No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 24 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ክቢ ሂርጴ ጠበቃ ምስጋኑ ሙለታ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ደጊቱ ባላሳ - ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ ከዘህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የገጠር እርሻ መሬት ይዜታ ክርክርን የሚመለከት ነዉ።ተጠሪ በኦሮሚያ ክልል በግንደበረት ወረዲ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ በቂጥሬ ክቹ ቀበላ በተለያዩ አምስ ቦታዎች የሚገኝ በክሱ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱ የመሬት ይዜታዎችን አዋሳኞቹን የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጠቅሰዉ የባለቤታቸዉ አያት በ1996 ዓ/ም በስጦታ ሰጥቷቸዉ እየተጠቀሙበት እያለ አመልካች በቀን 08/11/2011ዓ/ም በጉልበት ስለያዘብኝ እዱለቁልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ ከ1-4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰ መሬት መሰረቱ የሂርጴ ቤኛ ሆኖ እሳቸዉ በ2003ዓ/ም ሲሞቱ በአመልካች እጅ ትተዉ ስለሞቱ ወራሽም ከእኔ ዉጭ ላላ ስለላለ እስካሁን ድረስ በእጄ የሚገኝ እንጂ ለተጠሪና ለባለቤታቸዉ የተሰጠ አይደለም።ስለሆነም ተጠሪ የመክሰስ መብት የላቸዉም።በ5ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰዉ መሬት በ1984 ዓ/ም ከመንግስት አግኝቼ እስካሁን ድረስ በስሜ ተለክቶ እየተጠቀምኩበት ያለሁት እንጂ የተጠሪ አይደለም በማለት ክሱ ዉድቅ እንዱሆን በመጠየቅ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮና ምስክሮቻቸዉን በመስማት እንዱሁም ከገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ያስቀረበዉን ማስረጃ ጭምር መርምሮ በቀን14/05/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ ለክርክሮ መነሻ የሆኑ መሬቶችን የባለቤታቸዉ አያት ለተጠሪና ለባለቤታቸዉ በስጦታ መስጠታቸዉን የጽሁፍ ማስረጃ በማቅረብ አላስረደም፤ በምስክሮቻቸዉም በክሳቸዉ መሰረት አላስረደም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለምዔራብ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃዎችን መርምሮና መዛኖ በቀን 27/06/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን የመሬት ይዜታዎችን ተጠሪና ባለቤታቸዉ ከ16 ዓመታት በላይ ለጎጆ መዉጪያ ተብል ተሰጥቷቸዉ ስጠቀሙበት መቆየታቸዉን ማስረጃዎቹ ያሳያለ።የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በሰጠዉ ዉሳኔ የገጠር መሬት ይዜታ ለጎጆ መዉጪያ ተብል ለተጋቢዎች የተሰጠዉ የባልና የሚስት የጋራ ይዜታ እንደሆነ ትርጉ ሰጥቷል በማለት ለተጠሪና ለባለቤታቸዉ ለክርክሩ መነሻ የሆኑ ይዜታዎች ለጎጆ መዉጪያነት እንደተሰጠ የቀረበዉ ማስረጃ ያሳያል።እንዱሁም ተጠሪ ከ16 ዓመት በላይ ሲጠቀሙበት የነበረ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል። ስለሆነም አመልካች የያዘትን አምስቱንም የመሬት ይዜታዎች ለተጠሪ ሉለቁ ይገባል በማለት በመወሰን የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ሽሯል።
በመቀጠል አመልካች ይግባኝ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱንም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃዎችን መርምሮ በቀን 28/01/2013ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ መሬቶቹ በስጦታ እንደተሰጣቸዉ የጽሁፍ ማስረጃ ባያቀርቡም በአካባቢዉ ልማድ መሰረት የጋብቻ ስርዓት በፈጸሙበት ጊዚ ሟች የባለቤታቸዉ አያት ሰዎች ፉት በቃል እንደሰጧቸዉና ይህንንም ተከትል ለ18 ዓመታት መረቶቹን ይዖዉ ሲጠቀሙ እንደነበር ከምስክሮች ቃል እና ከማስረጃዎቹ ተረጋግጧል።በተጠቀሰዉ ስርዓት መሰረት የሚሰጥ ስጦታ በጽሁፍ ባይደረግም የአካባዉን በህል ተከትል የተደረገ መሆኑ ስለተረጋገጠ ክርክር የተነሳበትን ይዖታ አመልካች ለተጠሪ እንዱለቁ መወሰኑ ተገቢ ነዉ በማለት የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።እንዱሁም አመልካች ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታቸዉን ያቀረቡ ቢሆንም ችልቱ በመ/ ላይ በቀን 22/02/2013ዓ/ም በሰጠዉ ትእዙዛ ለሰበር የሚያበቃ ስህተት አልተፈጸመም በሚል በአቤቱታዉን ሰርዜታል። አመልካች በቀን 07/03/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በተጠቀሰዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዖት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
ተጠሪ ባቀረቡት ክስ ላይ የተጠቀሱትን መሬቶችን የባለቤታቸዉ አያት(የአመልካች አባት) ከባለቤታቸዉ ጋር ጋብቻ በፈጸሙበት ጊዚ በ1995 ዓ/ም በስጦታ ጎጆ መዉጪያ አድርገዉ እንደሰጧቸዉ ቢገልጹም የወረዲዉ መሬት እና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የሥጦታ ዉል የለም በማለት በገለጸበትና ተጠሪም የማስረዲት ሸክማቸዉን ባልተወጡበት ጉዲዩን በይግባኝ ያዩ ፍርድ ቤቶች የወረዲዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ መሻራቸዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።የገጠር መሬት በስጦታ ሉተላለፍ የሚችለዉ በኦሮሚያ ክልል ገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 5/5 እና 9/5 በጽሁፍ ሆኖ ስልጣን ባለዉ አካል መመዛገብ አለበት በሚል በአስገዲጅነት ደንግጎ እያለ ከዘህ በተቃራኒ በምስክሮች ወይም በባህላዊ መንገድ ለጎጆ መዉጫ በስጦታ ሉተላለፍ ይችላል በማለት መወሰናቸዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።የተጠሪ ባለቤት ተጠሪን ካገባ በኋላ የቤተሰብ አባል አልነበረም።ተጠሪ መሬቶቹ በ1995ዓ/ም በስጦታ ተላፍልናል ያለ ቢሆንም በይዜታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በ1997ዓ/ም የተሰጠዉ ለአመልካች አባት ነዉ።መሬት የማይንቀሳቀስ ንብረት በመሆኑ ባለመብትነት የሚረጋገጠዉ በጽሁፍ ማስረጃ እንጂ በምስክሮች ቃል በስጦታ ተላልፎል በሚል ላሆን አይችልም።በ5ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሰዉ የእርሻ መሬት በአመልካች ስም የተመዖገበ ነዉ።ስለሆነም የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች በሰጡት ዉሳኔ ከማስረጃ ምዖና አንጻርም ሆነ ከሕግ አተገባበር አንጻር መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለፈጸሙ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ ተጠሪ አከራካሪዎቹን የመሬት ይዜታዎች ያገኙት በስጦታ እንደሆነ ባመኑበት ሁኔታ ስጦታዉ የክልለ የገጠር የመሬት አስተዲደር አዋጅ መሰረት በሚመለከተዉ አካል ባልተመዖገበበትና ባልተረጋገጠበት ሁኔታ መሬቶቹ በባህላዊ ስጦታ ለተጠሪ የተላለፈ ናቸዉ በማለት በይባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ የስር የወረዲ ፍርድ ቤት ዉሳኔ የተሻረበትን አግባብ ተጠሪ ባለበት እንዱጣራ ትእዙዛ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 30/06/2013 ዓ/ም የተፃፈ በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርበዋል።
ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆኑ የመሬት ይዜታዎችን ከባለቤቴ ጋር ከ16 ዓመት በፉት በጎጆ መዉጫነት ተሰጥቶን እየተጠቀምን የምንገኘዉ እንደሆነ ተረጋግጦ የተወሰነ በመሆኑ በይዜታችን ስር አድርገን በመጠቀም ላይ የሚንገኘዉን መሬት አመልካች እንዱለቅልን በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም።የገጠር እርሻ መሬት በስጦታ ገቢ ለላለዉ የቤተሰብ አባል ሉተላለፍ እንደሚችል በአዋጁ በግልጽ ተደንግጓል።የመመዛገብ ግዳታን በተመለከተ ስጦታዉ ለሟች ባለቤት የተላለፈዉ ለጎጆ መዉጫነት እንጂ በቤተሰብ አባልነት ብቻ ስላልሆነ ለጎጆ መዉጫ የተሰጠ ማንኛዉም ስጦታ የግድ መመዛገብ አለበት የሚል ግልጽ ድንጋጌ እስከላለ ድረስ የመመዛገብ ግዳታ ስለላለ ከዘህ አኳያ የተፈጸመ ስህተት የለም።ለክርክሩ መነሻ የሆኑ የመሬት ይዜታዎችን ከባለቤቴ ጋር በጋራ ለጎጆ መዉጪያ እንደተሰጠን በስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ተረጋግጦ የተወሰነ በመሆኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ማስረጃ የመመዖን ስልጣን ስለላለዉና ከማስረጃ ምዖና አንጻርም የተፈጸመ ስህተት ስለላለ የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔዎች ይጽኑልኝ በማለት ተከራክረዋል።
ከዘህ በላይ የተመዖገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር የክልለ ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዖት ሲሆን እኛም ማስቀረቢያ ነጥቡን ከግምት በማስገባት ጉዲዩን በይግባኝ እና በሰበር ባዩት የክልለ ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም ጉዲዩ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆኑ የገጠር እርሻ መሬት ይዜታዎችን ተጠሪ ከባለቤታቸዉ ጋር የባለቤታቸዉ አያት በጎጆ መዉጫነት ሰጥተዋቸዉ ሲጠቀሙበት ቆይተዉ አመልካች አለአግባብ እንደያዘባቸዉ በመግለጽ እንዱለቁላቸዉ እንዱወሰን ዲኝነት በመጠየቅ ያቀረቡትን ክስ መነሻ ያደረገ ሲሆን አመልካችም የተጠሪ ክስ ይዖት ይህንኑ የሚመለከት እንደሆነ አልካደም። መሬቶቹን በተጠሪና በባለቤታቸዉ መካከል ጋብቻ ሲፈጸም የባለቤታቸዉ አያት ለጎጆ መዉጫ ስጥቷቸዉ ተጠሪ ከባለቤታቸዉ ጋር ሲጠቀሙ የቆዩበት ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉን አከራካሪ ጭብጥ ለማጣራት በወረዲዉ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ምስክሮች ተሰምተዋል እንዱሁም ከሚመለከተዉ አስተዲደር አካል ማስረጃ እንዱቀርብ ተደርጓል።የግራ ቀኙን ማስረጃ የመረመረዉ የወረዲዉ ፍርድ ቤት ተጠሪ መሬቶቹን ከባለቤታቸዉ ጋር በስጦታ ዉል ስለማግኘታቸዉ የጽሁፍ ማስረጃ በማቅረብ አላስረደም በሚል ምክንያት ክሱን ዉድቅ ያደረገ ቢሆንም ጉዲዩን በይግባኝ ያዩት የክልለ ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የግራ ቀኙን ማስረጃዎች መርምረዉና መዛነዉ ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን የመሬት ይዜታዎች የተጠሪ ባለቤት አያት ተጠሪ ከባለቤታቸዉ ጋር ጋብቻ በፈጸሙበት ጊዚ በአካባቢዉ ባህላዊ ልማድ መሰረት በሰዎች ፉት በጎጆ መዉጫነት ሰጥተዋቸዉ ከ16 ዓመት በላይ ተጠሪ ከባለቤታቸዉ ጋር መሬቶቹን ይዖዉ ሲጠቀሙ ስለቆዩ በጎጆ መዉጫነት እንደተሰጣቸዉ የጽሁፍ ማስረጃ በማቅረብ ባያስረደም የመሬቶቹ ባለመብት ተጠሪ ናቸዉ በማለት የወረዲዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ ሽረዋል።
በመሰረቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት እና የተፈጥሮ ሀብት የባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዛብ ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40/3 ላይ ተደንግጓል።ይህንኑ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ ተከትል የወጣዉ የፋዳራል የገጠር መሬት አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 456/1997 አንቀጽ 5/3 እንዱሁም በስራ ላይ ያለዉ የኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 5/5 እና 12 ድንጋጌዎች እንደሚያስገነዛቡት በገጠር መሬት የመጠቀም የይዜታ መብት የሚገኘዉ በመንግስት በሚደረግ ድልድል፣በዉርስ ወይም በስጦታ ወይም የግል ባለሀብት ከሆነ ደግሞ በኢንቨስትመንት ዉል ነዉ።ስለሆነም የገጠር መሬት ላይ የባለይዜታነት መብት አለኝ የሚል ሰዉ ከእነዘህ በአንደኛዉ አግባብ ይዜታዉን ያገኘ ስለመሆኑ ማስረዲት ይጠበቅበታል።
በተያዖዉ ጉዲይ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት የመሬት ይዜታዎች አስቀድሞ የተጠሪ አያት(የአመልካች አባት) የሂርጴ ቤኛ እንደነበር አከራካሪ አይደለም።አከራካሪዉ ጉዲይ ለክርክሩ መነሻ የሆኑ የመሬት ይዜታዎች ለተጠሪና ባለቤታቸዉ በባለቤታቸዉ አያት በጎጆ መዉጫነት ተሰጥቷቸዋል ወይስ አልተሰጣቸዉም የሚል እና የገጠር የእርሻ መሬት በጎጆ መዉጫነት መሰጠቱን ለማስረዲት ላቀርብ የሚገባን ማስረጃ በተመለከተ ነዉ። በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 9/5 ላይ እንደተደነገገዉ የገጠር መሬት የመጠቀም መብት ያለዉ አርሶ አደር ይዜታዉን ለቤተሰብ አባል ወይም ለልጆቹ በስጦታ ማስተላለፍ እንደሚችል ተመልክቷል።የስጦታ ዉል በወረዲዉ ጽ/ቤት መመዛገብ እንዲለበት በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 3/12 ላይ የተደነገገ ቢሆንም የስጦታ ዉለ በተለይም በልማድ የዲበረዉ በየአካባቢዉ ማሕብረሰብ ለጎጆ መዉጫነትነት ተብል የሚሰጥ የገጠር እርሻ መሬት የተለየ ፍርም እንዱኖረዉ የሚያስገድድ ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 130/1999 ላይ አልተመለከተም። ይህም የሆነዉ ይህ እሴት ያለዉን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታ ከግምት በማስገባት ጥብቅ ስርዓት መከተል አስፈላጊ እንደሆነ በማሰብ ነዉ ተብል ይመናል።ለጎጆ መዉጫ ተብል የሚደረግ የገጠር መሬት ስጦታ የተለየ የዉል ፍርም እንዱኖረዉ ህጉ የግድ የሚለዉ አለመሆኑን ይህ ሰበር ችልት በመ/ቁ/107840 እና ላልች መሰል መዛገቦች ላይ የሰጠዉ ዉሳኔ ያሳያል።ከዘህም የምንገዖበዉ የገጠር መሬት ይዜታ አጠቃቀም ጋር በተያያዖ በተለይም የባለይዜታዉ ልጅ ወይም ላላ የባለይዜታዉ የቤተሰብ አባል ትዲር ሲይዛ ለመተዲደሪያ የሚሆን በተለምድ ለጎጆ መዉጫ ተብል የሚደረግ የመሬት ስጦታ ጥብቅ የሆነ የአጻጻፍ ስርዓት ወይም የስጦታ ዉል ፍርም ባያሟላም በየማህበረሰቡ የዲበረዉን ልማድ እና ጠቃሚ እሴት ከግምት በማስገባት ሕጋዊ ዉጤት እንዱኖረዉ ማድረግ ተገቢነት ያለዉ ስለመሆኑ ነዉ።
ሲጠቃለል አከራካሪዎቹ የመሬት ይዜታዎች ለተጠሪና ለባለቤታቸዉ በባለቤታቸዉ አያት ተጠሪና ባለቤታቸዉ በጎጆ መዉጫነት ሰጥተዋቸዉ ተጠሪ ከ16 ዓመታት በላይ ከባለቤታቸዉ ጋር የአመልካች አባት (የተጠሪ ባለቤት አያት) በህይወት እያለ ጭምር በይዜታቸዉ ስር አድርገዉ ሲጠቀሙበት መቆየቱን የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ማስረጃዎችን መርምረዉና መዛነዉ ያረጋገጡት ፍሬ ነገር። በመሆኑ አመልካች አባታዉ ወይም የተጠሪ ባለቤት አያት መሞታቸዉን ተከትል እንደልጅ መሬቱ ለእኔ ይገባኛል በማለት የሚያቀርቡት ክርክርም ሆነ ተጠሪ በጎጆ መዉጫነት መሬቶቹ የተሰጣቸዉ ስለመሆኑ የጽሁፍ ዉል በማቅረብ አላስረደም በማለት የሚያነሱት ክርክር የሕግ ድጋፍ ያለዉ እንዲልሆነ አረጋግጠናል።በመሆኑም ጉዲዩን በይግባኝ እና በሰበር ያዩት የክልለ ፍርድ ቤቶች መሬቶቹ ለተጠሪ በጎጆ መዉጫነት የተሰጡ ናቸዉ በማለት የደረሱበት ድምዲሜ ከሕግ አተገባበር አንጻርም ሆነ ከማስረጃ ምዖና መርህ አተገባበር አንጻር የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የምዔራብ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 27/06/2012ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ፣ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 28/01/2013ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 336177 ላይ በቀን 22/02/2013ዓ/ም የሰጠዉ ትእዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንተዋል።
በዘህ ችልት የወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ትዔዙዛ በዉሳኔዉ መሰረት እንዱያስፈጽም የውሳኔው ግልባጭ ለክልለ ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዛገቡ ላይ የተሰጠ የዔግድ ትእዙዛ ካለ ተነስቷል ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.