No summary available.
የሰበር መዛገብ ሐምል 25 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካቾች፡- አቶ ወልዳ ወልደገብርኤል ጠበቃ አቶ በፍቃደ ስዩም ወ/ሮ አለምፀሐይ ወልዳገብርኤል ከ2ኛ አመልካች ጋር ቀርቧል ተጠሪ፡- አቶ ደጀኔ በቀለ አቶ ፀጋዬ በቀለ ፓስተር ሙለቀን በቀለ ቀርቧል ወ/ሮ ውድነሽ በቀለ አቶ እንዲልካቸው በቀለ አቶ ታዬ በቀለ ለምርመራ ተቀጥሮ የነበረው መዛገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ተጠሪዎች ከሟቿ ወ/ሮ መንበረ ወገብርኤል ጋር የዛምድና ትስስር ሳይኖራቸው የሟቿ ባለቤት የነበሩት የተጠሪዎች አባት ለሆኑት ሟች አቶ በቀለ ጅሩ ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም የተደረገ የቁም የኑዙዚ ሰነድ በማያያዛ አባታቸውን በመተካት የሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ድርሻ የሆነውን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 09 የሚገኘውን ቁጥሩ 817 የሆነው ቤት እና ይዜታ ይገባናል ክርክር ፤ የተጠሪዎች አባት ነሐሴ 8 ቀን 2005 ዓ/ም ከዘህ ዓለም በሞት ሲለዩ የቁም ኑዙዚ ሰጪዋ ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል በሕይወት የነበሩ በመሆኑና ኑዙዚውም ሟች አቶ በቀለ ጅሩ የተናዙዧን ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል የቀብር ሥነ ሥርዓት በአዲዱ ማሪያም ቤተክርስቲያን እንዱያስፈፅሙ የሚል ቅድመ ሁኔታ ያለበት ሆኖ ቅደመ ሁኔታው ሳይሟላ የተጠሪዎች አባት የሆኑት አቶ በቀለ ጅሩ ነሐሴ 8 ቀን 2005 ዓ/ም ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤልን ቀድመው የኑዙዚ ወራሽነታቸውን ሳያረጋግጡ መሞታቸው እና ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤልም ህዲር 18 ቀን 2011 ዓ/ም መሞታቸው ያልተካደ እና በማስረጃ የተረጋገጠ ሆኖእያለ ፣ ኑዙዚ የተደረገበት ቤትእና ይዜታ የባልና ሚስቱ የጋራ ንብረት ሆኖ ስምምነቱ በፍርድ ቤት ባልፀደቀበት ፣ ተጠሪዎች የአባታቸው ድርሻ ወራሽ በመሆን የእንጀራ እናታቸው ከሆኑት ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ተካፍለው እያለ የአመልካቾች እህት ድርሻ የሆነውን የውርስ ንብረት ተጠሪዎች በምትክነት ሉወርሱ ይገባል በማለት የተሰጠው ውሳኔ የሕግ መሰረት የላለው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ስህተቱ ታርሞ በአዱስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 09 የሚገኘው ቁጥሩ 817 የሆነው ቤት እና ይዜታ አመልካቾች የሟች እህታቸው ድርሻ ወራሾች ናቸው ተብል እንዱወስንላቸው ህዲር 27 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችልት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻነት መዛገቡ ተከፍቶ ለችልት ቀርቧል።
ጉዲዩ ሟቾቹ የተጠሪዎች አባት አቶ በቀለ ጅሩ እና የእንጀራ እናታቸው ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል በጋራ የነበራቸውን በአዱስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 09 ውስጥ የሚገኝ ቁጥሩ 817 የሆነ ቤት እና ይዜታ የሟች አባታቸው ድርሻ በውርስ የተላለፈላቸው ሲሆን ፤ የእንጀራ እናታቸው ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ከቤቱ ያላቸውን ደርሻቸው ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም በተደረገ ግልጽ ኑዙዚ ለሟች አባታቸው አቶ በቀለ ጅሩ ስላስተላለፈ የአባታቸው የውርስ ድርሻ እንዱጣራላቸው ተጠሪ በላለበት ለፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ወርስ እንዱጣራ አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም የሟች የአቶ በቀለ ጅሩ ውርስ ስለተጣራ መጣራት ያለበት የሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ነው በማለቱ ተጠሪዎች በዘሁ አግባብ ክሳቸውን አሻሽለው አቅርበዋል። ተጠሪዎች ተጣርቶ በቀረበው የውርስ አጣሪ ሪፖርት ላይ በሰጡት አስተያየት ሟች የእንጀራ እናታቸው ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ለሟች አባታቸው አቶ በቀለ ጅሩ ድርሻቸውን በኑዙዚ የሰጡ በመሆኑ አመልካቾች በክርክሩ ጣልቃ ገብተው የመከራከር መብት እና ጥቅም የላላቸው መሆኑን ፤ ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ባደረጉት ግልጽ ኑዙዚ ከሟች የተጠሪዎች አባት ጋራ ያፈሩትን የጋራ ንብረት ድርሻቸውን ሟች የተጠሪዎች አባት ለሆኑት አቶ በቀለ ጅሩ በተናዖዘት አግባብ እንዱጣራ የጠየቁ በመሆኑ አመልካቾች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ኑዙዚ ሳታኖር ከዘህ ዓለም በሞት የተለየች በመሆኑ እና እናት እና አባታቸው አስቀድመው ስለሞቱ ተተኪ ወራሽነታችንን አረጋግጠናል በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ተቃውመዋል።
አመልካችቾም በሰጡት አስተያየት አቶ በቀለ ጅሩ የሞቱት ሐምል 8 ቀን 2005 ዓ/ም ሲሆን ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ደግሞ ህዲር 18 ቀን 2011 ዓ/ም የሞቱ በመሆኑ ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም አድርገዋል የተባለውን ኑዙዚ አቶ በቀለ ጅሩ መቀበላቸው ባልተረጋገጠበትና አቶ በቀለ ጅሩ አስቀድሞ ስለሞቱ በኑዙዚው ላይ የተመለከተው ቅድመ ሁኔታ ባለመፈፀሙ አቶ በቀለ ጅሩ የኑዙዚ ግዳታቸውን ያልተወጡ በመሆኑ ሪፖርቱ ውድቅ እንዱሆን ጠይቀዋል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም አቶ በቀለ ጅሩ ከሟች ባለቤታቸው ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል በኑዙዚ ያገኙትን ሀብት ተጠሪዎች አባታቸውን ተክተው መውረስ መቻል አለመቻላቸውን እና ላልች አግባብነት አላቸው ያላቸውን ጭብጥ ይዜ የግራቀኙን ምስክሮች ሰምቶ እና ተገቢ ነው ያለውን ማጣራት አድርጎ ጉዲዩን እንደመረመረው፡- በአዱስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 09 የሚገኘው ቁጥሩ 817 የሆነው ቤት እና ይዜታ ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤልና የቀድሞ ባለቤታቸው አቶ ደምሴ ወልደማሪያም ጋብቻ ውስጥ ተፈርቶ አቶ ደምሴ ወልደማሪያም ስለሞቱ ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል የአቶ ደምሴ ወልደማሪያምን ድርሻ ለወራሾቻቸው ከፍለው ቤቱን የግላቸው ካደረጉ በኋላ ከአቶ በቀለ ጅሩ ጋር ሲጋቡ በጋብቻ ውል የጋራቸው እንዱሆን ከስምምነት የደረሱ ሲሆን ፤ ሟቿ ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ባደረጉት ኑዙዚ በቤቱ ላይ ያላቸውን ድርሻ እና ማንኛውንም የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ፣ በባንክና በማንኛውም ቦታ ያለውን ንብረታቸውን ለአቶ በቀለ ጅሩ መናዖዙቸውን የኑዙዚ ይዖት የሚያመለክት በመሆኑ አቶ በቀለ ጅሩ ጠቅላላ የኑዙዚ ወራሽ ስለሆኑ ተጠሪዎች በፍትሐ ብሓር ሕጉ ቁጥር 908(1) (ሀ) ድንጋጌ መሰረት አባታቸውን ተክተው ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤልን ሉወርሱ የሚችለ በመሆኑ የወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል የውርስ ሀብት ለተጠሪዎች እንዱተላለፍ በማለት የወሰነ ሲሆን አመልካቾች በውሳኔው ባለመስማማት ያቀረቡት የይግባኝ ቅሬታ በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረዘ በፍርደ መግቢያ ላይ የተመለከተውን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
No topics extracted.
አመልካቾች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልቱ የኑዙዚ ተጤቃሚው ከተናዙዧ በፉት መሞታቸው ከመረጋገጡ አኳያ ሟች በህይወት እያለ ያላረጋገጡትን መብት ወራሾች የመጠየቅ ከኑዙዚ የመነጨ ህጋዊ መብት ያላቸው መሆን አለመሆኑ መጣራት አለበት በማለቱ ተጠሪዎች በሰጡት መልስ፡- ሟች የእንጀራ እናታቸው ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ከሟች አባታቸው አቶ በቀለ ጅሩ ጋር የነበራቸውን ቤት ድርሻቸውን ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ባደረጉት ኑዙዚ ለሟች አባታቸው ተናዖው የተጠሪዎች አባት አቶ በቀለ ጅሩ አስቀድሞ ስለሞቱ ተጠሪዎች ወራሽነታቸውን አረጋግጠው አባታቸው በጠቅላላ የኑዙዚ ወራሽነታቸው ያገኙትን የውርስ ንብረት የእንጀራ እናታቸው ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ከሞቱ በኋላ አባታቸውን ተክተው የኑዙዚ ወራሽ የመሆን ከሕግ የመነጨ መብት ያላቸው በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚነቀፍ ባለመሆኑ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልካቾች በመልስ መልስ ክርክራቸው ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ባደረጉት ኑዙዚ አቶ በቀለ ጅሩ በሕይወት እያለሁ ይንከባከበኛል ፣ ይጦረኛል ፣ የሚያስፈልገኝን ከጎኔ በመሆን ያሟላልኛል እንዱሁም የቀብር ሥነ ሥርዓቴን በክብር ያስፈጽምልኛል በማለት ኑዙዚ ያደረጉ መሆኑን የቁም ኑዙዚ ስጦታው በግልጽ የሚያመለክት ሆኖ አቶ በቀለ ጅሩ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ሳይፈጽሙ ከተናዙዧዋ ቀድሞ ስለሞቱ ተጠሪዎች የኑዙዚ ስጦታ ተተኪ ወራሾች ሉሆኑ የሚችለበት የህግ አግባብ የለም በማለት ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ለሰበር ቅሬታው ምክንያት የሆነው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ሕግ አንፃር መዛገቡ እንደሚከተለው ተመርምሯል። አመልካችቾ ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ያደረጉት ኑዙዚ ቅድመ ሁኔታ ያለበት ሆኖ አቶ በቀለ ጅሩ ከወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ቀድመው በኑዙዚው ላይ የተመለከተውን ግዳታ ሳይፈጽሙ ስለሞቱ ተጠሪዎች አቶ በቀለ ጅሩን ተክተው ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ያደረጉት ኑዙዚ ተጠቃሚ መሆኑን አይችለም በማለት ተከራክረዋል። በዘህ ፍርድ ቤትም ባደረጉት ክርክርም ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ባደረጉት ኑዙዚ አቶ በቀለ ጅሩ በሕይወት እያለሁ ይንከባከበኛል ፣ ይጦረኛል ፣ የሚያስፈልገኝን ከጎኔ በመሆን ያሟላልኛል እንዱሁም የቀብር ሥነ ሥርዓቴን በክብር ያስፈጽምልኛል በማለት ኑዙዚ ያደረጉ ቢሆንም አቶ በቀለ ጅሩ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ሳይፈጽሙ ከተናዙዧዋ ቀድሞ ስለሞቱ ተጠሪዎች የኑዙዚ ስጦታ ተተኪ ወራሾች ሉሆኑ የሚችለበት የህግ አግባብ የለም በማለት አመልካቾች ያቀረቡትን ግልጽ ክርክር ተጠሪዎች በማስተባበል ያቀረቡት ክርክር የለም። ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ያደረጉት ኑዙዚ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ መሆን አለመሆኑን ፤ በሁኔታ ላይ ከተመሰረተ ሁኔታው መሟላት አለመሟላቱንና የኑዙዚውን ውጤት ተገቢነት ካላቸው የሕግ ድንጋገጌዎች አንፃር ከፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዛገቡን በማስቀረብ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ሟቿ ከአብራካቸው የተወለደ ልጅ ስለላላቸው በእሳቸው እና በሟቹ አቶ በቀለ ጅሩ ስም ተመዛግቦ በአዱስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 09 የሚገኘውን የቦታ ስፊቱ 450 ካ.ሜ የሆነውን የቤት ቁጠር 817 መኖሪያ ቤት ፣ ማንኛውንም በስማቸው ተመዛግቦ የሚገኝ የሚንቀሳቀስ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ፣ በባንክም ሆነ በየትኛውም ቦታ በስማቸው ያለውን ንብረት ድርሻቸውን ለሚንከባከቧቸው እና የሚያስፈልጋቸውን ሁለ ከጎናቸው በመሆን ለሚያሟለላቸው ባለቤተ አቶ በቀለ ጅሩ መናዖዙቸው ፤ ኑዙዚ ተቀባዩም ከህልፈተ ሕይወታቸው በኋላ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውን በአዲዱ ማሪያም ቤተክርስቲያን እንዱያስፈጽሙላቸው መናዖዙቸውን ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ያደረጉት ኑዙዚ ይዖት ያመለክታል። ከኑዙዚው ይዖት መገንዖብ እንደሚቻለው ሟቿ ከአብራካቸው የተወለደ በሕይወት እያለ የሚንከባከባቸውና ከጎናቸው ሆኖ የሚያስፈልጋቸውን የሚያሟላላቸው ሲሞቱም የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውን የሚያስፈጽሚላቸው ልጅ ስለላላቸው እነዘህን ተግባራት ለሚወጡት ባለቤታቸው ኑዙዚ ማድረጋቸውን ኑዙዚው ያመለክታል።
በተለይም ኑዙዚ ተቀባዩ የተኛዙዧዋን የቀብር ሥነ ሥርዓት በአዲዱ ማሪያም ቤተክርስትያን እንዱያስፈጽሙ ኑዙዚው የሚያመለክት ሲሆን ፤ ኑዙዚ ተቀባይ የሆኑት አቶ በቀለ ጅሩ ይህንኑ በኑዙዚው ላይ የተመለከተው ቅድመ ሁኔታ ሳይሟላ ህዲር18 ቀን 2011 ዓ/ም የሞቱትን ተናዙዧዋ ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤልን ቀድመው ነሀሴ 8 ቀን 2005 ዓ/ም የሞቱ መሆኑ ግራቀኙን አላከራከረም። ምንም እንኳን አቶ በቀለ ጅሩ የሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤልን የጠቅላላ ሀብት ወራሽ ቢሆኑም ፤ ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ያደረጉት ኑዙዚ ቅድመ ሁኔታ ያለበት በመሆኑና ሟቹ አቶ በቀለ ጅሩም በኑዙዚው ላይ የተመከለተው ቅድመ ሁኔታ ሳይሟላ አስቀድመው ስለሞቱ በኑዙዚው ላይ የተመለከተው ቅድመ ሁኔታ ባለመሟላቱ በፍትሐ ብሓር ሕጉ ቁጥር 916 እና 918(2) ድንጋጌ መሰረት ኑዙዚውን ቀሪ የሚያደርገው በመሆኑ ተጠሪዎች መውረስ የሚችለት በፍትሐ ብሓር ህጉ ቁጥር 826(2) መሰረት ሟች አባታቸው ያላቸውን መብት በመሆኑ ተጠረዎች ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ያደረጉትን ኑዙዚ መሰረት አድርጎ ሟች አባታቸው አቶ በቀለ ጅሩን ተክተው ሉወርሱ የሚችለበት የሕግ አግባብ የለም። ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ባደረጉት ኑዙዚ መሰረት ተጠሪዎች ሟች አባታቸው አቶ በቀለ ጅሩን ተክተው ለመውረስ በኑዙዚው ላይ የተመለከተው ሁኔታ ባለመሟላቱ ኑዙዚው ቀሪ በመሆኑ ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል የአመልካቾች እህት መሆናቸው አከራካሪ ስላልሆነ አመልካቾች በፍትሐ ብሓር ሕጉ ቁጥር 844(2) መሰረት ያለኑዙዚ የሚወርሱ ሆኖእያለ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ መሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ብይን እንዱሁም የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዛገብ የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ፍርድ ፣ ውሳኔ እና ትዔዙዛ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽራል።
ሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ታህሳስ 6 ቀን 1999 ዓ/ም ያደረጉትን በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ኑዙዚ ቅድመ ሁኔታው ባለመፈፀሙ ተጠሪዎች አባታቸውን ተክተው በአዱስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 09 የሚገኘውን የቦታ ስፊቱ 450 ካ.ሜ የሆነውን የቤት ቁጥር 817 መኖሪያ ቤት የሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ግማሽ ድርሻ ልወርሱ አይችለም።
አመልካቾች በአዱስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 09 የሚገኘውን የቦታ ስፊቱ 450 ካ.ሜ የሆነውን የቤት ቁጥር 817 መኖሪያ ቤት የሟች ወ/ሮ መንበረ ወ/ገብርኤል ግማሽ ድርሻ ያለ ኑዙዚ ወራሽ ናቸው በማለት ተወስኗል።
በዘህ መዛገብ ላይ ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ/ም እና የተሰጠው የዔግድ ትዔዙዛ ተነስቷል።
የሥር ፍርድ ቤት መዛገብ በመጣበት አግባብ ይመለስ።
በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የግላቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዖግቷል።