ከልጅ አስተዲደግ ክርክር ጋር በተያያዖ ልጁ ፍላጎቱን መግለጹን ብቻ መሰረት በማድረግ የሚወሰን ሳይሆን በማኅበራዊ ሳይንስ ባለሙያ የልጁ አስተዲደግና መልካም ደህንነት፣ጥቅምን ( the best interests of xiii ተ.ቁ የሕግ ትርጉም የተሰጠበት ጉዲይ the child ) በሕገ መንግሥቱና በዛርዛር ሕግ የተመለከተው በቀዲሚነት ታሳቢ ተደርጎ የሚወሰን ስለመሆኑ። የኢፋዳሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 36 የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁ /1992 አንቀጽ 218 የሕጻናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 3 ወ/ሮ ድንቅነሽ ስለሺ
No summary available.
የካቲት 28 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡ …….አቶ ገዙኽኝ ይልማ፡- የቀረበ የለም ተጠሪ፡ ………….ወ/ሮ ዱንቅነሽ ስለሺ፡- ቀርበዋል ይህ መዛገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የፍቺ እና የልጅ አስተዲደግ ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች እና የአሁን ተጠሪ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.260816 ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን ተጠሪ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት የክስ አቤቱታ፤ አመልካች እና ተጠሪ ጋብቻ ፈጽመን አንድ ልጅ ወልደን አብረን እየኖርን ሳለ አሁን በመካከላችን በተፈጠረዉ አለመግባባት አብረን መቀጠል ስለማንችል ጋብቻችን ፈርሶ የ7 ዓመት እድሜ የሆነዉ ኢዮኤል ገዙኽኝ ለመልካም አስተዲደጉ ሲባል በአሁን ተጠሪ ዖንድ እንዱያድግና አመልካች ቀለብ እንዱቆርጥ እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
የአሁን አመልካች በዘህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ ከተጠሪ ጋር ባለን ጋብቻ የተጠቀሰዉን ልጅ መዉለዲችን ይታወቃል፤ ለቀረበዉ የፍቺ ጥያቄ ማሰላሰያ ጊዚ እንዱሰጥ፤ ልጁ በመልካም ሥነምግባር እንዱያድግ በአመልካች ዖንድ እንዱያድግ እንዱወሰን በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በማከራከር በሳለፈዉ ዉሳኔ ግራ ቀኙ ጋብቻ መኖሩ ላይ የተማመኑ በመሆናቸዉ፣ እንዱታረቁ ጥረት ቢደረግም ሉሳካ በለመቻለ ጋብቻቸዉ በፍቺ ዉሳኔ ፈራሽ እንዱሆን የወሰነ ሲሆን፤ የልጅ አስተዲደግን በተመለከተ ፍ/ቤቱ የማህበራዊ ባለሙያዎች ሕጻን ኢዮኤል ገዙኽኝ ለመልካም አስተዲደጉ ሲባል ማን ቢያድግ ይበጃል የሚለዉን ጥናት አድርገዉ እንዱያቀርቡ ባዖዖዉ መሰረት ባቀረበዉ ሪፖርት ከሕጻኑ ጥቅምና ደህንነት አንጻር ከአሁን ተጠሪ ዖንድ ማደግ ይባል ያለዉን በተመለከተ የአሁን ተጠሪ አስተያየት ያቀረበች ሲሆን የአሁን አመልካች ያቀረበዉ አስተያየት ባለመኖሩ፤ ፍ/ቤቱ ሪፖርቱን በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ የማህበራዊ ባለሙያ ሪፖርት ተጨባጭ ሁኔታን መሰረት በማድግ የቀረበ በመሆኑ ተዓማኒ ነዉ በማለት በመቀበል፣ ለሕጻኑ እድገት የተሻለ የሚሆነዉ በእናቱ ዖንድ በአሁን ተጠሪ ዖንድ እንዱያድግ በማለት በመወሰን፣ የአሁን አመልካች ሕጻኑን የሚጎበኝበት አግባብና ቀለብ በወር ብር 3000 እንዱከፍል ወስኗል።
የአሁን አመልካች የሥር ፍ/ቤት የልጅ አስተዲደግና ቀለብን በተመለከተ ያሳለፈዉን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር ሕጻን ኢዮኤል ገዙኽኝ በእናቱ በአሁን ተጠሪ ዖንድ መወሰኑ የሚነቀፍበት አግባብ የለም፤
ቀለብን በተመለከተ ግን የአሁን አመልካች በወር ብር 2300 ለልጅ ቀለብ እንዱከፍል በማለት የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማሻሻል ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ30/10/2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የሥር ፍ/ቤት በሕጉ አግባብ የሕጻኑን ጥቅም ብቻ መሰረት በማድረግ ዉሳኔ መስጠት ሲገባዉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎቹ በአግባቡና በተሟላ ሁኔታ ጥናት ሳያደርጉ ያቀረቡትን ሪፖርትና ሪፖርቱም ልጁ ከአመልካች ጋር መኖር እንደሚፈልግ የሚገልጽ ሆኖ ሳለ፣ ሕጻን ኢዮኤል ገዙኽኝ ከአመልካች ዖንድ እንዱያድግ ተስማምተን በዘህ መሰረት ማመልከቻም አቅርበን፤ የሥር ፍ/ቤት ይህን ስምምነት በማለፍ በተጠሪ ዖንድ እንዱያድግ የሰጠዉ ዉሳኔ የሕጻኑን መብትና ጥቅም የሚጎዲና የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣የግራ ቀኙ ልጅ አስተዲደግ በተመለከተ የማህበራዊ ባለሙያ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ሪፖርት ልጁ ከአመልካች ጋር መኖር እንደሚፈልግ ተጠቅሶ እያለ፣ አመልካች በፍ/ቤቱ እና በባለሙያ ላይ አሳይተዋል በተባለዉ ባህርይ ብቻ ልጁ ከተጠሪ ጋር እንዱያድግ በማለት የመወሰኑን አግባብነት፣ ለማጣራት ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ ባዖዖዉ መሰረት ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ የሥር ፍ/ቤቶች የሕጻኑን አስተዲደግ በተመለከተ በማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች በማስጠናት ሕጻኑ በተጠሪ ዖንድ እንዱያድግ ያቀረበዉን ሪፖርት መሰረት በማድረግ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የላለዉ በመሆኑ እንዱጻናልኝ በማለት ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የመልስ መልስ ያቀረቡት ባለመኖሩ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ አመልካች ባቀረቡት ክርክር ለሕጻን ኢዮኤል ገዙኽኝ መልካም ሥነ-ምግባር ሲባል አመልካች ዖንድ ማደግ ይገባል በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤ ተጠሪ በበኩላቸዉ ባቀረቡት ክርክር ለሕጻኑ መልካም አስተዲደግ ሲባል ከተጠሪ ዖንድ ማደግ ይገባል በማለት ተከራክሯል። የሥር ፍ/ቤት ፍሬ ነገር የማጣራትና ማስረጃ የመመርመርና የመመዖን በሕግ በተሰጠዉ የዲኝነት ስልጣን መሰረት በማድረግ የሕጻኑን ደህንነትና ጥቅም ከግምት በማስገባት ማን ጋር ቢያድግ ይሻሻል የሚለዉን በተመለከተ ተጨባጥ ሁኔታን መሰረት በማድረግ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ጥናት አድርገዉ እንዱያቀርቡ ባዖዖዉ መሰረት ባለሙያዎቹ ባቀረቡት ሪፖርት አመልካች ከሚያሳየዉ በንግግር አለመግባት፣ ቁጡነት እና ሃይለኝነት ባህርይ አንጻር ሲታይ ከእናቱ ከአሁን ተጠሪ ዖንድ ቢያድግ የተሻለ መሆኑን የሚያመለክት ስለሆነ፣ ሪፖርቱም ተዓማኒ በመሆኑ፣ ሕጻኑ ከተጠሪ ጋር እንዱያድግ በማለት መወሰኑን የዉሳኔዉ ግልባጭ ያሳያል። በዘህ መሰረት አሁን ከግራ ቀኙ የቀረበዉን ክርክር አግባብነት ባላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች አንጻር መመርመሩ ተገቢ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ በኢፋዳሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 36 ሥር እንደተመለከተዉ ሕጻነት የወላጆቻቸዉን እንክብካቤ የማግኘት መብት ያላቸዉ መሆኑን፣ ማንኛዉም መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሕጻናትን የሚመለከቱትን እርምጃዎች በሚወስደበት ጊዚ የሕጻናቱን ደህንነት በቀደምትነት ታሳብ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸዉ አዉጆት እናገኛለን።
የሕጻናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 3 ሥር እንደተመለከተዉ ሕጻናትን አስመልክቶ ማናቸዉም እርምጃዎች የሕጻናቱን ደህንነትና ጥቅምን {the best interests of the child} በቀደምትነት ከግምት ማስገባት እንደሚገባቸዉ ተመልክቷል። እንዱሁም የፋዳራለ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 218 እና ላልችም ድንጋጌዎች የሕጻናት አስተዲደግን በተመለከቱ የሚወሰኑ ዉሳኔዎችና የሚወሰደ እርምጃዎች ለልጆች ደህንነት፣ ጥቅምና መልካም አስተዲደግ የሚበጁ መሆን እንዲለበቸዉ ይደነግጋለ።
በዘህ መሰረት አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ የሥር ፍ/ቤቶች የግራ ቀኙን የኑሮ ሁኔታ፣ የሚያሳዩትን ባህርይ እና የልጁን እድሜ ታሳቢ በማድረግ፤ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች እነዘህን ሁኔታዎች በማጥናት ያቀረቡትን ሪፖርት በመመርመር፤ ከልጁ ደህንነት፣ ጥቅምና መልካም አስተዲደግ አንጻር ሲታይ ሕጻን ኢዮኤል ገዙኽኝ በአሁን ተጠሪ ዖንድ እንዱያድግ ድምዲሜ ላይ በመድረስ ዉሳኔ ማሳለፈን ማየት ይቻላል። ከዘህ አንጻር አመልካች ባቀረቡት ቅሬታ የማህበራዊ ባለሙያዎች በአግባቡና የተሟላ ጥናት ሳያደርጉ ያቀረቡት ሪፖርት መሰረት ተደርጎ ዉሳኔ ተሰጥቷል ይበለ እንጂ በሪፖርቱ ላይ አስተያየታቸዉን እንዱያቀርቡ ትዔዙዛ ሲሰጥ በዘህ አግባብ ያለት ነገር አለመኖሩን፤ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደረገዉ ክርክርም እንዱህ አይነት ነገር መኖሩ የተረጋገጠበት ሁኔታ የሚያሳይ ነገር የለም።
በልላ በኩል አመልካች ባቀረቡት ቅሬታ በዘህ ሪፖርት ሕጻኑ ከአመልካች ጋር ለመኖር ገልጾ እያለ ይህ ፍላጎቱ ከግምት ሳይገባ ከተጠሪ ጋር እንዱያድግ መወሰኑ የሕግ ስህተት ነዉ በማለት የተከራከሩ ሲሆን፣ በሥር ፍ/ቤት የቀረበዉ ሪፖርት ይህን ሁኔታ እንደሚያመለክት ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ነገር ግን ከግራ ቀኙ ክርክር መረዲት እንደሚቻለዉ የግራ ቀኙ የጋራ ልጅ የሆነዉ ሕጻን ኢዮኤል ገዙኽኝ በወቅቱ እድሜዉ የ7 ዓመት ልጅ ሲሆን፣ የልጁን አስተዲደግ አስመልክቶ ዉሳኔ ከመሰጠቱ በፉት ሃሳቡን እንዱሰጥ ፍላጎቱን እንዱገልጽና በዘህ አግባብ ተሳታፍ እንደሆነ ማድረግ ተገቢ ቢሆንም፣ አጠቃላይ የግራ ቀኙን የኑሮ ሁኔታ እና የልጁ እድሜ መሰረት በማድረግ ለልጁ ደህንነት፣ ጥቅምና መልካም አስተዲደግ የሚበጃዉን በመመርመር ዉሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል እንጂ የልጁን ፍላጎት ብቻ መሰረት በማድረግ የሚወሰን ከሆነ፣ በሕገ መንግስቱና በዛርዛር ሕግ የተመለከተዉን የልጆች ደህንነት በቀዲምነት ታሳቢ መደረግ አለበት ተብል የተደነገገዉን ማሳካት የሚቻል አይሆንም። የልጁን ፍላጎት ከአጠቃላይ ከግራ ቀኙ የኑሮ ሁኔታና ባህርይ አንጻር ተመዛኖና ተመርምሮ መወሰን የሚገባዉ እንጂ የሕጻኑን ፍላጎት ብቻ መሰረት የሚያደርግ ከሆነ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎችን መድቦ ጥናት ማስደረግም ባላስፈለገ ነበር። በመሆኑም የአሁን አመልካች ባቀረቡት ቅሬታ የቀረበዉ ሪፖርት በአግባቡና የተሟላ ጥናት ሳይደረግ የቀረበና የልጁን ፍላጎት ታሳብ ያላደረግ ዉሳኔ ነዉ ያለት ፍሬ ነገርና የማስረጃ ጉዲይ መሆኑን ተገንዛበናል። ስለሆነም ይህ ችልት በኢፋዳሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80 (3፣ ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 (1) መሰረት ከተሰጠዉ የዲኝት ስልጣን አንጻር አመልካች ያቀረቡት ቅሬታ የፍሬ ነገርና የማስረጃ ጉዲይ መሆኑን ከሚያሳይ በስተቀር የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ መሆኑን የሚያመለክት ስላልሆነ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የግራ ቀኙን ክርክር መሰረት በማድረግ የልጅ አስተዲደግን በተመለከተ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ጥናት አድርገዉ እንዱያቀርቡ በማድረግ በማጣራት ለልጁ ደህንነትና መልካም አስተዲደግ ተጠሪ ዖንድ ማደግ ይሻላል በማለት የሰጡት ዉሳኔ በሕግ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት ስለማይቻል ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.260816 ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ጸንቷል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ችልት በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በአፈጻጸም መ.ቁ.281096 ላይ የተጀመረዉ የአፈጻጸም ክርክር እንዱታገድ የሰጠዉ ትዔዙዛ እና ከልጅ ጉብኝነት ጋር በተያያዖ ነሐሴ 5 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ በዘህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.