No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ወ/ሮ ተሚማ ሬድዋን በሽር ተጠሪዎች፡- 1ኛ. አቶ በድሩ ሰማን 2ኛ. አቶ ደሉል በድሩ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል::
ጉዲዩ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት በሆነ ንብረት ላይ ይገባኛል የሚለው ሰው በአንደኛው ተጋቢ ላይ ብቻ ክስ አቅርቦ ተከሣሹም ንብረቱ የከሣሽ ነው ሲል አምኖ መከራካሩን ተክተል በክሱ መሰረት ከተወሰነ በኋላ ላላኛው ተጋቢ የመቃወም አቤቱታ ሲያቀርብ ብቻውን ተከሻስ የነበረው ተጋቢ ቀደም ሲል ያቀረበውን ክርክር ሣይለውጥ በመቀጠለ የተወሰነው የንብረቱ ክፍል የተጋቢዎች የጋራ ሃብት መሆኑ ቢረጋገጥም በክርክሩ ያመነው ተጋቢ ድርሻ ለከሣሽ ወገን እንዱተላለፍለት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ተብል እንዱታረም የቀረበን የሰበር አቤቱታ ይመለከታል።
የጉዲዩ አመጣጥ እንዱህ ነው፡- ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 መሰረት ባቀረበችው የመቃወም አቤቱታ መነሻነት ሲሆን የአሁን ተጠሪዎች እንደ ቅደም ተከተላቸው የመቃወም ተጠሪዎች በመሆን ተከራክረዋል። አመልካችና ሁለተኛ ተጠሪ ባልና ሚስት 1ኛ ተጠሪ ደግሞ የ2ኛ ተጠሪ አባት ናቸው። ለአመልካች መቃወም አቤቱታ ምክንያት የሆነው ውሣኔ የተሰጠው መገኛ ቦታውና አዋሳኙ በክሱ ውስጥ የተጠቀሰውን የከተማ ይዜታ ላይ 1ኛ ተጠሪ የሰሩትን ቤት 2ኛ ተጠሪ ለጊዚው እንዱኖርበት ሰጥተውት እንዱያስረክባቸው ሲጠይቁት ፈቃደኛ ባለመሆኑ እንዱያስረክባቸው እንዱወሰንላቸው ክስ አቅርበው 2ኛ ተጠሪም ቤቱ የአንደኛ ተጠሪ መሆኑንና ለማስረከብ ፈቃደኛ መሆኑን በማመን መልስ መስጠቱን ተከትል በዘሁ መሰረት እንዱያስረክብ ተወስኗል። አመልካች ውሣኔ የተሰጠበት ንብረት በጋብቻ የተፈራ የአመልካችና የ2ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረት ሆኖ ሣለ በክርክሩ ሣትካፈል የተሰጠው ውሳኔ መብቷን የሚጎዲ መሆኑን በመዖርዖር ቀደም ሲል የተሰጠው ፍርድ እንዱሻር ግንቦት 23ቀን 2009ዓ/ም በተፃፈ የመቃወም አቤቱታዋን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 መሰረት አቅርባለች።
በመቃወም አቤቱታው ላይ መልስ እንዱሰጡ የታዖዘት ተጠሪዎች የመልስ ክርክራቸውን በተናጠል አቅርበዋል። በዘህም መሰረት 1ኛ ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ይዜታ ቀደም ሲል ከመምህር ምትኩ ወንድማገኝና ከወ/ሮ አስናቀች ካሣሁን የገዙው የራሱ ንብረት መሆኑን የመቃወም አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ተጋብተው ቤቱ ውስጥ ሲኖሩ የነበረው በ1ኛ ተጠሪ ፍቃድ በመሆኑ አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ቤቱ ላይ ምንም አይነት መብት የላላቸው መሆኑን፤ 2ኛ ተጠሪ በበኩለ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የመቃወም አመልካችና የ2ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረት አለመሆኑን ይልቁንም ኪራይ እየከፈለ እንዱኖሩበት አንደኛ ተጠሪ የሰጣቸው መሆኑን በመዖርዖር ቀደም ሲል የተሰጠው ፍርድ ሉለወጥ አይገባም ሲለ ተከራክረዋል።
የመቃወም አቤቱታው የቀረበለት የስር ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በኮልፋ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዲ 03 በቤት ቁጥር አዱስ ተብል የሚታወቀው ይዜታ ላይ አመልካች መብት አላት ወይስ የላትም? የሰራችው ቤት አለ ወይስ የለም? የሚለውን ጭብጥ ይዜ ክርክሩን ከመረመረ በኋላ ሐምል 23ቀን011 ዓ.ም በዋለው ችልት አንደኛ ተጠሪ ይዜታውን በሁለተኛ ተጠሪ ስም ገዛቶ ሁለት ክፍል ቤት ሰርቶ ሲያስተዲድረው የነበረ መሆኑ ስለተረጋጠ እነዘህ ሁለት ክፍል ቤቶች የአንደኛ ተጠሪ የግል ንበረቶች መሆናቸውን፤ በልላ በኩል አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ተጋብተው በቤቱ ውስጥ እየኖሩ አራት ልጆች አፍርተው ሁለት ክፍል ቤቶች መስራታቸውና ቤቶቹን ሲሰሩም አንደኛ ተጠሪ አለመቃወሙ ተረጋግጧል በሚል በአከራካሪው ይዜታ ላይ 2ኛ ተጠሪ በግለ በመገንባቱ ከተረጋገጡት ሁለት ክፍል ቤቶች በስተቀር ቀሪዎቹ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት መሆናቸውን ነግር ግን የሁለተኛ ተጠሪን ድርሻ በሚመለከት መብት የለኝም ሲል ክርክር ማቅረቡ መብቱን ለአንደኛ ተጠሪ እንደተወው የሚቆጠር በመሆኑ የሱ ድርሻ ለአንደኛ ተጠሪ የሚገባ መሆኑን በመዖርዖር ቀደም ሲል የሰጠውን ውሣኔ በመለወጥ ብይን ሰጥቷል።
አመልካች ይሀን ብይን በመቃወም የይግባኝ አቤቱታዋን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበች ቢሆንም ስለተሰረዖባት የያዛነውን የሰበር አቤቱታ አቅርባለች። አመልካች ሰኔ 13ቀን 2011ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታዋ አመልካችና 2ኛ ተጠሪ በጋራ ያፈሩት ቤት ይዜታ ላይ ሁለት ክፍል በጭቃ የተሰራ ቤት የ1ኛ ተጠሪ መሆኑ በተገቢው ሣይረጋጥ፣ የአመልካችና የሁለተኛ ተጠሪ የፀና ጋብቻ እያለ የጋራ ንብረታቸው የሆነውን ቤት ወደ ሶስተኛ ወገን እንዱተላለፍ መደረጉ፣ 2ኛ ተጠሪ ድርሻ የለኝም ብል መከራከሩን ተከትል የባልና ሚስት ንብረት ግማሹ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱተላለፍ መወሰኑ በጋብቻ የተወለደ ልጆችን ህጋዊ መብት የሚያሳጣ መሆኑን፣ ከኮ/ቀ/ክ/ከ/ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ይዜታውና ቤቱ በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ ባልና ሚስት ስም መሆኑን ማስረጃ ቀርቦ እንዱረጋገጥ በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 145 መሰረት የቀረበው ክርክር በማለፍ የተሰጠው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብል እንዱታረምላት ክርክሯን አቅርባለች።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ የመረመረው አጣሪ ችልት የአመልካችና የ2ኛተጠሪ ጋብቻ እንዱፈርስ ባልተወሰነበት የስር ፍ/ቤት የንብረት ክፍፍል ውሳኔ የመስጠቱ ተገቢነት ላይ ግራቀኙ እንዱከራካሩ ትዔዙዛ በመስጠቱ ክርክራቸውን በፅሁፍ አቅርበዋል።
1ኛተጠሪ ጥቅምት06ቀን2012 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው መልስ ክርክር የቀረበበትን ቤት ባልና ሚስቱ ሳይጋቡ መስራቱን መኖሪያ አጥተው ሲቸገሩ ኪራይ እየከፈለ እንዱኖሩበት ፈቅድላቸው ሲኖሩበት የቆየውን ቤት እንዱለቁለት ክስ ማቅረቡን፣ ባልና ሚስቱ በቤቱ ውስጥ ሲኖሩ የሰሯቸው ቤቶች በልላ ሰው ይዜታ ላይ ከባለቤቱ ተቃውሞ ውጭ ቤቱ ከተሰራ የቤቱ ባለቤት ይሆናል ቢባልም 2ኛ ተጠሪ ባመነው መሰረት የተወሰነለት መሆኑን፣ የስር ፍ/ቤት ውሣኔ የሰጠው የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ክፍፍል እንዱደረግ ሳይሆን ተጠሪ በፍ/ህ/ቁ 1257ና ተከታዮቹ ድንጋጌ መሰረት የጋራ ባለሀብቶች ንብረታቸውን ለመከፊፈል ያቀረበውን ክርክር መሰረት በማድረግ መወሰኑን፣ የጋራ ልጆችን መብት ይጎዲል የሚለው የአመልካች ክርክር በሚመለከት ተጋቢዎች ልጆቻቸውን የሚያሣድጉት በራሳቸው ንብረት እንጅ በልላ ሰው ንብረት አለመሆኑን በመዖርዖር የስር ፍ/ቤት የወሰነው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አልተፈፀመም ተብል እንዱፀናለት ክርክሩን አቅርቧል።
2ኛ ተጠሪ በበኩለ መስከረም 6ቀን 2012 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው መልሱ ክርክር የተነሳበት ቤት የ1ኛ ተጠሪ ሲሆን አመልካችና 2ኛ ተጠሪ እንዱኖሩበት በ1ኛ ተጠሪ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑን፣ በኋላም 1ኛ ተጠሪ ሣይፈቅድ አመልካችና 2ኛ ተጠሪ አንስቶ ለመውሰድ የማያስቸግሩ በላስቲክና በእንጨት ቀላል ቤቶችን መገንባታቸውን፣ ቤቶቹንም የገነቡት 1ኛ ተጠሪ እንዱነሳለት በፈለገ ጊዚ አንስተው ለመውሰድ ከአመልካች ጋር ተስማምተው መሆኑን፣ቤቶቹ በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ የተገነቡ የጋራ ንብረቶች ናቸው ከተባለ ክፍፍለ ላደረግ የሚገባው 1ኛ ተጠሪ በአንድ ወገን ሆኖ ቀሪው ወይም ግማሹ አመልካችና 2ኛ ተጠሪ በጋራ ሀብትነት እንጅ ለአመልካች ብቻ የሚከፈልበት ምክንያት ሉኖር አይገባም ሲል ክርክሩን አቅርቧል።
አመልካች ጥቅምት 24ቀን2011 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልሷ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን በልጃቸው ስም እንደገዘ የሚገልፁት በለማጭበርበር እንጅ በእርሳቸው ስም ምንም ነገር የላለና የክፍለ ከተማው አስተዲደር በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ ስም ካርታ ሉሰጣቸው በዛግጅት ያለ መሆኑን፣ በጋብቻ የተፈራን ንበረት ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ ዲኝነት ባልተጠየቀበት ሁኔታ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት ሉኖረው የማይገባ መሆኑን፣ 2ኛ ተጠሪ የአከራካሪው ንብረት ግማሽ ባለድርሻ መሆኑን በመግለፁ ርስ በርሱ የሚጻረር ክርክር ማቅረቡን፣ ጋብቻው በፍች ሳይፈርስ በጋብቻ የተፈራ የጋራ ሀብትን እንዱከፊፈል መወሰን ህጋዊ አለመሆኑን በመዖርዖር የሰበር ክርክሯን አጠናክራለች።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል የአመልካችን ቅሬታ ከስር ፍ/ቤት ውሣኔና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምረናል። እንደመረመርነውም በዘህ ችልት ውሣኔ እንዱሰጥበት የተፈለገው የክርክር ጭብጥ ተጋቢዎች በጋብቻቸው ወቅት የተፈራ የጋራ ንብረት ላይ የይግባኛል ክስ በቀረበ ጊዚ ከተጋቢዎች መካከል አንደኛው ቀርቦ ንብረቱ የባልና ሚስቱ የጋራ ንብረት ሣይሆን የከሣሹ ነው ሲል አምኖ በመከራከሩ በዘሁ መሰረት በተሰጠ ውሣኔ ላይ የመቃወም አቤቱታ ቀርቦ በክርክር ሂደቱ ንብረቱ በጋብቻ የተፈራ የጋራ ንብረት መሆኑ ቢረጋገጥም ከተጋቢዎች መካከል አንደኛው ንብረቱ የእሱ አለመሆኑን ማመኑ ድርሻውን ለከሣሹ እንደለቀቀ የሚያስቆጥረው ነው በሚል ጋብቻው ሣይፈርስ የጋራ ንብረቱን ግማሽ ንብረቱ የኔ ነው ሲል ለጠየቀው ይሰጥ ሲል የመወሰኑን ተገቢነት ነው።
መርምረን እንደተረዲነው አመልካች ያቀረበችውን የመቃወም አቤቱታ ተከትል በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ይዜታ 1ኛ ተጠሪ በሁለተኛ ተጠሪ ስም ገዛቶ ሁለት ከፍል ቤት መስራቱ፤ አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ትዲር መስርተው ልጆችን አፍርተው በአከራካሪው ቤት ውስጥ ከ1995ዓ/ም ጀምሮ እየኖሩ መሆኑና በይዜታው ውስጥም የተለያዩ ቤቶችን መስራታቸውንና እነዘህ ንረብረቶችም በጋብቻው የተፈሩ የጋራ ንብረት መሆናቸው፣ ጋብቻቸውም ያልፈረሰ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል።
በመሆኑም በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አንደኛ ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ይዜታ በሁለተኛ ተጠሪ ስም ስለመግዙቱና በዘህ ይዜታ ላይ ሁለት ክፍል ቤት የሰራ የተረጋገጠ ሲሆን ነገር ግን ሁለተኛ ተጠሪ እንደሚያቀርበው ክርክር በይዜታው ላይ የሚገኙት ሁለም ቤቶች የአንደኛ ተጠሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በማቅረብ አለማረጋጡን ተገንዛበናል። በመሆኑም በሁለተኛ ተጠሪ ስም ከላላ ሰው በተገዙው ይዜታ ላይ ከሚገኙት ቤቶች መካከል አንደኛ ተጠሪ ከሰራቸው ሁለት ክፍል ቤቶች በስተቀር ላልች ቤቶች በአመልካችና በሁለተኛ ተጠሪ በጋራ የተሰሩ የጋራ ሀብቶች መሆናቸው በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ተረጋግጧል።
በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 34(4) ድንጋጌን መሰረት በማድረግ በተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 መግቢያ ላይ እንደተደነገገው ጋብቻ በሕግ ልዩ ጥበቃ ላደረግለት የሚገባ በአንድ ወንድና አንድ ሴት መካከል የሚፈጠር በስሩ የሕብረተሰብ መነሻ የሆነውን ቤተሰብ የሚባለውን ተቋም የሚፈጥር መስተጋብር መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ልዩ ዛርዛር ሕግጋት ተደንግጋዋል። በተጋቢዎች መካከል የተፈፀመው ጋብቻ የሕግ ጥበቃ ይደረግለታል ሲባል ጋብቻ መፈፀሙን ተከትል ለሚመጡ ውጤቶች ጥበቃ ማድረግን የሚያጠቃልል ነው። በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል የሚፈፀመው ጋብቻ ሕጋዊ ድርጊት በመሆኑ ከሚያስከትላቸው ውጤቶች መካከል በተጋቢዎች መካከል ኢኮኖሚያዊ ውህደትን በመፍጠር የጋራ ንብረትን ማፍራትና በጋራ ማስተዲደር መብትን መፍጠሩ የሚጠቀስ ነው። የጋራ ንብረትን(ሃብትን) በጋራ ማስተዲደር ሲባል በጋራ ሃብቶቻቸው ላይ የይገባኛል ክስ ወይም ክርክር በቀረበ ጊዚ የሁለቱን ተጋቢዎችና ጋብቻው ያፈራቸውን የቤተሰብ አባላት መብትና ጥቅም ማስጠበቅ የሚችል እውነተኛ ክርክርን ማቅረብን የሚያካተት ላሆን ይገባል። ክርክሩ የቀረበላቸው ፍርድ ቤቶችም በጋብቻ ሣይፈርስ በተጋቢዎች የጋራ ሃብት ላይ የአንደኛውን ተጋቢ መብት ወይም ጥቅም በሚመለከት የሚሰጧቸው ውሳኔዎች የተጋቢዎች የጋራ ሃብት ጋብቻው እስካልፈረሰ በመርህ ረገድ እንደ አንድ ሀብት የሚቆጠር እንጅ የእያንዲደ ተጋቢ ድርሻ በእርግጠኝነት ተለይቶ የማይታወቅ መሆኑንም ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
በመሆኑም ተጋቢዎች በጋብቻቸው ወቅት ያፈሩትን የጋራ ሀብት እንደ አንድ ሀብት የሚቆጠር እንጅ ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ጊዚ ያለተጋቢዎች ስምምነት የጋራ ሀብት ሆኖ መቀጠለን የሚያሣጣ ውሣኔ መስጠት ንብረትን በሚመለከት በሕግ ጥበቃ የተደረገለትን የተጋቢዎች መብት የሚጥስ የጋብቻ ተቋማዊ ባህሪ የሚያሣጣ በመሆኑ ተቃባነት ሉኖረው አይገባም።
ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ክርክር ካስነሣው ቤት እና ይዜታ መካከል አንደኛው ተጠሪ በግለ መስራቱ በማስረጃ ከተረጋገጠው ሁለት ክፍል ቤቶች በስተቀር ላልች ቤቶችን አመልካችና የሁለተኛ ተጠሪ በጋብቻቸው ወቅት የሰሯቸው የጋራ ሀብታቸው መሆኑ በተረጋገጠበት፤
የአመልካችና የሁለተኛ ተጠሪ ጋብቻቸው ፀንቶ ባለበት፣ የእያንዲንደ ተጋቢ ድርሻ ተለይቶ ስለማይታወቅ እንደ አንድ ሀብት የሚቆጠረውን የጋራ ሃብት የጋራ ሀብት ሆኖ መቀጠለን በሚያሣጣ ሁኔታ 1ኛ ተጠሪ ከሰራው ሁለት ክፍል ቤት ውጪ ያለው ቤት የአመልካችና የ1ኛ ተጠሪ ነው ሲል መወሰኑ የፋዳራል መንግስቱን የተሻሻለ የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 62(1) እና 66 የደነገገጉትን መርህ የሚጥስ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ውሣኔ ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ ሐምል 23ቀን 2010ዓ/ም በዋለው ችልት በአሁን አመልካች የቀረበውን የመቃወም አቤቱታ ተከትል የቀረበውን ክርክር ከጣራ በኋላ የሰጠው ብይን እንዱሁም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ መጋት 17ቀን 2011ዓ/ም የሰጠው ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት አንደሚከተለው ተሻሽለዋል።
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው በኮልፋ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዲ 03 በምስራቅና በምዔራብ መንገድ በሰሜን አቶ አሰፊ ደስታ እና በደቡብ አቶ ንጉሴ ኢርሻ የሚያዋስነው ይዜታና በይዜታው ላይ የተሰሩት ቤቶች መካከል ሀ) አንደኛ ተጠሪ በግለ የሰራቸው ሁለት ክፍል ቤቶች የአንደኛ ተጠሪ ናቸው ብለናል።
ለ) በዘህ ውሳኔ ተራቁጥር 2(ሀ) ከተጠቀሱት ሁለት ክፍል ቤቶች በስተቀር በአከራካሪው ይዜታ ላይ የሚገኙት ላልች ቤቶች(ግንባታዎች) በሙለ አመልካችና ሁለተኛ ተጠሪ በጋብቻቸው ያፈሯቸው የጋራ ሀብታቸው ናቸው ብለናል።
በዘህ ክርክር ግራ ቀኙ ያወጡትን ወጪ በሚመለከት ግራ ቀኙ የዬራሣቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.