣትና የተለያዩ ተቋማትን በማደራጀት ጥበቃ ያደርጋል።
የሰብአዊ መብቶች ሁለ አቀፍ መግጫ (Universal Decaration of Human Rights) አንቀጽ 16(2) ጋብቻ የሚፈፀመው ለመጋባት በተፈቃቀደት ሰዎች ነፃና ሙለ ፈቃድ ብቻ መሆኑን ያመለክታል። የሲቪልና የፖለትካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዲን (International Covenants on civil and political Rights) አንቀጽ 23(2) ያለተጋቢዎች ነፃ እና ሙለ ፈቃድ ጋብቻ መመስረት እንደላለበት ያመለክታል። በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድላዊ ልዩነትን ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት ( Convention for the Elimination of All forms of Discrimination Against Women) አንቀጽ 16 (1) (ለ) ሴቶች የትዲር ጓደኛን የመምረጥና ጋብቻን በውዳታና በነፃ ፍላጎት ብቻ የመፈፀም መብት እንዲላቸው ይደነግጋል።
የኢ/ፋ/ዱ/ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 34(2) ጋብቻ በተጋቢዎች ነፃና ሙለ ፈቃድ ብቻ እንደሚመሰረት ይደነግጋል። የሕገ መንግስቱ ማብራሪያ ጋብቻ በሁለቱ ተጋቢዎች ነፃ ፈቃድ ካልሆነ በቀር በልላ ወገን ለምሳላ በወላጆች ወይንም በሽማግላዎች ወዖተ ምርጫ እና ውሳኔ እንዲይፈፀም ሕጉ ደንግጎ እያለ ይህን በመተላለፍ ከተጋቢዎቹ ፈቃድ ውጭ የተፈፀመ ጋብቻ ይፀናል ወይስ አይፀናም የሚለው በዛርዖር ሕግ የሚወስን ሲሆን ፤ እንድያገባ ወይንም እንዱታገባ የተገደደ ወይንም የተገደደች ተጋቢ በማንኛውም ጊዚ ጋብቻውን ለማፍረስ የመጠየቅ መብት አለው / አላት ብቻ ሳይሆን የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 34(2) ጋብቻ በተጋቢዎች ነፃና ሙለ ፈቃድ ብቻ ይመሰረታል ስለሚል የግዳታ ጋብቻ እንደ ጋብቻ ስለማይቆጠር ተጋቢዎች ጋብቻቸውን ለመቀጠል የተስማሙ እንደሆነ እንኳን ጋብቻው ያለፈውን የትዲር ዖመን በማካተት በአዱስ ውል እንደገና መፈፀም እንዲለበት ያመለክታል። ሕገ መንግስቱ በሃይማኖት እና በባሕል ሥርዓቶች ለሚፈፀም ጋብቻ እውቅና በመስጠት ዛርዖሩ በሕግ እንደሚወሰን አንቀጽ 34(4) ያመለክታል። በፍትሐ ብሓር ሕጉ ቁጥር 579 እና 580 እንደቅደምተከተላቸው ለሃይማት እና ለልማድ ጋብቻ እውቅና የተሰጠ ቢሆንም የአሁኑ ከበፉቱ የሚለይበት ትልቁ ነጥብ ለሃይማኖትና ለባሕል ጋብቻዎች ዔውቅና የሚሰጡ ሕጎች ከሕገ መንግስቱ የሰብአዊና ዱሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶች ጋር ሉጋጩ የማይችለ መሆናቸውን ፤ በተለይም የወንድ እና የሴት እኩልነት ፣ የጋብቻ በፈቃድ ላይ መመስረት ፣ በጋብቻ አፈፃፀም ፤ በጋብቻው ዖመንና በፍቺ ጊዚ የባልና ሚስት እኩልነት እና የመሳሰለት መሰረታዊ መብቶች ሉጣሱ ወይንም ሉቀነሱ የማይችለ መሆኑን የሕገ መንግስቱ ማብራሪያ ያመለክታል። ሕገ መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ በመሆኑ ማንኛውም ሕግ ፣ ልማዲዊ አሰራር ወይንም ውሳኔ ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደላለው ቁጥር 9(1) ይደነግጋል። ከላይ የተመለከተው ሕገ መንግስታዊ መርህን በዛርዖር ሕግ ሉንፀባረቅ የሚገባው መሰረታዊ መብት በመሆኑ በጋቻ አፈፃፀም የሶስተኛ ወገኖች (ወላጆች ፣ አሳዲሪዎች) ተጽኖ ተቀባይነት የላለው መሆኑን ለማመልከት በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/192 አንቀጽ 6 ሥር የተጋቢዎች ፈቃድና ፍላጎት በአስፈላጊ ሁኔታዎች ሥር እንዱሰፍር የተደረገው ዋናው አስፈላጊ ሁኔታ የወደፉት ተጋቢዎች ፈቃድ መሆኑን ለማሳየትም በክፍለ ውስጥ የመጀመሪያ አንቀጽ ሆኖ መቀረጹን የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ሐተታ ዖምክንያት(ማብራሪያ) ያመለክታል።
የፍደራል የቤተሰብ ሕግ ይዖት እና አተገባበሩ በሚል ርዔስ በታተመው መጽሐፍ የተጋቢዎች ፈቃድ ጋብቻን ለመፈፀም መሟለት ካለበቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሁለ ዋነኛ መሆኑን ለማመላከት በክፍለ በአንደኛ ተራቁጥር መቀመጡ ተመላክቷል። መጽሐፈ በመቀጠልም በአንዲንድ የሀገራች የማኀብረሰብ አካለት ለጋብቻ የፈቃደኝነት መኖር አስፈላጊ ቢሆንም የሚፈለገው ፈቃደኝነት የተጋቢዎቹ ሳይሆን የቤተዖመደ መሆኑን ፣ የተጋቢዎች ፈቃድ የሚፈለገው ለማጠናከሪያነት እንጅ የወሳኝነት ሚና ያልነበረው መሆኑን ፤ በቀድሞው አስተሳሰብ የሚጋቡት ባልና ሚስቱ ብቻ ሳይሆን ቤተዖሞድቻቸው ሲሆኑ ፤ በዖመናዊ አስተሳሰብ በቀዲሚነት እና በዋናነት ጋብቻ የተጋቢዎች ጉዲይ በመሆኑ በነፃ እና ሙለ ፈቃዲቸው ላይ መመስረት ያለበት በመሆኑ ለጉዲዩ አጽኖት ለመስጠት ታስቦ ሕገ መንገስታዊ ድንጋጌው በቤተሰብ ሕጉ ውስጥ እንዲለ እንዱካተት መደረጉን ያብራራለ።
ጋብቻ በነፃና ሙለ ፈቃደኝነት ሉመሰርት የሚገባ በመሆኑ በእንደራሴ መፈፀምን ሕጉ ይከለክላል። (የተሸሻለውን የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 12 ይመለከቷል)።
የተጋቢዎችን ፈቃድና ፍላጎት ለማረጋገጥ ጋብቻ በሚፈፀሚበት ጊዚና ቦታ ተጋቢዎች በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን ተጋቢዎች ፈቃድና ፍላጎታቸውን ገልፀው በአንድነት መገኘት የሚያስችላቸው ከባድ ሁኔታ ሲያጋጥም በእንዱህ ዓይነት ሁኔታ መገኘት የማይችል ተጋቢ ጋብቻ ለመፈጸም ፈቃደን በማያሻማ መልኩ የገለጸ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስትሩ ሲያረጋግጥ በእንደራሴ ጋብቻ ሉፈፀም እንደሚችል አንቀጽ 12(2) ያመለክታል። የቤተሰብ ሕጉ አወቃቀር ሲታይ የጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓቶችን ከዖረዖረ በኋላ የጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓቶቹ ማሟላት ያለባቸውን ሁኔታዎች በቅደምተከል ያስቀምጣል። እነዘህን መሰረታዊ ሁኔታዎችን አሟልቶ መገኘት ለሁለም የጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓቶች ግዳታ ሆኖ ጋብቻው የሚፈፀሚበት ሥርዓት የሚያስቀምጠውን መስፈርትም በተጨማሪነት ማሟላት እንዲለበት ይጠበቃል። በሕጉ የተመለከተውን መስፈርት አሟልቶ የተደረገ ጋብቻ በየተኛውም ሥርዓት ቢፈፀም ምንም ልዩነት ሳይደረግበት ተመሳሳይ ሕጋዊ ውጤት ያለው መሆኑን አንቀጽ 40 ያመለክታል።
የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዛቦች ክልላዊ መንግስት የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/1996 ምዔራፍ ሁለት ክፍል አንድ ሥር ልዩ ልዩ ጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓቶችን ( በክብር መዛገብ ሹም ፉት የሚፈፀም ፣ በሃይማኖት ሥርዓት እና በባህል ሥርዓት) የሚፈፀሙ መሆኑን ከዖረዖረ በኋላ በዘያው ምዔራፍ በክፍል ሁለት ሥር ሁለንም ዓይነት ጋብቻ ለመፈፀም ማለትም በክብር መዛገብ ሹም ፉት ፣ በሃይማኖት ሥርዓት እና በባህል ሥርዓት የሚደረገውን ጋብቻ ለመፈፀም መሟላት የሚገባቸውን ቅድመሁኔታዎችን በአንቀጽ 16 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ሥር ተመልክቷል። ከቅደመሁኔታዎቹ ውስጥ የሚፀና ጋብቻ ተፈጽሟል ለማለት የሚቻለው ተገቢዎቹ ለመጋባት ነፃና መለ ፈቃድ ሲሰጡ ብቻ መሆኑን አንቀጽ 16 ሥር በቀዲሚነት ይደነግጋል። ጋብቻ ሲፈፀም ሁለቱም ተጋቢዎች በግንባር ተገኝተው ፈቃዲቸውን መስጠት ያለባቸው ሲሆን በከባድ ምክንያት ጋብቻውን በአካል ቀርቦ መፈፀም ባለመቻለ ጋብቻን በውክልና መፈፀም የሚፈልግ ተጋቢ ፈቃደን በማያሻማ ሁኔታ መግለፁ በፍትሕ ቢሮ ኃላፉ ሲረጋገጥ ብቻ ጋብቻውን በውክልና ሉፈጽም እንደሚችል አንቀጽ 22 ይደነግጋል። በሕጉ የተመለከቱት ቅደመ ሁኔታዎችን አሟልቶ የተፈፀመ ጋብቻ በየትኛውም የአፈፃፀም ሥርዓት ቢፈፀም ውጤቱ ተመሳሳይ መሆኑን አንቀጽ 49 ያመለክታል።
በተያዖው ጉዲይ ተጠሪ በ2009 ዓ/ም ከአመልካች ጋር በእስልምና ሃይማኖት መሰረት ጋብቻ መስርተናል በሚለበት ጊዚ አመልካች በሀገር ውስጥ የላለ በአካል ቀርበው ከተጠሪ ጋር ለመጋባት ነፃና ሙለ ፈቃዲቸውን ያልሰጡ በመሆኑ የሚፈርስ ጋብቻ የለም በማለት ተከራክረዋል። በግራቀኙ መካከል ጋብቻው ተፈፅሟል በተባለ ጊዚ አመልካች በሀገር ውስጥ አለመኖሯቸው አላከራከረም። ተጠሪ ጋብቻው የተፈፀመው በእስልምና ሃይማኖት ሥርዓት ስለሆነ በዘህ ሥርዓት ለሚፈፀመው ጋብቻ ተገቢዎችን ወክለው ፈቃድ የሚሰጡት ከተጋቢዎቹ ውጪ ያለ ላልች ሰዎች በመሆናቸው የተጋቢዎቹ በአካል መኖርም ሆነ አለመኖር የሚያመጣው ለውጥ ባለመኖሩ እና በቤተሰብ ሕጉ ላይ የተመለከተው ውክልናም በእስልምና ሃይማኖት ሥርዓት ለሚፈፀም ጋብቻ ተገቢነት የላለው መሆኑን ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን የተመለከተው የምዔራብ አዖርነት በርበሬ ወረዲ ፍርድ ቤት የቤተሰብ ሕጉ በመርህ ደረጃ ሁለቱ ተጋቢዎች በተገኙበት ጋብቻ የሚፈፀም መሆኑን ቢደነግግም በየትኛውም የጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓት የተደረገ ጋብቻ እኩል በመሆኑ በእስልምና ሃማይኖት አንዱት ሴት ለመጋባት በወላጅ አባቷ ፣ አባት ከላላት በወንድም እያለ በቤተሰብ በኩል በውክልና ኒካ ከታሰረ በኋላ በአከባቢው በሕልና ልማድ ፤ እንዱሁም ከእስልምና ሃይማኖት አንፃር ባልና ሚስት እንደሆኑ ስለሚገመት በቤተሰብ ሕጉ የተደነገጉት ቅድመሁኔታዎች በሸርዓ ሕጉ የግድ የሚለ አለመሆኑ ከሸርዓ ፍርድ ቤት ጠይቆ የተረዲ በመሆኑ ፈቃዳን ባልሰጠሁበት እና በላለሁበት የተደረገ ጋብቻ የለም የሚለው የአመልካች ክርክር የቤተሰብ ሕጉ እሳቤ በሸርዓ ሕጉ የግድ የሚል አይደለም በማለት የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርጎ የፍቺ ውሳኔ ሰቷል።
ጋብቻ የተደረገበት የአፈፃፀም ሥርዓት ልዩነት ሳይደረግበት በሕግ ፉት እኩል ውጤት አለው መባለ ጋብቻን ለመፈፀም በሕጉ የተመለከቱት ቅደመሁኔታዎች ለሁለም የጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓቶች ተፈፃሚ እንዲይሆኑ ለማድረግ ሳሆን ሁለንም የጋብቻ አፈፃፀም ሥርዓት የሚመለከቱ ቅድመሁኔታዎችን ያሟላ ጋብቻ ፤ የተፈፀመበት ሥርዓት ታይቶ በውጤቱ ላይ ልዩነት እንዲይኖር ታስቦ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ይህን የእኩልነት መርህ አላግባብ ተጠቅሞ በእስልምና ሃይማኖት ሥርዓት ለሚፈፀመው ጋብቻ የተጋቢዎች ፈቃድ መኖር ተፈፃሚነት እንደላለው መውሰደ ተገቢነት የለውም። የተጋቢዎች ፈቃድ መኖር ግዳታ መሆኑ ከላይ በተመለከቱት የተለያዩ የዓለም አቀፍ ስምምነቶች በአስገዲጅነት ከመደንገጋቸውም በላይ በኢ/ፋ/ዱ/ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 34(2) ጋብቻ በተጋቢዎች ነፃና ሙለ ፈቃድ ብቻ እንደሚመሰረት በመደንገጉ ፤ ይህ መሰረታዊ ሰብዓዊ መብት ሳይሸራረፍ እንድከበር ቃልበቃል የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዛቦች ክልላዊ መንግስት የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/1996 በአንቀጽ 16 ሥር የተመለከተው ድንጋጌ በእስልምና ሃይማኖት ሥርዓት ለተፈፀመ ጋብቻ ተፈፃሚነት የለውም ማለቱ በሕጉ የተመለከተውን ግልፅ ክልከላ መተላለፍ ብቻ ሳይሆን በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 13(1) ሥር የተጣለበትን መሰረታዊ መብቶች እና ነጻነቶችን የማስከበር ኃላፉነትና ግዳታውን አለመወጣቱን ያመለክታል። ፍርድ ቤቱ የተጋቢዎች ፈቃድ መኖር በእስልምና ሃይማኖት ሥርዓት ለተፈፀመ ጋብቻ የግድ አይደለም ለማለት ያበቃው በሸርዓ ሕጉ ግዳታ አለመሆኑን ከሸርዓ ፍርድ ቤት ጠይቆ መረዲቱን ውሳኔው የሚያመለክት ሲሆን ፤
መደበኛ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ክርክር አግባብነት ባላቸው የሕገ መንግስቱ ፣ መደበኛ መሰረታዊ ህጎች እና የሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት ማድረግ እንጅ የሃይማኖት ሕጎችን መሰረት አድርጎ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን የለውም።
የሥር ፍርድ ቤት እንደሚለው እና ተጠሪም በሰበር ችልቱ ባቀረቡት ክርክር በግራቀኙ መካከል የተደረገው ጋብቻ በእስልምና ሃይማይኖት አንዱት ሴት ለመጋባት በወላጅ አባቷ ፣ አባት ከላላት በወንድም እያለ በወንድ ቤተሰብ በኩል በውክልና ኒካ ከታሰረ በኋላ በሃይማኖቱ ፣ በአከባቢው በሕልና ልማድ አንፃር ጋብቻ እንደተፈፀ ስለሚቆጠር በቤተሰብ ሕጉ ላይ የተመለከቱት ቅደመሁኔታዎች ለተያዖው ጉዲይ ተገቢነት የለውም የሚለውም ስታይ የሀገሪቱን የበላይ ሕግ የሆነው የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 34(2) ጋብቻ በተጋቢዎች ነፃና ሙለ ፈቃድ ብቻ እንደሚመሰረት የሚደነግገውን የሚቃረን በመሆኑ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት ተቀባይነት ሉኖረው የሚችል አይደለም። ፍርድ ቤቱ ለውሳኔው የሸርዓ ሕጉን መሰረት ማድረጉም የመንግስትና የሃይማኖት ተቋማትን ሚና መደበላለቅን የሚያመጣ በህገ በመንግስቱ ለመንግስት ተለይቶ ከተሰጠው ተግባር በመውጣት በሃይማት ጉዲይ ጣልቃ መግባት የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 11 ድንጋጌን የሚፃር ተግባር ስለሆነ ተቀባይነት የለውም።
ሲጠቃለል አመልካች ነጻና ሙለ ፈቃዲቸውን ሰጥተው ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ሳይመሰርቱና ለአንድ ቀን እንኳን አብሮ የመኖር ግዳታቸውን ሳይወጡ ፤ በግራቀኙ መካከል በሕግ ፉት የፀና ጋብቻ ሳይፈፀም የፍቺ ውሳኔ መሰጠቱ የሚነቀፍ በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል።
የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዛቦች ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚው ችልት በሰበር መዛገብ ነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት ጉዲዩን ያዩት በየደረጃው ያለት የሥር የክልለ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ፍርድ፣ ውሳኔ ፣ ብይን እና ትዔዙዛ በማጽናት የሰጠውን ውሳኔ እና ትዔዙዛ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሸሯል።
በኢ/ፋ/ዱ/ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 34(2) እንዱሁም በደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዛቦች ክልላዊ መንግስት የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/1996 አንቀጽ 16 መሰረት በአመልካች ነፃና ሙለ ፈቃድ በግራቀኙ መካከል የተፈፀ የሚጸና ጋብቻ የለም በማለት ተወስኗል።
አመልካች እና በተጠሪ መካከል የተፈፀመ ጋብቻ ሳይኖር በፍርድ ቤት የሚሰጥ የፍቺ ውሳኔ የለም ብለናል።
በዘህ መዛገብ ላይ መስከረም 10 ቀን 2014 ዓ/ም የተሰጠው የዔግድ ትዔዙዛ ተነስቷል ።
በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የግላቸውን ይቻለ።
በዘህ መዛገብ ላይ መስከረም 10 ቀን 2014 ዓ/ም የተሰጠው ዔግድ ተነስቷል።
ውሳኔው ግንቦት 4 ቀን 2014 ዓ/ም በችልት ተነቧል።
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዖግቷል።
No topics extracted.