የከተማም ሆነ የገጠር መሬት ድንበር መገፊት ጋር ተያይዜ የሚቀርበውን ጉዲይ ከሳሽ ወገን መጠኑን ገልጾ ከጠየቀው ዲኝነት እና በምስክሮች ወይም አስተዲዲሪ አካል አጣርቶ የቀረበው መጠን ከተጠየቀው ዲኝነት በላይ በሆነ ጊዚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መስጠት ያለባቸው ግዳታ ከሳሽ ወገን በጠየቀው ዲኝነት ልክ በመሆኑ በአስተዲዲሪ አካል ተጣርቶ የቀረበውን በማለፍ በተጠየቀው ዲኝነት ልክ መወሰን የሚገባ ስለመሆኑ። ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.182 (1) እና 224 (1)
No summary available.
ሚያዘያ 28 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተኽሉት ይመሰል 2. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 3. ቀነዓ ቂጣታ 4. ተሾመ ሽፈራዉ 5. ፀሐይ መንክር አመልካች፡ …… . . ወ/ሮ ዉቤ በላይነህ፡- ጠበቃ አቶ ነቢያት ግርማ ቀርበዋል ተጠሪ፡ ………. . . .1. ወ/ሮ ሰናይት ሀብተስላሴ 2. ወ/ሮ መሰለች መርጊያ ቀርበዋል ይህ መዛገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ ከሳሾች ሁኖ ሲከራከሩ ነበር። ይህ ጉዲይ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.211663 በ30/2/2011 ዓ.ም የሰጠዉን ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከቱ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሾች (የአሁን ተጠሪዎች) ባቀረቡት ክስ በየካ ክ/ከተማ ወረዲ 1 የቤት ቁጥር 347 የሆነዉን መኖሪያ ቤት እና በ610 ካ.ሜ ይዜታ ላይ የሚያርፈዉን ግብር የሚንገብርበት ሲሆን ሕጋዊ የግንባታ ፈቀድ አዉጥተን ግንባታ የጀመርን ቢሆንም በስተደቡብ ምስራቅ በኩል አዋሳኛችን የሆኑት ተከሳሽ ባቀረቡት አቤቱታ ምክንያት የየካ ክ/ከተማ አስተዲደር ወረዲ 1 ቀን ግንባታ ፍቃድ ክትትልና ቁጥጥር ጽ/ቤት ግንባታዉን እንዱናቆም አድርጎናል። ነገር ግን ተከሳሽ በስተደቡብ ምስራቅ 4 ሜትር ይዜታችን ዉስጥ ገብተዉ ሰርቪስ ቤት መገንባታቸዉ በመሐንዱስ የታወቀ ሲሆን ተከሳሽ ይህን ይዜታ እንዱያስረክቡን ቢንጠይቅም ፈቃደኛ ስላልሆነ ተከሳሽ በሕገ ወጥ መንገድ የገነቡትን ግንባታ አፍርሰዉ ይዜታዉን እንዱያስረክቡን በማለት ከሷል።
በዘህ ክስ ላይ በተከሳሾች የተያዖ እና የተገነባዉ ግንባታ የለም፤ ተከሳሽ የከሳሽን ግንባታ ያስቆምነዉ ከሳሽ ድንበር አልፈዉ ግንባታ በመገንባታቸዉ ነዉ፤ ተከሳሽ ሰርቪስ ቤቱን ከሳሾች ይዜታችን ዉስጥ ገብተዉ ነዉ የገነቡት ያለት ሀሰት ነዉ፤ ቤቱ የተገነባዉ ከ15 ዓመት በፉት ነዉ፤ ይህም ደግሞ በ2004 ዓ.ም በተሰጠ ካርታ ላይ በግልጽ ይታያል፤ ክሱ ዉድቅ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን የየካ ክ/ከተማ መሬትና ልማት ማናጅመንት ጽ/ቤት በማጣራት በሰጠዉ ዉሳኔ ተከሳሽ አሁን ግንብተዉ ያለዉ ቤት ወደ ከሳሽ ካርታ ከተሰጣቸዉ ይዜታ ዉስጥ 27.3 ካ.ሜ አልፍ የተገነባ መሆኑን አረጋግጦ ሪፖርት በማቅረቡ ተከሳሽ በከሳሾች ይዜታ ዉስጥ ገብተዉ የገነቡትን ግንባታ እንዱያነሱ እና 27.3 ካ.ሜ ይዜታ ለከሳሾች እንዱያስረክቡ ወስኗል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበለትን ይግባኝ ዉድቅ በማድረግ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ህዲር 12 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የአሁን ተጠሪዎች የአመልካች ወደ እኛ ይዜታ 4 ሜትር አልፊለች የሚል ሆኖ እያለ የሥር ፍ/ቤት ይህን አልፍ ከ15 ዓመት በፉት የተሰራዉን ሰርቪስ ቤት በመስመር ካርታም በ1997 ዓ.ም የተነሳ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ቀርቦ እያለ የሥር ፍ/ቤቶች ይህን ሳይመረምሩ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የማስረጃ ምዖና ስህተት ስለሆነ ሉታረምልኝ ይገባል። የአሁን አመልካች ያቀረብነዉን ክርክር ለማስረዲት የሰዉ ምስክሮች ዛርዛር አቅርበን እያለ የሥር ፍ/ቤት ሳይሰማ እና ስለጉዲዩ ከሚመለከተዉ አካል ተጨማሪ ማስረጃ ጠይቀዉ ሳያጣሩት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልኝ ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልኝ በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፤በዘህ ጉዲይ ተጠሪዎች 4 ሜትር ተገፍተናል በማለት ካቀረቡት ክስ አንጻር የሥር ፍ/ቤቶች 27.3 ካ.ሜ ገፍተዋል በማለት የመወሰናቸዉን አግባብነት፤ ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ባዖዖዉ መሰረት ታህሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። በመልሱም ይዖት በአጭሩ፡ የአሁን አመልካች ያለ ተጠሪዎች ፈቃድ በይዜታችን ላይ ቤት መስራቷ በሕጋዊ ካርታ የተረጋገጠ በመሆኑ የሰዉ ምስክሮች ሉፈርስ የሚችል አይደለም ምስክር መስማት ተገቢ አይደለም፤ ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች በዘህ ጉዲይ የሰጡት ዉሳኔ ሕጋዊና ተገቢ በመሆኑ ጸንቶልን መዛገቡ እንዱዖጋልን የጠበቃ አበል ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልን በማለት በዛርዛር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች በበኩላቸዉ የሰበር አቤቱታቸዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርመሮታል። እንደመረመርነዉ የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዲኝነት ተጠሪዎች ይዜታቸዉን በስተደቡብ ምስራቅ በኩል 4 ሜትር አልፈዉ ሰርቪስ ቤት በመገንባታቸዉ ይህን ግንባታ አንስተዉ ይዜታዉን እንዱለቁላቸዉ ጠይቋል። የአሁን አመልካች በበኩላቸዉ ባቀረቡት ክርክር ይህን ክስ ክዲዉ የተከራከሩ ሲሆን፤
በዘህ ይዜታ ላይ ቤቱ የተገነባዉ ከ15 አመት በፉት በመሆኑ የቀረበዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል። በዘህ ረገድ የየካ ክ/ከተማ መሬትና ልማት ማናጅመንት ጽ/ቤት ስለይዜታዉ አጣርቶ ባቀረበዉ ሪፖርት አመልካች በካርታ ከተመለከተዉ የተጠሪዎች ይዜታ መካከል 27.3 ሜትር አልፈዉ ግንባታ መገንባታቸዉን በማረጋገጥ ገልጾዋል። ይህ በሥር ፍ/ቤት የቀረበ ክርክርና የተረጋገጠ ፍሬ ነገር በመሆኑ በሕጉ አግባብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደሚታወቀዉ ከሳሽ በክስ ማመልከቻዉ ላይ የሚጠይቀዉን ዲኝነት በዛርዛር መግለጽ እንዲለበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.224 ሥር ተመልክቷል። በዘህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 1 ሥር እንደተመለከተዉ ‹‹ከሳሽ በሚያቀርበዉ የክስ ማመልከቻ ላይ በተለይ ወይም በምትክ ወይም በተለዋዋጭ የሚጠይቀዉን ዲኝነት መግለጽ አለበት። ነገር ግን ከሳሹ በጉዲዩ ላይ እንዱሰጠዉ የሚጠይቀዉ ዲኝነት ጠቅላላ ሲሆን ፍ/ቤቱ የክስ ጭብጥና የማስረጃዉን አካባቢ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ትክክለኛ መስል የታየዉን ፍርድ ሉሰጠዉ ይችላል›› በማለት ደንግጎታል። ፍ/ቤትም እንደጭብጥ በመያዛና በማጣራት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ መስጠት የሚገባዉ የተጠየቀዉን ዲኝነት መሰረት በማድረግ እንደሆነ ግልጽ ነዉ። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.182 (1) ሥር እንደተመለከተዉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከራካሪዎቹ ወገኖች በዛርዛር ባላቀረቡት ወይም በግልጽ ባላመለከቱት ጉዲይ ላይ ፍርድ ለማስጠት አይችልም።....በማለት ይደነግጋል።
ከዘህ አንጻር አሁን የተያዖዉን ጉዲይ ስንመለከት የአሁን አመልካች የተጠሪዎች ይዜታ አልፈዉ ይዖዉ ግንባታ ማከናወናቸዉ በሚመለከተዉ የከተማ አስተዲደር አካል የተረጋገጠ ቢሆንም የከተማዉ አስተዲደር ያቀረበዉ ሪፖርት አመልካች የተጠሪዎችን ይዜታ 27.3 ካ.ሜ አልፈዉ ይዖዋል የሚል ሲሆን ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ ደግሞ የጠየቁት ዲኝነት አመልካች የተጠሪዎችን ይዜታ ድንበር አልፈዉ ይዖዋል ያለት በስተደቡብ ምስራቅ በኩል 4 ሜትር ብቻ እንደሆነ ተገንዛበናል። የሥር ፍ/ቤቶች በሰጡት ዉሳኔ ተጠሪዎች በክሳቸዉ ከጠየቁት ዲኝነት ዉጪ አመልካች 27.3 ካ.ሜ ይዜታ ላይ የገነቡትን ግንባታ አንስተዉ ይዜታዉን እንዱለቁ መወሰናቸዉን የዉሳኔዉ ግልባጭ ያሳያል። ከዘህ መገንዖብ የሚቻለዉ የሥር ፍ/ቤቶች ተጠሪዎች በክሳቸዉ ከጠየቁት ዲኝነት በላይ መወሰናቸዉን እና ይህ ደግሞ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.182 (1) እና 224 (1) ድንጋጌዎችን የሚጥስ ሆኖ እናገኛለን። የአሁን አመልካች የተጠሪዎችን ይዜታ 27.3 ካ.ሜ ድንበር አልፈዉ መያዙቸዉ በባለሙያ ሪፖርት የተረጋገጠ ቢሆንም ተጠሪዎች በክሳቸዉ ከጠየቁት ዲኝነት በላይ ስለሆነ አመልካች ወደ ተጠሪዎች ይዜታ በስተደቡብ ምስራቅ በኩል 4 ሜትር ገብተዉ የሰሩትን ግንባታ ሉያነሱና ይህን 4 ሜትር ይዜታ ብቻ ለተጠሪዎች ለቀዉ ሉያስረክቡ ይገባል ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዲኝነት ይዜታቸዉን በስተደቡብ ምስራቅ በኩል አመልካች 4 ሜትር አልፈዉ ስለያዘባቸዉ በዘህ ቦታ ላይ የሰሩትን ግንባታ አንስተዉ ይዜታዉን እንዱያስረክቡ ጠይቀዉ እያለ ከተጠየቀዉ ዲኝነት በላይ 27.3 ካ.ሜ ይዜታ ላይ ያለዉን ግንባታ አፍርሰዉ አመልካች ለተጠሪዎች እንዱያስረክቡ በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.122488 በ19/6/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በ211663 በ30/2/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሻሽሎል።
የአሁን አመልካች የተጠሪዎችን ይዜታ በስተደቡብ ምስራቅ በኩል 4 ሜትር አልፈዉ የሰሩትን ግንባታ አፍርሰዉ እንዱያነሱ እና ይህንኑ 4 ሜትር ይዜታ ለተጠሪዎች ለቀዉ ሉያስረክቡ ይገባል ብለናል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
በ13/3/2011 ዓ.ም የተሰጠዉ የአፈጻጸም የእግድ ትዔዙዛ በዘህ ዉሳኔ ተነስቷል።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.