የውርስ ሀብት ድርሻን በተመለከተ ወራሾች በስምምነት ንብረቱን በዓይነት ለማከፊፈል የማይቻል ከሆነ ፍርድ ቤት የውርስ ድርሻ ክፍያ የሚፈጸመው ንብረቱን በባለሙያ ግምት ( Book Value ) መሰረት በማድረግ ሳይሆን በገበያ ዋጋ ( Market Value ) በሐራጅ ተሽጦ ለወራሾች የክፍያ ድርሻ መፈጸም የሚገባው ስለመሆኑ። ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.132-136፣250 - ፍ/ብ/ሕ/ቁ.1079፣1083፣1084
No summary available.
ሐምል 26 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካቾች፡-
ይህ የዉርስ ሀብት ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል በሐዊ ብሓረሰብ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካቾች የሥር ከሳሾች፣ የአሁን 1ኛ ተጠሪ የሥር ተከሳሽ፣ የአሁን 2ኛ- 3ኛ ተጠሪዎች የሥር ጣልቃ ገቦች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካቾች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.111575 በ16/6/2014 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሾች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አቤቱታ ሟች ወላጅ አባታችን አቶ አወቀ ተመስገን እና ተከሳሽ በትዲር አብረዉ ሲኖሩ በዲንግላ 05 ቀበላ ዉስጥ በ500 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈ የመኖሪያ ቤት፣ በዘሁ ከተማ ቀበላ ዉስጥ የሚገኝ ጅምር ፍቅ የንግድ ቤት፣ በዲንግላ ብድርና ቁጠባ አክስዮን ማህበር ድርሻና ትርፍ፣ በዲንግላ ኢንደስትሪ አክስዮን ማህበር ድርሻና ትርፍ፣ በዲንግላ ጤና ሳይንስ ኮላጅ አክስዮን ድርሻና ትርፍ፣ በመንገሻ ጀምበሬ መምህራት ቁጠባ ማህበር የተቆጠበ ገንዖብና ትርፍ፣ በትስኪ አክስዮን ማህበር ድርሻና ትርፍ፣ በአጠቃላይ ብር 10,950,000 የሚገመት ንብረት ላይ የአባታችን ድርሻ 5,975,000 ሁኖ ከዘሁ የከሳሾች ድርሻ 2,987,500 እንዱከፍለኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተከሳሽ በዘህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ መኖሪያ ቤቱንና የዲንግላ ጤና ሳይንስ ኮላጅ አክስዮን ማህበር ያለንን ድርሻ ሟች በሕይወት እያለ ለጋራ ልጆቻችን ለጣልቃ ገቦች ስጦታ አድርገንላቸዉ ዉለም በፍትሕ ተቋም ጸድቋል፣ ስለሆነም ንብረቶቹ የሟች አይደለም። ጅምር ፍቅ የንግድ ቤት በሟችም ሆነ በተከሳሽ ስም የተመዖገበ አይደለም፤ በዲንግላ ብድርና ቁጠባ አክስዮን ማህበር ያለዉ ድርሻ ቤት ለመስራት የተወሰደዉን እዲ ሉሸፍን አይችልም፤ ከዲንግላ ኢንደስትሪ አክስዮን ማህበር ያለዉ ድርሻም እዲን የሚሸፍን አይደለም፤ በመምህራት ቁጠባ የተቆጠበዉ ገንዖብ በግላ የቆጠብኩኝ ስለሆነ ሉጠየቁኝ አይገባም፤ በትስኪ አክስዮን ማህበር ድርሻ የለም በማለት ተከራክሯል። ጣልቃ ገቦችም ባቀረቡት አቤቱታ የመኖሪያ ቤት እና የዲንግላ የጤና ሳይንስ ኮላጅ የአክስዮን ድርሻ ሟች እና ተከሳሽ በ2007 ዓ.ም በ18/9/2007 ዓ.ም በተደረገዉ ስጦታ የሰጡትን ስለሆነ የሟች ንብረት አይደለም በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰዉ ምስክሮች በመስማት፣ ከማህበራትና ከማዖጋጃ ቤት ማስረጃ በትዔዙዛ እንዱቀርብ በማድረግ ሟች በሕይወት እያለ ከተከሳሽ ጋር ,ሁኖ አከራካሪዉን ቤት እና የጤና ሳይንስ ኮላጅ አክስዮን ድርሻ ለጋራ ልጆቻቸዉ ለሆኑት ለጣልቃ ገቦች በ18/9/2007 ዓ.ም በተደረገዉ የስጦታ ዉል ሰጥቷቸዉ ዉለም በወረዲዉ ፍትሕ ጽ/ቤት ጸድቋል። በመሆኑም በስጦታ የተላለፈዉን ንብረትን ጨምሮ አጠቃላይ የሟች ንብረት ግምት ምን ያህል ነዉ ሟች ከሳሾችን ሳያካትት ያደረገዉ የስጦታ ክፍፍል ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም የሟች እዲ ምን ያህል ነዉ ከሟች እዲ ተራፉ ንብረት አለ ወይ ለከሳሾች የሚከፈል የዉርስ ሀብት አለ ወይ የሚለትን ነጥቦች እንደጭብጥ በመያዛ፣ በዘህ መሰረት አከራካሪዉ የመኖሪያ ቤት የከተማዉ ማዖጋጃ ቤት ባለሙያ ግምት ብር 194,843.70 መሆኑን፣ በጤና ሳይንስ ኮላጅ ያላቸዉ አክስዮን ድርሻ ብር 28,000 መሆኑን፣ በዲንግላ ብድርና ቁጠባ አክስዮን ማህበር ብር 21,5594.40፣ በዲንግላ ኢንደስትሪ አክስዮን ማህበር ብር 10,000፣ በመንገሻ ጀምበሬ መምህራን ቁጠባ ማህበር ብር 101,953.75፣ በመምህራን ማህበር የተቆጠበዉ ገንዖብ የጋራ ሀብት ነዉ፣ በአጠቃላይ የሟች እና የተከሳሽ የጋራ ሀብት 550,391.85 ለሁለት ሲከፈል የሟች ድርሻ ሀብት ግምት ብር 275,195.93 መሆኑን መረዲት ተችሎል። የሟች እዲ ደግሞ ብር 572,079.05 መሆኑ የተጋገጠ በመሆኑ የሟች የዉርስ ሀብት ከመተላለፈ በፉት የበሰለ እዲ መከፈል አለበት። በትስኪ አክስዮን ማህበር የድርሻ ሀብት የላላቸዉ መሆኑ ተረጋገግጧል። የሟች ሀብት ግምት ካለዉ እዲ ጋር ሲመዙዖን እዲዉ ከፍ ያለ ሆኖ ስለተገኘ ከሳሾች የሚወርሱት ንብረት ስለላላ ተከሳሽ የምትከፍለዉ ንብረት የለም በማለት ወስኗል።
ከሳሾች በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በማከራከር የሟች ድርሻ ከእዲ ብር 445,135.50 ያነሳ ነዉ በማለት የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበለትን የሰበር አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካቾች በ28/6/2014 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ በዲንግላ ከተማ ቀበላ 05 ዉስጥ የሚገኘዉ በ325 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈዉን የመኖሪያ ቤት በተመለከተ የቤቱ ግምት እንዱቀርብ ባልተጠየቀበት፣ ፍ/ቤቱም የቤቱ ግምት እንዱቀርብ ለየትኛዉም አካል ትዔዙዛ ባልሰጠበት፣ ቤቱ በገበያ ዋጋ መገመት ሲገባዉ የቤቱን የግንባታ ዋጋ ብቻ በመዉሰድ ግምቱ ብር 194,843.70 ነዉ የተባለዉ፣ ከዲንግላ ብድርና ቁጠባ አክስዮን ማህበር ተወስዶል የተባለዉ የብድር ገንዖብ ለቤት ግንባታ አለመዋለ በማስረጃ ተረጋግጧል። በዲንግላ ጤና ሳይንስ ኮላጅ አክስዮን ማህበር፣ በዲንግላ ከተማ ብድርና ቁጠባ አክስዮን ማህበር፣ በዲንግላ ኢንደስትሪያል አክስዮን ማህበር እና ከመንገሻ ጀምበሬ መምህራን ቁጠባ ማህበር ያለዉ የአክስዮን ድርሻ በተመለከተ የወሰነዉ ዉሳኔ ተገቢ አይደለም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች በዘህ ጉዲይ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልን በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ባዖዖዉ መሰረት መጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ የሥር ፍ/ቤቶች በዘህ ጉዲይ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ አመልካቾች የጠየቁት የዲኝነት ጥያቄ የህግ መሰረት የለዉም ተብል ዉድቅ እንዱሆንልን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ እንዱጻናልን በማለት በዛርዛር ተከራክሯል። አመልካቾች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር በ21/8/2014 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በዘህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት ያለበት ጉዲይ ፣የሥር ፍ/ቤቶች አከራካሪዉን የዉርስ ሀብት ያስገመቱበት አግባብና ይህን ግምት መሰረት በማድረግ ያሳለፈት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መሆኑን ተገንዛበናል።
በዘህ መሰረት ከሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ መገንዖብ እንደሚቻለ ግራ ቀኛቸዉን ያከራከረዉን የዉርስ ሀብት የሆኑትን የመኖሪያ ቤት እና በተለያዩ ማህበራት የሚገኙትን የአክስዮን ድርሻ በተመለከተ ግምት እንደቀረበና ይህን ግምት መሰረት በማድረግ ዉሳኔ ማሳለፈን ነዉ። ነገር ግን የመኖሪያ ቤት ግምት በተመለከተ የባለሙያ ግምት መሆኑን እና የአክስዮን ድርሻ ግምት በተመለከተ ግምቱ መቅረቡን እንጂ ግምቱ ምን አግባብ እንዲደረገ የሚያመለክተዉ ነገር የለም።
እንደሚታወቀዉ ለክርክር መነሻ የሆነዉ ሀብት ግምት ወይም ዋጋ በተመለከተ ተከራካሪወ ወገኖች ወይም አንደኛዉ ወገን ባለመስማማት ክርክር ያስነሳ እንደሆነ ፍ/ቤቱ አከራካሪዉን ሀብት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.132—136 ድንጋጌዎች መሰረት የሀብቱ ግምት እንዱታወቅ ማረድግ እንደሚችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.250 ሥር ተመልክቷል። በልላ በኩል የዉርስ ሀብት ድርሻ የሚከፊፈልበት አግባብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1079 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት መሆኑን ተመልክቷል። ከእነዘህ ድንጋጌዎች ይዖትና ዓላማ መረዲት እንደሚቻለዉ በሕግ የጸና ኑዙዚ ካለ የዉርስ ሀብት የክፍያዉ ሥራ በዘህ አግባብ የሚፈጸም መሆኑን፣ የዉርስ ሀብቱ ግምት የሚደረገዉ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1083 እና 1084 አግባብ መሆኑን፣ የክፍያዉ ሥራ የሚከናወነዉ በወራሾች መካከል በሚደረገዉ ስምምነት መሆኑን፣ የዉርስ ሀብቱ በዓይነት የሚከፊፈል ከሆነ በዘህ አግባብ መፈጸም እንደሚገባዉ፣ ይህ ካልሆነ የዉርስ ሀብቱ በሐራጅ ተሽጦ ለወራሾች የክፍያ ድርሻ መፈጸም እንደሚገባዉ ያመለክታል። ከዘህ መገንዖብ እንደሚቻለዉ የዉርስ ሀብት የክፍያ ሥራን በተመለከተ በወራሾች መካከል ስምምነት ካለ እና ንብረቱን በዓይነት ማከፊፈል የሚቻል ከሆነ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ይህ የማይቻል ከሆነ ግን የዉርስ ሀብቱ የድርሻ ክፍያ የሚፈጸመዉ የንብረቱን የባለሙያ ግምት {Book Value} መሰረት በማድረግ ሳይሆን በገበያ ዋጋ {Market Value} መሆን እንደሚገባዉ ያመለክታል። በመሆኑም የዉርስ ሀብቱ በወራሾች ስምምነት ወይም በዓይነት መካፊፈል ያልተቻለ እንደሆነ፣ ክፍያዉ መፈጸም ያለበት በገበያ ዋጋ መሆን እንደሚገባዉ ነዉ።
በዘህ አግባብ አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ የሥር ፍ/ቤት አከራካሪዉን የዉርስ ሀብት ግምት ወይም ዋጋ መታወቅ ለግራ ቀኛቸዉ ክርክር እልባት ለመስጠት አስፈላጊ መሆኑን እስከተገነዖበ ድረስ፤ በሚመለከተዉ አካል አከራካሪዉ የዉርስ ሀብት የገበያ ዋጋ ተገምቶ እንዱቀርብ በማድረግ፣ የግራ ቀኙን ክርክር ከቀረበዉ የገበያ ዋጋ አንጻር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መወሰን ይገባዉ ነበር። ግራ ቀኙን ያከራካሩት ንብረቶች ሟች አቶ አወቀ ተመስገን በሕይወት እያለ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በጋብቻ ዉስጥ እያለ ያፈሩዋቸዉ ንብረቶች መሆናቸዉ በማስረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ በመሆኑ፣ የእነዘህ ንብረቶች ግማሽ ድርሻ የአሁን 1ኛ ተጠሪ የሚስትነት ድርሻ ሲሆን፣ የንብረቶቹ ቀሪ ግማሽ ድርሻ ደግሞ የሟች የዉርስ ሀብት ድርሻ በመሆኑ ለሟች ወራሾች የሚገባቸዉ ይሆናል ማለት ነዉ፡ ነገር ግን ሟች በሕይወት እያለ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ሁኖ ለአሁን 2ኛ--4ኛ ያለት ተጠሪዎች የመኖሪያ ቤቱን እና የጤና ሳይንስ ኮላጅ አክስዮን ድርሻ በስጦታ አስተላልፎል የሚባል ከሆነ ይህ ስጦታ ከአመልካች መብት አንጻር እንዳት ይታያል? እንዱሁም ከዉርስ ሀብቱ የሚፈለግ የዉርስ እዲ ካለ ዔዲዉን ከፍል ወራሾች የሚከፊፈለት ቀሪ የዉርስ ሀብት ድርሻ አለ ወይስ የለም?
የሚለዉን ነጥብ ለይቶ ለመወሰን የዉርስ ሀብቱ ትክክለኛ የገበያ ዋጋ መታወቅ አለበት። በዘህ መሰረት የሥር ፍ/ቤቶች አከራካሪዉን የመኖሪያ ቤት እና በተለያዩ ማህበራት የሚገኘዉን የአክስዮን ድርሻ በሚመለከተዉ አካል በገበያ ዋጋ ተገምቶ እንዱቀርብ በማድረግ፣ የግራ ቀኙን ከዘህ አንጻር በሕጉ አግባብ በመመርመር መወሰን ሲገባቸዉ የቤቱን የባለሙያ ግምት እና የአክስዮን ድርሻ ደግሞ በዘህ አግባብ መገመቱ ባልተገለጸበት ሁኔታ ያሳለፈት ዉሳኔ የህግ ድጋፍ የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች አከራከሪዉን የመኖሪያ ቤት እና አክስዮን ድርሻን በገበያ ዋጋ ተገምቶ እንዱቀርብ በማድረግ የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች አንጻር መርምሮ መወሰን ሲገባቸዉ ይህን ሳያደርጉ ያሳለፈት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የሐዊ ብሓረሰብ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.01-19340 በ17/7/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.56134 በ10/2/2014 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.111575 በ16/6/2014 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የሐዊ ብሓረሰብ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተዖጋዉን መዛገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሐተታዉ በተገለጻዉ አግባብ አከራካሪዉን የመኖሪያ ቤት እና የአክስዮን ድርሻ በተመለከተ የሚመለከተዉ አካል በገበያ ዋጋ ገምቶ እንዱቀርብ በማድረግ፣ በቀረበዉ ግምት ላይ የግራ ቀኙን አስተያየት በመቀበል፣ የግራ ቀኛቸዉን ክርክር በሕጉ አግባብ በመመርመር ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.343 (1) መሰረት ተመልሶለታል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ የሰበር ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ችልት የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠዉ የእግድ ትዔዙዛ በዘህ ዉሳኔ ተነስቷል።
ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.