No summary available.
መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ሲ/ር ሐምዘያ ሱለይማን -ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አያለው በቀለ-ጠበቃ ኩራባቸው ጎሳ ቀረቡ መዛገቡን መርምረን የሚከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ አደማ ልዩ ዜን በአደማ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የአሁን አመልካች በቀን 14/02/2009 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ከተጠሪ ጋር በ1983 ዓ.ም ጀምሮ በባህል ተጋብተው ሲኖሩ አራት ልጆች ማፍራታቸው በመግልጽ አመልካች በቅርብ ጊዚ ውስጥ ባህሪያቸው ስለቀየረ በተለያዩ ጊዚያት የሚደበድቧቸው፤የሚሰድቧቸው እንዱሁም የማያከብሯቸው በመሆኑ ጋብቻው ፈርሶ በጋራ አብረው ያፈሩት ንብረት ድርሻቸው እንዱወስነላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። ተጠሪም ራሷ ባህሪዋን ለውጣ እኔ ያልፈጸምኩት ድርጊት ፈጽመሃል በማለት እኔን መክሰሷ ትክክል አይደለም በማለት ትዲራችን በአመልካች ጥያቄ እና ፍላጎት በመሆኑ በእርሷ ምክንያት የሚፈርስ መሆኑ ተቆጥሮልኝ የሞራል ካሳ እንድትከፍለኝ በማለት ለአቤቱታው መልስ በመስጠት ተከራክረዋል። ነገር ግን አመልካች የፍቺ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት በመዛገቡ ለጊዚው እንዱዖጋ በማመልከታቸው ምክንያት የመንቀሳቀስ መብታቸው በመጠበቅ ተዖግቶ የነበረ ሲሆን አመልካች የተዖጋው መዛገብ እንዱቀሳቀስ በቀን 24/08/2009 ዓ.ም በተፃፈ ስለአመለከቱ ፍርድ ቤቱም ተዖግቶ የነበረው መዛገብ እንዱቀሳቀስ በማድረግ የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዖነ በኋላ በቀን 28/09/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት በግራ ቀኙ የነበረው ጋብቻ በፍቺ እንዱፈርስ ካደረገ ለጋብቻው መፍረስም ተጠሪ ምክንያት በመሆኑ በጋራ አፍርተው ካላቸው ንብረት ውስጥ ከተጠሪ ድርሻ 20 በመቶ ለአመልካች እንዱያካፍል እንዱሁም የሁለት ልጆች ቀለብ በወር ብር 1,500.00/ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ እንዱከፍል ሲል ወስኗል። የአሁን ተጠሪ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለአደማ ልዩ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቢያቀርቡም ተቀባይነት ሳያገኝ በትእዙዛ ሰርዜታል። በመቀጠል ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታው አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በማሻሻል በተከራካሪዎች መካከል የነበረው ጋብቻ በተጠሪው ጥፊት በመፍረሱ በጋብቻ ውስጥ 20 በመቶ ለአመልካች እንዱያካፍል በማለት የተሰጠው ወሳኔ ውድቅ በማድረግ የልጆች ቀለብ በማጽናት ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ጥር 23 ቀን 2010 ዓ.ም በፃፈው አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዖርዛረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት በታዖዖው መሰረት ሚያዘያ 26 ቀን 2010 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዖው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም የአመልካች ጥያቄ ልጆችን ለማሰዲደግ ደፊ ቀና ብዬ እንዱሁም በአሁኑ ወቅት አካል ጉዲተኛ ልጅ በሰው እርዲታ የሚኖር አሸብር አያላው የሚባለውን ለማሳደግ በጥረት ላይ እያለሁ እና አቅመ አዲም ያልደረሱ አዲን እና ኢለያላ አያላው የሚባለትን ለማሳደግ እና ለማስተማር በጥረት ላይ እያለሁ ይህ ተጠሪ በየጊዚው ረብሻ እየፈጠረ አፀያፉ ቃላት እየተናገረ ለዘህ ሁለ ለትዲር መበተን ዋና ተዋናይ እራሱ ሆኖ እያለ፤እንዱሁም ከእኔ ከአመልካች ጋር በጋብቻ ተሳስረን ወይም ተጋብተን እየኖርን እያለን ከትዲር ውጭ ከላላ ሴት ጋር በፈጸመው የግብረ ስጋ ግንኙነት አንድ ልጅ የወለደ ለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት በማያሻማ ተመስክሮበት መከላከል ያልቻለ ስለሆነ በገንዖብ መቀጮ ተቀጥቶ እያለ ምንም አይነት ጥፊት እንዲልፈጸመ ሰው ንብረቱን እኩል እንድንካፈል የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤት የተካሄደውን ክርክር እና ያቀረብኩትን አቤቱታ መርምሮ ከተጠሪ ድርሻ 20% /ሃያ በመቶ/ ለአመልካች ሉከፍል ይገባል የተወሰነው የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ውድቅ መደረጉ ምንም አይነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 እንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 83/96 የፍቺው ምክንያት ለፍቺው አስፈላጊ ባይሆንም ለውጤቱ በተለይም ለጋራ ንብረት ክፍፍለ ግን ግምት ውስጥ ሉገባ ይችላል። ለምሳላ ለፍቺው የተጠየቀው አንደኛው ወገን በፈፀመው ዛሙት ወይም ድብደባ ምክንያት ከሆነ ፍቺው ተወስኖ በሚደረገው የንብረት ክፍፍል ወቅት ንብረቱ በእኩል መከፊፈለ ቀርቶ ይህንኑ ጥፊት ግምት ውስጥ ያስገባ ክፍፍል ማድረግ ይቻላል። ምክንያቱም በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 እንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 83/96 አንቀጽ 111 ከባልና ከሚስት ባንደ የተፈጸመውና ለፍቺው ምክንያት ሆኖ የተገኘው ጥፊት በልላው ተጋቢ ላይ ጉዲት አስከትል ከተገኘ በዲዩ ላደረሰው ጉዲት ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ እንዱከፍል ፍርድ ቤቱ ይወስናል። ፍርድ ቤቱ በዘህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ/1/ መሰረት ከጋራ ንብረት በካሳ መልክ ያንደኛውን ተጋቢ ድርሻ አብዙኛውን ወይም ሙለውን በደል ለተፈጸመበት ወገን እንዱከፈል ሉወሰን ይችላል በማለት ተደንግጎ ይገኛል። በርግጥ ከፍቺ ወቅት የሚኖረው የጋራ ሀብት ክፍፍል በአንጽ 117 እንደተመለከተው የጋራ ሀብቱ ለሁለቱም እኩል የማከፊፊል ነው። ከዘህ አንፃር ሲታይ አንቀጽ 111 የአንቀጽ 117 ልዩ ሁኔታ መሆኑ ግንዙቤ ሉወሰድበት ይገባል። ወደያዛነው ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች የፍቺ ውሳኔ እንዱሰጥ አቤቱታ ሲያቀርቡ እንደምክንያት ያቀረቡት ተጠሪ ባህሪያቸው በመቀየር በተለያዩ ጊዚያት የሚደበድቧቸው፤ የሚሰድቧቸው እና የማያከብሯቸው ከመሆናቸውም በላይ ከትዲር ውጭ ከላላ ሴት ጋር በፈጸሙት የግብረ ስጋ ግንኙነት አንድ ልጅ የወለደ መሆናቸው በዘህ ተግባራቸውም በአፊር ክልል ልጊያ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.392/2009 በቀን 12/07/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት ጥፊተኛ በማለት በገንዖብ መቀጮ የቅጣት ውሳኔ የተወሰነባቸው መሆኑን በተጠሪ ከመታመኑም በላይ ፍሬ ነገሩን የማጣራትና የመመዖን ስልጣን የተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶችም ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። ስለሆነም ከላይ በዛርዛር እንደተመለከትነው በአመልካችና ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ መፍረስ በተጠሪ ጥፊት መሆኑና በአመልካች ጉዲት ስለመድረሱ ተረጋግጦ እያለ ተጠሪ ለአመልካች ካሳ የማይከፍለበት ህጋዊ ምክንያት የለም። ሲጠቃለል የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤቶች በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ በከፉል መሰረታዊ የሕግ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.269768 መጋቢት 7 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348/1/ መሰረት ተሻሽለዋል።
በአመልካችና ተጠሪ የነበረው ጋብቻ በፍቺ እንዱፈርስ እና ተጠሪ ለልጆች ቀለብ በወር ብር 1,500.00/አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/እንዱፍል የተሰጠ ውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
ተጠሪ ለአመልካች ካሳ ሉከፍል አይገባም ሲል የሰጠው ውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.101604 ግንቦት 28 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ ውስጥ በተከራካሪዎቹ መካከል የነበረው ጋብቻ በተጠሪ ጥፊት በመፍረሱ በጋብቻ ውስጥ በጋራ ከተፈራው ንብረት ውስጥ ተጠሪ ከድርሻው ውስጥ 20 በመቶ ለአመልካች እንዱከፍል በማለት የተሰጠው ውሳኔ በአዲማ ልዩ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.26872 ሰኔ 21 ቀን 2009 ዓ.ም በትእዙዛ ያጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ወጭ እና ኪሳራ የግራ ቀኙን ተከራካሪ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
በቀን 17/08/2010 ዓ.ም የተሰጠው እግድ ተነስቷል፣ ይፃፍ፡ መዖገቡ ተዖግተዋል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.